ለጵጵስና የተጠቆሙት በጥንቆላ አታላዩ: አባ ተክለ ማርያም አምኜ(ነቅንቅ) ማን ናቸው? በምስክርነት ሊቀርቡ የሚችሉ ካህናትና ምእመናን አቤቱታ

Aba Tekle Mariam Amigne

ለአስመራጭ ኮሚቴው መቅረቡ የተገለጸው የተቃውሞ አቤቱታ፤ አባ ተክለ ማርያም አምኜ፣ በትውልድ ሀገራቸው አካባቢ ሥርዓተ ጋብቻ ፈጽመው እንደኖሩ ሚዜዎቻቸውን በእማኝነት በመጥቀስ ያጋልጣል፡፡ ይህ በኾነበት ለኤጲስ ቆጶስነት መጠቆማቸው፣ በሥርዓተ ድንግልና መንኩሶ ቤተ ክርስቲያንን በክህነት ያገለገለ የሚለውን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ሕገ ቤተ ክርስቲያን በቀጥታ የሚቃረን ነው፡፡

 • የአዊ ሕዝብ ደግፎኛል፤ በሚል አሰባሰብኩ ያሉትን የምእመናን ፊርማ አቅርበዋል
 • በጥንቆላ ማታለል፤ ዝሙትን በጀብድ መናገር፤ ዘረፋና ማጭበርበር ልማዳቸው ነው
 • “ከሓላፊነት አውጥታችሁ፣ ከእይታ ዘወር ያለ ሥራ ሰጥታችሁ አሳርፉን”/አቤቱታው/

*               *               *

በቤተ ክርስቲያናችን የክህነት አሰጣጥ፥ ዕጩ ካህናት ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁ ያስፈልጋል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን የሚያውቁ፤ ከዚኽም ጋር ሙሉ አካልና የመንፈስ ጤንነት ያላቸው ካህናት እንዲሾሙ ታዟል፡፡ ዲያቆናት ሚስት ካገቡ በኋላ ወይም መንኵሰው የቅስና ማዕርግ ይቀበላሉ፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ለመኾን መብት ያላቸው ግን፡- በድንግልና የመነኰሱ፣ የቅስናና የቁምስና ማዕርግ ያላቸው ናቸው፡፡ ማዕርገ ዲቁና ከተቀበሉ በኋላ ሚስት ለማግባት ይቻላል፡፡ የቅስና ማዕርግ ከተቀበሉ በኋላ ግን ለማግባት አይቻልም፡፡

ኤጲስ ቆጶስ በማይገኝበት ቦታ፣ እንደ ኤጲስ ቆጶስ ኾኖ የሚያገለግል ቆሞስ በቤተ ክርስቲያናችን ይሾማል፡፡ የቁምስና ሹመት የሚሰጠው በኤጲስ ቆጶስ ነው፡፡ ቆሞስ የሚኾኑት በድንግልና የመነኰሱ የቅስና ማዕርግ ያላቸው ናቸው፤ ማዕርጉ የሚገባቸውም የገዳም አበምኔቶች ናቸው፡፡ እነዚኽን ቀኖናዎች በማያፋልስ ሥርዓት፣ ከቆሞሳቱና ከመነኰሳቱ መካከል በትምህርቱ በትሩፋቱ ልቆ የተገኘው አባት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተመርጦ፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አንብሮተ እድና በቅብዐት ይሾማል፡፡

“አቡን ቄስ ናቸው ቢሉ ተርፏቸው ለሌላ ይናኛሉ” የሚል ብሂል አለን፡፡ ኤጲስ ቆጶሳት፣ እንደ ሐዋርያት፣ በቀሳውስትም በዲያቆናትም ሥልጣን እንደሚሠሩበት ያሳያል፤ ሦስቱም ሥልጣናት ተሰጥተዋቸዋልና፤ ቀሳውስትን፣ ዲያቆናትን ይሾማሉ፤ ያስተምራሉ፤ ያጠምቃሉ፤ ያቆርባሉ፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን፣ በመንፈሳዊና በማኅበራዊ ኑሮ ችግር ሲደርስባቸው፣ ችግራቸውን ያቃልሉላቸዋል፤ እንደ አባት፣ እንደ አለቃም ኹነው ይመክሯቸዋል፤ እንደ ዳኛም ኹነው ይፈርዱላቸዋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጦ ለመሾም ባለው ዕቅድ መሠረት፡- ንጽሕ በመጠበቅ ክህነታቸውንና ምንኵስናቸውን ያስከበሩ፤ በትምህርት ዝግጅት፣ በአስተዳደር ብቃትና በራስ አገዝ ልማት ሥራዎች ውጤታማነታቸው የተመሰከረላቸውና የብዙኃን ተቀባይነት ያላቸው፤ በችግር ፈቺነታቸው እምነት የሚጣልባቸው ቆሞሳትና መነኰሳት እንዳሉን፣ በተጠቆሙት አባቶች ስም ዝርዝር ውስጥ ተመልክተናል፡፡

የዚያኑ ያኽል፣ ስንኳን ለኤጲስ ቆጶስነት ደርሰው አባታዊ በረከታቸውን ለሌላው ሊናኙ ቀርቶ፣ አኹን በተቀመጡበት የአገልግሎት ሓላፊነት ሊቀጥሉ የማይገባቸውና ከእይታ ዘወር መደረግ የሚኖርባቸው ተጠቋሚዎች እንዳሉ ከካህናትና ምእመናን የሚደርሱ መረጃዎችና አቤቱታዎች ያሳያሉ፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪን፣ አባ ተክለ ማርያም አምኜን በተመለከተ፣ እየቀረቡ ያሉ አቤቱታዎችና መረጃዎች ይህንኑ የሚያሳስቡ ናቸው፡፡

አባ ተክለ ማርያም፣ እንኳን ለማዕርገ ጵጵስና ለምእመንነት እንደማይበቁ የሚቃወመው አቤቱታው፣ ለሹመቱ የሚያደርስ ዕውቀትና ገዳማዊ ሕይወት እንደሌላቸው ይገልጻል፡፡ ቅድመ ምንኵስና እና ድኅረ ምንኩስና ባለባቸው የምግባር ብልሽት፥ ክህነታቸውን ማፍረሳቸውንና ምንኵስናቸውን ማዋረዳቸውን የሚያስረዳውም፡-

 • በጥንቆላ ሥራ የማታለል፣
 • ዝሙትን እንደ ጀብድ የመቁጠር፣
 • ዘረፋ እና የማጭበርበር ተግባር፣
 • ሙስናና የአስተዳደር በደል፤

መፈጸማቸውን በነጥብ ለይቶ እማኞችን እየጠቀሰ በመዘርዘር ነው፡፡

በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል ተጀምሮ ወደ ባሕር ዳር በቀጠለውና፣ በሰሜን አሜሪካ ቆይታ ተጠናክሮ ከዚያ መልስ በእልቅና በተመደቡባቸው አምስት የአዲስ አበባ አድባራት በተስፋፋው የአባ ተክለ ማርያም አምኜ አማሳኝነት፣ “ካህናት ቁም ስቅላቸውን አዩ፤ የሚቀየረው ተቀየረ፤ የሚባረረው ተባረረ፤ የሚመዘበረው ተመዘበረ፤ የሚገፈፈው ተገፈፈ፤” ይላል፤ አቤቱታው፡፡

ይህም “ውሻ፣ ውሻ” አሰኝቶ ከካህናቱና ከምእመናኑ እንዲገለሉ እንዳደረጋቸው ጠቅሷል፤ ነገር ግን፣ የሌብነት ተግባራቸው ከቀን ወደ ቀን ባልተቀየረበት ኹኔታ፣ “እንዲኽ ዓይነቱ ሰው በቤተ ክርስቲያን ላይ መሾም የለበትም የሚል አካል መጥፋቱ ካህናቱንና ምእመናኑን አስመርሯቸዋል፡፡

“ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም መርጣችኹ ማቅረብ እንድትችሉ እግዚአብሔር ይርዳችኹ፤” ሲሉ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ ከባድ ሓላፊነት ለተጣለበት የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ መልካም ምኞታቸውን የገለጹት አቤቱታ አቅራቢዎቹ፤ ስለ አባ ተክለ ማርያም አምኜ ጥንተ ማንነትና በደል ሊመሰክሩ የሚችሉ አገልጋዮችና ሠራተኞች ዛሬም ድረስ በሚገኙባቸውና በእልቅናም በሠሩባቸው፡-

 • በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል፤
 • በአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን፤
 • በየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፤
 • በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል፤
 • በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም እና
 • አኹን ባሉበት በአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፤ 

የኮሚቴው ብፁዓን አባቶች ልዑካን መድበው አልያም ራሳቸው ተገኝተው እንዲመረምሩ፣ እንዲያጠኑና እንዲያጣሩ ጠይቀዋል፡፡ “ከእልቅና፣ ቢቻል ከአጠቃላይ መንፈሳዊ አገልግሎት አውጥታችሁ ቢያንስ ከሰው እይታ ዘወር ያለ ሥራና ደመወዝ ሰጥታችሁ አሳርፉን፤” ሲሉም በእጅጉ ተማፅነዋል፡፡

የዛሬውን አባ ተክለ ማርያም አምኜ፣ ዲያቆን ሃይማኖት አሞኘ፣ ሲባሉ ጀምሮ የሚያውቋቸውና ከአስመራጭ ኮሚቴው ፊት ቀርበው ስለ አስከፊ ማንነታቸው ሊመሰክሩ የሚችሉ ካህናትና ምእመናን እንዲኽ ይጩኹ እንጂ፤ እርሳቸው ግን፣ የአዊን ምእመናን ውክልና በራሳቸው ጊዜ ወስደው፣ ከሀገረ ስብከቱ ካህናትና ምእመናን ያሰባሰብኩት ነው፤ በሚል ለሹመቱ መጠቆማቸውን የሚደግፍ ፊርማ በማቅረብ፣ የሹሙኝ ዘመቻቸውን በገሃድ ማጧጧፋቸው ታውቋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ጥንት ተለምኖ ነበር፤ የዛሬዎቹ ግን ሹሙኝ እያሉ የሚመጡ ናቸው፤” በማለት በ2007 ዓ.ም. የጥቅምት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተናገሩት እንዲህ ላሉት ነው፡፡ ከአስመራጭ ኮሚቴው ብፁዓን አባቶች አንዱና አንጋፋው የጎንደር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕም፣ ከትላንት በስቲያው የብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ክብረ በዓል፣ በአንድ የአዲስ አበባ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው ባስተማሩበት ወቅት፡- “6ሺሕ እና 7ሺሕ የሕዝብ ፊርማ አሰባስበናል፤ ካልተሾምን እያሉ መከራ የሚያሳዩን ብዙ አሉ፤ ብለው የገጠማቸውን ችግር በዐደባባይ ለመግለጽ ተገደዋል፡፡

ይህም ከፍተኛው የክህነት ደረጃ – ማዕርገ ጵጵስና ሳይገባቸው፣ በጎጠኛነትና በሲሞናዊነት ለመሸመት ያሰፈሰፉት ቆሞሳትና መነኰሳት ነን ባዮች፣ በውስጥም በውጭም በኮሚቴው ላይ አፍራሽ ተጽዕኖና ግፊት እየፈጠሩ እንዳሉ በጉልሕ አሳይቷል፡፡ ቀጣዩ የቤተ ክርስቲያናችን ዕጣ ፈንታ ከምር የሚያሳስበን ካህናትና ምእመናን ኸሉ፤ ሒደቱን በቅርበት እየተከታተልንና የድርሻችንን እየተወጣን ድምፃችንን ልናሰማበት ይገባል፡፡


አባ ተክለ ማርያም አምኜ፣ በቀድሞ ስማቸው ዲያቆን ሃይማኖት አሞኘ ይባላሉ፡፡ “ሃይማኖት እንዴት ያሞኛል?” በሚል የአባታቸው ስም አምኜ የተባለው፣ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል ባሉና እስከ አሁን እዚያው የሚገኙ አንድ ካህን ናቸው፡፡ በጎጃም ክፍለ ሀገር – ቡሬ – ሺሕ ሑዳድ ቀበሌ – አሽፋ ማርያም ደብር ተወልደው ያገደጉት አባ ተክለ ማርያም፤ ለሥራ ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ለስድስት ዓመት ደጅ የጠኑት፣ በዚሁ ካቴድራል ሲሆን፤ በተስፈኛነትም ከ1979 እስከ 1981 ዓ.ም. ድረስ ቆይተዋል፡፡

በካቴድራሉ በዲቁና ለመቀጠር የተፈተኑት በውዳሴ ማርያም ንባብና ዜማ ነበር፡፡ ንባብ የተፈተኑት በረቡዕ “ኆኅትሰ”፤ ዜማውን ደግሞ በዓርቡ “ማርያም ንጽሕት” ነበር፡፡ ሆኖም፣ ንባቡንም ዜማውንም በአግባቡ መወጣት ተስኖዋቸው በፈተናው ወድቀዋል፡፡ በወቅቱ ለግብረ ዲቁና እንኳ የሚበቃ ዕውቀት አልነበራቸውም ማለት ነው፡፡ ታዲያ፣ ተፈትነው የወደቁበት፣ “ኆኅትሰ”፣ ለተወሰነ ጊዜ ቅጽል ስም ሆኖባቸው ነበር፡፡

ዲያቆን ሃይማኖት፥ የግብረ ዲቁናውን ፈተና በመውደቃቸው፣ የመቀጠር ተስፋቸው መንምኖ ሲታያቸው፣ በካቴድራሉ ደቡብ ምዕራብ በሚገኘውና የርእሰ ደብር አምሳሉ በነበረው መቃብር ቤት፣ ቡና አስፈልተውና መጋረጃ አስጥለው፣ “ዕድላችኹን እከፍታለኹ፤ ጤንነታችኹን እመልሳለኹ፤ ቡና ቤታችኹን አትራፊ አደርግላችኋለሁ፤ በመስተፋቅር ከማንኛዪቱም ሴት ጋር አሳስተሳስራችኋለሁ፤ መንፈስ ልጠይቅላችሁ፤ አጋንንት ልሳብላችሁ” ወደሚል የጥንቆላ ተግባር ተሰማርተዋል፡፡

“መስተፋቅር ሠርቼልሃለሁ” ያሉት የአንድ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሹፌር፣ የተሠራለትን ይዞ በሹፌርነት የሚያገለግላትን አለቃውን(እመቤቲቱን) ቢጠይቃት ሳይሳካላት ከመቅረቱም በላይ፤ እንዴት ብትደፍረኝ ነው፣ ተብሎ አቤቱታ ቀርቦበታል፤ ወዲያውም ከሥራው በመባረሩና እንጀራውን በማጣቱ፣ ለዚህ ሁሉ ዳርገኸኛል፤ በሚል በጠላት ተነሥቶባቸው እንደነበር እናስታወሳለን፤ ይህ ሰው ዛሬ ኮተቤ አካባቢ ይኖራል፡፡

በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ከአምልኮተ እግዚአብሔርና ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የወጣ የጥንቆላ ተግባር ሲፈጽሙ፣ በካቴድራሉ ጥበቃ እጅ ከፍንጅም ቢያዙም፤ ጉዳዩ በሽምግልና እየታየ ሲሸፋፈንላቸው ቆይቷል፡፡ ይሁንና፣ በጥንቆላቸው ኑሯቸውን ያናጉባቸውና ቀን የሚጠብቁላቸው ወገኖች በየጊዜው ይዝቱባቸው ስለነበር እንዳይበቀሏቸው ስለሰጉ፣ ከካቴድራሉ ሸሽተው ወደ ወለጋ – ለቀምት አምርተዋል፡፡ ጸሎታቸው ይድረሰንና፣ የወቅቱ የክፍሉ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ፣ በሀገረ ስብከቱ ወረዳ ቤተ ክህነት ቢመድቧቸውም፣ ብዙም ሳይቆዩ በገንዘብ ማጭበርበር ተባረው ወደ ባሕር ዳር አቅንተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ሥራ ስጠኝ እያሉ የሚያስቸግሯቸውን ዲያቆን ሃይማኖትን አዘውትረው የሚመክሯቸው “መጀመሪያ ተማር” እያሉ ነበር፡፡ ብፁዕነታቸው፣ ወደ ሸዋ ሀገረ ስብከት ተዛውረው ሲመደቡ፣ ሃይማኖት አሞኘ፣ አባ ተክለ ማርያም አምኜ ተብለው መንኵሰው መጥተው በዚሁ ጥያቄ ቢወተውቷቸው፣ “መጀመሪያ መማር አለብኽ” ብለው ግብረ ዲቁና እንዲማሩ ወደ ደብረ ጽጌ ገዳም ይልኳቸዋል፡፡ አባ ተክለ ማርያም ግን፣ ትምህርት ጠል ነበሩና፣ ከቀድሞም የነበረባቸው የዝሙት አመላቸው አንዲት ባለትዳር ሴትን ያስቀላውጣቸዋል፤ ቀላውጠውም አልቀሩ፣ ባለትዳሯን ሲያማግጡ አባ ወራው ሰምቶ ኖሮ ገስግሦ ቢደርስ፣ ያወላለቁትን ቆብና ቀሚስ ለመሰብሰብ እንኳ ልብ ሳይቀራቸው፣ በሸሚዝና ሱሬ ገጠሩን አቆራርጠው እንደ በረሩ ደብረ ሊባኖስ ገዳም ገብተው ሕይወታቸውን አትርፈዋል፡፡

በሐጸ ዝሙት የመነደፋቸው ጉዳይ እንኳ፣ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል ደጀ ጠኚ ሳሉ ጀምሮ ከኮማሪቶች ጋር በነበራቸው የማይታበል ግንኙነት የሚታወቅ ነው፡፡ እንዲያውም፣ አስበ ደነሱን ይከፍሉላቸው ነበር የሚባሉና በስም ጭምር የሚጠቀሱ ግለሰቦች፣ “መምሬ ነቅንቅ” ነው የሚሏቸው – በፍና ተሣልቆ! እንዲህ መባላቸው፣ ሴቶቹን እያስጮኹና እያሠቃዩ ስለሚያሳድሯቸው ነው!! ‘ነቅናቂው’ ሃይማኖት አሞኘም፡- “ቁመቴን ቢሸበሽበው [ወንድነቴን] አረዘመው” እያሉ፣ አዳር አስተዳደራቸውን ያለኀፍረት በጀብደኝነት ይተርኩ እንደነበር፣ ወደ ካቴድራሉ ጎራ ያለ ሰው ሁሉ ሊያረጋግጠው የሚችለው እውነት ነው፡፡

በደላቸው ሲነቃባቸው፣ ራሳቸውን በተነሳሒነት ከማረም ይልቅ ቦታቸውን የሚቀይሩት አባ ተክለ ማርያም አምኜ፤ ለትምህርት ከተላኩበት ደብረ ጽጌ እግሬ አውጭኚ ብለው ቢያመልጡም፣ “የሚያውቁኝ ሰዎች ይገድሉኛል” በሚል ፍራቻ ከተሸሸጉበት ወደ ባሕር ዳር ተመልሰው፣ ባለራእይ ነኝ ለሚሉ አንድ ባሕታዊ በእልፍኝ አስከልካይነት ሰዎችን እየደለሉ በማቅረብ፣ በጥንቆላ ተግባራቸው ላይ የመንፈሳዊነት ካባ ለመደረብ ሞክረዋል፡፡ በዚኽ አፈ ጮሌነታቸው ቆይተው፣ በረከታቸው ይድረሰንና የብፁዕ አቡነ በርናባስ አቡነ ቀሲስና የሰላም አርጊው ቅድስት ማርያም አለቃ ሆነዋል፡፡ በከተማው ቀበሌ 16 የሚገኘውን ቪላ ቤት ያሠሩትም በዚኽ ወቅት በሰበሰቡት ገንዘብ ነበር፡፡ አመንኵሰውኛል ብለው የሚጠቅሱት ብፁዕ አቡነ ቶማስን ቢሆንም፣ ገዳማዊ ሕይወታቸውን ግን አናውቅም፡፡

አባ ተክለ ማርያም አምኜ፣ ከባሕር ዳር ወደ ሰሜን አሜሪካ ተሻግረው ቆይታ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ጉዟቸውም፣ የባለራእዩ ባሕታዊ እልፍኝ አስከልካይ በነበሩ ጊዜ በድለላቸው በሚያውቋቸው ወይዘሮ የተመቻቸና በሓላፊነታቸው አጋጣሚ ያካበቱትን የቤተ ክርስቲያን ሀብት በመርጨት የተገኘ ቪዛ ነበር፡፡

“በሰሜን አሜሪካ በነበራቸው ቆይታ፣ ምእመናንን ለማጭበርበር አመቺ ጊዜና ኹኔታ ገጥሟቸዋል፤” ይላል፤ የካህናቱና የምእመናኑ አቤቱታ፡፡ ለፈረሱ፣ ለተቃጠሉ አድባራት፣ ገዳማትና ገዳማውያን አባቶች እንዲኹም ለአብነት ት/ቤቶች እረዳለኹ፤ በሚል ከደጋግ ምእመናን ባሰባሰቡት የርዳታ ገንዘብ፣ በምሥራቅ አዲስ አበባ – ሲ.ኤም.ሲ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ባለአንድ ፎቅ ዘመናዊ ቪላ መሥራታቸውን ይገልጻል – አቤቱታው፡፡ ወደ አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ይህን ጉድ ሰምተው፣ በአባ ተክለ ማርያም በመታለላቸው ካዘኑት ምእመናን አንዷም የሸዋ ዳቦ ቤት ባለቤት ነበሩ፡፡ እኚህ ምእመንት ወደ አሜሪካ እንደተመለሱ፣ አባ ተክለ ማርያምን፡- “ለምን አታለልኸን? ለአሜሪካ መንግሥት አቤቱታ ልናቀርብብኽ ነው፤” ይሏቸዋል፡፡

ጥፋትን አምኖ ይቅርታ መጠየቅ የአባት ነው፡፡ አባ ተክለ ማርያም ግን በለመዱት ዘርፎ የመሰወርና የማምለጥ ስልታቸው፣ የምእመናኑን ማስጠንቀቂያ እንደሰሙ፣ ቅሌን ጨርቄን ሳይሉ አዲስ አበባ ይገባሉ፤ ጠያቂም ሳይኖርባቸው፣ በሀገረ ስብከቱ ታላላቅ አድባራት እየተመደቡ፣ ዓይን ያወጣ ምዝበራቸውንና በትምክህት የተሞላ የግፍ አስተዳደራቸውን የቀጠሉትም በዚሁ ስልት ነበር፡፡


አዲስ አበባ እንደገቡ፣ ከሰበሰቡት ዶላር መነዛዝረው፣ ለሚገባው የሚገባውን ያደርጉና የጥንታዊውና ታሪካዊው ደብር ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አለቃ ኹነው ይሾማሉ፡፡ ከዚኽ በኋላማ የቱን ተናግረን የቱን እንተዋወለን፤ ካህናት ቁም ስቅላቸውን አዩ፤ የሚቀየረው ተቀየረ፤ የሚባረረው ተባረረ፤ የሚመዘበረው ተመዘበረ፤ የሚገፈፈው ተገፈፈ፡፡


ከአሜሪካ መልስ፣ መጀመሪያ በእልቅና በተመደቡበት በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር፣ አቶ ዘውዴ መኩሪያ የተባሉ ደግ ምእመን፣ ከሎንዶን ድረስ አምጥተው ለደብሩ በስእለት ያገቡትና ለስፌቱ ብቻ ከመቶ ሺሕ ያላነሰ ብር የወጣበት መጋረጃ፣ ተሰቅሎ ከዋለበት ሳያድር ምሽቱን በአይሱዙ ተጭኖ ወጥቶ የተሸጠው፣ በአለቃው በአባ ተክለ ማርያምና ግብረ አበሮቻቸው እንደነበር በዓይን እማኞች ተረጋግጧል፤ ለሚዲያ ፍጆታም በቅቶ እነኾ በማኅደርነት ተቀምጧል፡፡

በወቅቱ የደብሩ ዲያቆን፣ ዝርፊያውን በዓይን ምስክርነት በማጋለጡ ወደ ወይብላ ማርያም እንዲዛወር ተደርጓል፡፡ እውነት ትመነምናለች እንጂ ውሏን አትስትምና ዲያቆኑ አቤቱታ አቅርቦ ወደ ቦታው ሲመለስ፤ በምትኩ፣ አባ ተክለ ማርያም የተነሡትና ወደ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ያለአንዳች ተጠያቂነት የተዛወሩት በዚሁ ሳቢያ ነበር፡፡

“አባ መጋረጃ” ያሰኛቸው ዘራፊነታቸው፤ ቀደም ብሎ በደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል በደጅ ጥናት ሳሉ፣ ለአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ሳይቀር ቅርስ በመሸጥ እንደጀመሩት የምናውቀው፣ በስፍራውና በጊዜው አብረናቸው የነበርነው ነን፡፡ በወቅቱ ፖሊስ ከቅርስ ሽያጩ ጋር በተያያዘ ወደ ካቴድራሉ መጥቶ፣ “ሃይማኖት አሞኘ የቱ ነው? አምጡ” ብሎ ሲጠይቅ፣ በትምህርት ቤቱ በኩል አጭሩን የግንብ አጥር ዘለው እንዳመለጡ ዛሬም እናስታውሰዋለን፡፡

በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራልም ሳሉ፣ በምዝበራ የተባበሯቸው በጊዜው ጊዜ በሕግ ሲጠየቁ እርሳቸው ግን፣ ወደ ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ተዛውረዋል፡፡ በዚያም፣ ለከት በሌለው ፍቅረ ንዋያቸው፤ የሥልጣን ማሳያና መጠቀሚያ ባደረጉት ግፈኛና ብኩን አስተዳደራቸው ነበር የሚታወቁት፡፡ “የአንድነት ገዳሙን ድርጎ ለመቅመስ የሚጠየፉ፤ በገዳሙ ቤት ያልኖሩ የመጀመሪያው አስተዳዳሪ ነበሩ፤” ይላሉ፣ ማኅበረ ካህናቱ፡፡

“ከጳጳሳት በላይ ደመወዝ ይገባኛል” የሚሉት አባ ተክለ ማርያም፣ በእልቅናው ከሚከፈላቸው በተጨማሪ፣ ከሁሉም የገዳሙ የገቢ ምንጮች(ከትምህርት ቤቱ፣ ከክሊኒኩና ከኬክ ቤቱ) በአበል ክፍያ ስም ያጋብሳሉ፡፡ እንደ ቀድሞዎቹ የገዳሙ አለቆች ከማኅበሩ ሳይለዩ፣ በማረፊያው ከመኖር ይልቅ፤ ጠዋት ሲመጡ፣ ቀን ለምሳና እና ማታም ለአዳር ሲ.ኤም.ሲ ወደሚገኘው ቪላቸው በገዳሙ መኪና ሲመላለሱ፣ ለከፍተኛ የነዳጅ ወጪ (በአንዳንድ ሁኔታዎች በቀን ከብር 2ሺሕ ያላነሰ) ዳርገውታል፡፡ ማምሻቸውንና አዳራቸውን፣ ቦሌ ደሳለኝ ሆቴል የሚያደርጉባቸውና አንዳንድ ብፁዓን አባቶችን ሳይቀር በግብዣ ለማባበል የሚሞክሩባቸው አጋጣሚዎችም ሳይጠቀሱ የሚታለፉ አይደሉም፡፡

አባ ተክለ ማርያም፣ በእልቅና በተመደቡባቸው አድባራት፣ አገልጋዩንና ሠራተኛውን ያለምክንያት እያዘዋወሩ ሰላምና የሥራ ዋስትና በማሳጣት ይታወቃሉ፡፡ በሰው፣ በትንሹ፣ ከ5ሺሕ ያላነሰ ብር ይቀበሉበትም ነበር፡፡ በተለይም በአገልግሎታቸው እንደ ዋርካ የሚታዩትንና የተመሰገኑትን ካህናትና ሠራተኞች እያጠኑ በማስነሣት፣ ሌሎችን ማስፈራራትና ሥልጣናቸውን ማሳየት ያስደስታቸዋል፡፡ ከፍተኛ “የሹሙኝ” ዘመቻ የያዙበት የማዕርገ ጵጵስና ተስፈኛነታቸው እንዲህ እንደ ሰሞኑ ፈጦ ሳይወጣ፣ የሊቃነ ጳጳሳቱም ወደረኛ ነበሩ፡፡

“ያለኝ ሀብትኮ ከሊቃነ ጳጳሳቱ ይበልጣል፤ ምን ያደርጉኛል?” ይሉ ነበር፡፡ የገዳሙ ትምህርት ቤት ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ፣ የቀድሞውን ፓትርያርክ በደብዳቤ እስከ መጠየቅ የደረሱት ፍትሕ ፍለጋ ሳይሆን፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን ሽቅብ በሚያዩበት ወደረኛነታቸው ግፊት ነበር፡፡ አባ ተክለ ማርያም፣ የተቃወሟቸውን በማዘዋወርና ከቦታቸው በማንሣት ማሸማቀቅ ብቻ ሳይሆን፣ በቤተ ክርስቲያን ገንዘብ በዓለም ሸንጎ በመክሠሥና ከዚያም አልፎ፣ ለጉልበተኞች እየከፈሉ በእጅ አዙር በማስደብደብ የሚታወቁ ክፉና በቀለኛም ናቸው፡፡

የገዳሙን አምስት ሠራተኞች፣ “ሁከትና ብጥብጥ በመፍጠር” በሚል፣ ከታኅሣሥ እስከ ሰኔ ወር፣ 2006 ዓ.ም. ድረስ ለሰባት ወራት በክሥ አጉላልተዋቸዋል፡፡ ይኹንና ሠራተኞቹ ንጽሕናቸው ተረጋግጦ የታገዱትም ወደ ሥራቸው እንዲመለሱ፣ ከመንበረ ፓትርያርኩ የተላለፈውንና በፍርድ ቤት ውሳኔም የተደገፈውን ትእዛዝ ባለመቀበል፣ ሠራተኞቹ እንዳይገቡ ለማድረግ ተፈጥሮ የነበረው ዓምባጓሮ የክፋታቸውን ልክ የሚያስረዳ ነው፡፡ ከገዳሙ ሲነሡም “እንዲያውም አይመጥነኝም” ያሉበት እብሪት ሥነ አእምሯቸውን ያሳያል፡፡

ዛሬ፣ የአስኮ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል አለቃ ብቻ ሳይሆኑ፣ መኪናና ቤት እየገዙ በመሸጥ ሥራም መሰማራታቸው የሚነገርላቸው አባ ተክለ ማርያም፤ ከነውርና ከፍቅረ ንዋይ መራቅን፣ ኃዳጌ በቀልን፣ ትሑትና ርኅሩኅ የሕዝብ አባት መሆንን ለሚጠይቀው ማዕርገ ጵጵስና እንደማይበቁ በሥራቸው የሚያውቋቸው የአምስት አጥቢያዎች ካህናትና ምእመናን ምስክሮች ናቸው፤ “ከእልቅና፣ ቢቻል ከመንፈሳዊ ሓላፊነት አውጥታችሁ፣ ቢያንስ ከሰው እይታ ዘወር ያለ ሥራና ደመወዝ ሰጥታችሁ አሳርፉን፤” ሲሉም ይማፀናሉ፡፡

Advertisements

22 thoughts on “ለጵጵስና የተጠቆሙት በጥንቆላ አታላዩ: አባ ተክለ ማርያም አምኜ(ነቅንቅ) ማን ናቸው? በምስክርነት ሊቀርቡ የሚችሉ ካህናትና ምእመናን አቤቱታ

 1. Anonymous July 14, 2016 at 1:21 pm Reply

  ስለ አባ ተክለማርያም አምኜ የተጻፈው ጽሁፍ በጣም በጣም ያሳዝናል ምንጊዜም ጀግና ይፈራል ማንም ሰው ከመሬት ተነስቶ ቢጽፍ አባ ተክለማርያም አምኜ ምርጥ የቤተክርስቲያን አባት እና በሄዱበት አብያተክርስቲያናት ሁሉ ተከብረው ቤተክርስቲያንንም አስከብረው የሚኖሩ አባት ናቸው እንጅ እናንተ እንደለቀለቃችሁት እና የወሬ ሱስ ያዛቸው የቤተክረስቲለያን ጠላቶች እንጅ የቤተክርስቲያን ልጆች የጻፉት አለመሆኑን አውቆ አስመራጭ ኮሚቴው ሊያስምርበት ይገባል እላለሁ ።

  • Anonymous July 14, 2016 at 8:20 pm Reply

   Full of negativity የተረገማችሁ የዲያቢሎስ ልጆች ። ፖለቲካና ሐይማኖት ለይታችሁ የማታውቁ።

 2. Meklet Houston July 14, 2016 at 5:37 pm Reply

  እናንተ ሆይ በህይወታችሁ የምትፈሩት ነገር አለ እንዴ.. ዋና ኣላማችሁ አባቶችን መውውንጀል ቤተክርስትያንን ማናጋት ሰውን ማስናከል ነው እንዴ። የዲያቢሌሎስ መልክተኞች መሆናችሁ አፅያፊ ስራችኁ ይመስክራል። እሱ እራሱ አለቃችኁ ዲያብሎስ ይፈራችኇል እነዚህ እኔ የማልደፍረውን ደፍረዋል ብሎ በፍርድ ግዜ ይመሰክርባችኇል። እሱ እኮ እግዚአብሔርን ይፈራል ስለዚህ እንደናንተ ባለ ደፉር እግዚአብሄርን በማትፈሩ መርዝ መልክቱን ያስተላልፋል። ግድ የለም በአሁኑ ግዜ የፅድቅ ሰማዕትነት በሰይፍ አይደለም የዘመናችን ስይፉ የእናንተ እና የመሰሎቻችሁ ክፉ ምላስ ነው። ለምናከብራቸው እባቶቻችን የነፍስ እረኞቻችን የፅድቅን አክሊን ይጏናፅፉበታል።
  ስማችንን መልሱ ተዋህዶን አትወክሉም።አረ ለመሆኑ መንፈስ ቅዱስን እየሰደባችሁ መሆናችሁ ኣውቃችኇል።እግዚአብኄር ያከበራቸውን እናንተ ትቃወማላች። ይህ ማለት ደግሞ ከ እግዚአብሔር ምህረትን አታገኙም። እሱ ባለቤቱ ይፋረዳችሁ።

 3. መክለት houston መዘምራን July 14, 2016 at 7:27 pm Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ይቅር ይበላችሁ።
  እናንተ እግዚአብሔርን አትፈሩም። ለማንኛውም ዲያቢሎስን በክፉ ምግባር በልጣችኁታል: እሱ እኮ እግዚአብሔርን ይፈራል እናንተ ግን መንፈሳዊ ጥበብ በልባችሁ አልተሳለም ስለዚህ የልባችኁን ክፋት እና ድፍረት አይቶ ለዚህ ክፉ ስራ መረጣችሑ። አባታችው ዲያቦሎስ ያልደፈረውን ደፈራችሑ። ወዮ ለነፍሳችሑ ወዮታ አለባት።
  የአባቶቻችን ህይወት ለናንተ ይከብዳል ለመረዳት ደግሞ ቅንና እውነተኛ በ ሀይማኖት የታፀ ልብ ይፈልጋል። ይሄ ደግሞ በናንተ የሀሰት ህይወት ወይም አለም ቦታ የለውም።
  አባቶቻችን የሚናፍቋት ታላቋ የቅዱሳን ሀገር መንግስተ ስማያት ናት። እናንተ የምትናፍቁትን የዚህ አለም ሙገሳና ክብር አይደለም።
  የዘመናችን የፅድቅ ሰማዕትነት የምትገኘው ከ ሰይፍ ሳይሆን ከእናንተ ምላስ ነው።

  • Anonummes July 14, 2016 at 8:45 pm Reply

   እያንዳንድህ ከላይ አስተያየት የሰጠህ ስለ ተክለ ማርያም ምን ታውቃለህ የካ ሚካኤልን ባዶ ያስቀረው ዘመዶቹ ጎጃሜዎችን የሰገሰገ ዘረኛ መሆኑን ከፀሐፊው እና ከመሐይሙ ሣህሉ ጋር የሰሩትን ስራ የት ታውቁታላችሁ ይህ ሰው እንኳን ለጵጵስና ለምዕመንነትም ሲበዛበት ነው ጳጳስ ከሆነ አንድ ቀን አያድርም

  • አምሐ ግርማ July 15, 2016 at 3:30 am Reply

   በጣም የሚገርመኝ ምነው የምትሰጡት አስተያየት የእውነት ምስክርነት ከሆነ ለምን ትደበቃላችሁ እስቲ አንዳችሁ እንኳን በስማችሁ ኑና እንመናችሁ። ለማንኛውም ሐራዎች ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትሉ እውነት ማፈላለጉን ቀጥሉበት። እግዚአብሔር እውነተኛ አባትና እረኛ ያድለን። ሹሙኝ የሚለውን ሳይሆን ፍቅረ ሲመት የጠፋለትን እንደ ጥንቶቹ አባቶች “እስመ ፍቅረ ሲመት ደዌ ሰይጣናዊት” የሚለውን አባት ይስጠን!

 4. Anonymous July 14, 2016 at 10:06 pm Reply

  yegnanis hatiat man yinagerew wedaje

 5. Anonymouse July 14, 2016 at 10:30 pm Reply

  @መክለት houston መዘምራን ,You stand against the truth ! why ? you don’t know anything what is happening and now you start crying .The blog is stating what is others are talking ,making it public .There is nothing wrong .If people are not doing good they should NOT be in the system at all.Your name indicates you don’t belong here ! …kebe anguache … ale ye agere sew

  @ haratewahedo keep up the good work!

 6. Anonymous July 15, 2016 at 1:41 am Reply

  ያለምንም መረጃ አሉባልታ ወሬ አትጻፉ

 7. Chrstian Amare July 15, 2016 at 10:25 am Reply

  Egzio new yemlew,lela min elalehu. Egziabher lehulum ewnetun yawtaw.

 8. ተስፋ ሚካኤል July 15, 2016 at 10:48 am Reply

  “የሚገድላችሁ ሁሉ እግዚአብሔርን እንደሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል” ዮሐ16፣2፡፡ መድኃኑታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እርሱን በትጋት ለማገልገል ከዓለም የተለዩ ቅዱሳን በሚያገለግሉበት ወቅት የሚደርስባቸውን ፈተና በግልጥ ነግሯቸዋል፡፡ “የሚገድላችሁ ሁሉ አግዚአብሔርን የሚያገለግል የሚመስልበት ጊዜ ይመጣል” የሚለው አምላካዊ ቃልም አንዱ ነው፡፡ ይህ አምላካወዊ ቃልም በትጉኃን አገልጋዮች ሐዋርያት ላይ ተፈጽሟል፤ በዘመኑ የነበሩ የክርስቶስ ጠላቶች አገልጋዮቹ ሐዋርያትን ማዋረዳቸውን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት እንደማቅረብ አድርገው ይቆጥሩት ነበር፤ የሐራ ጦማሪዎች ሆይ እናንተም እንደእነርሱ ናቸሁ፡፡ በዚህ እኩይ ተግባራችሁ እግዚአብሔርን የምናስደስተው ከመሰላችሁ እጅጉን ተሳስታችኋል፤በብእር ጥይት የእግዚአብሔር ትጉህ አገልጋይ ክቡር መልአከ ገነት ቆሞስ አባ ተክለ ማርያም አምኜን እየገደላችሁ ነውና፤ በእርግጥም ለእናንተ ይምሰላችሁ እንጂ እርሳቸው በእግዚአብሔርና በተለያየ ሓላፊነት ባገለገሉት ሕዝብ ዘንድ ሕያውና የልማት አባት ናቸው፡፡
  ሐራዎች ክርስቶስን የሰቀሉ ሐራ ጲላጦስ ብትሆኑ እንጂ በየትኛውም መስፈርት ሐራ ተዋሕዶ ልትባሉ አትችሉም፡፡ ምክንያቱም የተዋሕዶ አርበኞች በሃያና በሠላሳ ሺህ ሕዝብ ላይ የተሾሙ ትጉኃን አባቶችን ሰድቦ ለሰዳቢ አይሰጥምና፡፡ ይህን ሚድያ የተሻለ መረጃ የሚሰጥ እንደሆነ አስብ ነበር፤ ነገር ግን እጅግ በጣም የወረዱ የሀሰት መረጃወችን እየሰበሰበ ይሉኝታ በሌለው ባለጌ ብእሩ ክቡራን አባቶችን የሚዘልፍ ምእመናንን ተስፋ ለማስቆረጥ የሚሠራ የመናፍቅ ሚድያ እንደሆነ ተረድቻለሁ፡፡ ይህ ዓይነቱ ተግባር ከጥንት ጀምሮ የነበረ የመናፍቃን ተግባር ነውና፡፡ እኒህ ታላቅ አባት በተለያዩ ታላላቅ ሓላፊነት ቦታዎች እንዳገለገሉ ይታቃል፡፡በዚህን ወቅት በቤተ ክርስቲያኒቱ ምንም ዓይነት ቦታ ሊኖራቸው የማይገባቸው ነገር ግን የእንስሳትን ደም እንደሚመጥ “መዢገር” ያለምንም አንዳች ሥራ በቤተ ክርስቲያን የተተከሉ ዓይነኬ የሚባሉና የሚፈሩ ሰዎችን በተገቢው ሁኔታ አስወግደው በቤተ ክርስቲያንን አጽድተዋል፡፡ በገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ በምስካየ ኅዙናን የነበረው እውነተኛ ታሪክም ይህ ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ ተግባርም ያስመሰግናቸዋል እንጂ አያስነፈፋቸውም ነበር፤ በእርግጥም ሐራ አቡነ እገሌን፣ አባ እገሌን፣ ዲ/ን እገሌን እንዲህ አደረጉ በማት የጻፈችው አባታችን በቤተ ክርስቲያን ላይ እንደ ጉልኮስ የተተከሉ ሙያ አልባ ሰዎችን አስወግደዋል፡፡ በዚህም የአጥቢያው ምእመናን እያመሰገኗቸው ይገኛሉ፡፡ ሕን እውነታም ሐራ ከቦታው ድረስ በመሄድ ማረጋገጥ ይቻላት ነበር፡፡ ይህ ሁሉ ተራ የሰፈር ወሬ የመጣውም ከእነዚህ ጥቅማቸው የተነካ አካላት እንደሆነ አንባቢው ሊገነዘብ ይገባል፡፡ እኒህ አባት እውነታውን አሽቀንጥረው ጥለው ተመሰሳስለው የሚበሉና አድር ባይ አባት ቢሆኑ ኖሮ ከማሃል ከተማ ተነሥተው ዳር ከሆነ ቦታ አይመደቡም ነበር፡፡ ይህን ጉዳይም “ሐራ” ባለፈው ጊዜ ጽሑፏ አማሳኞችን ያልደገፉና የአዲስ አበባ ሀ/ ስ/ ሊ/ ጳጳስ አቡነ እስጢፋኖስ ያስጠኑትን ጥናት በመደገፋቸው ወደአስኮ ገብርኤል መመደባቸውን እንደ ጥንካሬ /መልካም ጎን/ በማንሣት አስነብባለች፡፡ ዛሬ ግን ጥቅማቸው በተነካ ሰዎች ሥር የወደቀችው ሐራ የእኒህ ታላቅ አባት የአስተዳድር ብቃት የቅዳሴ ችሎታ፣ ሕዝብን በሚማርክ አቀራረብ ዘመኑን የዋጀ ስብከት የመስበክ ጸጋ እንዳላቸው አጉልቶ ከማሳየትና ወደተሸለ የኃላፊነት ደረጃ ቢመጡ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ ችግር የሚፈቱ መሆናቸውን ለሚመለከተው ከማስገንዘብ ይልቅ እርሳቸውን የማይገልጥ ጽሑፍ መጻፏ እጉጁን ያሳዝናል፡፡ ብዙ እውነተኛ ክርስቲያኖችንም ያሳዘነ ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ጽሑፍ ነው፡፡
  በመሆኑም፣
  ሀሰትን ፈጽሞ የሚጠላ እግዚአብሔር ቤቱ በሥረዓቱ እንዲገለግል ትጉህና አቋም ያላቸው አገልጋዮችን ስለሚሻ ለእኒህ ታላቅ አባት የተሸለውን የአገልግሎት ሥልጣን እንደ ሚያድላቸው ባለሙሉ ተስፋ ነኝ፡፡

  • Meklet houston tx ሰንበት ት/ቤት July 17, 2016 at 3:22 pm Reply

   ቃለ ህይወት ያሰማህ የኔ ወንድሜ ኣአንተ ነህ የተዋህዶ ፍሬ።

  • Abel July 17, 2016 at 9:15 pm Reply

   Evry body calm down .. yea he is yekidase memeher so? Ena betam keletafa , yea so ?
   Weha ayanesam , koy fo real tawkutalachehu ? Am deacon and I know him well , MN aynet mnkusena new? With rava 4 & executive cars ,2 villa house , what the hell?? Ene Aba mekars nachew weyis entons? Enesus be demena neber …. I sware aGod he don have to be bishop … I dont know if if he is witch or not bt i donow that he drunk so mch , ena agafarim kesegebzem , likediakonm lhun endemil , relatively ke abatoche menekosat gar sasteyayew he is not good at it . fiker mibal neger yekewm , thetena , bcha sebawinet mibal neger yigolewal
   !!! I sware. AGod i dnt lie … I tell u all the truth so there are better monks than him …. If he is gonna to b beshope i hope , may be he change him self other with he will never support or help or our church … Enkuan zenbobsh drowm teza nesh …..

 9. Anonymous July 15, 2016 at 3:35 pm Reply

  ስለ አባ ተክለማርያም በጻፋችሁት። ለምን ነው ክፋትን ብቻ እየመረጣችሁ ምተጽፉ? እውነት ብትጽፉ ኑሮ አታልፉትም ነበር። ለምሳሌ ስለእውቀታቸው ስትጽፉ ለብፁዕ አቡነ በርናባስ አቡነ ቀሲስ በነበሩ ጊዜ በጎንደር ዙሪያ ደንቢያ በሚባል አካባቢ ቅዳሴ ቤት በመቆየት ተመልሰዋል። ስለዚህ ለምንድን ነው መልካም መልካሙን እየቀበራችሁ ክፉ ክፉ የሚታያችሁ?

 10. anonymus July 15, 2016 at 6:34 pm Reply

  I sware agod he is devil , I know him personally , he gat ” rava 4 ,executive,b/dar villa , and in Addis too , ) he is not real monk !!!!! Mariamn!!
  Ene like likawent Ezra , ene Aba fikre Mariam tesfa Mariam balubet , even Aba fikre Mariam rasu new cook miaregw,set ayasgebam Betu, bettam migermew tsebayu zmtaw, tselotu, tsom yemifetaw bedbk ke Yemenite gar …. Mariamn ! Be ayne be Beretu selayehut new ewnet Aba fikre Mariam fiker new … ahun miskaye hizunan yilegnal , ….. like likawentenm be aakal akachewalu , selenesu tenagre alcheresem he is so reall , btam migermegn hule slemitemetemu menekuse aymeslugnm neber … ewnet yigeref achewal , tekleariam gn Mariamn aygebawm

 11. abel July 15, 2016 at 6:35 pm Reply

  I sware agod he is devil , I know him personally , he gat ” rava 4 ,executive,b/dar villa , and in Addis too , ) he is not real monk !!!!! Mariamn!!
  Ene like likawent Ezra , ene Aba fikre Mariam tesfa Mariam balubet , even Aba fikre Mariam ras

 12. warled July 16, 2016 at 8:47 pm Reply

  first of hara is talkative why do u right positively about aba teklemariyam aba teklemariam is more knwlegable ; fast spritual administrator so respect our spritual fathers

 13. TIRSIT WUBIE July 17, 2016 at 5:08 pm Reply

  እ ውነተ ኞ ቹ አ ባ ቶ ች ብ ቻ የ ሚመረ ጡበ ት እ ንደነ ዚ ህ ያ ሉ አ ታ ላ ዮ ች የ ሚለ ዩበ ት ይ ሁ ን አ
  ሁ ን ም እ ናመሰ ግ ናለ ን ሐ ራ ዎ ች

  2016-07-14 13:33 GMT+03:00 “ሐራ ዘተዋሕዶ” :

  > haratewahido posted: ” የአዊ ሕዝብ ደግፎኛል፤ በሚል አሰባሰብኩ ያሉትን የምእመናን ፊርማ አቅርበዋል
  > በጥንቆላ ማታለል፤ ዝሙትን በጀብድ መናገር፤ ዘረፋና ማጭበርበር ልማዳቸው ነው “ከሓላፊነት አውጥታችሁ፣ ከእይታ ዘወር
  > ያለ ሥራ ሰጥታችሁ አሳርፉን”/አቤቱታው/ * * * በቤተ ክርስቲያናችን
  > የክህነት አሰጣጥ፥ ዕጩ ካህናት ሃይማኖታቸውን ጠንቅቀው እንዲያውቁ”
  >

 14. Samuel July 17, 2016 at 9:09 pm Reply

  Evry body calm down .. yea he is yekidase memeher so? Ena betam keletafa , yea so ?
  Weha ayanesam , koy fo real tawkutalachehu ? Am deacon and I know him well , MN aynet mnkusena new? With rava 4 & executive cars ,2 villa house , what the hell?? Ene Aba mekars nachew weyis entons? Enesus be demena neber …. I sware aGod he don have to be bishop … I dont know if if he is witch or not bt i donow that he drunk so mch , ena agafarim kesegebzem , likediakonm lhun endemil , relatively ke abatoche menekosat gar sasteyayew he is not good at it . fiker mibal neger yekewm , thetena , bcha sebawinet mibal neger yigolewal
  !!! I sware. AGod i dnt lie … I tell u all the truth so there are better monks than him …. If he is gonna to b beshope i hope , may be he change him self other with he will never support or help or our church … Enkuan zenbobsh drowm teza nesh …..

 15. yalemsew July 19, 2016 at 7:41 pm Reply

  ኡባ ተክለማርያም ታላቅ ስራ የሰሩ ቀልጣፋ ስለምን በጎ ነገር አትጽፉም የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ የሆነ ይህንን ጥላሸት ኡትቀቡ

 16. YENEALEM ACHENEF July 28, 2016 at 5:39 am Reply

  Mnm kalat yelegnm,bicha ye KIDUSAN AMLAK EGZIABIHERE BE EDME BE TSEGA YTEBKLIN,YE FIKIR ENAT KELIJWA GA BETIBEKAWA ATLEYACHU AMEN AMEN AMEN

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: