የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት 16 ነው፤ በየአካባቢው የተለዩትን ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ወቅታዊ የስም ዝርዝር ይመልከቱ

Askema Abew Papasat

 • መረጃዎችና አቤቱታዎች በዋና ጸሐፊው በኩል ለአስመራጭ ኮሚቴው ይቀርባሉ
 • ማስረጃዎቹ እና አቤቱታዎቹ ባለቤታቸው የታወቁ እና የተረጋገጡ ሊኾኑ ይገባል
 • ትኩረትና ተጨማሪ ማስረጃ የሚያስፈልጋቸውን ተጠቋሚዎች ለመለየት አግዘዋል
 • የምንኵስና፣ የክህነት፣ የትምህርትና የውጤታማነት ማስረጃዎች በጥብቅ ይፈተሻሉ

*                 *                *


የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዕጩነታቸው ካመነባቸው በኋላ፣ በቅርቡ ተመርጠው እንደሚሾሙ የሚጠበቁት ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት፣ 16 እንደኾነ ተገለጸ፡፡

በየአህጉረ ስብከቱ ክፍት በኾኑ መንበረ ጵጵስናዎች፣ ብቁ ኤጲስ ቆጶሳትን መርጦ ለመሾም ቅዱስ ሲኖዶስ በያዘው ዕቅድ መሠረት፣ በቅርቡ 16 ኤጲስ ቆጶሳት እንደሚሾሙና፤ ለዚኽም 32 ዕጩዎች በተወዳዳሪነት እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡

ባለፈው ዓርብ፣ ሐምሌ 1 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በተካሔደው የቋሚ ሲኖዶስ መደበኛ ስብሰባ፣ በርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው፣ የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ የሥራ ክንውን ውይይት ከተደረገበት በኋላ መመሪያዎች መሰጠታቸው ተጠቅሷል፡፡

ከ118 ያላነሱ ቆሞሳትንና መነኰሳትን ስም ዝርዝር፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጥቆማ የተቀበለው ኮሚቴው፤ ተጠቋሚዎቹን በየአካባቢው ከለየ በኋላ የማጣራት ሥራውን በማከናወን ላይ እንዳለ ተመልክቷል፡፡

ኮሚቴው፣ ቆሞሳቱንና መነኰሳቱን በየአካባቢው ከለየ በኋላ በቀጠለው የማጣራት ተግባር፣ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ሰዓት ድረስ፣ የያዛቸው ተጠቋሚዎች ብዛት ወደ 86 ዝቅ ማለቱ ተገልጧል፡፡ የምርምራው፣ የጥናቱና የማጣራቱ ሒደት በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ለሚካሔደው ምርጫ በዕጩነት የሚቀርቡ 32 አባቶች ተለይተው እስኪታወቁ ድረስ ቀጣይነት ይኖረዋል፡፡

ሹመቱ፣ ክፍት በኾኑና መንበረ ጵጵስና ባለባቸው 16 አህጉረ ስብከት የሚደረግ ሲኾን፤ ለየመንበረ ጵጵስናው ኹለት፣ ኹለት ዕጩዎች በምርጫ ይወዳደራሉ፡፡

የምርጫው ሥርዓት ከመከናውኑ በፊት፣ አስመራጭ ኮሚቴው የሚያቀርባቸው ዕጩዎች፣ የምልአተ ጉባኤውን ተቀባይነት ማግኘታቸው መረጋገጥ እንዳለበት በሕገ ቤተ ክርስቲያን ተደንግጓል፡፡ ለኤጲስ ቆጶስነት ዕጩ ለመኾን የሚያበቁ መስፈርቶችና የምርጫ ሥርዓት ደንቡ፤ ባለፈው ዓመት ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶሱ ምልአተ ጉባኤ መጽደቁ ይታወሳል፡፡

አስመራጭ ኮሚቴው በተጠቋሚዎች ላይ በሚያደርገው ማጣራት፣ ከማኅበረ ካህናትና ምእመናን በድጋፍም በተቃውሞም የሚመጡ አስተያየቶች፣ መረጃዎችና አቤቱታዎች፣ ከፍ ያለ አዎንታዊ እገዛ ማድረጋቸው ተገልጧል፡፡ በተለይም፣ “ትኩረት ያሻቸዋል” እና “ተጨማሪ ማስረጃ ያስፈልጋቸዋል” የተባሉትን ተጠቋሚዎች ማንነት ተረድቶ ሚዛናዊና ተገቢ አቋም ለመያዝ በብዙ ረድቷል፤ ተብሏል፡፡


መረጃዎቹና አስተያየቶቹ በአንድ በኩል፡- ፈተናውንና መሰናክሉን ኹሉ አልፈው ንጽሕ የጠበቁ፤ በብሔር አቀፍና በዓለም አቀፍ ትምህርት የበሰሉ፤ የወቅቱን የቤተ ክርስቲያንና የሀገር ችግር ለመረዳት ንቃተ ኅሊና ያላቸውና እምነት የሚጣልባቸው፤ በልቡናቸው ከሐኬት የራቁና ለተልእኮ የሚፋጠኑ አባቶች ከተጠቆሙት መካከል እንዳሉበት ሲያመለክቱ፤ በሌላ በኩል ደግሞ፡-

 • ምንኵስናቸውና ገዳማዊ ሕይወታቸው አጠራጣሪና በቂ ማስረጃ የሌላቸው፤
 • በትውልድ አገራቸው በሥርዓተ ተክሊል ያገቡና ጋብቻቸውን ያፈረሱ፤
 • ጋለሞታዎችን(ዝሙት አዳሪዎችን) የሚያሳድዱና በዚኽም ርምጃ የተወሰደባቸው፤
 • ባለትዳሮችን የሚያማግጡ(ከእናትም ከሴት ልጇም የወደቁ አንድ ተጠቋሚ አሉ)
 • ከተለያዩ ሴቶች የወለዱ፤ በግብረ ሰዶማዊነትም የሚታሙ፤
 • ከዘማዊነታቸው የተነሣ ለተላላፊ በሽታ የተጋለጡና ከቫይረሱ ጋር የሚኖሩ፤
 • በአብነቱም በዘመናዊውም ትምህርት ያልደከሙበትንና የተጭበረበረ ማስረጃ የያዙ፤
 • በምዝበራቸው የተባረሩ እና ያልተዘጋ የፍርድ ቤት ክሥ ያለባቸው፤
 • መንኖ ጥሪት ይቅርና በመዘበሩት ወደ ‘ኢንቨስተርነት’ና ደላላነት የተቀየሩ፤
 • ጵጵስናውንም የዚኹ ሽፋን አድርገው ሀብት ለማድለብ የሚቋምጡ፤
 • በጠንቋይነትና አስጠንቋይነት፤ በመተተኛነት ለነፍስ መጥፋት ምክንያት የኾኑ፤
 • ኦርቶዶክሳዊ ውግንናና ቀናዒነት የጎደላቸውና አጉል ዩኒቨርሳሊዝም የሚያጠቃቸው፤
 • በእምነታቸው ጉልሕና ተጨባጭ ሕፀፅና ነቀፌታ ያለባቸው፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንም በኅቡእ የሚሠሩና ሽፋን የሚሰጡ፤
 • ትውፊተ አበው የሚተናነቃቸው፤ የአባትነት ጸጋ የሌላቸው፤ ለተቀብዖ የማይመቹ አደዝዳዦችና ተኩነስናሾች፣ በትዕቢት የተነፉ፣ ችኩሎችና ቀዥቃዦች፤
 • ጠባያቸውን አርመው፤ ካህናትንና ምእመናንን አክብረው፣ አዳምጠውና አሳትፈው ለመሥራት የማይችሉ ዓምባገነኖች፤ ፖሊቲከኛነት የሚጫናቸው ጎጠኞችና አድርባዮች፤
  … ወዘተ መኖራቸውን በተጨባጭ የሚያስረዱ ናቸው፡፡

በቀጣይም፣ አቤቱታዎችና መረጃዎች፣ ባለቤት ያላቸውና አድራሻቸው በሚታወቁ የድጋፍ ፊርማዎች መቅረባቸው እንዲረጋገጥ ያሳሰበው ቋሚ ሲኖዶሱ፤ በአስረጅነት በተመደቡት የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ አማካይነት ለአስመራጭ ኮሚቴው እንዲደርሱ እንዲደረግም መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ክልል ትግራይ፣ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ዋግ ኽምራ – ሰቆጣ፣ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ክልል ኦሮሚያ፣ ወላይታ፣ ከምባታ እና ሐዲያ፣ ጉራጌ(ከደቡብ ክልል) እንዲኹም ጋምቤላ እና ኢሉባቦር፤ ተጠቋሚዎቹ በሀገረ ሙላዳቸው የተለዩባቸው አህጉረ ስብከት ናቸው፡፡

ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳቱ የሚከናወንባቸው አህጉረ ስብከት ደግሞ፤ ሽሬ፣ አኵስም፣ ዓዲግራት፣ ደቡብ ጎንደር፣ አዊ፣ ፍኖተ ሰላም፣ ግልገል በለስ(መተከል)፣ ዋግ ኽምራ – ሰቆጣ፣ ቄለም ወለጋ፣ ከምባታና ሐዲያ፣ ጉራጌ፣ ቦረና፣ ደቡብ ኦሞ – ጂንካ፣ ጋምቤላ፣ ኢሉባቦር፣ አሶሳ ናቸው፡፡

*                *                *

በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፣ እስከ ሐምሌ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ባለው ጊዜ፤ በየአካባቢው የለያቸውና ማጣራት እያካሔደባቸው ያሉት 86 ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ስም ዝርዝር እና የሚገኙባቸው ቦታዎች፤

ከትግራይ አህጉረ ስብከት፤

 1. አባ ፍቅረ ማርያም ተስፋ ማርያም(የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አለቃ)
 2. አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ(የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስ)
 3. አባ ዘርዓ ዳዊት ኃይለ ሥላሴ(የመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል አለቃ)
 4. አባ ጥዑመ ልሳን(የማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ካቴድራል አለቃ)
 5. አባ ገብረ እግዚአብሔር ኃይሉ(መቐለ መድኃኔዓለም)
 6. አባ ኢያሱ ገብረ አልፋ(በምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የቅኔ መምህር)
 7. አባ ፍሥሓ ጽዮን(የኢየሩሳሌም ገዳም መጋቤ)
 8. አባ ገብረ ማርያም ወልደ ሐዋርያት(ደቡብ አፍሪቃ)
 9. አባ ኃይለ ሥላሴ ገብረ እግዚአብሔር(አሜሪካ – ሎስአጀንለስ)
 10. አባ ገብረ ፃድቕ አረፈ ዓይኔ(የማእከላዊ ዞን ትግራይ – አኵስም ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ)

ከወላይታ ሀገረ ስብከት፤

 1. አባ ዮሐንስ ገብረ ሥላሴ(የወላይታ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የወላይታ ደብረ መንክራት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም አበምኔት)

ከጋምቤላ እና ኢሉባቦር አህጉረ ስብከት

 1. አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ(የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ)

ከጉራጌ ሀገረ ስብከት፤

 1. አባ ሰይፈ ገብርኤል ኦብሰን(አሜሪካ – የሲያትል ደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል አለቃ)
 2. አባ ገብርኤል ወልደ ዮሐንስ(የቡታጅራ ቅድስት ማርያም ደብር አለቃ)
 3. አባ ፊልጶስ ከበደ(አሜሪካ – የቨርጂኒያ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ደብር አለቃ)
 4. አባ ፈቃደ ሥላሴ(አሜሪካ – የዲሲ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ምክትል አስተዳዳሪ)
 5. አባ ዘድንግል ኑርበገን(ፈረንሳይ)

ከሐዲያ እና ከምባታ ሀገረ ስብከት፤

 1. አባ ኄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ (የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አለቃ)
 2. አባ ሚካኤል ገብረ ማርያም (የከምባታ – ዱራሜ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 3. አባ ቢንያም መንቸሮ (የሆሳዕና ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ)

ከጎንደር አህጉረ ስብከት

 1. ሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ ሐዲስ (የጎንደር መድኃኔዓለም አለቃና የ፬ቱ ጉባኤያት መምህር)
 2. አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል(የታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም ሊቀ ጉባኤ)
 3. ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ(የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ)
 4. አባ ቴዎድሮስ መስፍን (የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሊቃውንት ጉባኤ አባል)
 5. አባ ብርሃነ መስቀል ደርበው (የአዘዞ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ደብር አለቃ)

ከሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት

 1. አባ ፊልጶስ አሻግሬ(አሜሪካን – ሚችጋን ዴትሮይት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደብር)
 2. አባ ኃይለ ማርያም ገብረ ሚካኤል(አሜሪካ – ኢንዲያና ቅዱስ ሚካኤል)
 3. አባ ኃይለ ማርያም አረጋ(የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ አለቃ)
 4. አባ ዘውዱ በየነ(የደብረ ብርሃን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 5. ፀባቴ አባ የማነ ብርሃን ዓሥራት(አሜሪካ – የአትላንታ መድኃኔዓለም አለቃ)
 6. አባ ለይኩን ግፋ ወሰን (መንበረ ፓትርርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት)
 7. አባ ማቴዎስ ከፍ ያለው(እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም)
 8. አባ ተክለ ሃይማኖት ወልዱ(የናዝሬት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን አለቃ)
 9. አባ ኃይለ ጊዮርጊስ ተረፈ(የሶማሌ – ጅግጅጋ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 10. አባ ብርሃኑ ክበቡ
 11. አባ ገብረ ጻድቅ ደበብ
 12. አባ ሐረገ ወይን ወልደ ኢየሱስ(ኢየሩሳሌም ገዳም)
 13. አባ እስጢፋኖስ ባሕሩ(አሜሪካ)

ከዋግ ኽምራ – ሰቆጣ ሀገረ ስብከት

 1. አባ ብርሃነ መስቀል ዕንቊ ባሕርይ ወልዱ
 2. አባ ወልደ ዐማኑኤል ዘድንግል(የባሕር ኪዳነ ምሕረት ገዳም አበምኔት)
 3. አባ ፍቅረ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት(የሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም አበምኔት)

ከወሎ አህጉረ ስብከት

 1. አባ ያሬድ ምስጋናው(የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት ገዳም መምህር)
 2. አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎርዮስ(የጎፋ ጥበበ እድ ማሠልጠኛ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ)
 3. አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን(የእንጦጦ ቅድስት ማርያም ገዳም አለቃ)
 4. አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ(የደሴ ቅዱስ ገብርኤል አለቃ)
 5. አባ ገብረ ሥላሴ በላይ(የደሴ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 6. አባ ሳሙኤል ገላነው(የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ መምህር)
 7. አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ(የቅዱስ ላሊበላ ደብር አለቃ)
 8. አባ ገብረ ኪዳን እጅጉ(ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም)
 9. አባ ወልደ ማርያም አድማሱ(የደብረ ሊባኖስ ገዳም ፀባቴ)
 10. አባ ለይኩን ወንድ ይፍራው(የደሴ ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት ሊቀ ካህን)
 11. አባ ሢራክ አድማሱ(ደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት የመጽሐፍ መምህር)
 12. አባ ገብረ ጻድቅ መኰንን(አሜሪካ – ኖርዝ ካሮላይና)
 13. አባ ገብረ መድኅን በየነ(ምሥራቅ ሸዋ – ናዝሬት)
 14. አባ ጥዑመ ልሳን አዳነ(የደቡብ አፍሪቃ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ)
 15. አባ ብርሃነ መስቀል ወልደ ማርያም(ጀርመን)
 16. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ኃይለ ሚካኤል(ዓለም ገና)

ከኦሮሚያ አህጉረ ስብከት

 1. አባ ገብረ ሕይወት ፍሥሓ (ጀርመን – ሙኒክ)
 2. አባ ሞገስ ኃይለ ማርያም (የመናገሻ ማርያም አለቃ)
 3. አባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ አምላክ (የደብረ ሊባኖስ ገዳም መምህር)
 4. አባ ወልደ መድኅን ተክለ ብርሃን (እንጦጦ ቅዱስ ራጉኤል)
 5. አባ ተከሥተ ጐፌ (ደብረ ጽጌ/ሙገር ቅዱስ ሩፋኤል)
 6. አባ ገብረ እግዚአብሔር ታደለ (ብሥራተ ገብርኤል ደብር)
 7. አባ ዘተክለ ሃይማኖት (የደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል)
 8. አባ ገብረ ኢየሱስ ገለታ (አዲስ ዓለም ጽዮን ማርያም)
 9. አባ ገብረ ማርያም ነጋሳ (ሰበታ)
 10. አባ ተክለ ወልድ ገብረ ጻድቅ (የደብረ ጽጌ ማርያም አለቃ)
 11. አባ ተክለ ማርያም ስሜ (ሰሜን ምዕራብ ሸዋ – ሰላሌ)
 12. አባ ዘሚካኤል ደሬሳ (ዴንማርክ)
 13. አባ ገብረ ዐማኑኤል አያና ቶላ
 14. አባ ሣህለ ማርያም ገብረ አብ(አሜሪካ – ቨርጂንያ)
 15. አባ ጌዴዎን ጥላሁን(አሜሪካ – ፍሎሪዳ)

ከጎጃም አህጉረ ስብከት

 1. አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ መንግሥቱ (ጀርመን – በርሊን ቅዱስ ዐማኑኤል)
 2. አባ ወልደ ሐና ጸጋው (የባሕር ዳር መካነ ቅዱሳን ቤተ ደናግል ገሪማ የእናቶች ገዳም አስተዳዳሪና የሀገረ ስብከቱ ሊቃውንት ጉባኤ)
 3. አባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ ሐዋርያት (የደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍት መምህር)
 4. አባ ገብረ ሥላሴ ይርሳው (አዲስ አበባ ቅዱስ ሩፋኤል)
 5. አባ ቀለመ ወርቅ አቡኔ (የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የብሉይ መምህር)
 6. አባ ገብረ ሥላሴ ጠባይ (የጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ደብር አለቃ)
 7. አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና (የካርቱም መድኃኔዓለም ደብር አለቃ)
 8. አባ ተክለ ማርያም አምኜ (የአስኮ ቅዱስ ገብርኤል ደብር አለቃ)
 9. አባ ኃይለ ኢየሱስ ተመስገን (የሽሮሜዳ ቅድስት ሥላሴ ደብር አለቃ)
 10. አባ ኅሩይ ወንድይፍራው (አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት)
 11. አባ ኃይለ ኢየሱስ ገብረ ማርያም(ምሥ.ጎጃም – የቀድሞ የመርጡለ ማርያም ርእሰ ርኡሳን)
 12. አባ ገብረ ሥላሴ (ኢየሩሳሌም ገዳም)
 13. አባ ወልደ መስቀል ግርማ
 14. አባ ገብረ ሚካኤል ሙላቱ
Advertisements

32 thoughts on “የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት 16 ነው፤ በየአካባቢው የተለዩትን ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት ወቅታዊ የስም ዝርዝር ይመልከቱ

 1. Bete Zewudu July 12, 2016 at 1:56 pm Reply

  አባ ሀይለመለኮት ተስፋማርም
  ቁጥር ፰፩ ጳጳስ ለመሆን
  ሲራክ ወልደሥላሴ ፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ጀርመኔ

  በፖሊቲካ ጥገኝነት የሚኖሩ አባ ሲራክ አገርቤት ሲሄዱ በአውሮፖ አቆራርጠው ነዉ የሚሄዱ ምክንያቱም
  ፖስፖርታቸው የሥደኞ ስለሆነ በቀጥታመሄድ ስለማይፈቀድላቸው

  በጣምደደብ ከመሆናቸው ብዛት ዜግነት የላቸውም ብዙጊዜአመልክተው ተከልክለዋል

  እስካሁንሥማቸውን አይፅፉም ሀገራቸው ሽሬ ጥብላ ሲሆን ጎንደር ነውሀገሬ አባ ጳውሎስ አሰደደኝ ጎንደሬስለሆንኩኝ
  ብለው በመክሰስ ከአውሮፓጳጳስ አቡነኤልያስ ድጋፍእስፅፈውነው መኗሬያወረቀትያገኙትጳጻሱንበጊዜውእኔም ቀራቢስለነበርኩለመኝላቸውአለሁኝ ታዲያካአነስ እንኳን የስደተኞውፓስ
  ሣይቀየር ነው

  እንግዲህ ጉድናወንጀል በሀገርቤቱሲኖዾሥለመሾም ጉብስቀና ግን ሁሉም ወንጀል ነው

  አምሐ ሸንንቁጤ የተባለ ክርስቴያን የሰበካ ጉባየ ገንዘብያዢ ስለብልቩ አሰራራቸው ስራት እዲይዙ አባ የማርያምን ገንዘብ
  አይስረቁ ገንዘብ ከቸገረወት እኞ እንረደወትአለን የንስሐልጆችወን ንስሐ ለሰዉአያውሩ
  ብሎሲጠይቃቸው ለማየት ያብቃህ ገና ጳጳስ እሆናለሁ ብለው ዛቱበት

  እኒህ ሰዉየ ክርስቲያኖች የሀይማኖት አባት ብለው ቅዱስ ሥጋውን ለመቀበል ብለው ንስሐ ሲነግሮአቸው ቤታቸው
  ሣይደርሱ ነው የክርስቲያኖችንስሀ የሚያወሩት በዚህ ምክንያት ብዙዎች ሀገርእስከ መቀየር ደርስዋል
  ብዙወች ከጏደኞቻቸው ማህበራዊኑሮ ተገልለዋል ሞራናቸው ተነክቷል

  እኔም ንስሀየን አውጥተብኞል በጃቸው ከባለቤቴጋር ካቆረቡኝ በኌላ አንድ ነገር ሣይቀር ንስሀየን ለሰውተናገሩብኝ
  በዚህ ምክንያት የምወደውን ከተማትቸ ከተማቀይሬ ከባለቤቴር እኖራለሁ እደአንድ ክርስቲያን አላፌነቴለመወጣት
  የዚህ ወሸታም መነኩሤ ክፉ ስራ ከሞላጎደል ለማጋለጥነው የፅውፉ አላማ
  ከአርባምንጭ ቅዱስገብርኤል እስከፍራንክፈርት ያለውንጉድ ለመለውአለም
  ወደ ሀገርቤት በረራባለቁጥር ውራጂና ሞባይል ይዘው ኤርፖርት ለመላክ ያጠመደ ይይዛቸዋል ብሎ አምሀ ሸንቁጤፅፎባቸውነበረ ልክነው ሁሉያገኞቸዋል፣

  ለዚህነው የብዞችንስሐየሚናገሩት
  በርግጥ በወቅቱ ምእመናን ነገሩን ትኩረት ያልሰጡት ሲኾን፣ እንዲሁም እሣቸው ምንያውቃሉ እያሉብዙወች ይከራከሩላቸውነበረ እሩቅሣንሄድ በትላንትነው እሁድብቻ ቁጥራቸው ከአስርያላነሱክርስቲያኖችን አባሲራክ ለምን
  ጥያቄአነሣችሁ ብለው ካዳራሽ አባረዋቸዋል
  ህዝቡን በቋንቋ እና በዘር ከፋአፍለውት ይገኞል በተለይ በዚህ ሰሀት
  ሊቀጳጳሱም ለሲኖዶስ የጻፉት ደብዳቤ እውነት ያላዘና የልቅስ ወገናዊ ይመስላልና አስመራጭኮሜቲው በራሱመንገድ
  ሰለነውረኞመነኮሣት እዲያጣራ በትትናእናሣስ

 2. Mulugeta July 12, 2016 at 2:59 pm Reply

  የሚነሶታው ኣባ ዘርኣዳዊት እና የመዘክር ክፍል ሀላፊው ንቡረእድ ገብረ ማርያም በዝርዝሩ አለመካተታቸው ምክንያቱ ይታወቃልን? ኣባ ዘራዳዊት ቤተ ክርስቲያናቸውን በታማኝነት እያገለገሉ ኣሉ መልካም ኣባት ናቸው። በምንኩስና ህይዎታቸውና በምህርታቸውም ምንም እንከን ያልታየባቸውና እራሳቸውን በዘመናዊ ትምህርት ይንውፁ መልካም ኣባት ናቸው። ንቡረድ ገብረማርያም የአድስ ኣበባ ስራኣስኪያጅ በነበሩበት ጊዜ ሃገረስብከቱን ከዘረፋ የጠበቁ ታማኝ ኣባት ናቸው እርግጥ ስለትምህርት ደረጃቸው ብዙ ባላቅም ጥቅመግብነትን ያሸነፉ ኣባት ስለነበሩ ብዙዎች የጎደላቸውን ዘረፊነት የተፀየፉ ስለነበሩ ይካተታሉ የሚል ግምት ነበረን።

  የቨርጅኒያው ኣባ ፊልጶስ የመጀመሪያውን ማጣሪያ ማለፍቸው የሚያስገርም ንው። የጫኑት ሳንጣ ልብስ ሰርቱኣል ማለት ነው፤ ነገር ግን ኣባ ፍልጵስ በከፋፋይነትቸው ስርኣተ ቢተ ክርስቲያንን በማቃለልና በሊላም የስጋ ድካም የሚታሙ ናቸውና ሁለተኛውን ማጣሪያ ባያልፉ ጥሩ ነው።

  ሹመት ከሚያስፈልጋቸው ሃገረ ስብከቶች የሰሜን ኣሜሪካው የካሊኦርኒያ ሃገረ ስብከት ኣለመካተቱ ምክንያቱ ምንድን ነው። ወይንስ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ኣቡነ አዎስጣቴዎስ ወደቦታቸው ሊመደቡ ታስቦ ይሆን። ቢሆንም መልካም ነበር።

  በጠቅላላው ለኮሚቴው ኣባቶቻችን ጥበቡን ገልፆላቸው ለቢእተርስቲያን የሚጠቅሙትን በሃይማኖት የፀኑትን ህዝበ ክርስቲያኑን የሚመክሩትን የሚመክሩትን የሚያፅናኑትን ችግሩን ኣብረው የሚቸገሩለትን ከፍቅር ንውይ የራቁትን በክህድት ኣብዜ ያላበዱትን ከታወቁት የስጋ ፈተናዎች ሃሜት የፀዱትን መልካሞቹን ይመርጡ ዘንድ እግዚኣብሄር እንድረዳቸው በፀሎትም እንግዛቸው። ኣስተያየትና ጥቆማ ብቻ መስጠቱ በቂ ኣይደለምና።

  ያባሰረቀና ያባ ቃለፅድቅ ስም ኣለመካተቱ መልካም ነው፤ ነገር ግን፣ የቢተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የስራ ኣመራርም መሆን አለባቸው ብየ አላምንም፤ በክህደትና በዘራፊነት የተሳተፉ ኣገልጋዮች ለጥፋታቸው ተመጣጣኝ የሆነ ቅጣት እንጅ ከዘረፉበት ወዳልዘረፉበት እያዛዎሩ ቤተ ክርስቲያንን የሌባ መጫዎቻ ማድረግ በሃላፊነት ማስጠየቅ ኣለበት፡፡ ይህንን የምያደርግ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ኣመራር ከዘራፊዎቹ የበለጠ መጠየቅና እስልጣኑ መሻር ኣለበት ጳጳስም ቢሆን ፓትርያርክም ቢሆን። ተጠያቂነት ያላበት ከፍተኛ የአሰራር ሂደት ከአጥቢያ እስከ ሲኖዶሱ መዘጋት ኣለባት።

  • Anonymous July 12, 2016 at 6:11 pm Reply

   ጥሩ ብለሀል። የሰው ሐሳብና የመንፈስ ቅዱስ ሐሳብ ግን ልዩ እንደሆነ አትርሳ።

  • Anonymous July 12, 2016 at 6:29 pm Reply

   ኧረ አትቆስቁሱን እንኳን ስማቸው ሳይወጣ ቀረ፤ መቼም ጉዳቸው ከሚወጣ ስማቸው ባይወጣ እንደሚመርጡ እተማመንባቸዋለሁ፣ በተለይ የውጪዎቹ “መነኮሳት”

 3. Anonymous July 12, 2016 at 6:27 pm Reply

  “ፀባቴ አባ” የማነ ብርሃን ዓሥራት / አሜሪካ– አትላንታ መድኃኔ ዓለም አለቃ/???????????????????????

 4. Anonymous July 12, 2016 at 9:59 pm Reply

  ሊቀጰጳሱ አባ ሙሴ ለአባ ሲራክ ከጻፉ ምንማለት ነው።

 5. axumita July 12, 2016 at 11:56 pm Reply

  በቃ እኛ የአባቶቻችን ሀጥያት ገምጋሚዎች ሆንን አረ ምእመናን ወዴት እየሄድን ነው ቆም ብለን እናስብ እንጸልይ ለአባቶቻችን ቀርቶ ሀጥያተኞች ናቸው ብለን በሙሉ አፋችን እንናገራለን።

 6. እምነት ስለእውነት July 13, 2016 at 6:06 am Reply

  በጣም ያሳዝናል ለመሆኖ ጳጳሳቱ በሕይወት አሉ ወይስ አልቀዋል። ምንም ማህበረ ቅዱሳን ቢያሽከረክራቸውም ነገ ለምታልፍ አለም ሕልውናቸውን ክደው ይህን አይነት የወረዳ ሥራ ይሠራሉ ተብሎ አይገመትም። ወይም ቤተክርስቲያንን አሳልፈው ለማህበሩ ይሰጣሉ ብሎ መገመትም በጣም ያስቸግራል። ለመሆኑ አባ ሰረቀ እና አባ ቃለ ፅድቅ አልተካተቱም ማለት ቁማር መጫወት ማለት ነው ። ፍትህ በሌለበት ሀይማኖት ከመኖር በደዊ መሆኑንና መለየት ይመረጣል አባቶች እባካችሁ ለእግዚአብሔር ብላችሁ በሐቅ ሥሩ ቸር ይግጠመን ።

  • Anonymous July 13, 2016 at 2:49 pm Reply

   ዥልጥ የመናፍቅ ቡችላ

 7. kidane1 July 13, 2016 at 7:45 am Reply

  የውስጡን ባላውቅም የተሰጠው አስተያየት እና ሂስ በጣም ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ነው፡፡ እግዚአብሄር ከዘረኝንተት ፈተና ይጠብቅልን ብየ ልመርቃቹ እፈልጋሎህ፡፡

 8. kidane1 July 13, 2016 at 7:54 am Reply

  በስመ ክርስትናቸው እና ስመ ክህነታቸው ስለሚጠሩ እንጆ ትግሬዎች አይደሉም ፡፡ ገግሞ ትግሬ ተሾመ ብለው እንዳያምፁብን ማብራሪያ ለመስጠት ነበር፡፡

 9. Anonymous July 13, 2016 at 9:19 am Reply

  ባለፈው ስማቸው በተጠቀሱ እንከን ባለባቸው የተወሰኑ መነኮሳት አዝነን ነበር፡፡ አሁን አልተጠቀሱም ፡፡ ጥሩ እየሄደ ይመስለኛል፡፡ እንግዲህ እግዚአብሔር መንጋውን የሚጠብቁለትን ይምረጥ፡፡ የንታ ዕዝራ ግን ባንድ በኩል ጳጳስ ቢሆኑ የሚያስደስት ሲሆን የመጻሕፍት ትርጓሜው ጉባዔ ነገር ግን ያሳስባል፡፡ ጉባዔውን ባይለቁ፣ ጳጳስ ከሚሆኑ ሌሎች ብዙ ጳጳሳትን ቢወልዱ አይሻልምን፡፡ ብቻ የጉባኤ መምህራን ባይነኩ ጥሩ ነበር፡፡

 10. teddy July 13, 2016 at 10:41 am Reply

  የንታ ዕዝራ ግን ባንድ በኩል ጳጳስ ቢሆኑ የሚያስደስት ሲሆን የመጻሕፍት ትርጓሜው ጉባዔ ነገር ግን ያሳስባል፡፡ ጉባዔውን ባይለቁ፣ ጳጳስ ከሚሆኑ ሌሎች ብዙ ጳጳሳትን ቢወልዱ አይሻልምን፡፡ ብቻ የጉባኤ መምህራን ባይነኩ ጥሩ ነበር!!!

 11. Anonymous July 13, 2016 at 11:23 am Reply

  የአባ ፊልጶስ አሻግሬ(አሜሪካን – ሚችጋን ዴትሮይት አቡነ ተክለ ሃይማኖት ደብር) በዕጩነት መቅረብ በጣም የሚደነቅና ለቤተ ክርስቲያን ኩራት ነው፡፡ በቃል ብቻ ሳይሆን በህይወት የሚያስተምሩ በመንፈሳዊም ሆነ በዓለማዊ ዕውቀት የመጠቁ፤ ወቅቱ የሚፈልጋቸው ዕንቁ የቤተ ክርስቲያን ልጅ ናቸው፡፡ በትክክል የመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ሆኖም እንደሚመረጡ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ይደልዎ! ይደልዎ! ብለናል፡፡

 12. Anonymous July 13, 2016 at 12:02 pm Reply

  መንፈስ ቅዱስ አዋቂ ነው፤ እኛ ተንጫጫን አልተንጫጫን ለበረከት ከፈቀደልን ብሩካን ጳጳሳት በዚህ ዝርዝር ውስጥ ኖሩም አለኖሩም በረቀቀ ምሥጢሩ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ይመርጥልናል፡፡ ለምህረት አትበቁም እስክትመለሱ ንስሐ እስክትገቡ አሳልፌ እሰጣችሆለሁ ካለም ወደ ሕሊናችን መመለስ ንስሐ መግባት ነው እንጂ ሌላ ምርጫ አይኖረንም፡፡

 13. […] Source: የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት 16 ነው፤ በየአካባቢው የተለዩትን … […]

 14. ዳዊት July 13, 2016 at 3:06 pm Reply

  እውነትም ጥሩና ከፍተኛ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አባ ቃለ ፅድቅ ከዚህ ውድድር ውጪ መሆኑ ብቻ ያሳያል።ሀራ ተዋህዶዎች እናመሰግናለን።እባካችሁ ለአስመራጭ ኮምቲዎቻችን የበረከትና የፀጋ ባለቤት የሆኑትን አባቶች በጥንቃቄ እንዲመርጡ ንገሩልን።አሁንማ እኮ አባት አባት የሚሸት ጳጳስ እንዳይጠፋ ያስፈራል።ስብከት እና ፀጋ ከላይ የተቸራቸው የቤተ ክርስቲያን እንቊ የሆኑት አባት አባ ወልደ ሀና ፀጋው፣እግዚአብሄር ፈቅዶ እርሳቸው ቢመረጡ በሚያስተምሩት ትምህርት ህይወታችንን የሚያለመልሙበትን ፀጋቸውን የበለጠ ይሰሩበታል ብየ አምንባቸዋለሁ።ይህ ደግሞ የኔ ብቻ ሳይሆን የሳቸውን ጉባኤ የተከታታለና የሚያውቃቸው ሁሉ ምኞት ነው።ምክንያቱም ንፅህናን ከእውቀት እንዲሁም ከትህትና ጋር አሟልቶ ሰጥቷቸዋል።በረከትዎ ይድረሰኝ አባታችን

 15. YEMANEBERHAN July 13, 2016 at 9:14 pm Reply

  As Bisrate Gabriel Ethiopian Orthodox Church begins the 2012 New Year we are faced with new opportunities to grow
  spiritually and unite as a strong church family to face and overcome obstacles. Towards this end, with God’s grace,
  we are making great progress in addressing our biggest challenge in our church history thus far – the transition into a
  new era without the leadership of Tsebate Yemanebrhan. The parish council recognizes that this transition and
  reasons surrounding this change in leadership is at times difficult to comprehend and more often painful for our
  members to absorb. However, we want our members to be encouraged by the fact that the parish council has
  administered decisions regarding this matter in a manner that is Godly and at all times in the best interest of the
  members of the church.
  As the parish council struggled and deliberated on decisions during past year, our primary focus was to ensure that
  our church remains a peaceful, safe and orderly place of worship and refuge for members and friends. At this
  juncture in the transition period, the parish council would like to provide our members with insight on the
  deliberations that occurred and the body of evidence that supported the final decision to accept Tsebate’s resignation
  of January 2011 and to reject his request to return to his leadership position in November 2011. We hope that this
  information will clarify questions that our members may have regarding this matter. The following information,
  while difficult and painful to digest, is part of the body of evidence that was available to our parish council that
  required decisive action to protect the ongoing concern of our church family. Our members and friends can rest
  assured that the parish council has lived up to the fiduciary responsibility of representing our congregation in
  addressing this difficult challenge in our church history with compassion, justice and charity.

 16. YEMANEBERHAN July 13, 2016 at 9:14 pm Reply

  A: Information relative to Tsebate’s Resignation:
  1. Resignation
  (Exhibit No. 1 – Exit Plan email dated December 1, 2010)
  Tsebate was paid regular salary for December 2010 and January 2011.
  In addition, the church paid Tsebate a lump sum of $15,000, details are as follows:
  1. $8,500 for retroactive salary adjustment (to compensate for last salary increase which occurred in 2005)
  2. $4,000 for years of service appreciation
  3. $2,500 for annual Christmas gift
  Total= $15,000
  The church members collected 2 monetary farewell gifts for Tsebate to assist in his journey
  1. $8,030 was collected and given to Tsebate on 1/16/2011
  2. $1,400 was collected and given to Tsebate on 1/23/2011
  Total = $9,430
  The church purchased Tsebate’s personal furniture for $1,915
  The church also rented Tsebate’s personal condominium to house the new priest. ($750 monthly)
  Tsebate’s official relationship with the church ended on January 31, 2011.
  Witnesses for the email – Mimi Moges, Zewde Tesfaye, Samuel Belete, Ethiopia Mengestu, Solomon Yonas, and
  Tsehay Berhanu
  Page 2
  2. Request To Return – May 2, 2011
  (Exhibit No. 2 – Request to Return email dated May 2, 2011)
  On May 2, 2011, Tsebate wrote an email expressing interest in returning to Atlanta and asked for air ticket and for
  church guest quarters to be prepared for him.
  Witnesses for the email – Mimi Moges, Zewde Tesfaye, Samuel Belete, Ethiopia Mengestu, Solomon Yonas, Tsehay
  Berhanu, and Mariamawit Habtamu
  3. Response to May 2, 2011 Email – June 5, 2011
  (Exhibit No. 3 – Response to May 2, 2011, email dated June 5, 2011)
  On June 5, 2011, the administrative committee (Parish Council) wrote back Tsebate indicating he has permanently
  separated from this church, and that he should not entertain a return and resumption of formal duties.
  Witnesses for the email – Mimi Moges, Zewde Tesfaye, Samuel Belete, Ethiopia Mengestu, Solomon Yonas, and
  Tsehay Berhanu
  4. 2nd Request to Return – November 29, 2011
  On November 29, 2011, Tsebate and Parish Council met and he requested that he be allowed to return to his
  position as Head Priest and Administrator.
  Witnesses for the Meeting – Mimi Moges, Zewde Tesfaye, Samuel Belete, Ethiopia Mengestu, and Tsehay Berhanu

  5. Rejection of Tsebate’s Request to Return – December 1, 2011
  On December 1, 2011, the Parish Council met and evaluated all relevant information pertaining to Tsebate and his
  request. Based on evidence, credible information, and suggestion from legal counsel, Parish Council, by majority
  vote, decided to reject Tsebate’s request to return to the church. He was instructed not to come to the church.
  Witnesses for this Action – Mimi Moges, Zewde Tesfaye, Samuel Belete, Ethiopia Mengestu, Tsehay Berhanu, and
  Mariamawit Habtamu
  B. Body of Evidence that was instrumental in the Parish Council’s Decisioning Process:
  Tsebate is alleged to have committed several offences for which the parish council has denied his request to
  return to the church as head priest. The following is a list of these alleged offences and the evidence
  supporting each offense:
  NOTE: The parish council has absolute proof of the statements made herein, however upon the advice of legal
  counsel, the recommended verbiage to communicate information to congregants is to use terms such as
  allegations/alleged as protection from unnecessary litigation. In the opinion of the majority of the parish
  council, there is no doubt in our minds that the following information warrants Tsebate’s complete and
  permanent removal from any authoritative position or attendance of any services or activities to be held now or
  in the future at Debre Bisrat St. Gabriel Ethiopian Orthodox Church in Atlanta Georgia. The parish council is
  providing this information to the members of the church so that they may also come to their own conclusion
  regarding the moral integrity of Tsebate and the potential legal liability any future association with him may
  impose upon the church and or its members.
  Page 3
  1. Allegations of sexual Misconduct supported by Tsebate’s confession:
  a. Specific and separate instances allegedly occurring with adult women between early 2009 and Nov
  2010 for which he has confessed to parish council members
  b. An alleged lifetime history of living a double life of sexual misconduct with adult women for which he
  has confessed to parish council members in a meeting held on Nov 29, 2011
  c. Tsebate has recently retracted one specific incident and confession of sexual misconduct however all
  other admissions and confessions remain as stated and are outstanding.
  NOTE: “sexual misconduct” is defined as Tsebate’s contravention of his oath of celibacy
  2. Allegations of attempted extortion and coercion:
  a. The parish council obtained an email wherein Tsebate threatened the recipient of the email with
  emotional and physical harm if he or she did not assist in Tsebate’s return to the church. Tsebate also
  threatened to file criminal charges based on allegedly false accusations of wrongdoing. The recipient of
  the email was forced to hire an attorney.
  b. The attorney’s response to Tsebate’s email includes the following warnings regarding his alleged
  attempts to blackmail the attorney’s client:
  i. The purpose of this letter is to place you on formal notice that you are hereby demanded to
  cease and desist from undertaking any further action to harass, threaten, cause emotional
  distress to, blackmail, demean, impugn the character and reputation of [the client]
  ii. Our office is in receipt of numerous correspondences you have sent to [client] wherein you
  threaten emotional and physical harm to our client unless [client] assists you in coming back to
  Debre Bisrat St. Gabriel Ethiopian Orthodox Church
  iii. You also illegally attempt to blackmail [client] and force [client] to aid in your return after you
  violated your oath as a priest and pledge of purity
  c. Tsebate attempts to intimidate a parish council member and makes 2 demands. In an email the parish
  council obtained, Tsebate demands the parish council member to do the following:
  i. “My last question to you is based on your vow to my return to my church; do you want me to
  return to my church? I need just two things from you: 1. facilitate my coming and make it
  smooth. 2. You have to fire the individuals that you hired to do the dirty job for you;”
  3. Alleged threats of violence:
  a. The attorney warns Tsebate regarding his threats to the client and quotes Tsebate’s threats. According
  to the attorney, Tsebate allegedly wrote the following:
  i. :” . . . you will shade not only regular tears but tears mixed with blood. As you made them lose
  what they sacrificed everything for, you will lose everything that you have sacrificed and labored
  for…”
  Page 4
  ii. “I don’t want to hurt anybody and destroy anybody’s life…So I don’t want to regret later by doing
  the thing that I don’t want to do it on anybody’s life.”
  b. Having read Tsebate’s emails, the attorney told Tsebate: “Your threats are an outrage and go against
  the very fabric of everything expected from a spiritual leader.”
  4. Alleged breach of the penitent-priest privilege:
  a. Written evidence that Tsebate released information that he received in confession by a congregant.
  b. One of the reasons why the parish council has been advised not to share either Tsebate’s emails or the
  attorney’s letters is because there is no way to share this correspondence without perpetuating
  Tsebate’s breach of the penitent-priest privilege, which we hold sacred.
  5. Allegedly false misrepresentations:
  a. As evidenced in a recent retraction letter to the attorney of a congregant, Tsebate confesses that he lied
  and made slanderous comments because of his rage and anger towards the attorney’s client.
  b. In a recent radio broadcast, Tsebate denies having received any notice from parish council members
  stating that he cannot return to his position. Parish council sent an email to Tsebate in June 2011 and
  Tsebate responded specifically quoting the Parish Council’s email in a June 14, 2011 email.
  i. Parish council’s letter to Tsebate recommending he does not return to his position as priest (see
  Exhibit 3)
  ii. Tsebate’s response to Parish council’s letter (June 14, 2011) (see Exhibit 4)- excerpts are as
  follows:
  1. “I received your email; thank you for asking the well-being of my family and myself. I
  found your email as very disappointing and hurting. I didn’t expect this kind of
  saddening response from the very people that I chose to assist me in administrating the
  church…. Do I not deserve to visit my church and celebrate the holiday even for one
  time? Am I the most wanted criminal not to be in America?
  2. “Regarding your request to chose a clergyman that can assist you in giving a verdict on
  my priestly life and my future, nobody has the right to give a death sentence on my
  priestly life and future except God and the congregation. And as I told Samuel, when I
  come there, I will make everything clear to the congregants, my past, present and future.
  Then you will get the chance to question me whatever you have in mind.”
  3. “You warned me ‘not to entertain’ returning to the church. If I committed crimes against
  the church, individuals, or the American government, I will be judged by the law not by a
  few individuals that I handpicked to serve the church temporarily not lifetime service like
  the justices of the Supreme Court.”
  c. As evidenced in recent radio broadcast, Tsebate denies any wrong doing and thereby continues a
  pattern of deception that attempts to mislead members of the church & community

  • Anonymous July 14, 2016 at 6:01 am Reply

   ሀራዎች የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከቱ መናፍቅ በዚህ ላይ ጉበኛ ስራ አስኪያጅ መናገርያ አፍ ስለሌለው ወደዳችሁት አይደል በጠራራ ፀሀይ በአይነ ስውር ደላላነት የሊቃውንት ጉባኤ አባል ጉቦ አቀባይ ከሆነ ሌብነት ሀጢአት አይደለም ወደሚለው አስተሳሰብ ይመጣና ከቤተክርስቲያን አልፎ ለሀገር ችግር ስለሚሆን መጋቢ እዝራ ተው መንገድህ አይደለም ብትሉት ስራውን ትቶ የአለቆችና ፀሀፊዎች ደላላ ሲሆን ጒይቶምስ ቢሆን አይናማ ሌባ አጥቶ ነው እንዲህ የሚሰራው ሆዳም መናፍቅ በሉት

   • Anonymous July 14, 2016 at 11:02 am

    እግዚአብሄር ይባርክህ አንተም እንደኔ ጒይቶም በልቶሀል የእውር ሲሳይ ሁነሀል

   • Anonymous July 14, 2016 at 11:17 am

    እግዚአብሄር ያፅናህ አንተም እንደኔ ጒይቶም በልቶሀል የእውር ሲሳይ አድርጎሀል ዋይ 30 ሺህ 17 ሺው የብድር ምን ልሁን ልበድ ዋይ የሀይማኖት መረ ሰሚ ጆሮ ይጥፋ ዋይ ማን ይሆን ይህ የማይታወቅ ጅብ ፈቶ የለቀቀብን የስራ ቛንቛ አማርኛ ሳይማር ዘረፋው ምኔ ተማረው ዋይ ዋይ የተቀደደ ጫማ ከወር በፊት አድርጎ ገብቶ ዛሪ የቱርክ የጣልያን ጫማ ኪሱ በብር አጭቆ ይወጣል ሲወጣ የሚካፈለው ከሌለው በቃ ሚልዪነር ነው ግን አማኝም ቢሆን የአባት

 17. Anonymous July 17, 2016 at 5:48 am Reply

  ከሐድያ ና ከንባታ ሀገረ ስብከት ለኤጵስቆጶስነት በዕጬነት የቀረቡት አባ ኄኖክ ተክለ ጊዪርጊስ የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የደብር አለቃ ቤተክርስቲያንን በቅንነት፥በታማኝነት እያገለገሉ ያሉ አባት ናቸው ከዚህ በተጨማረ ቤተክርሰቲያን በልማቱ ዘርፍ እራሷን እድትችል ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ምእመናን በማሥተባበር ከፍተኞ ውጤት አሥመዝገበዋል ለዚህም ከዚህ በፈት ተመድበው ያገለገሉባቸዉ አና አሁን እያገለገሉ የሚገኙበት ቤተክርስቲያን ምእመና ምሥክር ናቸው ስለዚህ እኝህ አባት በሁሉም ዘርፍ ለቤተክርስቲያን ሙሉ አገልግሎት የሚያበረክቱ ናቸው።

 18. Dawit Teklu July 18, 2016 at 7:06 am Reply

  አባ ሄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ ለጵጵስና መታጨታቸው ይገርማል አባትነታቸው ለአማንያን ሳይሆን ለከሃድያን ካልሆነ በቀር። የሳቸው አይነት ከዲያቢሎስ የከፋ አታይ ለምንኩስናው እንኳን ስድብ ነው።

  • Anonymous July 22, 2016 at 2:40 pm Reply

   ….እንያልን ዘወትር በጸሎተ ኪዳኑ እንደምንለምነው፤ የሆሳዕና ደብረ ገነት ፍሬ፤ የገዳመ ኢየሱስ መነኮስ፤ የብጹ አቡነ መልከጸዲቅ የመንፈስ ልጅ ፤ በትህትናቸው ለሁሉም እኩልገና አክብሮትን በመስጠት ፍቅርን የሚሰብኩ፤ የወንጌል አርበኛ፤ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርትን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ያደጉ ፤ ለሰው አዛኝ ፤ ሰውን በሰውነቱ የሚያከብሩ በሄዱበት ሁሉ መልካም ስራን የሰሩ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ለታላቁ ማእረገ ምንኩስና የተጠሩ፤ የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋይ ፤ ቆሞስ አባ ኄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ (የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አለቃ) እጅግ ትሁት እና የፍቅር አባት በመሆናቸው በተለይም አሁን ለኤጲስቆጶስነት ለታጩበት አህጉረ በተለይምቦታውስብከት ለቦታው የሚያስፈልጉ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ የሚፈልጋችው በመሆናቸው ሁላችንም ልንደግፋቸውና በጸሎት ልናስባቸው ይገባል ።

   ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

 19. Dawit Teklu July 18, 2016 at 7:08 am Reply

  አባ ሄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ ለጵጵስና መታጨታቸው ይገርማል አባትነታቸው ለአማንያን ሳይሆን ለከሃድያን ካልሆነ በቀር። የሳቸው አይነት ከዲያቢሎስ የከፋ አታላይ ለምንኩስናው እንኳን ስድብ ነው።

  • ዲያቆን አብርሃም አንዳርጌ July 22, 2016 at 2:29 pm Reply

   ….እንያልን ዘወትር በጸሎተ ኪዳኑ እንደምንለምነው፤ የሆሳዕና ደብረ ገነት ፍሬ፤ የገዳመ ኢየሱስ መነኮስ፤ የብጹ አቡነ መልከጸዲቅ የመንፈስ ልጅ ፤ በትህትናቸው ለሁሉም እኩልገና አክብሮትን በመስጠት ፍቅርን የሚሰብኩ፤ የወንጌል አርበኛ፤ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርትን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ያደጉ ፤ ለሰው አዛኝ ፤ ሰውን በሰውነቱ የሚያከብሩ በሄዱበት ሁሉ መልካም ስራን የሰሩ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ለታላቁ ማእረገ ምንኩስና የተጠሩ፤ የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋይ ፤ ቆሞስ አባ ኄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ (የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አለቃ) እጅግ ትሁት እና የፍቅር አባት በመሆናቸው በተለይም አሁን ለኤጲስቆጶስነት ለታጩበት አህጉረ በተለይምቦታውስብከት ለቦታው የሚያስፈልጉ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ የሚፈልጋችው በመሆናቸው ሁላችንም ልንደግፋቸውና በጸሎት ልናስባቸው ይገባል ።

   ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

 20. Anonymous July 18, 2016 at 9:09 pm Reply

  ለሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አህጉረ ስብከት ምን ታስቧል?

 21. ብሩክ አከለ July 19, 2016 at 1:19 am Reply

  አባ ፊሊጶስ ከበደ በአሜሪካ በጣም የተወደዱና መካሪ አስታራቂ በተለይ በሒውስተን ቴክሳስ ከተማ ህጻናቶችን ግዜ ወስደው በማስተማር የሀገራቸውን በዓልና የቤተክርስቲያኒቷን ስርዐትና ደንብ በማስተማር ለድቁና ማእረግ በማድረስ ምእመኑን በፍቅር በመያዝ የታወቁ ጥሩና ለወደፊቱም ትልቅ ሚና የሚጫወቱ ትሁትና መካሪ ለትንሹም ለትልቁም ታዛዥ አባት ናቸው።

 22. Abrham Degene July 22, 2016 at 2:41 pm Reply

  ….እንያልን ዘወትር በጸሎተ ኪዳኑ እንደምንለምነው፤ የሆሳዕና ደብረ ገነት ፍሬ፤ የገዳመ ኢየሱስ መነኮስ፤ የብጹ አቡነ መልከጸዲቅ የመንፈስ ልጅ ፤ በትህትናቸው ለሁሉም እኩልገና አክብሮትን በመስጠት ፍቅርን የሚሰብኩ፤ የወንጌል አርበኛ፤ የቤተክርስቲያኒቱን ትምህርትን ጠንቅቀው የሚያውቁ፤ ከልጅነታቸው ጀምሮ በቤተክርስቲያን ጥላ ስር ያደጉ ፤ ለሰው አዛኝ ፤ ሰውን በሰውነቱ የሚያከብሩ በሄዱበት ሁሉ መልካም ስራን የሰሩ፤ በመንፈስ ቅዱስ ጥሪ ለታላቁ ማእረገ ምንኩስና የተጠሩ፤ የእግዚአብሔር እውነተኛ አገልጋይ ፤ ቆሞስ አባ ኄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ (የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል ደብር አለቃ) እጅግ ትሁት እና የፍቅር አባት በመሆናቸው በተለይም አሁን ለኤጲስቆጶስነት ለታጩበት አህጉረ በተለይምቦታውስብከት ለቦታው የሚያስፈልጉ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ የሚፈልጋችው በመሆናቸው ሁላችንም ልንደግፋቸውና በጸሎት ልናስባቸው ይገባል ።

  ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: