ካህናትና ሕዝቡ በተሳተፉበት ምርጫ ጵጵስና መሾም ታላቅ ዕድል ነው፤ ከነቀፌታ የጸዱትን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ያሻል/ብፁዕ አቡነ ሙሴ/

His_Grace_Abune_Mussie

 • ለኤጲስ ቆጶስነት ከሚያበቁ መስፈርቶች ቀዳሚው፣ የቅድስና ሕይወት ነው
 • የቅድስና እና የድንግልና ሕይወቱ፤ በሕዝብ የተመሰከረለት መኾን አለበት
 • የሕዝብ አስተያየትና የካህናቱ ግምገማ ከሌለ፣ አባቶችን ማግለል ይከተላል
 • ከምርጫ በኋላ ሳይሾሙ ማቆየት፣ ችግር ያለባቸውን ለመቃወም ያስችላል
 • ሢመቱ፥ በወገን ብዛት፣ በገንዘብ ኃይል አይደለም፤ መኾንም የለበትም
 • ከእኛ የተሻሉ፤ከነቀፌታ የጸዱ አባቶችን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ያሻል

*               *               *

ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ አኹን ለደረሱበት ከፍተኛ ሓላፊነት፣ በ1989 ዓ.ም. ከሌሎች ጋር ተወዳድረው ከተመረጡ በኋላ፤ በ1991 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ በኤጲስ ቆጶስነት ማዕርግ ተሾሙ፡፡ እንደተሾሙ፣ በተባበሩት ዐረብ ኤምሬትስ ለተወሰነ ጊዜ ከሠሩ በኋላ፤ በምሥራቅ ትግራይ ሀገረ ስብከት ለኹለት ዓመታት አገልግለዋል፡፡

ብፁዕነታቸው፣ ምሥራቅ ትግራይ(ዓዲ ግራት) ከገቡ በኋላ፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ ይከሠት የነበረው ድርቅ ተወግዶ በምትኩ ዝናም በመዝነሙና አዝመራው ተሳክቶ ጥጋብ በመኾኑ የዓዲ ግራት ሕዝብ፣ “የበረከት አባት” የሚል የቅጽል ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ ከምሥራቅ ትግራይ ወደ ሀገረ እንግሊዝ እንደተዛወሩም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ አብያተ ክርስቲያናትን አስፋፍተዋል፡፡

ዳግም ወደ አገራቸው ተመልሰው፣ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ በእነዚኽ ዓመታት ካከናወኑዋቸው መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ክንዋኔዎች መካከል በወሊሶ ከተማ ያሠሩት ባለአምስት ክፍል መንበረ ጵጵስና እና ሙዓለ ሕፃናት ት/ቤት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በአኹኑ ጊዜ የአውሮጳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመኾን በማገልገል ላይ ናቸው፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ፣ በሰኔ ወር 2004 ዓ.ም. እትሙ፡- ስለ ሢመተ ጵጵስና፤ ስለ መነኰሳት ወይም ጳጳሳት ሀብትና ንብረት መያዝ፤ በጳጳሳት ምርጫ ስለ ዕጩዎች ዜግነት፤ ከብፁዕነታቸው ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ፣ ለወቅቱ የቤተ ክርስቲያናችን የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎች ምርጫና ሢመት አጀንዳ ካለው ጠቀሜታ አንፃር እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን፡- ቤተ ክርስቲያናችን ሢመተ ጵጵስናን(የጳጳሳት ምርጫን) በተመለከተ የራስዋ የኾነ የምርጫ ሥርዓትና ሕግ እንዳላት ይታወቃል፤ ነገር ግን፣ አኹን አኹን ይህ ሕግ እየላላ መጥቷል፤ የሚሉ ወገኖች እየተበራከቱ ነው፡፡ ብፁዕነትዎ፣ በዚኽ ነጥብ ዙሪያ ያለዎት አስተያየት ምንድን ነው?

ብፁዕ አቡነ ሙሴ፡- እንደተባለው፣ ቤተ ክርስቲያናችን ሕግ አላት፡፡ ለኤጲስ ቆጶስነት ከሚያበቁት መስፈርቶች ቀዳሚው የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ ከልጅነቱ ጀምሮ የነበረው አኗኗሩ፤ የምንኵስና ሕይወቱ፤ የትምህርት ደረጃው የመሳሰሉትም አብረው ይታያሉ፡፡ ከዚኽም በላይ የቅድስናና የድንግልና ሕይወቱ በሕዝብ ዘንድ የተመሰከረለት(የታወቀ) መኾን አለበት፡፡ በፍትሐ ነገሥቱ በግልጽ እንደተቀመጠው፣ ከተመረጠ በኋላ ተመልሶ የሚያገለግለው ሕዝቡን ስለኾነ በምርጫ ጊዜ የሕዝብ ተሳትፎ ሊኖር ይገባል፡፡

በአኹኑ ጊዜ ሕዝቡ በመቃወምና በመደገፍ አስተያየት ስለማይሰጥና በምርጫው ስለማይሳተፍ፣ በካህናት በኩልም ግምገማ ስለማይኖር፤ አባቶችን የማግለል ኹኔታ ሊያስከትል ይችላል፡፡ አብረው ተማክረው የሠሩት ነገር ኹሉ ተቀባይነት አለው፡፡ በዚኽ መሠረት በድሮ ጊዜ፣ አባቶች ከየገዳማቱ ይመረጣሉ፤ በንጉሡና በሕዝበ ክርስቲያኑ በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው፣ ከታላላቅ አድባራት ጭምር የሚመረጡበት ኹኔታም ነበር፡፡

ከደርግ ጊዜ ወዲኽ ግን፣ ከየገዳማቱ ተመርጠው የመጡ ብዙ የሉም፡፡ እኛም የተመረጥነው፣ ከዚያ ቀጥሎ ባለው የኢሕአዴግ ጊዜ ነው፡፡ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የፕትርክና ዘመን፣ ቁጥራችን ወደ 40 የምንኾን ሊቃነ ጳጳሳት ሳንመረጥ አልቀረንም፡፡ እኛ የተመረጥነው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ እንጂ የሕዝብ ወይም የካህናት ተሳትፎ ባለው ኹኔታ አልነበረም፡፡

በእርግጥ እኛ ከተመረጥን በኋላ ሳንሾም ለኹለት ዓመት ቆይተናል፡፡ እንዲኽ መኾኑ ጥሩ ነው፤ ምክንያቱም፣ በዚኽ ጊዜ ከመካከላችን ችግር እንኳ ያለበት ቢኖር ተቃውሞ ሊቀርብበት ይችል ነበር፡፡ ከእኛ በኋላ በነበሩ ምርጫዎች ግን፣ ወዲያው ተመርጠው ወዲያው ነው የተሾሙት ማለት ይቻላል፡፡

እንደኔ እንደኔ፣ ካህናትና ሕዝቡ በተሳተፉበት ምርጫ መሾም ትልቅ ዕድል ነው፤ ምክንያቱም፣ ሢመቱ የሚገባው ከኾነ መንፈሳዊ ሥልጣን ነውና ይገባዋል፤ የማይገባው ከኾነ ደግሞ፣ ምንም አይደለም፣ ዋናው የምንኵስናው ሕይወት ነው፡፡

ኤጲስ ቆጶስ ለመኾን በቅድስና እና በንጽሕና ላይ የተመሠረተ የምንኵስና ሕይወት ሊኖር ይገባል፡፡ በቅድስናና በንጽሕና ሕይወት ያልቆየ ሰው፣ ደርሰው ትልቅ ሰው ነኽ፤ ቢሉት ያስቸግራል፡፡ የዚኽ ዓይነቱ አካሔድ ለሕዝቡም ለቤተ ክርስቲያንም ችግር ማስከተሉ አይቀርም፡፡

ከኹሉ በፊት ግን መታወቅ ያለበት፣ መንፈሳዊ ሥልጣን፥ በወገን ብዛት፣ በገንዘብ ኃይል የሚኾን አይደለም፤ መኾንም የለበትም፡፡ የቅድስና ሥራ ስለኾነ የሚከናወነው በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ነው፡፡ ወዳጅነትና ድጋፍ የሚሰጠው ለሥጋዊ ሥራና ሥልጣን ሲኾን ነው፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን፡- ብፁዕነትዎ እንደሚያውቁት፣ በቤተ ክርስቲያናችን ሕግ አንድ መነኵሴ ወይም ጳጳስ የግል ንብረትና ቤት ሊኖረው አይችልም፡፡ አኹን ግን አንዳንድ አባቶች፣ “የመንግሥት ባለሥልጣናት ታላላቅ ሕንፃዎችን ይገነቡ የለም ወይ? እኛስ አንዳንድ ጎጆ ብንቀልስ ምን ችግር አለው? በዐፄ ኃይለ ሥላሴ ጊዜም የግል ቤት የሠሩ አባቶች ነበሩ፤” ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ እርስዎ ምን ይላሉ?

ብፁዕ አቡነ ሙሴ፡- በመሠረቱ ቀደም ሲል ለመግለጽ እንደሞከርኩት፣ በምንኵስና ሕይወት የግል የሚባል ነገር ጨርሶ የለም፡፡ እኛ፣ ከመጀመሪያ ጀምሮ፣ እንኳንስ ሀብት ሕይወታችንን ለእግዚአብሔር ሰጥተን፤ ድህነትን ወደንና ፈቅደን በመምረጥ ነው እዚኽ የገባነው፡፡ እኛኮ ከሌላው የምንበልጠው፣ በገንዘብ የማይገኝ፤ በቅድስና የሚጠበቅ የምንኵስና ሥልጣን ስላለን ነው፡፡ በዓለማዊ ዕውቀት፤ በፍልስፍና፣ በአስተዳደር ጥበብ በመሳሰሉትማ የዓለም ሕዝብ ይበልጠናል፡፡ የምንኵስና ሕይወት የምናኔ ሕይወት ነው፤ የምንኵስና ሕይወት፣ ከሴትና ከገንዘብ መራቅ ነው፡፡

ሌሎች ሰዎች የነበራቸውን ሀብት ለቤተ ክርስቲያን ሲሰጡ፣ እኛ ያልነበረንን፣ የማይገባንን ሀብት እንደገና ወደ መሰብሰብ ከገባን፣ ሥራችን መንፈሳዊ መኾኑ ቀርቶ ሥጋዊ ስለሚኾን ለሥራችን ትልቅ ዕንቅፋት ይኾንብናል፡፡ እኛኮ በአኹኑ ጊዜ፣ ሥጋዊ ጠባያችንን ስላልተውን ይኾናል እንጂ፣ እንደ ድካማችን ተኣምራት ማድረግ እንችል ነበር፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ግቢ፣ ለእያንዳንዳችን ቤት ሠርታ የሰጠችን፣ የጋራ ማዕድ ያዘጋጀችው የግል የሚባል የላቸውም ከሚል ነው፡፡ የምንኖርበት ቤት፤ የምንበላው ምግብ የሕዝብ ሀብት ነው፤ ደመወዝ ምናምን የሚሰጠን እኮ ለግል ኪሳችን አይደለም፡፡ ለሐዋርያዊ ጉዞ ከቦታ ቦታ ስንቀሳቀስ፣ ገዳማት እንድንረዳበት፤ ደቀ መዛሙርት እንድናግዝበት፤ ድኾችን እንድንረዳበት እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ አንድ ሊቀ ጳጳስ የያዘው ሥልጣን የቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ በመኾኑም ለተወሰኑ የሥጋ ዘመዶቹ የቆመ ከኾነ፣ ሥልጣኑ የቤተ ክርስቲያን መኾኑ ቀርቶ የቤተሰብ(የግል) ይኾናል፤ ማለት ነው፡፡

የግል ሀብት ካለ የአሠራር አድልዎና ከሰው ጋር መጣላት ይኖራል፡፡ ደግሞኮ ትልቁ ኃጢአት ገንዘብ መውደድ መኾኑ መታወቅ አለበት፡፡ ባለጸጋ መነኵሴ ለእግዚአብሔር ሊገዛ አይችልም፡፡ በሀብት ብዛት የእግዚአብሔርን መንግሥት መውረስ አይቻልም፡፡ ምእመናንም በገንዘባቸው ምጽዋት ካልመጸወቱበት፤ ቤተ እግዚአብሔርን ካልሠሩበት፤ የተቸገሩትን ካልረዱበት አይመጻደቁበትም፤ አይሰመገኑበትም፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን፡- በ1991 ዓ.ም. ከወጡ አዲስ የሕግ አንቀጾች መካከል አንዱ፤ የውጭ ዜግነት ያላቸው ሰዎች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች እስከኾኑ ድረስ ጳጳስ ኾነው መመረጥ ይችላሉ፤ ይላል፡፡ ይህ ዓይነት ሕግ ቤተ ክርስቲያናችንን ዳግም ወደ ቅኝ አገዛዝ ሥር አያስገባትም ወይ?

ብፁዕ አቡነ ሙሴ፡- በበኩሌ ይህ ሕግ ጥሩ ነው፤ ባይ ነኝ፤ ምክንያቱም፣ ቤተ ክርስቲያናችን በአኹኑ ጊዜ መዋቅርዋን እያሰፋች፣ ዓለም አቀፋዊ እየኾነች ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በደቡብ አፍሪቃ እና በካሪቢያን በርካታ ተከታዮች አሉን፡፡ እግዚአብሔር ፈቅዶ ለዚኽ ደረጃ ቢደርስ፣ ጳጳስ ቢኾን ምን ችግር አለው? ለእነዚኽ ሕዝቦች ኢትዮጵያዊ ጳጳስ ብቻ ይሾምላቸው ካልን ሊከብድ ይችላል፡፡ አሠራሩ ከእምነታችን ጋርም አብሮ አይሔድም፤ ምክንያቱም፣ እምነታችን በቋንቋና በዘር ላይ የተመሠረተ አይደለም፤ መሠረታችን ክርስትና ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ኾኖ ዜግነቱን ለውጦ የሌላ ሀገር ዜጋ ከኾነ በኋላ ግን ትክክል አይደለም ባይ ነኝ፡፡

ዜና ቤተ ክርስቲያን፡- በአኹኑ ጊዜ ብዙ አባቶች፣ በእርጅናና በበሽታ ተዳክመው ይገኛሉ፤ በሞት የተለዩም አሉ፡፡ በአንፃሩ የቤተ ክርስቲያን ሥራ እየሰፋ ነው የመጣው፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ተተኪ አባቶችን ለመሾም አልዘገየምን?

ብፁዕ አቡነ ሙሴ፡- እርግጥ ነው፣ እኛ ከተሾምን ወዲኽ እንኳን፣ ከኻያ በላይ አባቶች በሞት ተለይተውናል፤ ያሉትም በሕማምና በእርግና ደክመዋል፡፡ በሌላ በኩል እንደተባለው፣ ሥራው እየሰፋ መጥቷል፤ ተቃዋሚም በዝቷል፤ በውስጥም በውጭም አህጉረ ስብከት ጨምረዋል፡፡ ከእነዚኽ እውነታዎች ተነሥተን ስናይ፣ በርግጥ ተተኪ ያስፈልጋል፤ ነገር ግን በቅዱስ ሲኖዶስ እና አሜሪካ ባሉት አባቶች የተጀመረው የዕርቅ ድርድር እልባት እስኪያገኝ ተብሎ ነው፣ እንዲዘገይ የኾነው፡፡

ኹለተኛው ምክንያት፣ በሚያስነቅፍና ባልተጣራ የምርጫ ኹኔታ መምረጡ አስቸጋሪ ስለኾነ ነው፡፡ ከእኛ የተሻሉ፤ ከነቀፌታ የጸዱ አባቶችን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ስለሚያስፈልግ ጊዜ ወስዶብናል፡፡ መጪው ምርጫ በገንዘብ እና በድጋፍ የማይኾን፤ ከገዳማት በአገልግሎትና በቅድስና የተመሰከረላቸው አባቶች የሚካተቱበት፣ የሚሳተፉበት መኾን ስለአለበት ነው የዘገየው፡፡

Advertisements

9 thoughts on “ካህናትና ሕዝቡ በተሳተፉበት ምርጫ ጵጵስና መሾም ታላቅ ዕድል ነው፤ ከነቀፌታ የጸዱትን ለማግኘት ብዙ ማጣራት ያሻል/ብፁዕ አቡነ ሙሴ/

 1. Anonymous July 11, 2016 at 11:54 am Reply

  እግዚአብሔ ር ይርዳን

 2. Bete Zewudu July 11, 2016 at 12:02 pm Reply

  ውድ አንባብያን ለንገልፅላችሁ እምንፈልገው ሰሞኑን የሀገርቤቱ ሲኖዶስ አዳዲስ የጲስ ቆጶሣትን በቁጥር ብዙ
  መነኮሣትን ለመሾም ፈልጎ ኮሚቴ አቋቁሞ ንፁህ ቅድሰናያላቸውን አባቶችን በመፈለግለይ ይገኞል
  በዚሁልክ የቩመና የአፍቅሮ ነዋይሱስ አያደረባቸው የስምመነኮሣት ባዮች በዚህ ዘመን በጣም ብዙናቸው
  ክርስቶስ ካሰተኞቹ መምህሪን ተጠንቀቁ ብሎአስተምሮናል ስለዚህ ምንያህል ከአሰተኞች ተጠብቀን ኑረናል
  ይህንን እድፅፍ ያነሣሣኝ በፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ቤተርስቲን ለይ ለሓያ አመት ሙሉ አንድነገር
  ሣያደርግ ህዝብን ከህዝብ አያላቀሰ የተጠራቀመው ገንዘብ እስከሚያልቅ ደመወዜን ተከፍሉኝ አላችሁ
  እያለ ህዝብ እያላቀሰ ለምን አባ እንዲህ ያደርጋሉ
  ለቤተክርስቲያኑ ምንእናድርግ ሲሉት እኔ ትግሬ ስለሆንኩኝ ሰው አይታዘዘኝም ሽዋ ብሆን ይታዘዘኝ ነበረ
  አባ ሲራክ ይህንን ይበልንጂ እራቱ ናምሰዉ የሽዋ ወይዛዝርት ነው ሲርበው
  እንደአዝማሪ ወሮ እከሊት ወጥ ይጣፍጣል የከሊትክትፎ ይ ጣፍጣል
  እያለ አንድነገር ለቤተክርስቲያን ሰይሰራ ሀያአመትሙሉ እንደሐረር ሰንጋ ደልቦብን ይገኞል
  እሁድ በማለዳ መቅደሱን ከፍቶ ፊቱን ወደህዝቡ መልሶ በስመአብ ከማለቱ በፊት ሶስት ጊዜ ያዛጋል
  አሀዱሲልም እያቛረጠ ይስላል አንድቀን ስማን መጥራት እማልፈልገው የሚስጢር ጓዸኝ ለምድነው መቅደስ ሲገባ አባ
  የሚያዛገው አሀዱሲል አቋርጠው የሚሥሉት አለች ልማድ ቀርቶበት ይሆናል ተባብለን ዝም አልን
  ይህ አጢያቱ የበዛ መነኩሴ ጳጳስ እሆናለሁ ብሎ ተነሳ
  ጳጳስ ተብየውም ድጋፍእንደጻፉ ሰማን
  መነኩሴው ሀያ አመት በሙሉ
  ለፍራንክፈርት ማርያም ምእንም ከጤያት ስራ በስተቀር
  ከዝሙት

  ጾም ከመቫር በስቀር
  እየበሉ ከመቀደስ በስተቀር
  ሌላችግር የለባቸውም
  ሞያ ሁሉም በጀርመን ሀገር ያሉ ካህናት ያአባ ሲራክን ደቆሮነት
  ያዉቁታል ክብረባል በመጣቁጥር የካህናቱን ስም ጠርተው ለህዝብ በደንብ ማስተዋወቅ አችሉም
  እሄ አሰቴ ከሆነ የፍንክፈርት ህዝብ ይጠየቅ
  ሀራተዋህዶ በተባለው ወብሳይ ሊቀጳጳስ ሙሲ
  ስለሹመቱ ሲናገሩ ቅድስና ያላቸውን ፈልጎ መሾም
  በካህናት እና በህ ዝብ የተመሰከረትን ብለውተናግረው አይቻለሁኝ
  ጳጳሱ ይህንን ይበሉንጂ
  ህጉንባልጠበቀ በሰካራም ነቱ
  በዝሙተኞ ነቱ
  በጫትና በሲጋራ አጫሽነቱ
  ብሎም ከሁሉም የቤተክርስቲያን እውቀት በዜሮነቱ
  ህዝብን በማላቀስ ብቻ የሚታወቀው ለባ ሲራክ ጳጳስ እንዲሆን አቡነ ሙሲ ደብዳቤ ፅፈዋል
  የህዝበክርስቴያኑን ምራል ለመጠበቅ ተብሎነበር እስካሁን የዚህ ምግባረ ብልሹ መነኩሴባይ ሲራክ ወልደስላሴ ያስፀያፌ
  ስራ ለሱቀርቶ አቆረበን ባረከን ለሚሉት እና እሱመነ ኩሴነው ብለው ለሚከራከሩት አንገት የሚስደፋ ፎቶ በጃችን
  ደርሶናል በቅርብ ቀን ይፋእደርጋለን

 3. Bete Zewudu July 11, 2016 at 2:33 pm Reply

  Bete Zewudu
  2 Std. ·

  አደባባይ: ሰውየው ምን እያደረጉ ነው?

 4. Bete Zewudu July 11, 2016 at 2:34 pm Reply

  ADEBABAY.COM|VON ADEBABAY A
  Gefällt mirWeitere Reaktionen anzeigenKommentierenTeilen
  Kommentare
  Bete Zewudu

  Kommentieren …

  Datei auswählen

 5. Anonymous July 11, 2016 at 9:05 pm Reply

  ጅብ በማያውቁት ሀገር ሄዶ ቆዳ አንጥፉልኝ አለ ይባላል

  • Anonymous July 24, 2016 at 7:44 pm Reply

   ዝንጀሮ የራሷን ምን ሳታይ ……………

 6. ድልነሳ ደባሱ July 12, 2016 at 2:40 pm Reply

  አባታችን በእድሜ በጸጋ ይጠብቅዎ በረከትዎም ትድረሰን፡፡ ቡሩክ አምላካችን ቤተክርስቲያንን ከአማሳኞች ጠብቅልን፡፡

 7. Anonymous July 24, 2016 at 7:42 pm Reply

  የአቡነ ሙሴን ወደ እንግሊዝ ሀገር አካሄድ ምነው ሸፋፈናችሁት። ከኢዝራኤል ወደ እንግሊዝ በመሄድ በመጀመሪያ የፖለቲካ ጥገኝነት ቢጠይቁ ዛሬሳ ጳጳስም ጥገኝነት ሊጠይቅ መጣ ብለው ያሳለቁብን፤ በስልጣን ያለው መንግስት የእርሳቸው ብሄር ጵጵስና የተሾሙት በዚሁ መንግስት ዘመን አወጣጣቸው ለሕክምና በቤተ ክህነት ገንዘብ ምንም የፖለቲካ ችግር እንደሌለባቸው ተጣርቶ ከሀገረ እንግሊዝ እንዲወጡ የተወሰነባቸው ፤አንደኛውን ወገን በፊለፊት ሌላኛውን በጓሮ በር እያስገቡ የለንደንን ምእመን የከፈሉ እሳቱም እስከዛሬ እየነደደ አልጠፋ ያለ ይህንኑ ድርጊታቸውን በሮም ማርያም ቤተ ክርስቲያን የደገሙ ሥራቸው ቢያሳፍራቸውም ያለ ቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ ከፓትርያርኩ እውቅና ውጭ እንግሊዝ ከነበሩ ጳጳስ ጋር በመሻረክ የርሳቸው የነበሩ ክልሎችን አሳልፈው በመስጠት ለመደበቂ ይሆነኛል ያሉትን ጀርመንን ለእርሳቸው በማድረግ የጴጥሮስን መንበር ለቀው የፈረጠጡ ቤተ ክርስቲያን በሌለበት ጽላት ለጠቀሟቸው የሚያስታቅፉ እጅግ ባህታዊና ንዋይ የማይወዱ መስለው የሚታዩ መርዘኛ ሰው ናቸው። ለመሆኑ የለንደን ምእመን እጁን ዘርግቶ በደስታ የሚቀበላቸው ይመስላቸው ይሆን እየተጠቀሙባቸው ካሉ አካላት ውጭ በመላው አውሮፓ እርሳቸውን የሚፈልግ እንደሌለ እያደር የሚታይ ጉዳይ ይሆናል። እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይጠብቅልን አሜን።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: