የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎችን የማሳወቂያው ጊዜ በ15 ቀናት ተራዘመ፤ ከ118 ባላነሱ ተጠቋሚዎች ላይ ግምገማና ምዘና እየተካሔደ ነው

አስኬማ ጳጳሳት

 • ካህናት እና ምእመናን መረጃዎችንና አቤቱታዎችን ወደ አስመራጭ ኮሚቴው እያጎረፉ ነው
 • የዕጩ ኤጲስ ቆጶሳት እና የሚሾሙባቸው አህጉረ ስብከት ቁጥር እንደሚጨምር ተጠቁሟል
 • የኑፋቄው ሕዋስና የአማሳኙ ቡድን፥ ምልምሉን ለማሾምና ‘ስጋቱን’ ለማስወገድ እየሠራ ነው
 • ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ሢመቱ፣ ከዘመን መለወጫ በፊት እንዲከናወን ፍላጎት አላቸው
 • ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ እንጂ ሕዝብን የሚያሳዝን እንዳይኾን ማሳሰቢያዎች እየተሰጡ ነው

*               *                *

eotc patriarchate head office
በቅዱስ ሲኖዶስ የተቋቋመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፣ ተጠቋሚ መኰሳትንና ቆሞሳትን ገምግሞና መዝኖ ተወዳዳሪ ዕጩዎችን በመለየት የሚያሳውቅበት ጊዜ በ15 ቀናት መራዘሙ ተገለጸ፡፡

ኮሚቴው፣ ተጠቋሚዎቹን በመመርመር፣ በማጥናትና በማጣራት ውጤቱን እስከ ትላንት፣ ሰኔ 30 ቀን 2008 ዓ.ም. እንዲያቀርብ፣ ቅዱስ ሲኖዶሱ በርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው ወስኖ የነበረ ቢኾንም፤ የተጠቋሚዎቹ ብዛትና ሒደቱ የሚጠይቀው ከፍ ያለ ጥንቃቄ የቀነ ገደቡን መራዘም አስፈላጊ አድርጎታል፡፡

ቀደም ሲል ለሹመት የሚያስፈልጉት ሐዲሳን ኤጲስ ቆጶሳት ከ14 – 16 እንደሚኾኑ ቢገለጽም፤ በሞተ ዕረፍት በተለዩትና በእርግና በሚገኙት አባቶች ምክንያት ክፍት ከኾኑት መንበረ ጵጵስናዎች ብዛት አንፃር፣ በኮሚቴው የሚቀርቡ ዕጩዎችና የሚሾሙባቸው አህጉረ ስብከት ቁጥር የተወሰነ ጭማሪ ሊያሳይ እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

ተጠቋሚዎችን አጣርቶ ለውድድር የሚቀርቡትን ዕጩዎች ቁጥር ለማሳወቅ የሚያስፈልገው ጊዜ ከሰንበት ዕለታት ውጭ በ15 የሥራ ቀናት ቢራዘምም፤ ተወዳዳሪ ዕጩዎችንና የሚሾሙባቸውን አህጉረ ስብከት ቁጥር ለመጨመር በአስመራጭ ኮሚቴው የቀረበው ጥያቄ ውሳኔ የሚያገኘው፣ በዛሬው የቋሚ ሲኖዶስ ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባ እንደኾነ ተገልጧል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ብፁዕ ዋና ጸሐፊን በአስረጅነት የያዘውና ሰባት አባላት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ፣ በምልአተ ጉባኤው የተሰጠው ቀነ ገደብ መጠናቀቁን አስመልክቶ፤ ትላንት፣ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ተወያይቷል፡፡ ቅዱስነታቸው፣ ሥርዓተ ሢመቱ ከዘመን መለወጫ በፊት እንዲካሔድ ያላቸውን ፍላጎት የገለጹ ሲኾን፣ ኮሚቴው በጀመረው መንገድ፣ ተጠቋሚዎቹን አጣርቶ ዕጩዎቹን በየአካባቢው የመለየቱ ሥራ በከፍተኛ ጥንቃቄ የማካሔዱ ጉዳይ ቀዳሚ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ታምኖበታል፡፡

ሥራውን በይፋ ከጀመረ ኹለት ሳምንታትን ያስቆጠረው አስመራጭ ኮሚቴው፣ እስካለፈው ሳምንት መጨረሻ ድረስ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተቀበላቸውን ከ118 ያላነሱ ተጠቋሚዎችን በመያዝ፥ የመመርመር፣ የማጥናትና የማጣራት ሥራውን በከፍተኛ ትጋትና ግልጽነት በተመላበት ውይይት እያካሔደ ይገኛል፡፡

የተጠቋሚዎች ስም ዝርዝር፣ በማኅበራዊ ብዙኃን መገናኛዎች ይፋ መኾኑን ተከትሎ፣ ማኅበረ ካህናትና ማኅበረ ምእመናን፣ መረጃዎችንና አቤቱታዎችን በተለያዩ መንገዶች ለአስመራጭ ኮሚቴው እያጎረፉ እንደሚገኙና ይህም ለማጣራት ሥራው አዎንታዊ እገዛና ድጋፍ እያደረገ እንዳለ ተጠቅሷል፡፡

ድጋፍም ተቃውሞም የሚታይባቸውን የካህናትና የምእመናን መረጃዎችና አቤቱታዎች፣ እንደ ግብአት ከመጠቀም አንፃር፣ በኮሚቴው የመጀመሪያዎቹ የሥራ ቀናት በብርቱ አከራክሮ እንደነበር ታውቋል፡፡ ማጣራቱ፥ ተጠቋሚዎቹ በቤተ ክህነት ባላቸው ማኅደር ላይ ብቻ ተመሥርቶ መካሔድ አለበት፤ በሚል የተንጸባረቀው አቋም፣ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በምርጫ ማስፈጸሚያ ደንቡ፣ የካህናትንና የምእመናን ተሳትፎ አስፈላጊና ግድ የሚያደርጉትን ድንጋጌዎች ያላገነዘበና ተቀባይነት ያለው የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ከማካሔድ አኳያም አግባብነት የሌለው ኾኖ ተገኝቷል፡፡ የመረጃዎችንና የአቤቱታዎችን ይዘትና መግፍኤ በጥንቃቄ በማንጠር መጠቀም እንደሚገባም የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

ኮሚቴው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ የተጣለበትን ሓላፊነት ክብደት ተረድቶ፣ ከማንኛውም አሉታዊ ግፊትና ተጽዕኖ ተጠብቆ ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ አባት ለማስመረጥ እንጂ ሕዝብን የሚያሳዝን ሥራ እንዳይሠራ የተለያዩ አካላት እያሳሰቡ ሲኾን፤ አጋጣሚውን የሞት ሽረት ያደረገው የተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋስና የአማሳኙ ቡድን በበኩሉ፥ ግንባር ፈጥሮ፣ ምልምሎቹን ለማሾምና ስጋቶቼ ናቸው የሚላቸው ንጹሐንና ቀናዕያን ኦርቶዶክሳውያን አባቶች ከዕጩዎች እንዳይገቡ በብርቱ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በጠቅላይ ጽ/ቤት በመምሪያ ሓላፊነትና ጸሐፊነት፣ በሀገረ ስብከትና በክፍለ ከተማ ሓላፊነት፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በስብከተ ወንጌል ሓላፊነትና ሠራተኝነት የሚገኙት የኑፋቄው ሕዋስ አባሎች፤ ሥራቸውን ትተው ጠዋትና ማታ በብፁዓን አባቶች ማረፊያዎች በማንዣበብና በማጨናነቅ፤ ከተጠቋሚዎቹ መሀል ለጥፋታቸው ከለላ የሚሰጧቸውንና እንዲሾሙላቸው የሚፈልጓቸውን በመለየት በዕጩነት እንዲገቡላቸው ውትወታቸውን ማጠናከራቸው ተገልጿል፡፡

በተጠቋሚዎችና በብፁዓን አባቶች መካከል በአንድ ወቅት የተፈጠሩ አለመግባባቶችን እያስታወሱ፣ ምልምሎቻቸውን የሚልቁ፣ ከዓላማቸውና ከጥቅሞቻቸው አንፃርም እንደ ዕንቅፋት የሚያዩዋቸውን ተጠቋሚ አባቶች ማጥቆርና ቅራኔን ማባባስ፤ እንዲኹም፣ በጎጠኝነት መከፋፈል ዓይነተኛ ስልቶቻቸው ሲኾኑ፤ ዳጎስ ያለና አማላይ ገንዘብ፣ የቤት፣ የተሽከርካሪና መሰል የቁሳቁስ ስጦታዎችም እንደሚገኙበት ተመልክቷል፡፡

በምዝበራ ሰንሰለቱ ያሉ የአንዳንድ አድባራት አለቆች፣ በአማሳኝነት ካከበቱት የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ እንዲያዋጡ ሲጠየቁ፤ የተሐድሶ ኑፋቄ ሕዋሱም፣ ከአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ኃይሎች በሚያገኘው ድጋፍ ሲሞናዊነቱን አጠናክሮ፣ ወኪሎቹን ለከፍተኛው ማዕርገ ክህነት በማድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ሰርጎ ለመግባት በማሰፍሰፉ አስመራጭ ኮሚቴውና ብፁዓን አባቶች በአጠቃላይ እንዲያውቁበትና እንዲነቁበት ያስፈልጋል፡፡

በየአጥቢያው ሙስናንና ኑፋቄን በመዋጋት፥ ለዕቅበተ እምነት፣ ለፍትሕና ለመልካም አስተዳደር መስፈን ሲጋደሉ የቆዩ ወገኖች፤ የኑፋቄውንና የአማሳኝ ቡድኑን ኅቡእ እንቅስቃሴ፣ በፀረ ኑፋቄና በፀረ ሙስና ስልቶች በንቃት እየተከታተለ በማጋለጥ፣ የሤራውን ባሕርይና አስፈላጊ መረጃዎችን ለአስመራጭ ኮሚቴውና ለሚመለከታቸው አካላት እያሳወቀና እያስገነዘበ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

Advertisements

12 thoughts on “የኤጲስ ቆጶሳት ዕጩዎችን የማሳወቂያው ጊዜ በ15 ቀናት ተራዘመ፤ ከ118 ባላነሱ ተጠቋሚዎች ላይ ግምገማና ምዘና እየተካሔደ ነው

 1. Anonymous July 8, 2016 at 9:08 am Reply

  መራዘሙም መልካም ነው ባግራውንድ ጥናቱም ጠለቅ ያለ ቢሆን መልካም ነው
  ነገር ግን ዝም ብሎ ሥም ማጥፋት እንዳይሆን ሕፀፅ አለበት የተባለው ሰው በጽሁፍና በምስል የተደገፈ ቢሆን መልካም ነው

 2. Molalign Dires From Bahir-dar July 8, 2016 at 1:37 pm Reply

  ውድ አባቶቻችን በጥንቃቄ እንዲታይ ትጉ

 3. Anonymous July 8, 2016 at 1:57 pm Reply

  ድጋፍም ተቃውሞም የሚታይባቸውን የካህናትና የምእመናን መረጃዎችና አቤቱታዎች፣ እንደ ግብአት ከመጠቀም አንፃር፣ በኮሚቴው የመጀመሪያዎቹ የሥራ ቀናት በብርቱ አከራክሮ እንደነበር ታውቋል፡፡ ማጣራቱ፥ ተጠቋሚዎቹ በቤተ ክህነት ባላቸው ማኅደር ላይ ብቻ ተመሥርቶ መካሔድ አለበት፤ በሚል የተንጸባረቀው አቋም፣ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በምርጫ ማስፈጸሚያ ደንቡ፣ የካህናትንና የምእመናን ተሳትፎ አስፈላጊና ግድ የሚያደርጉትን ድንጋጌዎች ያላገነዘበና ተቀባይነት ያለው የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት ከማካሔድ አኳያም የሚያገለግል ባለመኾኑ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ የመረጃዎቹንና የአቤቱታዎችን ይዘትና መግፍኤ በጥንቃቄ በማንጠር መጠቀም እንደሚገባም የጋራ ግንዛቤ ተወስዷል፡፡

 4. anggile July 8, 2016 at 6:12 pm Reply

  በዘረኝነት ጎሳዊ/ጎጣዊ አስተሳሰብ ሕሊናቸው የተበላሸባቸው፣ አማሳኞች፣ በጥቅም የተሳሰሩና ሃይማኖትን ንግድና ማትረፊያ ያደረጉ መንፈሳዊ ከባን ከደረቡ በግልና በቡድን የተደራጁ ሰዎች የዘመናችን ቤተ ክርስቲያን ብቻ ሣይሆን የአገሪቱም ከባድ ፈተና እየኾኑ ነው፡፡ ሃይማኖት አለን በምንለውና በዓላማውያኑ መካከል ያለው የልዩነት ድንበር ደብዝዞ መለየት እስከሚሳን ድረስ የተፈጠረው መቀላቀልና ውህደት የመንፈሳዊ ሕይወት ማራኪ ውብትን እጅጉን አድብዝዞታል፡፡
  ተምሳሌት የሚኾነውና ባለ ራእይ የኾነ መንፈሳዊ መሪና አባት ያጣው ትውልድም በአገሩ ፖለቲካዊም ኾነ ሃይማኖታዊ ተቋማት ክስረትና ውድቀት እጅጉን አዝኖና ተክዞ ያለ በቀቢጸ ተስፋ የተዋጠ ትውልድም እጅጉን እየተበራከተ ነው፡፡ ይህን የባዘነ ትውልድ- ሃይማኖቱን በሚገባ አውቆና ተረድቶ ለቤተ ክርስቲያኑ የሚጠቅም፣ ለነገው ትውልድ ተስፋ የሚኾን፣ ለአሩና ለወገኑ ፍቅርና ተቆርቋሪነት ያለው ባለ ራእይ መሪና አባት እንዲኖረን ያስፈልጋል፡፡
  ከዚህም ጋር የኢትዮጵያ ቤ/ን መሪና አባት በሥነ ምግባር የታነጸ፣ ጉቦንና ሙስናን የሚጸየፍ፣ ለእውነትና ለፍትሕ የሚቆም ትውልድን በማፍራት- ለአገራቸው ክብር፣ ለወገናቸው ኩራት የኾኑ ሀገራዊ ግዴታቸውን የሚወጡ ዜጎችን ማፍራት፡፡
  አምላክ ሆይ ዘመኑን የሚዋጁ የቁርጥ ቀን መሪና አባት አታሳጣን፡፡
  እግዚአብሄር ይስጥልን::

 5. Anonymous July 8, 2016 at 7:35 pm Reply

  የምዕመና አስተያየት እንዴት ለአባቶች እየደረሰ ይሆን ?

 6. akbong July 9, 2016 at 6:47 am Reply

  ከጊዜ ወደ ጊዜ የምንሰማው ነገር እያስጨነቀን ቤተክርስቲያኒቱ ግራ ወደሚያጋባ ነገር እየሄደች እንደሆነ እየተሰማን ነው፤ እኛ በጋምቤላ የምንኖር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና ካህናት ተጨንቀናል ይህም ስለ ነገ የቤተክርስቲያኒቱ ሆኔታ እያሳሰበን መሆኑ እንዲታወቅ እንፈልጋለን፡፡
  ቅዱስ ፓትርያርኩ አሰመራጭ ኮሚቴው ለቤተክርስቲያን የሚያስቡ አባቶች ይሾሙልኝ ማለታቸውን ስንሰማ ደስ ብሎን ነበር ነገር ግን በጋምቤላ ሃገረስብከት ተጠግተው ገንዘብ የሚሰበስቡ ባለሃብቶች ከአባ ተክለሃይማኖት ጋር የጥቅም ተካፋይ የሆኑ የሆቴል ቤቶችና መበለቶች እንዲሁም ሆድ እንጂ ጭንቅላት የሌላቸው የሀገረ ስብከቱ ሰራተኞች ድግሱን እና መዋጮውን ሲያጧጡፉት ስናይ እየገረመን ነው፡፡
  አዲስ አበባ ተቀምጠው ተክለሃይማኖት የሚከፍላቸው ሳይሰሩ የሚበሉ ሰባኪ ነን ባዮች ለአባ ተክለሃይማኖት ከፍተኛ ቅስቀሳ እያደረጉ እንደሆነ እየሰማን ነው፡፡ ትላንት ደግሞ እነዚሁ አካላት እንደተናገሩት ቅዱስ ፓትርያርኩ ለአስመራጭ ኮሚቴው በስብሰባ ማእከል ቆመው እባካችሁ ተክለሃይማኖትን ሹሙልኝ ጋምቤላ በሄድኩበት ወቅት ቃል ገብቻለው ብለዋል እያሉ ማስወራት ጀምረዋል ፡፡ የኛ ጥያቄ ለጵጵስና መስፈርቱ ምንድን የሚል ነው ፡፡
  1ኛ በእምነቱ ህጸጽ የሌለበት ተክለሃይማኖት በእምነቱ ህጸጽ አለበት ለማለት አንደፍርም ነገር ግን ለተሃድሶዎች ከፍ ያለ ጠበቃ እና ጥላ ነው ያም ሆነ ይህ ፕሮቴስታንቱ ጋትሉዋከ ግን ሊመሰክርለት አይችልም ፡፡ አንድ አባት እንደአባትነት ሁሉንም በእኩል አይን ማየት አለበት ነገር ግን የማህበረ ቅዱሳን አባላት የሚላቸውን ሰወች እያሳደደ አባት ነው ለማለት አንደፍርም ተሃድሶን የሚደግፍ አባት ሌላ ምን ሊባል ይችላል
  2ኛ መንፈሳዊ የሆነ አባት ወደ ጋምቤላ ሲመጡ አባተክለሃይማኖት መንፈሳዊ ናቸው ሲባል ሰምቼ ነበር እውነት ሰዓታት ቆመው ኪዳኑን የሚመሩ አሊያም ከርሳቸው በፊት እንደነበሩት እንደ አባ ተክለያሬድ ማህሌታዊ ሆነው እጣን እጣን ይሸታሉ ብለን ነበር እረ እንዳውም ቀድሰው ቆርበው ያቆርቡናል ብለን ነበር ፤ይሀው ከመጡ አመታት ተቆጥረዋል አንድ ቀን እንደ መስኮብ ቄስ እንኩዋ አላየንም ሳይቀድሱ የግሪክ እጣን ከማጠን በቀር ፡፡
  ሁኔታው ግን ከጊዜ ወደጊዜ ስናያቸው መንፈሳዊነታቸው የታይታ ነበር ያውም በጉባኤ መሃል የተደጎሰ መጽሐፍ ማንበብ፤ በጦም መንበረ ጵጵስና ተደብቆ ………… ኅሊና ይፍረደው…
  ..የሰውነት ግዝፈቱ ከየት የመጣ መሰላችሁ
  ሃሜቱስ ቢሆን ልክ እንደሴት ወሬ ሲሰልቁ መኖር፤ ስለመንግስት መስበክ፤ ደሃን ማሳሰር የሀገረ ስብከቱን እንዲሁም የኪዳነምህረትን ካዘና አንደ ግል ንብረት ማየት ፤ የተሃድሶ አቀንቃኞች የሆኑትን ዘርፌን ማጋባት እዝራና ሃዋዝን መጋበዝ ታምራት ሃይሌን መጥራት የተሃድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝ ሰባኪዎችን መጋበዝ በጋሻውን እንዲፈነጭበት ማድረግ ወዘተ….
  3ኛ እውቀት ያለው እ ኛ እውቀታቸው ምን ይሆን እያልን ሁል ጊዜ እንጠይቃለን ፤አንድ ቀን አይቀድሱ አያወድሱ ወይ መናፍቃንን ተከራክረው አይመልሱ ፤ መንፈሳዊነት ቢያጣ እውቀት ይኖረዋል ታድያ በየጊዜው ለመሾም ከባድ ጥረቱ ማድረግ ብቻ ምን ያደርጋል ሆነው ካልተገኙ ፤ ከቦረና ጀምሮ እስከ ከፋ ከከፋ እስከ ጋመቤላ ሁል ጊዜ እንዲሾም ሰው ከማሳመጽ ለምን አብሮት ካለው አባ ቆንጆ ውዳሴ ማርያም አያጠናም ፤፤
  አንድ እውቀት ግን አላቸው አባ ተክለሃይማኖት ቃል ገብቶ አለመፈጸም ፤ ሁል ጊዜ ዉሸት ሁል ጊዜ ዉሸት………
  አንድ እውቀት ግን አላቸው እንደ ወይዘሮ ዘዉዴ ሰዎችን ማጥመቅ ፤ትንሽ ከሴቲቱ የሚያንሱት የተጠመቁት ቁጥራቸው ይጋነናል ከዚያም ጠያቂ የላቸውም እንደ ወይዘሮ ዘውዴ ወደ አዲስ አበባ ወስደዋቸው አያስተምሩም
  • ለሲመት ብቻ ..
  • በሰበካ ጉባኤ ወቅት ደግሞ አበል እየተከፈላቸው ካቶሊኮችን ሰቨን ዳዮች ምስክርነት ይሰጣሉ
  • ደቡብ ሱዳን …………………. የእውነት ይመስላችሁዋል ፍርዱን ለእናንተ……..
  • ሢመቱ ለአንዳንድ ሰወች መጠቀሚያ እንዳይሆን አባቶች ቢያስተውሉ እንላለን
  • ፓትርያርኩም ታሪካዊ ስህተት እንዳይሰሩ ሰባት ጊዜ ለክተው አንድ ጊዜ ቢቆርጡ
  • ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለማርያም እንጂ አባ ኃይለማርያም እንዳላመሰገኑዋቸው ልብ ማለት ያሻል
  • በሴት የማይታሙት ሰውዬ በወንድስ ;
  • ደግሞ ከባሮ ቆላ ….. ከኤርፖርት ….. በነገራቸን ላይ ጋትሉዋክ ይፈርም እንጂ የደብዳቤው ደራሲ ብታምኑም ባታምኑም ንቡረእድ ኤልያስ ነው

 7. akbong July 9, 2016 at 6:47 am Reply

  Sከጊዜ ወደ ጊዜ የምንሰማው ነገር እያስጨነቀን ቤተክርስቲያኒቱ ግራ ወደሚያጋባ ነገር እየሄደች እንደሆነ እየተሰማን ነው፤ እኛ በጋምቤላ የምንኖር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና ካህናት ተጨንቀናል ይህም ስለ ነገ የቤተክርስቲያኒቱ ሆኔታ እያሳሰበን መሆኑ እንዲታወቅ እንፈልጋለን፡፡

 8. Bete Zewudu July 9, 2016 at 2:00 pm Reply

  ዜና

  የዛሬሶስት አመት ገደማ ነበረ ማህበረ ቅዱሣን ከጀርመን ፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ቤተክርስቲያን
  ፩ እደይዘምሩ
  ፪ እደያስተምሩ
  ዲያቆን ዶክተር ሄኖክ ሐይሌና ዲቆን ወንዶሰን
  ከኬለር እንኳን ሣይቀር ከምመናኑጋር
  በዚህ ከፋፋይ የሰም መነኩሴ ባይ
  አባ ሲራክ ወልደሥላሴ
  ወይም አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የተባረሩት
  ሶስት አመትሞላ ዜና ቤተክርስete Zewuduቲያን ታሬክ ይዘክረዋል

 9. Anonymous July 9, 2016 at 2:28 pm Reply

  mahebere kedusan yezare sost amet gedema neu kferankfert kedst mariamedyezemeru ena edyastemeru yetbareru d c henokna meselohaheu
  be abba herak gudu papas kkkkkkk

 10. Anonymous July 13, 2016 at 7:21 pm Reply

  ለጳጳሳት ለመነኮሳት የእለት ጉርስ ይበቃቸዋል https://www.youtube.com/watch?feature=player_embedded&v=E1Nm1gU9Xo4#t=3779

 11. Yohannes August 2, 2016 at 12:23 pm Reply

  አባ ሞገስ የመናገሻ ጋራ መድኃኔዓለም እንዲሁም የከተማው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስተያን አስተዳዳሪ በቲዖሎጂ የድግሪ ምሩቅ፣ ከገዳም አድገው እስከ ቁምስና የደረሱ፣ አሰረ ምንኩስናቸውን በክብር ጠብቀው የሚኖሩ፣ ከላይ በአስተዳዳሪነት የተሸሙባቸውን አብያ ክርስቲያናት ህንጻቸውን በግሩም ማሳነጽ ብቻ ሳይሆን በመነኮሳት መካከል አንድነትን ያመጡ፣ ምዕመናንን ከመነኮሳት በፍቅር ያስተሳሰሩ፣ ከምዕመናን በተገኘ አገዛ የቅኔ፣ የቅዳሴ የዜማ እና የአቋቋም የአብነት ት/ቤት በመገንባት ለተማሪዎች ቀለብ አዘጋጅተው ቤተክርስቲያንን ሊገመት በማይችል መልኩ ታላቅ ለውጥ እንድታሳይ ያደረጉ፣ ከብዙዎች የጎደውን ከአፍቅሮተ ነዋይ፣ ከዘርና ከዓለማዊነት ያሟሉ በመሆናቸው ለዚህም የብዙዎችን ምስክርነት የተቸራቸው ቅን አባት በመሆናቸው ለዚህ ስልጣን ቢበቁ ቤተክርስቲያን አንድ ገዳማዊ አባት አገኘት ማለት ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: