ለጵጵስና በተጠቆሙት የቨርጂኒያው አባ ፊልጶስ ከበደ ላይ የምእመናን አቤቱታ ቀረበ፤ ፀረ ቅዱሳን፣ ሞያ ቢስ፣ ሐኬተኛና አድመኛ ናቸው

Aba Filipos Kebede Virginia

 • በቅስናቸው በቂ ሞያ የሌላቸው፣ ካህናትንና ምእመናንን የሚከፋፍሉ አድመኛ ናቸው
 • በሂዩስተን ሕፃናትን በግብረ ሰዶማዊነት በማበላሸት (child molestation) ይታወቃሉ
 • በፖሊቲካ ጥገኝነት የሚኖሩት ቤተ ክርስቲያንን በማሳጣትና ሲጠሩም ፈርጥጠው ነው
 • ክብረ ክህነትንና የተቀደሱ ምስጢራትን የሚያቃልሉ፣ ሐኬተኛና እምነት አልባ ናቸው
 • ለተወገዱት ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በርካታ ገንዘብ እንደሰጡ ተናግረዋል
 • የዘመናት ምኞታቸው ጵጵስና ነው፤ በሻንጣ ልብስ በመደለል እንደሚያገኙት ያስባሉ

*          *          *

ኤጲስ ቆጶስ በሕዝብ ተመርጦ ለሕዝብ የሚሾም የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፡፡ በሹመቱ “ገብር ኅሩይ ዘእግዚአብሔር = የእግዚአብሔር ምርጥ አገልጋይ” ሊባል የሚችለው፡- ስለ ደግነቱና ትሩፋቱ፤ ስለ ንጽሕናውና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ፣ ሊቀ ጳጳሱ በሚመራው ጉባኤ በካህናትና በምእመናን ምስክርነት ሲረጋገጥለት ነው፡፡ ደግነቱ ያልታወቀ፣ ስለ ሠናይ ተግባራቱ መልካም ምስክርነት የሌለው ቆሞስ እና መነኵሴ ነኝ ባይ ኹሉ፥ በሲሞናዊነት፣ በአድርባይ ፖሊቲከኞችና በጎጠኞች መንገድ ካልኾነ በቀር ኤጲስ ቆጶስነት ሊሾም አይችልም፤ አይገባም፡፡

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያናችንና የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንቡ፥ ሹመቱ ስለሚገባቸው ቆሞሳትና መነኰሳት ያስቀመጧቸው መመዘዎች፤ የተቆጠሩና የሚለኩ ናቸው፡፡ ኤጲስ ቆጶስ ኖላዊ/ጠባቂ/ ነው፤ የሚለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ለዕጩነት የሚቀርበው ተሿሚ፡- በምንኵስናውና ድንግልናዊ ሕይወቱ የማይነቀፍና ነውር የሌለበት፤ በልቡናው ከሐኬት የነቃ፤ የሚያረጋጋ፤ እንግዳ መቀበልን የሚወድ፤ ብሉይና ሐዲስ የተማረና ለማስተማር የሚበቃ፤ በጠባዩ ትሑት፤ የማይጣላ፤ ትዕግሥተኛ፤ ሰውን የሚያስታርቅ፤ ገንዘብ የማይወድ፤ ሰካራምና ቁጡ ያልኾነ፤ ከቂም በቀልና ከዓመፃ የተለየ፤ ብልህና ዐዋቂ መኾን እንደሚገባው በግልጽ አስቀምጧል፡፡

በአስመራጭ ኮሚቴው ከተያዙትና ቀደም ሲል በጡመራ መድረኩ ስማቸው ከተዘረዘሩት ተጠቋሚ ቆሞሳትና መነኰሳት መካከል ግን፣ ስንኳን ለመጨረሻው ማዕርገ ክህነትና ከፍተኛ ጥንቃቄ ለሚያስፈልገው ኤጶስ ቆጶስነት ሊበቁ ቀርቶ ቅስናቸውንም በሚገባ ያገኙት ለመኾኑ መመርመር የሚገባቸው ናቸው፡፡

ካህን የወል ስም በመኾኑ ቀሳውስትንም ኤጲስ ቆጶሳትንም ይወክላል፡፡ ማዕርገ ቅስና ለክህነት እጅግ አስፈላጊው ደረጃ ነው፡፡ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሕዝቡን የማያስተምርና የማይመራ፤ ጉቦ ሰጥቶ የተሾመ፤ የኃጢአተኛውን ንስሐ የማይቀበል፤ በሐሰት የሚመሰክር፤ ሰውን የሚያጣላ፤ የሚኮራ፤ ኮከብ የሚቆጥር፤ የሚሰክር፤ አራጣ/ወለድ/ የሚቀበል፤ በሐሰት የሚምል፤ የጠንቋዮችን ነገር እውነት ነው ብሎ የሚቀበል፤ ከሴሰኛ ሴት የደረሰ፤ ሥር የማሰ ቅጠል የበጠሰ፤ ሰውን የሚማታ፤ ከመናፍቃን የተጠመቀ፤ የመናፍቃንን ቁርባን የተቀበለ፤ አብሯቸው የጸለየ፤ የሰረቀ፤ እመነኵሳለኹ፣ ተባሕትዎ እይዛለኹ ብሎ ሚስቱን የተወ፣ ያሰናበተ ካህን ከሹመቱ እንዲሻር ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያናችን ያዛል፡፡

ከአሜሪካ – ቨርጅንያ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን የደረሰን፣ የምእመናን አቤቱታ፣ ለኤጲስ ቆጶስነት ከተጠቆሙት አንዱ ስለኾኑት የደብሩ አስተዳዳሪ አባ ፊልጶስ ከበደ ያትታል፡፡

እንደ አቤቱታው፣ ተጠቃሹ መነኵሴ ኹሉም ዓይነት ችግሮች ያሉባቸው ናቸው፡፡ ክብረ ቅዱሳንንና ክብረ ክህነትን የሚያቃልሉ፤ ጾምና ንስሐ አያስፈልግም፤ የሚሉ በመኾናቸው በሃይማኖታቸው ጥያቄ የሚነሣባቸው ናቸው፤ የትምህርት ደረጃቸውም ለቅስና ስለማያደርሳቸው ምእመኑን ለማስተማር፣ ለመናዘዝና ቀድሶ ለማቍረብ ስለማያበቃቸው ሞያቸው መፈተን ያለበት ነው፤ በሐሰት የሚምሉና የሚመሰክሩ፤ ለጸሎት የሰነፉ፣ ለመብል የፈጠኑ፤ ለአድማ የሚተጉ በመኾናቸው ሐኬተኛና ዓመፀኛ ናቸው፡፡ በግብረ ሰዶማዊነትም ስለሚታሙ ምንኵስናቸውና ድንግልናዊ ሕይወታቸው ነውር ያለበትና የሚነቀፍ ነው፡፡

ይኹንና የማይገባቸውንና ለዓመታት ሲመኙት የነበረውን ማዕርገ ጵጵስና በሲሞናዊ መንገድ ለማግኘት ካሰፈሰፉት አንዱ ናቸውና፣ አስመራጭ ኮሚቴው የምእመናኑን አቤቱታ በጥሞና መርምሮ ተቀባይነት ያለው የጋራ አቋም እንዲይዝበት ተጠይቋል፡፡ 


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ አሜን፡፡

ቀን 14/10/ 2008 ዓ.ም.

ብፁዓን አባቶች ሆይ፡- ቤተ ክርስቲያንን ከለምድ ለባሽ ተኩላ ታደጉልን!

ከሁሉ አስቀድሞ የብፁዓን አባቶቻችን በረከታችኹ ይድረሰን እንላለን፡፡ እንደሚታወቀው ሁሉ፣ በዘንድሮ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ፣ ሐዲሳን ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደወሰነና ለተግባራዊነቱም የብፁዓን አባቶች አስመራጭ ኮሚቴ እንደሠየመ ሰምተናል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በውሳኔው፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና የማስፈጸሚያ ደንቡን መሠረት ያደረገ መመሪያ ለኮሚቴው ሰጥቷል፡፡ የተጠቋሚዎች አገልግሎትና ብቃት ከሚረጋገጥባቸው መንገዶች አንዱ የካህናትና የምእመናን ምስክርነት መሆኑን በመረዳታችን፣ እኛም እንደ ቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን ያለንን መረጃ ወደ እናንተ ስንልክ በታላቅ አክብሮት ነው።

ይህ አካሔድና ውሳኔ፣ መልካምና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስፈላጊ እንደ ኾነ የታመነ ነው። ብዙ ነገር አስከፊ በሆነበት፣ በተለይም የበግ ለምድ ለብሰው ከመንጋው የገቡ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ሕዝቡን እያወኩና ተስፋ እያስቆረጡ ባሉበት ሰዓት፣ ሕዝቡን የሚያጽናና፤ ምእመናንን የሚጠብቅ፤ በቅድስና ሕይወቱ የሚባርክ፤ ከተደቀነብን ፈተና በጸሎቱ የሚያድን አባት ያስፈልገናል።

ይሁን እንጂ ይህን የማዕርገ ጵጵስና የሹመት ዜና የሰሙና ለዘመናት ወደዚህ ወደተቀደሰው ክብር ለመድረስ የሚመኙ፤ አልፎም እንደ ሲሞን መሠሪ፣ በገንዘብ ይህን ሹመት ለመግዛት ሌት ተቀን የሚደክሙ ሰዎች እንዳሉ ለእናንተ ለብፁዓን አባቶች የተሰወረ አይደለም። አንዳንድ መነኰሳት፣ ቆቡንና ቀሚሱን ለብሰው ሲታዩ ኦርቶዶክሳዊ የሚመስሉ፤ አባቶች ዘንድ ሲቀርቡ ፍጹም መንፈሳዊ መስለው ነገር ግን በስውር ለመናፍቃን የሚላላኩ፤ አባቶቻችን ያቆዩትን ዶግማና ሥርዓት የሚንዱ፤ ሲደረስባቸው “አላወቅሁም፤ ይቅርታ” ብለው በሌላ ጊዜም ተመሳሳይ ጥፋት የሚሠሩ አሉ

ይህን ጽሑፍ ለመጻፍ ያነሣሣን ዋናው ምክንያት፤ በአሜሪካ ቨርጂኒያ ክፍለ ግዛት በማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም ቤተ ክርቲያን የሚገኙ አባ ፊልጶስ ከበደ ስለሚባሉ ‘መነኮስ’ አቤቱታ ለማቅረብ ነው

እኚህ ሰው፣ ወደዚህ ሀገር የመጡት ከ12 ዓመት በፊት ነው፡፡ ከመምጣታቸው በፊት በቤሩት ተመድበው ሠርተዋል፡፡ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በነበረው አለመግባባት ምክንያት ቦታውን ለቀው ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ፣ በወቅቱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጥሪ ሲደረግላቸው፣ የቅዱስነታቸውን ቃልና የቤተ ክርስቲያኒቱን ድምፅ ወደ ጎን በመተው የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ወደ አሜሪካ መጥተው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀዋል።

ወደ አሜሪካ መምጣታቸው ጥፋት ባይኾንም፣ ቤተ ክርስቲያኒቷ እንዳሳደደቻቸው፤ ፓትርያርኩም በዘረኝነት ሥራ እንደከለከሏቸው፤ መንግሥትም ከፓትርያሪኩ ጋር ተመሳጥሮ እስራትና ግርፋት እንዳደረሰባቸው አድርገው የፖለቲካ ጥገኝነቱን ለማግኘት ችለዋል። እውነታው ግን፣ የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ ጥለው መምጣታቸው እንጂ ቤተ ክርስቲያን ያልገፋቻቸው መሆናቸው ነው፡፡

በቆይታም፣ በዲሲ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለተወሰነ ጊዜ በመቆየት ወደ ቴክሳስ ግዛት አቅንተው በሂዩስተን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ተቀጥረዋል። በደብሩ በለስላሳ አቀራረባቸው ብዙ ሕዝብ መማረክ የቻሉ ቢኾንም፤ ውስጥ ውስጡን ግን የቤተ ክርስቲያንን ቀኖና የሚቃረኑ ነገሮችን ለሕዝቡ ማስተማር ጀመሩ

በተለይም ከጾም ጋር ተያይዞ፣ ከኅብረተሰቡ ተቀባይነት የሚያገኙ መስሏቸው፣ አለመጾም ኃጢአት አለመኾኑን፤ በጾም ወተት መጠጣት ማለት ነጭ ውኃ እንደ መጠጣት እንደኾነ፤ ኃጢአትን ለንስሐ አባት መናገሩ ምንም እንዳልኾነ… ወዘተ በተናጠል ለቀረቧቸው ምእመናን ማስተማሩን ተያያዙት።

በርግጥ በወቅቱ ምእመናን ነገሩን ትኩረት ያልሰጡት ሲኾን፣ እንዲሁም ጾም የማይወዱት “እርሳቸው የገባቸው ናቸው” እያሉ ድጋፍ ይሰጧቸው ነበር። በሒደት ግን አለመግባባቶች ሲፈጠሩ ሁሉም እርስ በርሱ መነጋገር ጀመረ። ከዚህም ባሻገር አባ ፊልጶስ፣ በርካታ ወጣት ወንዶችን ብቻ እየሰበሰቡ አስተምራለሁ፤ ይሉ የነበረ ሲሆን፣ አንዳንድ ወንዶች ልጆች እርሳቸው ጋር እየገቡ አልወጣም፤ በማለታቸው ቤተሰቦቻቸው አጥብቀው ክትትል ማድረግ ጀመሩ፤ በኋላም አባ ፊልጶስ “ግብረ ሰዶማዊ ናቸው” የሚል ወሬ መናፈስ ጀመረ፤ እሳቸውም ነገሩን ሲሰሙ በሌሊት በጠፍ ጨረቃ ጠፍተው ወደ ቨርጂኒያ መጡ

ቨርጂኒያ ሲደርሱ፣ በወቅቱ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ቦታውን ለቀው ወደ አዲስ አበባ የሚሔዱበት ወቅት ነበርና አባ ፊልጶስ አባት እንዲኾኑ መደቧቸው። በወቅቱ ብዙ ምእመናን በብፁዕነታቸው መሔድ ያዘኑና የከፋቸው ስለነበሩ፣ አባ ፊልጶስ በለስላሳ ጠባያቸው ሕዝቡን ማጽናናት ችለዋል። በአጭር ጊዜም በርካታ ደጋፊዎችን አፈሩ። ሁላችንም አጨብጭበን ተቀበልናቸው።

በጣም የሚገርመው፣ በወቅቱ ከነበሩበት ቦታ ጠፍተው ስለመጡበት ኹኔታ ቢነገረንም፣ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለን ሳንሰማው ቀርተናል። ውሎ አድሮ ግን አባ ፊልጶስ የሚሠሩት ሥራ እጅግ አሳፋሪና አጸያፊ እየሆነ መጣ። ሰውዬው እምነት አልባ እንደሆኑ ብዙዎቻችን በቅርቡ የተረዳን ቢሆንም፣ ጥቂቶች ግን አኹንም አላወቁባቸውም። አባ ፊልጶስ ውስጥ ውስጡን ተደብቀው የሚፈጽሟቸው በርካታ ነገሮች ቢኖሩም፤ በእኛ አቅም ያየነውን የተወሰኑትን ጉዳዮች በጥቂቱ ለማሳያነት እንደሚከተለው እናቀርባለን።

 • በቤተ ክርቲያን ውስጥ ጸሎት ሲያሳርጉ አንድም ቀን የቅዱሳንን ስም አንሥተው አያውቁም። ዕለቱ ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ገብርኤል፣ ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት … ወዘተ ቢሆን እንኳ “ከበዓሉ በረከት ይደርብን” የሚባል ጸሎት ከአባ ፊልጶስ ሰምተን አናውቅም።
 • ምእመናን ንስሐ አባት እንዲሆኑን ስንጠይቃቸው ‹‹እሺ›› ካሉን በኋላ፣ ኃጢአትን መናዘዝ አስፈላጊ እንዳልሆነ ደጋግመው ይነግሩናል። እንዲሁም፣ ጾም እንደገደፍን ነግረናቸው ንስሐ እንዲሰጡን ስንጠይቃቸው፣ “ምንም አይደለም” እያሉ ንስሐ ሰጥተውን አያውቁም።
 • በአሁን ሰዓት ደብሩን በምክትል ሊቀ መንበርነት የሚያገለግለው፣ ንስሐ ገብቶ ለመቁረብ ሲጠይቃቸው፣ ኹለት ከወለደችለትና ዘጠኝ ዓመት አብራው ከኖረችው ሕጋዊ ባለቤቱ ጋር እንደ አዲስ በሥርዓተ ተክሊል በዐደባባይ ድረዋቸዋል። በወቅቱ “ይህ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት አይደለም” ብለው የተቃወሟቸውን ሰዎች በማሸማቀቅ አባረዋል።
 • እጅግ በጣም የሚያሳዝነውና የሚዘገንነው ተግባራቸው፤ በአሁን ሰዓት በዚሁ በእኛ ደብር ያለ “መነኩሴ ነኝ” የሚል ሰው አለ። ስሙም አባ ሀብተ ገብርኤል፣ በፊት ስሙ ደግሞ ንጉሤ ይባላል፡፡ ሥልጣነ ክህነት ሳይኖረው ለረጅም ዘመናት ሥልጣነ ክህነት እንዳለው አስመስለው ረዳት ቄስ ኾኖ እንዲቀድስ፣ ኪዳን እንዲያደርስና ታቦት እንዲያከብር ሲያደርጉት ቆይተዋል፡፡ በኋላ ነገሩ ሲጣራ፣ ሰውዬው ሥልጣነ ክህነት እንደሌለው ታወቀ፡፡
 • አባ ፊልጶስም፣ በወቅቱ በእንግድነት መጥተው የነበሩትን ብፁዕ አባታችን አቡነ ገብርኤልን በማሳሳት ሥልጣነ ክህነት እንዲሰጠው ሊያስደርጉ ሲሉ ሌሎች በደብራችን የሚገኙ ካህናትና ከዚህ ቀደም ሰውዬውን በተለያየ ደብር የሚያውቁት ካህናት፣ ብፁዕ አባታችን ነገሩን እንዲያጤኑት በማሳሰባቸው ክህነቱን ሳይሰጡ ቀሩ። ይኹንና አባ ፊልጶስ ግለሰቡን በጎን ወደ ኢትዮጵያ ልከው ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ቅስና እንዲቀበል እንዳስደረጉት ሰማን።
 • እጅግ የሚያሳዝነው፣ ይህ ግለሰብ ለሥልጣነ ክህነት የማይበቃ፣ ድል ባለ ዓለማዊ ጋብቻ የተጋባ፣ የጥንት የኢትዮጵያ አትሌት የነበረ ሰው ነው። ባለቤቱ ጥላው ስለሔደች ወደ ቤተ ክርስቲያን ቀርቦ መነኰስኩ በማለቱና አባ ፊልጶስን በተለያየ ጥቅማጥቅም በመያዙ ያለምንም ትምህርትና ንጽሕና ለዚህ አብቅተውታል። ይህ ግለሰብ አስቀድሞ በውጩ ሲኖዶስ ሥር ባለው ዲሲ ገብርኤል የነበረና እነሱ እንኳ “አይገባህም” ያሉት፤ ቀጥሎም ወደ ዲሲ ማርያም ሔዶ በተመሳሳይ የተባረረ በመጨረሻ ግን አባ ፊልጶስ ለእምነት ደንታ እንደሌላቸው በማወቁ ወደ እርሳቸው ቀርቦ ተሳክቶለታል።
 • ይሁን እንጂ የደብራችን ካህናት የግለሰቡን ማንነትና ምስጢሩን ስለደረሱበት፣ ሰውዬው በክህነት እንዳያገለግል አድርገውታል። ይህንንም በማድረጋቸው ካህናቱን ጠምደው በመያዝና ቲፎዞዎቻቸውን በመቀስቀስ በደብራችን ውስጥ እሳት አንድደው ይኸው ላለፉት ሦስት ዓመታት ሰላም አጥተን እየታወክን እንገኛለን
 • አባ ፊልጶስ እንኳን ኤጲስ ቆጶስ ኾነው ቤተ ክርስቲያንን ለመምራት ቀርቶ አንድን ደብር በእልቅና መምራት የማይችሉ፤ ሰነፍ፣ ሌሊቱን ሙሉ ፌስቡክ ላይ ተጥደው አድረው ቀን ላይ ተኝተው የሚውሉ ሰው ናቸው። በዚህም ምክንያት የልደታ ቤተ ክርስቲያን ላለፉት ዐሥራ አራት ዓመታት ቦታ አጥታ በየሥፍራው እየተንከራተተች ትገኛለች። በሕዝብ ብዛት በቨርጂኒያ ካሉ አብያተ ክርስቲያናት ቀዳሚ ብትሆንም፣ በቅርብ የተመሠረቱት አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ራሳቸውን እየቻሉ ሕንፃ ሲገዙ ቤተ ክርስቲያናችን ግን በአባ ፊልጶስ ስንፍና ባለችበት ወደ ኋላ ቀርታ ትገኛለች።
 • እውነት ለመናገር፣ አባ ፊልጶስ ስንፍና ብቻ ሳይሆን ሞያም የላቸውም። ድፍረት ባይሆንብን፣ አባቶች ከፊታችሁ አስቀርባችሁ፣ እንደ ሊጦን፣ መስተብቁዕ… ወዘተ የቅስና ሞያ ብትጠይቋቸው ያን ጊዜ ትረዷቸዋላችሁ። ይህን ሁኔታ ማለትም ስንፍናቸውንና በቂ ዕውቀት የሌላቸው መሆኑን የአስመራጩ ኮሚቴ ሰብሳቢ ብፁዕ አባታችን አቡነ ገብርኤል ያውቃሉ።
 • ከስንፍናቸው በተጨማሪ የጸሎት ሕይወት የሌላቸው፣ ከእንቅልፋቸው በተነሡበት ሰዓት ዐይናቸውን እያሻሹ ፍሪጅ ከፍተው ለእህል የሚሰለፉ ሰው ናቸው። ይህንንም በተለያየ ጊዜ አብረዋቸው የኖሩ ካህናትና ዲያቆናት የሚመሰክሩት ነው። አንዳንዶቹ ደፍረው፣ “ለምንድነው ጸሎት የማያደርጉት?” ብለው ሲጠይቋቸው፣ “ባነበነበ ነው እንዴ?” እያሉ ይሣለቃሉ። በውጭው ግን ለምእመኑ ፍጹም ጸሎተኛ፣ እህል የማይበሉ፣ ጿሚ፣ ተኃራሚ እንደሆኑ ያስመስላሉ
 • አባ ፊልጶስ፣ እርሳቸው ጋር ለመኖር ከገቡት ካህናት ጋር በሙሉ ተጣልተው ነው የሚለያዩት፤ ምክንያቱም ግልጽ ነው። በውጭ የሚያሳዩትን ሕይወት በሐቅ ስለማይኖሩት ከራሳቸው ወዳጆችና ግድ ብለው ካስመጧቸው አባቶች ጋር ሳይቀር በከባድ ጠብ ነው የተለያዩት። ይህንንም እስከ ዛሬ ከአባ ፊልጶስ ጋር የኖሩትን አባቶችና ወንድሞች በሙሉ ብታነጋግሩ እውነቱን ትደርሱበታላችሁ።
 • አባ ፊልጶስ በሥራ ሰነፍ ይሁኑ እንጂ አድማ ለመሥራት፣ ሰውና ሰውን ለማለያየት ተግተው የሚሠሩ ሰው ናቸው። በተለይ በደብራችን ውስጥ የሚገኙትን ኹለቱን ካህናት፥ ቀሲስ ጥበቡንና ቀሲስ ብሥራትን እርስ በርስ ሲያጣሉና ሲያለያዩ ኖረዋል። ካህናቱ ግን በአሁን ሰዓት የሰውዬውን ተንኰል ተረድተው አንድ ሲሆኑ ደግሞ፣ ሁለቱንም ካህናት ከሕዝብ ጋር ማጣላቱን ሥራዬ ብለው ይዘውታል። በዚህም ምክንያት ምእመናን ተስፋ እንድንቆርጥ እያደረጉን ነው፡፡ በርካታ ምእመናን በነገሩ ተበሳጭተውና አዝነው ከቤተ ክርስቲያን ሸሽተው ከቤታቸው ተቀምጠዋል። ይህንንም ካህናቱን መጠየቅና ማረጋገጥ ይቻላል።
 • አባ ፊልጶስ የዘመናት ምኞታቸው ጳጳስ መሆን ነው፡፡ ይህንንም ለማግኘት የማይቆፍሩት ጉድጓድ፣ የማይቧጥጡት ተራራ፣ የማይወጡት ዳገት የለም። “ለገዳማት” በሚል ሽፋን፣ በየዓመቱ ወደ ኢትዮጵያ በሔዱ ቁጥር ከዐሥር አስከ ዐሥራ አራት ሻንጣ በመያዝ ከምስኪኑ ምእመን የሚሰበስቡትን ገንዘብ ብፁዓን አባቶችን እንደሚደልሉበት ይገልጻሉ፡፡ በርግጥ የእኛ አባቶች እርሳቸው በሚያመጡት መደለያ ታላቁን የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን እንደማይሰጡ ብናምንም፣ እርሳቸው ግን በዚህ ለመግባት ብዙ እንደሚጥሩ እናውቃለን።
 • በርካታ ገንዘብም ንቡረ እድ ኤልያስ ለሚባሉ ሰው እንደሰጡ፣ ከኢትዮጵያ ተመልሰው ሲናገሩ ተሰምተዋል። እንዲሁም ለዝዋይ ገዳም በርካታ ነገሮችን እንደሚያደርጉ ይታወቃል። እውነት ለመናገር አባ ፊልጶስ በቤተ ክርስቲያን አምነውና ለገዳሙ አዝነው ቢሆን ምንም ባልከፋን ነበር። የእርሳቸው ዓላማ ግን ይህን በማድረጋቸው ከብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሞገስ አግኝተው ለጵጵስና እንዲያበቋቸው በማሰብ ነው። ይህን አምላከ ቅዱሳን ያውቀዋል።
 • በፊት ለፊት ይህን ያድርጉ እንጂ አቡነ ጎርጎርዮስ፥ ከኢትዮጵያ እንዳባረሯቸው፣ በኋላም ወደ ቤሩት እንዳስመደቧቸው፣ ከአባ ጳውሎስ እንዳጣሏቸው፣ በአጠቃላይ ደመኛቸው እንደሆኑ ሲናገሩ ነው የኖሩት።

በአጠቃላይ ስለ አባ ፊልጶስ ከበደ ተናግሮ መጨረስ ስለማይቻል፣ ብፁዓን አባቶች የአስመራጭ ኮሚቴው አባላት፣ ይህን ፍንጭ በመያዝ ነገሩን አጥንታችሁ እንድትደርሱበት እንማፀናችኋለን፡፡

“የተቀደሰውን ለውሻ አትስጥ” በሚለው የወንጌል ቃል መሠረት፣ የቤተ ክርስቲያን ዕውቀት ለሌላቸው፤ በግብረ ሰዶም ለሚጠረጠሩ እንዲሁም፣ ለቤተ ክርስቲያን ዶግማና ቀኖና ክብርና ዋጋ ለማይሰጡ ሰው የተቀደሰውን የእግዚአብሔር ሥልጣን ከመስጠታችሁ በፊት ነገሩን እንድትመረምሩ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አምላክ በልዑል እግዚአብሔር ስም ከእግረ መስቀላችሁ ሥር ወድቀን እንለምናችኋለን።

በረከታችሁ ይድረሰን!

በቨርጅንያ ማኅደረ ስብሐት ልደታ ማርያም የምንገኝ ምእመናንና ቀድሞ በዚሁ ደብር ቆይተን በአሁን ሰዓት በሌሎች አብያተ ክርስቲያናት የምንገኝ ምእመናን

የአስመራጭ ኮሚቴው ብፁዓን አባቶች ለበለጠ መረጃ በተጠቀሰው የስልክ አድራሻችን ሊያነጋግሩን ይችላሉ፡፡ 

Advertisements

75 thoughts on “ለጵጵስና በተጠቆሙት የቨርጂኒያው አባ ፊልጶስ ከበደ ላይ የምእመናን አቤቱታ ቀረበ፤ ፀረ ቅዱሳን፣ ሞያ ቢስ፣ ሐኬተኛና አድመኛ ናቸው

 1. Anonymous July 21, 2017 at 1:32 pm Reply

  Whomever wrote these nasty comments may God have mercy upon you. Devils tongue. You spread lies and should withdraw these false accusations! Aba Phillipos is a blessed man. Truly one who does not judge as it says to do so in the Bible. A quality unfortunately many do not have!

 2. Derek July 21, 2017 at 1:45 pm Reply

  May God have mercy on you for spreading these lies. Devils tongue.
  Aba Phillip is a kind soul. Truly someone that does not judge as it says to do in the Bible. You presents the facts of the Bible and leds people to Christ. A true messenger. You should be absolutely ashamed of yourselves.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: