ሰበር ዜና – የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከልዩ ጽ/ቤቱ ተወገዱ!

 • ምንም ዓይነት ምደባ አልተሰጣቸውም
 • ምደባቸውን በውጭ ኾነው ይጠባበቃሉ
 • “ቦታ የለኝም”/ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ/
 • ቀጣዩ ልዩ ጸሐፊ ከዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር በመመካከር ይመደባል፤ ተብሏል

*               *               *

 Pat Abune Mathias and Nibure'Ed Elias Abreha
በፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የልዩ ጸሐፊነት ሥልጣናቸው ተገን፣ የሙስና ሰንሰለት ዘርግተው ሕገ ወጥ ሀብት በማካበትና በክፉ ምክራቸው ለበርካታ የውስጥ አለመግባባት መንሥኤ የነበሩት የመዝባሪዎች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ከሓላፊነታቸው ተወገዱ!!

ልዩ ጸሐፊው፣ በእጃቸው የሚገኘውን ንብረት፣ ዛሬ፣ ሰኞ፣ ሰኔ 27 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አቡነ ቀሲስ፣ አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ አስረክበው፣ ልዩ ጽ/ቤቱን እንዲለቁ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ከቅዱስነታቸው በተላለፈ ትእዛዝ መሠረት ነው፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከልዩ ጽ/ቤት ሓላፊነታቸው የተወገዱት፡፡

ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ከሓላፊነታቸው ከተወገዱ በኋላ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከሚገኙት ድርጅቶች አልያም መምሪያዎች በአንዱ፣ በዋና ሓላፊነት ሊመደቡ እንደሚችሉ ቀደም ብሎ ቢዘገብም፣ ምንም ዓይነት ምደባ እንዳልተሰጣቸውና በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ ቦታ ተገኝቶላቸው እስኪመደቡ ድረስ እንዲጠባበቁ በፓትርያርኩ ከተጻፈላቸው የማሰናበቻ ደብዳቤ ለመረዳት ተችሏል፡፡

ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የንቡረ እዱን ተለዋጭ ምደባ አስመልክቶ ከፓትርያርኩ እንደተጠየቁና፣ “ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ውጭ ካልኾነ፤ ቦታ የለኝም፤” ማለታቸውን የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ምንጮች ጠቅሰዋል፡፡

ንቡረ እዱ፣ በአስተሳሰባቸው ይኹን በተግባራቸው ያሉበት ብልሹ ተክለ ሰብእና፣ ከመንበረ ፓትርያርኩም ኾነ ከልዩ ጽ/ቤቱ ደረጃ እና ክብር ጋር በመሠረቱ የማይጣጣምና የቅዱስነታቸውም ልዩ ረዳት ሊኾኑ እንደማይገባ በመጥቀስ ከቦታው እንዲርቁ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በምልአተ ጉባኤ ደረጃ፤ ቋሚ ሲኖዶሱም በመደበኛ ስብሰባዎቹ እንዲኹም፣ ብፁዓን አባቶችና የፓትርያርኩ የቅርብ ወዳጆች እንደ ግለሰብ፤ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሲመክሩና ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡

በግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ልዩ ጸሐፊው ሳይገባቸው ከያዙት ቦታ በአጭር ጊዜ እንዲነሡ፣ ምልአተ ጉባኤው ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥብቅ ማሳሰቢያ እንደሰጣቸውና ቅዱስነታቸውም፣ ይህንኑ እንደሚፈጽሙ ማረጋገጣቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ 

“አንዴ፣ ምልአተ ጉባኤው ሳያልቅ አያንሡኝ፤ ሌላ ጊዜ ትምህርቴን እስክጨርስ ይታገሡኝ” የሚለው የንቡረ እዱ ተማኅፅኖ፣ ፓትርያርኩን እስከ አኹን ድረስ እንዳዘገያቸው ቢገለጽም፤ ዋናው መንሥኤ፣ በቦታው የሚተካና የፓትርያርኩ ምርጫ የኾነ ሰው አለመገኘቱ ነው፤ ይላሉ የመንበረ ፓትርያርኩ ምንጮች፡፡

ልዩ ጸሐፊው፣ ልዩ ጽ/ቤቱን ዛሬ ከቀትር በኋላ ለአቡነ ቀሲሱ ሲያስረክቡ፣ የካህናት አስተዳደር መምሪያው ዋና ሓላፊ መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም፣ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ሰላም ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ በእማኝነት ተገኝተዋል፤ ተብሏል፡፡

የኒውዮርክ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና በአሜሪካ ስለ ጤና አገልግሎት አስተዳደር በሚያማክር ብሔራዊ ኩባንያ ውስጥ በፕሬዝዳንትነት የሚሠሩ የፓትርያርኩ የቅርብ ወዳጅ፣ ዶ/ር ሙሴ ሐረገ ወይን ቦታውን እንደሚይዙና ጥሪም እንደተላለፈላቸው ሲገለጽ ቢቆይም፣ ፓትርያርኩ ለኤጲስ ቆጶስነት ከጠቆሟቸው ቆሞሳት መካከል አንዱ የኾኑት፣ አወዛጋቢው ቆሞስ አባ ሠረቀ ብርሃን ሊተኩ እንደሚችሉ ከወዲኹ ተገምቷል፡፡

በሌላ በኩል፣ የግንቦቱ የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤ፣ የልዩ ጽ/ቤቱ አወቃቀር፣ ተግባርና ሓላፊነት በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረቱን ይዞ፤ በአስፈላጊው የሰው ኃይል ተደራጅቶ በሊቀ ጳጳስ እንዲመራ የወሰነው ተግባራዊ እስኪኾን፤ ቀጣዩ ልዩ ጸሐፊ፣ ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቡነ ዲዮስቆሮስ ጋር በመመካከር እንደሚመደብ ነው፣ እየተገለጸ የሚገኘው፡፡

Nibure'Ed Elias Abreha Mesfin
በአቋቋም የመዘምርነት ሞያ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ መስፍን፣ ከአንድ ዓመት በፊት ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማታው መርሐ ግብር በሥነ መለኰት በዲፕሎማ፣ ዘንድሮ ደግሞ በዲግሪ 
“በከፍተኛ ማዕርግ” ተመርቀዋል፤ ከአልፋ ዩኒቨርስቲ በማኔጅመንት በርቀት የወሰዱት ሌላ ዲፕሎማ እንዳላቸውም ተገልጧል፡፡

ንቡረ እዱ፣ በልዩ ጸሐፊነት ልዩ ጽ/ቤቱን ከተቆጣጠሩበት ካለፈው ዓመት ወዲኽ ያለው ጊዜ አጭር ቢኾንም፣ የሚሰጡትን ክፉ ምክርና የሚያረቋቸውን ደብዳቤዎች ተከትሎ፣ ፓትርያርኩ ባራምዷቸው ሕግንና ምክረ አበውን የሚጥሱ አቋሞች፤ የቤተ ክርስቲያናችንን መልካም ስምና ዝና የሚጎዱ በርካታ ውዝግቦች ተፈጥረዋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችንና የቋሚ ሲኖዶስ መመሪያዎችን በቸልታ እየተላለፉ፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱንና የአህጉረ ስብከትን ሥልጣንና ተግባር እየተሻሙ፣ ከብፁዓን አባቶችና ሌሎች አስፈጻሚ አካላት ጋር አባታዊ እና የሥራ ዝምድናን የሚያሻክሩ ከፍተኛ አለመግባባቶች ተከሥተዋል፡፡ 

ፓትርያርኩ ራሳቸው፣ በየመድረኩ የሚናገሩላቸው፤ ትክክለኛውን ሰው በትክክለኛው ቦታ የሚያስቀምጡ፤ ግልጽነትንና ተጠያቂነትን የሚያሰፍኑ፣ በበጎ ፈቃድ የተደከመባቸው የተቋማዊ ለውጥ ተስፋዎችና ጅምሮች በከንቱ መክነዋል፡፡

Addis Ababa Sunday Schools at the Holy Synod Opening Prayer
ይህም በውጤቱ በፈጠረው የብዙኃን ተቃውሞና ግፊት፣ ፓትርያርኩ ንቡረ እዱን መልሰው የወቀሱባቸው ጥቂት አጋጣሚዎች የነበሩ ቢኾንም፣ በአብዛኛው ግን፣ በፓትርያርኩ ዘንድ የማይተኩ አለኝታ ተደርገው የታዩበትና፤ ከጥቂት ባለሥልጣናት ጋርም ልዩ ቅርበት የፈጠሩበት አጋጣሚ እንደነበር ነው የሚታመነው፡፡

አዲስ አበባ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት ከመኾኑም ጋር ተያይዞ፣ ንቡረ እዱ ቀደም ሲል በሥራ አስኪያጅነት ሲሠሩ በዘረጉትና በልዩ ጸሐፊነታቸው ተገን ባጠናከሩት የምዝበራ ሰንሰለት፤ ከጉዳይ ማስፈጸም፣ ከአለቆችና ሠራተኞች ዕድገትና ዝውውር ተቀማጫቸውን አድልበዋል፤ በቀጣይም፣ በከተማው የተለያዩ ይዞታዎቻቸው ለከፍተኛ ‘ኢንቨስትመንት’ መዘጋጀታቸው ይነገራል፡፡

በቤተሰባዊነት የሚዛመዷቸውን የወቅቱን የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅ በማስመደብ፤ እንዲኹም፣ በቅርቡ፣ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ በሌሉበት፣ ከአስተዳደር ጉባኤው ዕውቅና ውጭ አልቆ በመጣው ከደርዘን በሚልቁ የአድባራት አለቆችና ጸሐፊዎች ዝውውርና ምደባ፣ፓትርያርኩን በመወትወት ጭምር የነበራቸው ወሳኝ ሚናና ያተረፉበት ኹኔታ፤ ‘የኢንቨስትመንት’ ድልባቸውን ያጠናከሩበት መሰናበቻ እንደነበር ተጠቁሟል፡፡

በሀገረ ስብከቱ፣ በሥራ አስኪያጅነት በሠሩበት 2003 ዓ.ም.፣ በምዝበራ ሰንሰለቱ ያሉ የጥቅም አጋሮቻቸው፣  በልማት ጉብኝት ስም አጥንተው በሚያመቻቹላቸው የዘረፋ ስልት፣ በየአድባራቱ በሚዘዋወሩበት ወቅት፣ “የኮቴ” የተሰኘና በእያንዳንዱ ከ25ሺሕ ያላነሰ ብር የሚቀበሉበት አማሳኝነት/አንቃዥነት፣ በንቡረ እዱ የተጀመረ ውርስ እንደኾነ፣ ከእርሳቸውም በኋላ የቀጠለና ዛሬም ድረስ የሚነገር እውነታ ነው፡፡

ከመናፍስት ጋር በተያያዙ ክፉ ልማዶች ጭምር ስማቸው የሚነሣው የቀድሞው መሪጌታ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ንቡረ እድ ከተባሉበት የርእሰ አድባራት ወገዳማት አኵስም ጽዮን ካቴድራል በሕዝብ እንዲባረሩ ያደረጋቸው ይኸው የምዝበራ አመላቸው ነበር፡፡ ከአዲስ አበባ አድባራት ራሱን ችሎ በሙዳየ ምጽዋት በሚሰበሰብ ገንዘብ የሚሠራው የካቴድራሉ ሙዝየም ግንባታ ውል፣ በተፈጸመበት ኹኔታም ክፉኛ መወቀሳቸው አልቀረም፡፡

ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ ለአጭር ጊዜም ቢኾን፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ እና በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በዲንነት፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነት መንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ሥራ አስኪያጅነትም ሠርተዋል፡፡

Nibure'Ed Elias Abreha00
ብልጡ መለኛ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የመወገዳቸው ጉዳይ፣ ለረጅም ጊዜ በተለያየ መልክ ሲገለጽ ቢቆይም፣ ዛሬ ተጨባጭ እስኪኾን ድረስ፣ ብዙዎችን፣ “ካላየን አናምንም” አሰኝቷቸዋል፤ አይነኬ እና ልዩ ምትሃዊ አድርገው የሚያዩዋቸውም አልጠፉም፡፡

ንቡረ እዱ፣ በተማሪ ቤት ሥልጥንናቸውን ያሳዩበትን የአቋቋም ሞያ ይዘው፣ ወደ አዲስ አበባ በ1980ዎቹ አጋማሽ ሲገቡ፣ አገልግሎታቸውን የጀመሩት በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመዘምርነት ነበር፡፡ ከልዩ ጽ/ቤቱ መወገዳቸው እውን ኾኖ ዛሬ ከሓላፊነታቸው ሲነሡ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ቦታ ይፈለግላቸው ቢባልም፣ ትክክለኛ ምደባቸው ከመዋቅራዊ ሓላፊነት ውጭ በተወሰነ ቦታ እንዲኾን ብዙዎች ይሻሉ፤ መቼም ለተጠያቂነት ሥርዓቱ አላደለንምና!!


 

Advertisements

20 thoughts on “ሰበር ዜና – የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከልዩ ጽ/ቤቱ ተወገዱ!

 1. Anonymous July 4, 2016 at 3:57 pm Reply

  Ketayu tsehafi Dr Musie ze_america sihon Nibured elisas mikitil sira askiani yihonalu (aba dr. Hailemariam sishomu). Wait!!!!!

  • GETNET GEZE July 4, 2016 at 4:48 pm Reply

   IDONT THINK BROTHERS he has worked for 9 years as vice manager before ABA DR. Haule Mariam was appointed. The only place he deserve is JAIL!

 2. abrham July 4, 2016 at 5:30 pm Reply

  ታላቁ ጋኔን ወደቀ

  • Anonymous July 4, 2016 at 8:16 pm Reply

   ዛቲ ዕለት እንተ ገብረ እግዚአብሄር ንትፈሳህ ወንትሀሰይ ባቲ ንቡረ ዕድ ኢልያስ አብርሃ ከቤተክህነት ወጥቶ ጉምሩክ ቢቀጠር ጥብቅ ቁጥጥር ስለሚደረግበት አይጎዳም ይጠቅማል ምክንያቱም አዲስ ታክስ የመፍጠር አቅም ስላለው ነው በቤተክርስቲያንዋ ያልነበሩ ንቡረዕዱ የፈጠራቸው የዘረፋ ገቢዎች
   1ኛ የኮቴ ግብር ከብር 10000-25000 ሽህ
   2ኛ የአዲስ ቅጥር ገቢ ከብር 30000-80000 ሽህ
   3ኛ የዝውር ገቢ ከብር 40000-100000 እልቅና
   4ኛ ሙዳየሙፅዋት ከሚዘረፍበት ደብርና ገዳም 6ኛተካፋይ በመሆን በሽፋንሰጭነት ምሳሌ ከልደታ ማርያም፡ ከቦሌ መድሀኔዓለም ፡ከብስራተ ገብርኤል ፡ ከአክሱም ኮሚቴ ፡ ከተጎዱ አብያተክርስቲያናት ፡ከውጭ አካላት እንዲሁም ከማስፈራራት ከዚህ ውጭም የአቡነ ጳውሎስ ዕረፍት ምክንያት አድርጎ ከማፍያዎች ጋር የአክሱም ሙዚየም ዲዛይን የተሰራበት በማለት 250ሽህ ዶላር በሌለው ስልጣን ውል ተዋውሎ ሊያጭበረብር ተደርሶበታል ከኢትዮጵያ ሌቦች አልፎ እስከጣልያን ማፍያዎች የሌብነት ህብረት ያለው በታላላቅ የፖለቲካ ሰዎች የሚነግድ ደረቅ ሌባነው ንቡረ ዕድ ሳይ ሆን መባልያለበት ነውራም ዕጅ ነው ቤተክርስቲያን ዕንኴን ከዚህ መንፈሳዊ መሳይ አይነደረቅ ሌባ ገላገለሽ በመሰረቱ ንቡረ ዕዱ ለቀባሪ አረዱት ነው እንጂ ሰውም ይበላልተምቤኖች ዕንደነገሩን ወስብሀት ለእግዚአብሄር

 3. Anonymous July 4, 2016 at 7:56 pm Reply

  ዋናው ሰይጣን ተባሯል አሁን የቀረው ሌላው ሰይጣን አቡነ ማትያስ ተብዬውን ነው።

 4. Anonymous July 4, 2016 at 8:53 pm Reply

  እርጉሙ ሐዋርያ!

 5. Anonymous July 5, 2016 at 5:10 am Reply

  ለአንደበትህ አደብ አድርግበት

 6. Anonymous July 5, 2016 at 6:34 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን!! ገና እንጠብቃለን ለሁሉም ጊዜ አለው ብሏል፡፡ ሁሉንም እንደስራው የሚሰጥ አምላክ ዝም አይልም ቢቆይም ዋናው ነገር እግዚአብሔር መልስ እንዲሰጥ ወደ እሱ ማልቀስና ማንባት ይሻላል፡፡ ለሁሉም እንደስራው የሚከፍል እሱ ነውና እባካችሁ አሁንም ክርስቲያኖች በሙሉ ወደ አምላካችን እንጩኽ መልሱ ከሱ እንዲሆን፡፡ ይቆያል እንጂ ዝም አይልም ለንቡረእዱም የንፁሐን አምላክ እግዚአብሔር የስራውን ቆጥሮ ሰፍሮ ይሰጠዋል በእርግጠኝነት አምናለው ያከማቸውንም የቤተ ክርስቲያን ሐብት ንብረት ይበላዋል ብላችሁ ነው…
  እውነተኛ አምላክ እሱ ይፍረደው ኦ እግዚአብሔር ሆይ ተመስገን ተመስገን እንልሐለን ሁል ጊዜ፡፡

 7. Anonymous July 5, 2016 at 7:30 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ታላቅ ነገር አደረገልን ደስም አለን ብሏል፡፡ እባካችሁ አባቶቼ አሁንም ጥንቃቄ አድርጉ በቦታው የሚቀመጠውን አባት ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን ምረጡ ከሰው ጋር ሆኖ ከመምረጥ ይልቅ ምክንያቱም ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆንብን እንባችንን እግዚአብሔር አብሶታል፡፡ ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሳት ትልቁ የቤተክርስቲያን ጠላት /ጋኔል/ ቦታውን ለቀቀ ወደቀ ተመስገን አምላክ ሆይ ለቤተክርስቲያን ለሐገር የሚያስብ አባት አምጣልን በቦታው ለንቡረእዱ ደሞ እንደስራው ዋጋውን ክፈለው ሌላ ምንም አልልም ተመስገን አምላክ ሆይ፡፡ መቼም መቼም ቢሆን እንደዚህ አይነት /ጋኔል/ አይመጣምም የለምም አባት ሆን ተመስገን፡፡ ይህንን ያሳየኸን አምላክ ክብር ምስጋና ይድረስህ አሜን፡፡

 8. Anonymous July 5, 2016 at 8:01 am Reply

  ርኩስ መንፈስ ግን ከሰው በወጣ ጊዜ/Nibure Ed Elias /፥ ዕረፍት እየፈለገ ውኃ በሌለበት ቦታ ያልፋል፥ አያገኝምም።
  በዚያን ጊዜም። ወደ ወጣሁበት ቤቴ እመለሳለሁ ይላል፤ ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል።
  ከዚያ ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎችን አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል/Ene Aba Se’re’ken/፥ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ፤ ለዚያም ሰው ከፊተኛው ይልቅ የኋለኛው ይብስበታል/Le Aba Matiays/። ለዚህ ክፉ ትውልድ ደግሞ እንዲሁ ይሆንበታል።

 9. Anonymous July 5, 2016 at 9:55 am Reply

  temesgen! Yemechereshaw mejemeriya hone

 10. Anonymous July 5, 2016 at 1:10 pm Reply

  ስራ ባለቤቴ በድንገት መስሬቤት ትቀነሳች እንዲህ ከሆነገች አስር ይበቃናል ብለን መክፈል ስንጀምር
  አንድቀን እድቀን እደአባት ሰላም ብሎየማያውቀው የስም መነኩሴ ተብየ አባ ሲራክ እንዴት አስሩን ትቀንሣላችሁ እየተመካከራችሁ አይደል ስብሰባ ገብታችሁ ለመናገር እንዲያመቻችሁ ብላችሁ እንጂ እስካሁን ጨርሶ ትወጡነበር
  እኔን ለመበጥበጥ ነው ከዚህ የምትመጡ ብሎሰደባት ባለቤን ተመልከቱ
  አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የሗላታሬኩ እደሜስረደው ከአርባምንጪ ገብርኤል ወደቅዱስሜካኤል
  በምን ምክንያት እደተዛወረ አርባምንጪ አገርስብከት መረዳት አዲስ አበባቅድስትማርያም ምንይሰራእንደነር
  በአጭሩ መረዳት ይቻላል ቆቡን አውልቆ በየሴታዳሬወች ሲዞር
  እንዲሁም ባለትዳሮችን ለማስቀደስ ፈተና እስከሚሆንባቸው ድረስ
  ሌላው በጫት ሱስ እና በሲጋራ አጫሽነት ሀገርቤት ይታወቃል
  ከዚህ ፋንክፈርት ጀርመን ህይወቱ ተመሣሣይ
  ነው በተለምዶ ፋራንክፈርት ካይዘር እስትራሰ እየተባለ በሜጠራው ሴታዳሬወች ቦታ
  ሲመላለስ ሁሉም ሰውያገኝዋል ክርስቲያኑ ቀርቶ አስላች ያውቁታል
  በዝሙቱ ይህንን ስእፅፋ ልዮጥላቻ ለእሱ ኑሮኝ ሣይሆን ካህን ስላይደለነው
  ገዳም ነበርኩኝ ይላል አወገዳም ነበረ ፈተነውን መቇቇም አቅቶት ይህንን ሁሉ
  ሐጤያት የሚያሠረው ከገዳም ያወጣው ሰይጣን ነው አንዴ አባ ሲራክ
  አንዴ አባ ሐይለመለኮት መልም ሰራእንጄ ሰም በመቀየር ሹመት አይገኝም
  ጉልቻ መቀየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል
  የያዘው ሰይጣን ክርስቴያኖችን ማሳደድ አስር ጌዜየ ማህበረቅዱሳን እረበቨኝ
  በነጻ እየረዱት ሄኖክ ወንድወን
  እባክህ ብለን ብንለመነው ማህበረቅዱሣን ይውጣልኝ ብሎ ከፈላችው
  ይህ ኖለት ጳጳስ ቢሆን ጥሩይሰራይሆን እውነቱን እናጋልጥ አለም አዲትመንደር ሁናለች
  እና እውነትወታ በሲራክ ሴራ ከሁለት የተከፈለው የፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ምመናን አንድመሆን
  አለበት እንላለን እውነቱን ስንናገር እኔ ትግሬስለሆንኩኝ ነው እያለ በየዋህ ክርስቴያኖች ቤት ማልቀሱ የማይቀርነው
  ግን ትግሬ በመሆኑሣይሆን ሐጤያተኞ የመቤታን ካዝና በአዶ ያስቀረ ህዝብ የበተነ ዛሬየተናገረውን ነገ የማይደግም
  ትግሬኮሜቴ ካልተመረጠ ብሎ ተመረጠለት ግን የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ ነውና
  ትክክል እንስራ ሲሉት ሲቆጣጠሩት ስም መጥራት ጀመረ ቴዎድሮ እላሠራኝ አለ ሰለተቆጣጠረው እኮነው
  ሰለዚህ ገንዘብ ያላግባብ ሲዘርፋ እና ሲዘሙት እያየ ዘምያላለሰው ለአባ ሲራችክ ጥሩ አይደለም
  ኮሦኮሦም ቢይላቸው አባ ሲራክ ተብየው እውነት እንናገራለን ለድንግልርያም ብለንከፋል ኑረን
  Gefällt mir · Antworten · 2. Juli um 13:33

  Leave a Reply

 11. ምን አገባህ July 5, 2016 at 7:05 pm Reply

  መቸም ከሰይጣንም እኮ ጥሩ ወሬ አይጠፋም። ዶክተር ሙሴ የኒውዮርኩን ማለታቸሁ ነው እረ ተው አታስጎምጁን ዶክተር እኮ በጣም ትልቅ ሥራ ያላቸው ሰው ናቸው ። እውነት ሆኖ ኦሺ ካሉ እዚያው ሆነው ሥራቸውን እየሰሩ በስልክ ብቻ እንኳ ሊያስተዳድሩ የሚችሉ ታላቅ ምሁር አዋቂ ናቸው ። አይ እግዚአብሔር ፊቱን መለሰልን ይቅርም አለን ማለት ነው ዶክተርን ከሰጠን ።

 12. Anonymous July 6, 2016 at 2:51 am Reply

  Betam yemasazinew. Dr. Muse has a great job in the US. Considering him as assistant to the Pope is an insult.

 13. ገሊላ July 6, 2016 at 5:42 am Reply

  መጀመሪያ ኑብረዕድ ኤልያስ ማለት ካህን ናቸው ቤተ ክህነት ከእናንተ ለእሳቸው ይቀርባል ። ዝውውር ያለ ነገር ነው አልተመደቡም የምትሉት ይመደባሉ ያውም ደረጃቸውን በጠበቀ መልኩ።
  በእርግጥ ማህበረ ቅዱሳን ከሚባል አጋንንት ጋር ስለማይሞዳሞዱ ብቻነው የምትለፈልፉት ። ኑብረዕድ ከቤተክርስቲያኗ ምንሞ ሊያስቀራቸው አይችልም ።
  ወሬ አታብዙ

  • Anonymous July 7, 2016 at 5:46 am Reply

   ገሊላ ገላህ ይጠበስና ንቡረ አድ ሌባ አይደለም እያልከን ነው አንተ ራስህ የተጎዱ አቢያተክርስቲያናት ወይም የዐክሱም ሙዳዬ ሙፅዋት ቆጣሪ ነህ ወይም የቅጥርና ዝውውር ደላላ ነህ ማን ያርዳ የቀበረ ማን ያርዳ የነበረ ሌላ ይቅርና የብስራተ ገብርኤል አለቃ የነበረው ሀይሌ አብርሃ ሰንዳፋ ላይ ብቻው ቤት የገዛለት ለሌብነቱ ሽፋን ስለሆነለት እንጂ ሽማግል አባቱ ሆኖ ነው እንዴ ስማ ለንቡረእዱ የኮቴ ብር ያልከፈለ አስተዳዳሪ በምድር ላይ የለም ግን ሰውየው አያፍርም ይሉኝታ ቢስ ነው አዙሮ የሚያይበት አንገት የለውም ጉበኝነት ፈቃድ ያለው ስራ አድርጎታል ጉበኛ ጎጠኛ አድመኛ በበላበት አፍ የሚናገር የፈጣሪ መኖር የማያምን እንዲህ ያለውን (ወለብሳ ለሀፍረት )

 14. Bete Zewudu July 6, 2016 at 2:39 pm Reply

  1Bete Zewudu
  Kommentare
  Bete Zewudu
  Bete Zewudu ስራ ባለቤቴ በድንገት መስሬቤት ትቀነሳች እንዲህ ከሆነገች አስር ይበቃናል ብለን መክፈል ስንጀምር
  አንድቀን እድቀን እደአባት ሰላም ብሎየማያውቀው የስም መነኩሴ ተብየ አባ ሲራክ እንዴት አስሩን ትቀንሣላችሁ እየተመካከራችሁ አይደል ስብሰባ ገብታችሁ ለመናገር እንዲያመቻችሁ ብላችሁ እንጂ እስካሁን ጨርሶ ትወጡነበር
  እኔን ለመበጥበጥ ነው ከዚህ የምትመጡ ብሎሰደባት ባለቤን ተመልከቱ
  አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የሗላታሬኩ እደሜስረደው ከአርባምንጪ ገብርኤል ወደቅዱስሜካኤል
  በምን ምክንያት እደተዛወረ አርባምንጪ አገርስብከት መረዳት አዲስ አበባቅድስትማርያም ምንይሰራእንደነር
  በአጭሩ መረዳት ይቻላል ቆቡን አውልቆ በየሴታዳሬወች ሲዞር
  እንዲሁም ባለትዳሮችን ለማስቀደስ ፈተና እስከሚሆንባቸው ድረስ
  ሌላው በጫት ሱስ እና በሲጋራ አጫሽነት ሀገርቤት ይታወቃል
  ከዚህ ፋንክፈርት ጀርመን ህይወቱ ተመሣሣይ
  ነው በተለምዶ ፋራንክፈርት ካይዘር እስትራሰ እየተባለ በሜጠራው ሴታዳሬወች ቦታ
  ሲመላለስ ሁሉም ሰውያገኝዋል ክርስቲያኑ ቀርቶ አስላች ያውቁታል
  በዝሙቱ ይህንን ስእፅፋ ልዮጥላቻ ለእሱ ኑሮኝ ሣይሆን ካህን ስላይደለነው
  ገዳም ነበርኩኝ ይላል አወገዳም ነበረ ፈተነውን መቇቇም አቅቶት ይህንን ሁሉ
  ሐጤያት የሚያሠረው ከገዳም ያወጣው ሰይጣን ነው አንዴ አባ ሲራክ
  አንዴ አባ ሐይለመለኮት መልም ሰራእንጄ ሰም በመቀየር ሹመት አይገኝም
  ጉልቻ መቀየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል
  የያዘው ሰይጣን ክርስቴያኖችን ማሳደድ አስር ጌዜየ ማህበረቅዱሳን እረበቨኝ
  በነጻ እየረዱት ሄኖክ ወንድወን
  እባክህ ብለን ብንለመነው ማህበረቅዱሣን ይውጣልኝ ብሎ ከፈላችው
  ይህ ኖለት ጳጳስ ቢሆን ጥሩይሰራይሆን እውነቱን እናጋልጥ አለም አዲትመንደር ሁናለች
  እና እውነትወታ በሲራክ ሴራ ከሁለት የተከፈለው የፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ምመናን አንድመሆን
  አለበት እንላለን እውነቱን ስንናገር እኔ ትግሬስለሆንኩኝ ነው እያለ በየዋህ ክርስቴያኖች ቤት ማልቀሱ የማይቀርነው
  ግን ትግሬ በመሆኑሣይሆን ሐጤያተኞ የመቤታን ካዝና በአዶ ያስቀረ ህዝብ የበተነ ዛሬየተናገረውን ነገ የማይደግም
  ትግሬኮሜቴ ካልተመረጠ ብሎ ተመረጠለት ግን የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ ነውና
  ትክክል እንስራ ሲሉት ሲቆጣጠሩት ስም መጥራት ጀመረ ቴዎድሮ እላሠራኝ አለ ሰለተቆጣጠረው እኮነው
  ሰለዚህ ገንዘብ ያላግባብ ሲዘርፋ እና ሲዘሙት እያየ ዘምያላለሰው ለአባ ሲራችክ ጥሩ አይደለም
  ኮሦኮሦም ቢይላቸው አባ ሲራክ ተብየው እውነት እንናገራለን ለድንግልርያም ብለንከፋል ኑረን
  Gefällt mir · Antworten · 2. Juli um 13:33
  Gefällt mir · Antworten · 4. Juli um 13:47

 15. Anonymous July 6, 2016 at 3:43 pm Reply

  ይሙት

 16. Mebrahtom August 9, 2016 at 6:34 pm Reply

  እኔ የሚገርሞኝ የሐራ ተዋህዶ(ማህበረ ቅዱሳን) ዓላማቹ ምንድ ነው ? ቤተክርስትያን እና ሀገር እየጠቀማቹ አይደለም፤ ዘር እየለያችሁ፡ ብሄር እየለያችሁ፡ያልሆነ ስም እየቀባቹ ፡ በሀይማኖት ምክንያት አድርጋቹ ፡ግን ፖለቲካዊ ስራ እየሰራቹ ያላቹ መሆችሁን አረጋግጠናል፡ስለዚህ ከነዚህ እንቅስቃሴዎች እንድትቆጠቡ አሳስባለሁ፡፡ የምትሉት ሁሉ ውሸት መሆኑን የማረጋግጠው ” ንቡረ እድ ኤልያስ ከአክሱም ተባረዋል” የሚለው ነው ፡፡ምክንያቱም እኔ እዛ ስለነበርኩኝ፡ በጥሩ ምስግና እንደሄዱ ነው የማውቀው፡፡ ባንዋሽ ጥሩ ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: