የአ/አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በተሐድሶ ኑፋቄ አደጋ ውስጥ! ‘አባ’ አፈ ወርቅ ዮሐንስ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመደበ፤15 አለቆችና ጸሐፊዎችም ተዛውረዋል

Aba Afework Yohannes

ከሆሮ ጉድሩና ወሊሶ በምግባር ብልሽትና በእምነት ሕፀፅ ቢባረርም፤ በቀድሞው የሀገረ ስብከቱ አስተዳደር በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ሥራ አስኪያጅነት ተመድቦ በምዝበራ የቆየውና፤ ከውጭ ጉዳዩ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ ጋር ባለው የዓላማና የጥቅም ግንኙነትከፓትርያርኩ በተሰጠ ቀጥተኛ አመራርና በሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም ያይኑ በተፈረመ ደብዳቤ፣ በዛሬው ዕለት፣ በሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅነት የተመደበው፣ መናፍቁ እና ዋልጌው መልአከ ገነት ’አባ’ አፈ ወርቅ ዮሐንስ

  • በምደባው፥ የውጭ ጉዳዩ ‘አባ’ ቃለ ጽድቅ ፓትርያርኩን በመማለድ ሚና ተጫውቷል
  • በአሜሪካ ያሉት፣ ረዳት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ስለማወቃቸው አጠያያቂ ኾኗል
  • ከወሊሶ በብልሹነቱ ሲባረር፣ በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከተማ በሥ/አስኪያጅነት ተመድቦ ቆይቷል
  • በክፍለ ከተማው፣ በአጥቢያዎች የቦታ ኪራይ ሙስና፣ በእምነት ሕፀፅና በዘለፋው ይታወቃል
  • ከጎይትኦም ቀጥሎ፣ በከፍተኛ ሓላፊነት የተቀመጠ የተሐድሶ መናፍቅ መኾኑ ነው!!!

*               *             *

  • ዝውውሩ፥ ጎይትኦም ያይኑ፣ ከአስተዳደሩ ይልቅ ከንቡረ እድ ኤልያስጋ የመከረበት ነው
  • ሀገረ ስብከቱ፣ ተሸጠናል” በሚሉት እና ዝውውሩን በሚደግፉት መካከል እየታመሰ ነው
  • እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ በሥራ አስኪያጁ አማካይነት በመቶ ሺሕዎች አጋብሰውበታል
  • በኑፋቄ፣ በሙስና እና በአቅም ማነስ መጠየቅ‘ጂ ዕድገቱ እና ዝውውሩ የማይገባቸውም አሉበት
  • ከደ/ሲና እግዚአብሔር አብ የተባረሩትና የተጠያቂነታቸው ጉዳይ ያልተቋጨው አለቃም ይገኙበታል፡፡

*               *              *

A.A Dio Head Offረዳት ሊቀ ጳጳሱ ባልተገኙበት፣ የሀገረ ስብከቱን የሰው ኃይል አስተዳደርና የካህናት አስተዳደር ዋና ክፍሎች ሓላፊዎችን በመጫንና ለአስተዳደር ጉባኤው ዱብ ዕዳ በኾነ የሥራ አስኪያጁ ጎይትኦም ያይኑና የንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ምክርና ተጽዕኖ የተደረገው የአድባራት አለቆች ዝውውር፤

  • የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ወደ ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል
  • የቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
  • የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል
  • የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ቃሊቲ ቁስቋም
  • የቃሊቲ ቁስቋም ወደ ደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • የደብረ ይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ጃቲ ኪዳነ ምሕረት
  • የጃቲ ኪዳነ ምሕረት ወደ አንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል
  • የአንቀጸ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል በጡረታ ተገልለዋል፤
  • ወደ ውጭ ጠፍተው የነበሩትና ፓትርያርኩን ይቅርታ ጠይቀው በመመለሳቸው ትእዛዝ የተሰጠላቸው የቀድሞው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ሊቀ ሥልጣናት አባ ኪሮስ ጸጋዬ በአያት ኪዳነ ምሕረት ሲመደቡ፤ የአያት ኪዳነ ምሕረቱ ወደ ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ፤
  • የቱሉ ዲምቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ አየር ማረፊያ ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • የአየር ማረፊያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • የሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሉቂ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
  • የሉቂ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ከአስተዳዳሪነት ተነሥተው በክህነት ደረጃ እንዲያገለግሉ ተደርገዋል፡፡

*“ሕዝብን ሳንሰማ የአለቆችን የበላይነት እናረጋግጣለን” ሲባል የነበረበት የቀድሞው አስተዳደር ዘይቤ ተሽሮ ለምእመናንና ለሰበካ ጉባኤያት ጥያቄ ምላሽ የተሰጠበት ዝውውር እንደኾነ ቢነገርም፤“ተሸጠናል፤ ያለደረጃችን ተመድበናል፤ ቦታችንን ተነጥቀናል” በሚሉትና “ከ80ሺሕ እስከ 150ሺሕ ለንቡረ እዱ የከፈለንበት ነው፤ መጽድቅ አለበት” በሚሉት መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ አስከትሎ ሰንብቷል፡፡

ለቋሚ ሲኖዶሱ በቀረበበት ወቅትም፣ እንደ መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል ካሉትና፣ በአማሳኝነታቸው ጉዳያቸው በእንጥልጥል ላይ ከሚገኙት አለቆች አንፃር፣ ከፓትርያርኩ ጋር ከፍተኛ ጭቅጭቅ አስነሥቶ ነበር፡፡

ከአማሳኝነቱም ጋር፣ በሃይማኖት አቋማቸው በተነሣባቸው ጥያቄ፤ ከደብረ ብርሃን ሀ/ስብከት ቢባረሩም፤ በአኹኑ ዝውውር በቱሉ ዲምቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ የተመደቡት እንደ መልአከ ብርሃናት አባ ማርቆስ ብርሃኑ ዓይነቱም የሚገኙበት ነው፡፡

*                *               *

ሥራ አስኪያጁ፣ ከአስተዳደር ጉባኤው ዕውቅና ውጭ መክረውና ወስነው ያዛወሯቸው ጸሐፊዎች፤

  • የየካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል ወደ ደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት
  • የደብረ አሚን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ የካ ደብረ ሣህል ቅዱስ ሚካኤል
  • የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል ወደ ጎላ ጽርሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል
  • የጎላ ጽርሐ ጽዮን ቅዱስ ሚካኤል ወደ ደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ
  • *የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ወደ ጃቲ ኪዳነ ምሕረት
  • የጃቲ ኪዳነ ምሕረት ወደ ሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ*
  • የሰሚት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ፈረንሳይ ለጋስዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ
  • የፈረንሳይ ለጋስዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቡልቡላ መድኃኔዓለም
  • የቡልቡላ መድኃኔ ዓለም ወደ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም
  • የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ወደ ቦሌ ቅድስት ማርያም
  • የቦሌ ቅድስት ማርያም ወደ ጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤል
  • *የቱሉ ዲምቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ቲሊ ዶሮ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
  • የቲሊ ዶሮ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ወደ ቱሉ ዲምቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ፤

*ዝውውሩ በዋናነት፤ በየአድባራቱ ያለውን አለመግባባትና ብጥብጥ፤ ለመፍታት የታሰበበት ነው ቢባልም፤ ለሀገረ ስብከቱ የአስተዳደር ጉባኤ ቀርበው የታዩት፣ የሦስት አድባራት ጉዳዮች ብቻ እንደኾኑ ተገልጧል፡፡

የተቀሩት፣ ለአስተዳደር ጉባኤው ሳይቀርቡና ሳያውቀው፣ ሥራ አስኪያጁ፣ ጸሐፊዪቱንና መዝገብ ቤቷን፣ ባለፈው ቅዳሜ በድንገት በመጥራት፣ ደብዳቤአቸው ተዘጋጅቶና ተፈርሞ በዛሬው ዕለት ወጪ የተደረጉ ናቸው፡፡

ያለብቃታቸውና ያለደረጃቸው ዕድገት ያገኙ፤ ስማቸውን እንኳ በአግባቡ መጻፍ የማይችሉ፤ በፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ በማጭበርበራቸው ርምጃ የተወሰደባቸው፤ አስከፊ ሙስናን ጨምሮ ከአገልጋይ ሰብእና በራቁ እንደ ጫት መቃም ባሉ ሱሶችና የሥነ ምግባር ችግሮች ተጠምደው፤ የተመደቡባቸውን ቦታዎች በመረበሽና በማስረበሽ የሚታወቁ ጸሐፊዎችም እንዳሉበት ተመልክቷል፡፡

8 thoughts on “የአ/አበባ ሀ/ስብከት ጽ/ቤት በተሐድሶ ኑፋቄ አደጋ ውስጥ! ‘አባ’ አፈ ወርቅ ዮሐንስ በምክትል ሥራ አስኪያጅነት ተመደበ፤15 አለቆችና ጸሐፊዎችም ተዛውረዋል

  1. Anonymous June 28, 2016 at 12:01 am Reply

    የወንድሞች ከሳሾ፤ ውሸት መዋሸት አይሰለቻችሁም ማለት ነው ቆሻሾች እግዚአብሔር ይይላችሁ ሰላም የነበረችውን ቤተክርስቲያን አመሳችኋት ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በወንድሞች መካከል ፀብ ስትዘሩ እይኸው 25 ዓመት ሆናችሁ አሁንማ ከአጠቃላይ አገልጋዩ ጋር እንደ ውሻ ተባልታችሁ ልትሞቱ ነው መጥኔ ለእናንተ

  2. ሰው ባገኝ June 28, 2016 at 1:35 am Reply

    የጳጳሳትን የምርጫ ሂደት ለማጨናገፍ፣ አቅጣጫ ለማሳትና ትኩረት ለመሳብ ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ የኤልያስ ተንኮል ነው። እንጂ በዚህ ወሳኝ ወቅት እንዲህ ዓይነት የቤት ሥራ ለቅዱስ ሲኖዶስ ብሎም ለቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ በመስጠት አቅጣጫ በማሳት ወይም ትኩረትን በመሻማት በእጩ ጳጳሳት የማጣራት ሂደትን ለማወክ የተቀነባበረ ሴራ ነው። ይህቺን ይህቺን ኢህአዴግ በሚገባ ተጠቅሞባታል። ይህቺ ጨዋታ የተበላ ዕቁብ ስለሆነ አስመራጭ ኮሚቴው በዚህ ግርግር እንዳይዘናጋ እና በያዘው የማጣራት ሂደት እንዲቀጥል የልጅነት ምክሬን እለግሳለሁ።
    ” እባብ ለእባብ ይተያያሉ ካብ ለካብ ” ማለት ይኸው ነው።
    ይቆየን።

  3. Anonymous June 28, 2016 at 6:23 am Reply

    በሚገርም ሁኔታ እራሱና የዓላማ ተከታዮቹ በፈጸሙት የውንብድና ስራ ወሊሶ ስትታመስ መቆየቷ ይታወቃል፤በመሐል የዞኑና የከተማው ከፍተኛ የመንግስት ባለስስልጣናት በተገኙበት እየተደረገ በነበረበት ሰላም የማውረድ መድረክ ላይ ከሚናገራቸው አጸያፊና ጋጠወጥ ንግግሮቹ ባለስልጣናቱ ተሸማቀው ክቡር አባታችን እርስዎ የሃይማኖት መሪ ኖት፣ከእርስዎ እኛ መማር አለብን፣እኛም ሃይማኖታችን እንድንቀይር ያስደረገን ተመሳሳይነት ባለው የአባቶች ግድፈት ነው፤ስለሆነም ቀሪውን ሕዝባችሁን ከማሳዘንና እንደኛ ተማሮ ሃይማኖቱን ከምታስቀይሩት ያነሳውን የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ብትመልሱለት አይሻልም ብለው ሲጠይቁት ባልታረመውና በለመደው ጋጠወጥ ምላሱ ሄዳችሁ አልሄዳችሁ ጉዳያችን አይደለም በቂ ሕዝብ አለን ብሎ በድፍረት የተናገረና ለምእመናን መበተን ተግቶ የሚሰራ ማፈሪያ መሆኑን ጠንቅቀን የመምነናወውቀወው መናፍቅና ሌባ ነው፡፡

  4. Anonymous June 28, 2016 at 7:32 pm Reply

    ለአባ ቃለፅድቅ የሁሉ ተባባሪ ናቸው አባ አፈወርቅም እደዛው አኛ ካቅማችን በላይ ሆኖ ለእግዚአብሔር ትተነዋል በጂቡቲ ምሥራቀ ፀሀይ እየተሠራ ያለው ሥራ የነሡም እጅ አለበት ህዝቡን ለመደለል አዛ ድረሥ መተው ነበር አበሶ አባ ቃለፅድቅ የዚ የበረሀ ህዝብ ፀሎት ይፋረዶታል ለነገሩ አልገባዎትም እንጂ ከጂቡቲ ሢመለሡ ቅዱሥ ገብርኤል ቤት ዋሽተው ጉቦ በልተው ሢመለሡ የደረሠቦትን የመኪና አደጋ ለምልክት ነበር ግን ገንዘብ በለጠቦት በሆዶት የእግዚአብሔርን ቤት ሸጡ ዛሬ ግን የሥም ግም ከሥብ ይበልጣል ይባላል የጆትን አገኙ የሡን ሥራ ቁጭ ብለን እንመለከታለን የዘገየ ቢመሥለንም የሚቀድመው ሥለሌለ እጠብቀዋለን ምእመናን ምእመናት በፀሎታቹ አሥቡን ቤተክርሥቲያኑን የወረሩት አሥተዳዳሪውም ሆነ ሌሎቹ ፀረ ተሀድሶዎች ናቸው ደና አባቶችንና ዲያቆናትን አባረው ብቻቸውን እያመሡት ነው እግዚአብሔር ህዝቡንና ቤተክርሥቲያናችንን ይጠበቅ እባካቹ ለሚመለከተው ሁሉ አሥተላልፉልን አሥተዳዳሪው በገንዘብ ነው እዚ የተመደቡት ሠፈረ ገነት ቅድሥት ሥላሤ በሌብነት ተባረዋል ሁሉም ያውቃቸዋል የቤተክርሥቲያን መሬት በመሸጥ ይታወቃሉ አረ ብዙ ነው እባካቹ እባካቹ ቤተክርሥቲያን መሄድ አልቻልንም የሚሠበከው ሌላ ነው ህዝበ ክርሥቲያን ታደጉን እላለው አመሠግናለው

  5. Anonymous June 29, 2016 at 9:21 am Reply

    የሚገርመው ነገር ሰው ሐያ አራት ሰአት ሥለሠው ያወራል እንዴ አንተ ሌላውን ሌባ የምትል አንተው ማነህ ሌላውን አመንዝራ የምትል ሌላውን መናፍቅ የምትል በውኑ ራስህን ማነኝ ብለህ ታውቃለህ ራስህን እንደጻድቅ የምትቆጠር እውር ፈሪሣዊ በጣም ታሣዝናላችሁ <>ምሳ30%12እንደእናንተ ያለ ሁሉ አባቶቹን የሚያዋርድ ቤተክርስቲያን በአህዛብ ፊት እንድታፍር የምታደርጉ ቤተክርስቲያንን ብሎም ሀገርን ሠላም የምትነሡ ግድ የለም የአበው እንባቸው የሚተዋችሁ መሥሏችኀል

  6. Anonymous June 29, 2016 at 9:24 am Reply

    ተቸህ ማለት ነው

  7. Anonymous June 29, 2016 at 1:00 pm Reply

    እግዜአብሔር ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ያድርግላት ብለን እንፀልይ

Leave a comment