ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የቆሞሳትና መነኰሳት ጥቆማ እየተካሔደ ነው፤ የካህናትና የምእመናን መረጃና አስተያየት በእጅጉ ይፈለጋል

04PatriarchAbuneBasilios1st_jpg(መመዘኛውንና የተጠቆሙትን ቆሞሳትና መነኰሳት የስም ዝርዝር ይመልከቱ)

 • የሚሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት ብዛት ከ14 ‐ 16 ሲኾኑ፤ 28 ዕጩዎች ብቻ ለውድድር ይቀርባሉ
 • ተጠቋሚዎች፣ የሚሾሙበትን ሀ/ስብከት ቋንቋ ማወቅ ከመሠረታዊ መመዘኛዎች አንዱ ኾኗል
 • አስመራጭ ኮሚቴው በቀጣዩ ሳምንት የተጠቋሚዎችን ማንነት ማጣራት ይጀምራል፤ ተብሏል

 *               *               *

 • ከተጠቋሚዎቹ፣ ንጹሐንና ብቁዎች ያሉትን ያኽል ኑፋቄ፣ ነቀፌታና ነውር የሞላባቸውም አሉ
 • አስመራጭ ኮሚቴውን በአማላጅ፣ በእጅ መንሻና በውዳሴ ከንቱ የሚያጨናንቁ እንዳሉ ታውቋል
 • ካህናትና ምእመናን፣ ስለብቃታቸው፣ ከነውርና ነቀፌታ ስለመራቃቸው ሊመሰክሩላቸው ይገባል

 *               *               *

ማስገንዘቢያ፡‐

 • ከዚኽ በታች የሰፈረው የተጠቋሚ መነኰሳትና ቆሞሳት የስም ዝርዝርበተለያዩ መንገዶች የተሰበሰበና ከእነርሱም የሚበዙት ለአስመራጭ ኮሚቴው ስለመድረሱ የተገለጹትን ብቻ የሚያካትት ነው፤ በመኾኑም ዝርዝራቸውን የማሳወቁ ኹኔታ ቀጣይነት ይኖረዋል፤
 • የስም ዝርዝሩ፣ ለጡመራ መድረኩ በተላከበት ቅደም ተከተል የቀረበ ሲኾን፤ የተጠቋሚዎችን አስማተ ማዕርጋት ያልያዘና በተወሰነ መልኩም የአባት ስም ያልተጠቀሰበት ነው፤
 • ሹመት የሚያስፈልጋቸው አህጉረ ስብከት፡- ሰሜን ምዕራብ ትግራይ/ሽሬ/፣ ምሥራቅ ትግራይ/ዓዲ ግራት/፣ ማዕከላዊ ዞን ትግራይ/አኵስም/፣ደቡብ ጎንደር/ደብረ ታቦር/፣ ዋግ ኽምራ/ሰቆጣ/፣ ደቡብ ወሎ በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን/ከሚሴ/፣ ምዕራብ ጎጃም/ፍኖተ ሰላም/፣ አዊ፣ ግልገል በለስ/መተከል/፣ ጋምቤላ፣ ኢሉባቦር፣ አሶሳ፣ ቄለም ወለጋ፣ ከምባታና ሐዲያ፣ ጉጂ ሊበን ቦረና፣ ጅግጅጋ እና ዳውሮ ኮንታ መኾናቸው ተጠቁሟል፤
 • የእኒኽ ተጠቋሚ መነኰሳትና ቆሞሳት ስም ዝርዝር የደረሳቸው፣ በተለያዩ አህጉረ ዓለም የሚገኙ ካህናት እና ምእመናን፣ በየአህጉረ ስብከታቸው አልያም በያሉበት ኾነው መረጃዎቻቸውንና አስተያየቶቻቸውን ለአስመራጭ ኮሚቴው እንዲደርስ ማድረግ ይችላሉ
 • በግንቦቱ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ የተቋቋመው የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ፤ ሰባት ብፁዓን አባቶች በአባልነት የሚገኙበት ሲኾን፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በሰብሳቢነት፤ ብፁዕ አቡነ አብርሃም በጸሐፊነት ይመሩታል፤ ብፁዕ አቡነ ገሪማ፣ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ እና ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በአባልነት ይገኙበታል፤
 • ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ ቤተ ክርስቲያንን መሠረት አድርጎ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. በጸደቀው የተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት የመመዘኛ መስፈርትና የምርጫ ሥርዓት ደንብ ሥራውን የሚያከናውነው ኮሚቴ፣ እስከ አኹን ድረስ ከ100 ያላነሱ ተጠቋሚዎችን ከብፁዓን አባቶች የተቀበለ ሲኾን፤ ያልጠቆሙትም በቀጣዮቹ ኹለት ቀናት እንደሚያሳውቁ ይጠበቃል፡፡ 

*               *              *    

Ordination of Bishiopsለኤጲስ ቆጶስነት በዕጩነት የሚቀርቡ ቆሞሳትና መነኰሳት መመዘኛና የምርጫ ሥርዓት ደንብ

 • ወደፊት ስለሚመረጡ ቆሞሳት መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጀትና በሥራ ላይ ማዋሉ አስፈላጊ ኾኖ በመገኘቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሚከተለውን የመመዘኛ መስፈርት አውጥቷል፡፡
 • ይህ የመመዘኛ መስፈርትና የምርጫ ሥርዓት፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን አንቀጽ ፴፭ ቁጥር ፪ በተደነገገው መሠረት የወጣ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የሚፈጸመው፡-

 • አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት እንዲሾሙ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ሲታመንበትና ሲወሰን፤
 • ኤጲስ ቆጶሳት ያልተመደቡባቸው ነባር አህጉረ ስብከት ሲኖሩ፤
 • አዲስ ሀገረ ስብከት ሲመሠረትና አስተዳደራዊ መዋቅር ሲዘረጋለት፤
 • መንበረ ጵጵስና እንዲመሠረት ኹኔታዎች የተሟሉ መኾናቸው ከተረጋገጠ በኋላ ነው፡፡

ተጠቋሚ መነኰሳትንና ቆሞሳትን በሚከተለው ዝርዝር መመዘኛ መስፈርትና የምርጫ ሥርዓት መሠረት ለዕጩነት ይቀርባሉ

 1. በሥርዓተ ምንኵስና በታወቀ ገዳም በድንግልና መንኵሶ በክህነት ቤተ ክርስቲያንን የሚያገለግልና በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተቋቋመው አስመራጭ ኮሚቴ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ዕጩ ኾኖ የተመረጠ፤
 2. ከመነኰሰበት ገዳም ስለ ምንኵስና ሕይወቱና ስለ ክህነቱ በቂ ማስረጃ ማቅረብ የሚችልና በመነኰሰበት ገዳም በቅንነትና በታማኝነት ቢያንስ ለአምስት ዓመት ያገለገለ መኾኑ የተረጋገጠለት፤
 3. ለሀገር ውስጥ አገልግሎት ወይም ኢትዮጵያውያን ለሚኖሩበት የውጭ ሀገረ ስብከት የሚሾም ከኾነ ዜግነቱና ትውልዱ ኢትዮጵያዊ የኾነ፤
 4. በውጭ ሀገር ለሚገኙና የውጭ ሀገር ዜጎች ከራሳቸው መካከል አባት መሾም እንዲቻል በቅድሚያ ከመካከላቸው ወደ አገር ቤት መጥተው አስፈላጊውን ትምህርት እንዲያገኙ፤ ሥርዓተ ገዳምና ሥርዓተ ምንኵስናን እንዲያውቁ ይደረጋል፤
 5. ኢትዮጵያውያን ያልኾኑ ወይም ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለሚኖሩበት የውጭ ሀገረ ስብከት የሚሾም ከኾነ፤ ዜግነቱ/ትውልዱ ኢትዮጵያዊ የኾነ ወይም ከትውልደ ኢትዮጵያውያን ወገን የኾነ ወይም ኢትዮጵያዊ ኾኖ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን እምነት ተቀብሎ በሥርዓተ ክህነት መቀደስና ማስተማር የሚችል፤ እስከ ቆሞስነት ደረጃ የደረሰ በሚሾምበት ሥፍራ ለማገልገል የትምህርት ዝግጅትና የቋንቋ ችሎታና ብቃት ያለው፤
 6. የብሔረሰቡ ተወላጅ የኾነና በብሔረሰቡ ቋንቋ የማስተማር ችሎታ ያለው ወይም ተወላጅነቱ ሌላ ብሔረሰብ ኾኖ በተሠየመበት ሀገረ ስብከት በብሔረሰቡ ቋንቋ ማስተማር የሚችል፤ እንዲኹም በብሔረሰቡ ቋንቋ የሚናገር ከሌለ ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሳዊ ሕይወቱ የታመነበት አባት ይመድባል፡
 7. ለአንድ ቦታ አምስት ተጠቋሚዎች ለግምገማ የሚቀርቡ ሲኾን፤ ለምርጫ ቀርበው የሚወዳደሩት ግን ኹለት ናቸው
 8. በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት/ነገረ መለኰት/ በቂ ዕውቀትና የማስተማር ችሎታ ያለው፤ የቤተ ክርስቲያኒቱን ሥርዓተ ቀኖና ጠንቅቆ ያወቀ ለመኾኑ የተረጋገጠ ማስረጃ ያለው፤ ከቤተ ክርስቲያን የአብነት ት/ቤቶች ቢያንስ በአንድ ጉባኤ የተመረቀ፣ ወንበር ዘርግቶ ያስተማረ ቢኾን፤ ቢቻል ኹለገብ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርት ያለው ኾኖ ከመንፈሳዊው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቢያንስ ዲፕሎማ ያለው፤
 9. በመንፈሳዊ ሕይወቱና በግብረ ገብነቱ በአስተዳደር የሥራ ልምዱና በሥራ አመራር ችሎታና ብቃቱ በነበረበት አካባቢ/የሥራ ቦታ/ በሚገኙ ሊቀ ጳጳስ ሰብሳቢነት በካህናትና በምእመናን የተመሰከረለት ስለመኾኑ የተረጋገጠለት፤
 10. የምእመናንንና የካህናትን መንፈሳዊና ማኅበራዊ ችግር የመረዳትና የችግር አፈታት ልምድና ችሎታ ያለው፤
 11. የቤተ ክርስቲያኒቱ ቋንቋ የኾነውን ግእዝ በሚገባ የሚያውቅ ኾኖ ቢቻል ከዓለም አቀፍ ቋንቋዎች አንዱን የሚያውቅ፤
 12. በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጽኑዕ የኾነ፤
 13. ሙሉ አካል ያለውና ጤንነቱ የተሟላ፤
 14. ዕድሜው ከ45 እስከ 60 ዓመት የኾነ፤
 15. ቢቻል የተሾመበትን ሀገረ ስብከት ቋንቋ የሚያውቅ፤
 16. አዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም እንደ ሌሎች አህጉረ ስብከት ጥቆማ የመስጠት ድርሻው የተጠበቀ ነው፤
 17. በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙ የተመረጡት ቆሞሳት፣ ከመሾማቸው በፊት ስለ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንና የሥራ አመራር በአባቶች፣ በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንና በምሁራን የሦስት ወራት ሥልጠና እንዲሰጣቸው ይደረጋል፡፡

*               *               *

እስከ አኹን ድረስ በተለያዩ መንገዶች የተጠቆሙና በአብዛኛውም አስመራጭ ኮሚቴው ከብፁዓን አባቶች እንደተቀበላቸው የተገለጹ ቆሞሳትና መነኰሳት ስም ዝርዝር

 1. አባ ዘውዱ በየነ/የደብረ ብርሃን ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 2. አባ ኃይለ ማርያም አረጋ/የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ/
 3. አባ ያሬድ ምስጋናው/የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት መጻሕፍትና ድጓ መምህር/
 4. አባ ገብረ ሥላሴ ጠባይ/የጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል አስተዳዳሪ/
 5. አባ ዘርዓ ዳዊት ኃይለ ሥላሴ/የመርካቶ ቅዱስ ራጉኤል አስተዳዳሪ/
 6. አባ ፍቅረ ማርያም ተስፋ ማርያም/የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳዳሪ/
 7. አባ ኃይለ ጊዮርጊስ/ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 8. አባ ገብረ ጻድቅ ደበብ
 9. አባ ሣህለ ማርያም ገብረ አብ/አሜሪካ ‐ ቨርጂንያ)
 10. አባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ ሐዋርያት/የደብረ ሊባኖስ ገዳም መጽሐፍ መምህር/
 11. ሊቀ ጉባኤ አባ ተክለ ሃይማኖት/የናዝሬት ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ/
 12. አባ ኃይለ ሥላሴ ገብረ እግዚአብሔር/አሜሪካ ‐ ሎስ አንጀለስ/*
 13. አባ ፊልጶስ ከበደ /አሜሪካ ‐ቨርጂንያ/
 14. አባ ጽጌ ገነት ወልደ ኪዳን/አሜሪካ ‐ቨርጂንያ/
 15. ጸባቴ አባ የማነ ብርሃን(አዳሙ) ዓሥራት/አሜሪካ ‐ ቨርጂንያ/
 16. አባ ለይኩን ግፋ ወሰን/ደብረ ሊባኖስ ገዳም/
 17. አባ ፍቅረ ማርያም/ቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም አስተዳዳሪ/
 18. ዬኔታ ጳውሎስ/ደብረ ሊባኖስ ገዳም/
 19. አባ ልሳነ ወርቅ ደለለኝ/ደብረ ጽጌ ገዳም/
 20. አባ መሐሪ ሀብቴ/አኵስም/
 21. አባ መርሐ ጥበብ ተሾመ/የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ገበዝ/
 22. አባ ኢሳይያስ/የዝቋላ ገዳም አበምኔት/
 23. አባ ማቴዎስ ከፍያለው/እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት/
 24. አባ ገብረ ሕይወት ፍሥሓ/ጀርመን ‐ ሙኒክ/
 25. አባ ገብረ ሐና ታደሰ/ዱባይ/
 26. አባ ገብረ መድኅን ወልደ ሳሙኤል(ኳታር)*
 27. ዶ/ር አባ ኃይለ ማርያም መለሰ/የጠቅላይ ጽ/ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ/
 28. አባ ኪዳነ ማርያም ደስታ/የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ቀሲስ/
 29. አባ ሠረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል/የጠቅላይ ጽ/ቤት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ ዋና ሓላፊ/
 30. አባ ሞገስ ኃይለ ማርያም/የመናገሻ ቅድስት ማርያም አስተዳዳሪ/
 31. አባ ዘድንግል ኑርበገን/ፈረንሳይ/
 32. አባ ገብረ ማርያም ገብረ ሥላሴ/መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የገዳማት መምሪያ ዋና ሓላፊ/
 33. አባ ገብረ ጻድቅ ዐረፈ ዓይኔ/የአኵስም ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 34. አባ መንግሥተ ኣብ ገብረ ሥላሴ/የቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አስተዳዳሪ/
 35. አባ ገብረ አድኃኔ ወልደ ማርያም/የደብረ መንከል ገዳም አስተዳዳሪ/
 36. አባ ጥዑመ ልሳን/ማኅደረ ስብሐት ልደታ ለማርያም አስተዳዳሪ/
 37. አባ ወልደ መድኅን ተክለ ብርሃን/እንጦጦ ኪዳነ ምሕረት/
 38. አባ ዘተክለ ሃይማኖት/የደብረ ገሊላ ዐማኑኤል ካቴድራል ሰባኬ ወንጌል/
 39. አባ ወልደ ገብርኤል አማረ/ድሬዳዋ ሀገረ ስብከት የትርጓሜ መምህር/
 40. አባ ኢሳይያስ/ድሬዳዋ ቅድስት ሥላሴ
 41. ንቡረ እድ አባ ገብረ ሕይወት/ድሬዳዋ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ/
 42. ሊቀ ሊቃውንት አባ ዕዝራ ሐዲስ/ጎንደር መጻሕፍት መምህር/
 43. ሊቀ ጉባኤ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል/ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም/
 44. አባ ኪዳነ ማርያም ሞላልኝ/ባሕር ዳር/
 45. አባ ብርሃነ መስቀል ደርበው/አዘዞ/
 46. አባ ቴዎድሮስ መስፍን/የሊቃውንት ጉባኤ አባል/
 47. አባ ወልደ ጊዮርጊስ ጸጋው/ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም መምህር/
 48. አባ ተክለ ያሬድ ጎርጎሬዎስ/ጎፋ ጥበብ እድ ሥራ አስኪያጅ/
 49. አባ ኃይለ ማርያም/ሐዋሳ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 50. አባ ተክለ ማርያም አምኜ/አስኮ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ/
 51. አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና/ካርቱም ሀገረ ስብከት/
 52. አባ ብርሃነ መስቀል ተድላ/ጀርመን ‐ በርሊን/
 53. አባ ኄኖክ ተክለ ጊዮርጊስ/መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል አለቃ/
 54. አባ ብንያም ከበደ/የሆሳዕና ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 55. አባ ገብርኤል ወልደ ዮሐንስ
 56. አባ ሰይፈ ገብርኤል ኦብሰን/አሜሪካ ‐ ሲያትል/*
 57. አባ ሚካኤል ገብረ ማርያም/የዱራሜ ሀ/ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 58. አባ ስብሐት ለአብ/ጀርመን/
 59. አባ ኢያሱ ገብረ አልፋ/የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ቅኔና መጻሕፍት መምህር/
 60. አባ ኃይለ ሚካኤል/መቐለ ቅዱስ ጊዮርጊስ አስተዳዳሪ/
 61. አባ ኃይለ ሚካኤል ወልደ ሚካኤል/የደብረ ሊባኖስ ገዳም መምህር/
 62. አባ ፍቅረ ዮሐንስ ገብረ ሕይወት/ሐይቅ እስጢፋኖስ አበምኔት/
 63. አባ ኤልያስ ታደሰ/የደሴ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ/
 64. መልአከ ሰላም አባ ገብረ ኪዳን/አሜሪካ ‐ ቬጋስ/
 65. አባ ተክለ ሃይማኖት/ዋሽግንተን ዲሲ/
 66. አባ ፍቅረ ማርያም/ዋሽንግተን ዲሲ/
 67. አባ ገሪማ አያልቅበት/ዱባይ/
 68. አባ ብርሃነ መስቀል ዕንቁ
 69. አባ ወልደ ትንሣኤ አባተ/የቅዱስ ላሊበላ ደብር አስተዳዳሪ/
 70. አባ ጌዴዎን/አሜሪካ ‐ ፍሎሪዳ/
 71. አባ ገብረ ኪዳን እጅጉ/
 72. አባ ቀለመ ወርቅ/ምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም/
 73. አባ ወልደ ሐና ጸጋው/የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ/
 74. ሊቀ ጉባኤ አባ ሳሙኤል/ኢጣልያ/
 75. አባ ገብረ ማርያም/ዱባይ/
 76. አባ ገብረ ሥላሴ/ኢየሩሳሌም ገዳም/
 77. አባ ኃይለ ኢየሱስ ተመስገን/የሽሮ ሜዳ ቅድስት ሥላሴ አስተዳዳሪ/
 78. አባ ዮሐንስ ገብረ ሥላሴ/የወላይታ ሶዶ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 79. አባ ሀብተ ማርያም ገብረ መስቀል/ሲዳማ ጌዴኦ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 80. አባ ተክለ ማርያም ስሜ/ሐዋሳ/
 81. አባ ኃይለ መለኰት ተስፋ ማርያም/ጀርመን/
 82. አባ ኃይለ ሚካኤል/ኢየሩሳሌም ገዳም/
 83. አባ ኃይለ ጊዮርጊስ/ሲውዘርላንድ/
 84. አባ ላእከ ማርያም ገብረ ጊዮርጊስ/ዓዲ ግራት/
 85. አባ ገብረ ኪዳን/ማይጨው/
 86. አባ ዮሐንስ ከበደ/አየር ላንድ/
 87. አባ ገብረ ኢየሱስ መኰንን /እንጦጦ ቅድስት ማርያም ገዳም አስተዳዳሪ/
 88. አባ ገብረ መድኅን/ታዕካ ነገሥት በዓታ ለማርያም ገዳም መምህር/
 89. አባ ሳሙኤል ገላነው/የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ መምህር/*
 90. አባ ፈቃደ ሥላሴ/ዋሽንግተን ዲሲ/
 91. አባ ወልደ ማርያም አድማሱ/የደብረ ገዳም ጸባቴ/
 92. አባ ገብረ ሥላሴ በላይ/የደሴ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 93. አባ ጽጌ ሥላሴ መዝገቡ/የደሴ ቅዱስ ገብርኤል አስተዳዳሪ/
 94. አባ ናትናኤል/የአየር ጤና ኪዳነ ምሕረት አስተዳዳሪ/
 95. አባ ቃለ ጽድቅ ሙሉጌታ/የጠቅላይ ጽ/ቤት ውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊ/
 96. አባ መልአኩ/ቅዱስ ፍሬምናጦስ አባ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን ኮሌጅ/
 97. አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ/የጋምቤላ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ/
 98. አባ ወልደ ዐማኑኤል/አሜሪካ/
 99. አባ ገብረ ጻድቅ/ምዕራብ ሸዋ/
 100. አባ ክንፈ ሚካኤል ልሳኑ/መንበረ ፓትርያርክ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር/
 101. አባ ገብረ ማርያም/ደቡብ አፍሪካ/
 102. ዬኔታ ይባቤ በላይ/ምዕራብ ጎጃም የሐዲሳትና የቅኔ መምህር/
 103. ሊቀ ሥልጣናት አባ ገብረ ሥላሴ/መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል/
 104. አባ ዘርዓ ዳዊት/አሜሪካ ‐ ሚኒሶታ/
 105. አባ ወልደ ሰማያት/አሜሪካ ‐ ሲያትል/
 106. አባ እስጢፋኖስ/ዋሽንግተን ዲሲ/
 107. አባ ዘሚካኤል ደሬሳ/ዴንማርክ/
 108. አባ ዕንቁ ሥላሴ ተረፈ/መዝገበ ምሕረት ካራ ቆሬ ፋኑኤል አስተዳዳሪ/

  *በቀደመው ዘገባ ከነበረው የአጻጻፍና የድግግሞሽ ግድፈት አንፃር እርማት ተደርጎባቸዋል፡፡

Advertisements

76 thoughts on “ለኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ የቆሞሳትና መነኰሳት ጥቆማ እየተካሔደ ነው፤ የካህናትና የምእመናን መረጃና አስተያየት በእጅጉ ይፈለጋል

 1. Anonymous July 5, 2016 at 8:12 am Reply

  ከሊቃውንት መጠቆማቸው አጅግ አስደስቶናል በተጨማሪም ለቤተ ክርስቲያኗ ከሚጠቅሙ ሊቃውንት መካከል በታእካ ንገስት በአታ ልማርያም ገዳም ለሃያ ዓመታት ያህል እገለገሉ ያሉ በትምህርታቸውም በቛቛም፣ በዜማ፣ በቅኔዉ፣ በመጻሕፍት ትርጓሜዉ እንዲሁም በዘመናዊዉ BA እና MBA የተሞሉ፣ በስነምግባራቸው፣በግብረገብነታቸዉ፣ በባሕርያቸው ተመሰከረላችዉ፤ ለሃይማኖታቸዉ ቀናእያን፤ የቤተክርስቲያናቺን እንቁዎች፣ በንጽሕና በድንግልና የሚኖሩ ሊቃዉንቶች ቤተክርስቲያናችን አሉዋት፡፡ ቤተ ክርስቲያኗን በእጅጉ የሚጠቅሙ ሊቃዉንቶች ናቸው፡፡ ምናለ በጥቆማው ውስጥ ያልገቡት ባለመመንኮሳቸው ከሆነ እንደሌሎቹ አባቶች ቀደም ሲል ይደረግ እንደነበረው የምንኩስና ሥርዓቱ ተፈጽሞላቸው ጵጵስናው ቢሰጣቸው ይህንን ያልንበት ምክንያት እኚህ ታላላቅ ሊቃዉንቶች ማጋነን ባይሆንብንም የምንኩስና አስኬማ የሌላቸው ነገር ግን ከልባቸው የምንኩስና ሕይወትን የሚኖሩ ታላላቅ ሊቃዉንቶች ምን አለ ብትመርጡልን?

 2. Anonymous July 6, 2016 at 2:34 pm Reply

  28. Juni um 17:38 ·
  አባ ኃይለ መለኰት ተስፋ ማርያም/ጀርመን/ ከዚህ በፊት ያላቸው የኋላ ታሪክ ምን ይመስላል የሚለውን ምዕመናን እንዲያውቁትና አስመራጭ ኮሚቴው በራሱ መንገድ ማጣራት ያካሂድ ዘንድ ፤ ለቤተክርስቲያን ያለፉት አመታት የተከናወኑት ድርጊቶች ዳግም እንዳንመለከታቸው አሁን ላይ ሆነን ሃላፊነታችንን ከመወጣት ምዕመኑን ከማንቃት አንጻር እንዲህ አቅርበነዋል፡፡

 3. Anonymous July 6, 2016 at 2:36 pm Reply

  1Bete Zewudu
  Kommentare
  Bete Zewudu
  Bete Zewudu ስራ ባለቤቴ በድንገት መስሬቤት ትቀነሳች እንዲህ ከሆነገች አስር ይበቃናል ብለን መክፈል ስንጀምር
  አንድቀን እድቀን እደአባት ሰላም ብሎየማያውቀው የስም መነኩሴ ተብየ አባ ሲራክ እንዴት አስሩን ትቀንሣላችሁ እየተመካከራችሁ አይደል ስብሰባ ገብታችሁ ለመናገር እንዲያመቻችሁ ብላችሁ እንጂ እስካሁን ጨርሶ ትወጡነበር
  እኔን ለመበጥበጥ ነው ከዚህ የምትመጡ ብሎሰደባት ባለቤን ተመልከቱ
  አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የሗላታሬኩ እደሜስረደው ከአርባምንጪ ገብርኤል ወደቅዱስሜካኤል
  በምን ምክንያት እደተዛወረ አርባምንጪ አገርስብከት መረዳት አዲስ አበባቅድስትማርያም ምንይሰራእንደነር
  በአጭሩ መረዳት ይቻላል ቆቡን አውልቆ በየሴታዳሬወች ሲዞር
  እንዲሁም ባለትዳሮችን ለማስቀደስ ፈተና እስከሚሆንባቸው ድረስ
  ሌላው በጫት ሱስ እና በሲጋራ አጫሽነት ሀገርቤት ይታወቃል
  ከዚህ ፋንክፈርት ጀርመን ህይወቱ ተመሣሣይ
  ነው በተለምዶ ፋራንክፈርት ካይዘር እስትራሰ እየተባለ በሜጠራው ሴታዳሬወች ቦታ
  ሲመላለስ ሁሉም ሰውያገኝዋል ክርስቲያኑ ቀርቶ አስላች ያውቁታል
  በዝሙቱ ይህንን ስእፅፋ ልዮጥላቻ ለእሱ ኑሮኝ ሣይሆን ካህን ስላይደለነው
  ገዳም ነበርኩኝ ይላል አወገዳም ነበረ ፈተነውን መቇቇም አቅቶት ይህንን ሁሉ
  ሐጤያት የሚያሠረው ከገዳም ያወጣው ሰይጣን ነው አንዴ አባ ሲራክ
  አንዴ አባ ሐይለመለኮት መልም ሰራእንጄ ሰም በመቀየር ሹመት አይገኝም
  ጉልቻ መቀየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል
  የያዘው ሰይጣን ክርስቴያኖችን ማሳደድ አስር ጌዜየ ማህበረቅዱሳን እረበቨኝ
  በነጻ እየረዱት ሄኖክ ወንድወን
  እባክህ ብለን ብንለመነው ማህበረቅዱሣን ይውጣልኝ ብሎ ከፈላችው
  ይህ ኖለት ጳጳስ ቢሆን ጥሩይሰራይሆን እውነቱን እናጋልጥ አለም አዲትመንደር ሁናለች
  እና እውነትወታ በሲራክ ሴራ ከሁለት የተከፈለው የፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ምመናን አንድመሆን
  አለበት እንላለን እውነቱን ስንናገር እኔ ትግሬስለሆንኩኝ ነው እያለ በየዋህ ክርስቴያኖች ቤት ማልቀሱ የማይቀርነው
  ግን ትግሬ በመሆኑሣይሆን ሐጤያተኞ የመቤታን ካዝና በአዶ ያስቀረ ህዝብ የበተነ ዛሬየተናገረውን ነገ የማይደግም
  ትግሬኮሜቴ ካልተመረጠ ብሎ ተመረጠለት ግን የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ ነውና
  ትክክል እንስራ ሲሉት ሲቆጣጠሩት ስም መጥራት ጀመረ ቴዎድሮ እላሠራኝ አለ ሰለተቆጣጠረው እኮነው
  ሰለዚህ ገንዘብ ያላግባብ ሲዘርፋ እና ሲዘሙት እያየ ዘምያላለሰው ለአባ ሲራችክ ጥሩ አይደለም
  ኮሦኮሦም ቢይላቸው አባ ሲራክ ተብየው እውነት እንናገራለን ለድንግልርያም ብለንከፋል ኑረን
  Gefällt mir · Antworten · 2. Juli um 13:33
  Gefällt mir · Antworten · 4. Juli um 13:47

 4. Bete Zewudu July 6, 2016 at 2:37 pm Reply

  1Bete Zewudu
  Kommentare
  Bete Zewudu
  Bete Zewudu ስራ ባለቤቴ በድንገት መስሬቤት ትቀነሳች እንዲህ ከሆነገች አስር ይበቃናል ብለን መክፈል ስንጀምር
  አንድቀን እድቀን እደአባት ሰላም ብሎየማያውቀው የስም መነኩሴ ተብየ አባ ሲራክ እንዴት አስሩን ትቀንሣላችሁ እየተመካከራችሁ አይደል ስብሰባ ገብታችሁ ለመናገር እንዲያመቻችሁ ብላችሁ እንጂ እስካሁን ጨርሶ ትወጡነበር
  እኔን ለመበጥበጥ ነው ከዚህ የምትመጡ ብሎሰደባት ባለቤን ተመልከቱ
  አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የሗላታሬኩ እደሜስረደው ከአርባምንጪ ገብርኤል ወደቅዱስሜካኤል
  በምን ምክንያት እደተዛወረ አርባምንጪ አገርስብከት መረዳት አዲስ አበባቅድስትማርያም ምንይሰራእንደነር
  በአጭሩ መረዳት ይቻላል ቆቡን አውልቆ በየሴታዳሬወች ሲዞር
  እንዲሁም ባለትዳሮችን ለማስቀደስ ፈተና እስከሚሆንባቸው ድረስ
  ሌላው በጫት ሱስ እና በሲጋራ አጫሽነት ሀገርቤት ይታወቃል
  ከዚህ ፋንክፈርት ጀርመን ህይወቱ ተመሣሣይ
  ነው በተለምዶ ፋራንክፈርት ካይዘር እስትራሰ እየተባለ በሜጠራው ሴታዳሬወች ቦታ
  ሲመላለስ ሁሉም ሰውያገኝዋል ክርስቲያኑ ቀርቶ አስላች ያውቁታል
  በዝሙቱ ይህንን ስእፅፋ ልዮጥላቻ ለእሱ ኑሮኝ ሣይሆን ካህን ስላይደለነው
  ገዳም ነበርኩኝ ይላል አወገዳም ነበረ ፈተነውን መቇቇም አቅቶት ይህንን ሁሉ
  ሐጤያት የሚያሠረው ከገዳም ያወጣው ሰይጣን ነው አንዴ አባ ሲራክ
  አንዴ አባ ሐይለመለኮት መልም ሰራእንጄ ሰም በመቀየር ሹመት አይገኝም
  ጉልቻ መቀየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል
  የያዘው ሰይጣን ክርስቴያኖችን ማሳደድ አስር ጌዜየ ማህበረቅዱሳን እረበቨኝ
  በነጻ እየረዱት ሄኖክ ወንድወን
  እባክህ ብለን ብንለመነው ማህበረቅዱሣን ይውጣልኝ ብሎ ከፈላችው
  ይህ ኖለት ጳጳስ ቢሆን ጥሩይሰራይሆን እውነቱን እናጋልጥ አለም አዲትመንደር ሁናለች
  እና እውነትወታ በሲራክ ሴራ ከሁለት የተከፈለው የፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ምመናን አንድመሆን
  አለበት እንላለን እውነቱን ስንናገር እኔ ትግሬስለሆንኩኝ ነው እያለ በየዋህ ክርስቴያኖች ቤት ማልቀሱ የማይቀርነው
  ግን ትግሬ በመሆኑሣይሆን ሐጤያተኞ የመቤታን ካዝና በአዶ ያስቀረ ህዝብ የበተነ ዛሬየተናገረውን ነገ የማይደግም
  ትግሬኮሜቴ ካልተመረጠ ብሎ ተመረጠለት ግን የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ ነውና
  ትክክል እንስራ ሲሉት ሲቆጣጠሩት ስም መጥራት ጀመረ ቴዎድሮ እላሠራኝ አለ ሰለተቆጣጠረው እኮነው
  ሰለዚህ ገንዘብ ያላግባብ ሲዘርፋ እና ሲዘሙት እያየ ዘምያላለሰው ለአባ ሲራችክ ጥሩ አይደለም
  ኮሦኮሦም ቢይላቸው አባ ሲራክ ተብየው እውነት እንናገራለን ለድንግልርያም ብለንከፋል ኑረን
  Gefällt mir · Antworten · 2. Juli um 13:33
  Gefällt mir · Antworten · 4. Juli um 13:47

 5. Anonymous July 8, 2016 at 10:19 am Reply

  ኣሳዛኝ ክሥተት……………………!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: