የጋምቤላ ፕሬዝዳንት: የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጵጵስና እንዲሾሙላቸው ፓትርያርኩን ጠየቁ፤ ሌላ አባት ቢመደብ ክልሉ እንደማይቀበል አስጠነቀቁ

Gambella's President Gatluak Tut Khot plea to Megabe Aelaf Aba Tekleክልላዊ መንግሥቱ፡-

 • የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ጳጳስ ኾነው በአባትነት እንዲቀመጡ ጠይቋል
 • በ2ሺሕ ካ.ሜ. መሬት መንበረ ጵጵስና እያስገነባ ሲኾን፤ የቤት መኪናም አዘጋጅቻለኹ፤ ብሏል
 • ሕገ መንግሥቱ እንደሚያዝ የሕዝብ ድምፅ ይከበርልን ሲል ክልላዊ አቋም እንደኾነ ገልጧል
 • ለ7ኛ ጊዜ መጠየቁን አስታውሶ፣ ሌላ ጳጳስ ቢመደብ ከባሮ ቆላ ከኤርፖርት አናሳልፍም ብሏል

***

ርእሰ መስተዳደሩ ጋትሉዋክ ቱት ኮት፡-

 • “ከአባ ተክለ ሃይማኖት ውጪ ጳጳስ፣ አባት አንፈልግም፤ ሲኖዶስ በጫና ቢመድብብን የግንኙነት መስመራችን ይበጠሳል፤ ቢመጣም ከባሮ ቆላ ከኤርፖርት አናሳልፍም፤ አንቀበልም፡፡”

***

 • ጵጵስና፣ ክህነታዊ ማዕርግ በመኾኑ ቀኖናዊና መንፈሳዊ ሹመት እንጂ እንደ ሕዝባውያን በ“ድምፃችን ይከበር” ዓይነት ውትወታ(lobby) ብቻ የሚወሰን አይደለም፤ የሥራ አስኪያጁ የአገልግሎት ፍሬዎችና የድጋፍ መሠረቶች፣ በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት ተረጋግጦ፤ ጥቆማውም፣ በደንቡ መሠረት መቅረብ ይኖርበታል፡፡ በዛቻና በማስፈራሪያ መልክ የቀረበው የርእሰ መስተዳደሩ ጥያቄ ኢ-ሕገ መንግሥታዊና ኢ-ቀኖናዊ በመኾኑ ያለማመንታት መታረም ይኖርበታል
 • ይህንንም በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንንም ራሳቸውንም የማስከበሩ ቅድሚያ፣ ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጀመር ይገባዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ “ይደልዎ፤ ይደልዎ” ተብሎ ለመሾም የሐቅ ምስክርነቱና ሥራቸው ብቻ በቂ ነውና! አልያ፣ በመለካዊ እጅ ጥምዘዛ አስገዳጅ ኹኔታ በመፍጠር ሹመቱን ለመሸመት በእጅ አዙር የቀረበ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ስላለመኾኑ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?

***

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ በጋምቤላ ክልል የምታከናውነውን ልማት፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ ለማስቀጠል፣ የሥራ አስኪያጁ የመጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ መኖር አስፈላጊ ነው፤” ያሉት የክልሉ ርእሰ መስተዳድር አቶ ጋትሉዋክ ቱት ኮት፤ አባ ተክለ ሃይማኖት ኤጲስ ቆጶስነት እንዲሾሙላቸው ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩንና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላትን  የጠየቁ ሲኾን፤ ሌላ አባት፣ ጳጳስ ኾኖ ቢመደብ እንደማይቀበሉም አስጠነቀቁ፡፡

ርእሰ መስተዳድሩ፣ በቁጥር መ2/6384/አ28/1 በቀን 02/10/2008 ዓ.ም. በአድራሻ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በጻፉትና፤ በግልባጭ ደግሞ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤትና ለፌዴራል እና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ባሳወቁበት ደብዳቤአቸው፤ ጥያቄውን ለሰባተኛ ጊዜ ማቅረባቸውን አስታውሰዋል፡፡

ይኸው አቋም÷ የክልሉ መንግሥት፣ የማኅበረ ካህናቱ፣ የሕዝቡ፣ የሀገር ሽማግሌዎችና የሰንበት ት/ቤቶች ተማሪዎች ድምፅ እንደኾነ በማስታወቅም፣ “ሕገ መንግሥቱ እንደሚያዘው፣ የሕዝብ ድምፅ ይከበርልን፤” በማለት ነው አጽንዖት የሰጡት፡፡

የክልሉ መንግሥት፣ ለመጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት መንበረ ጵጵስና ማሠርያ፣ 2ሺሕ ካሬ ሜትር መሬት መስጠቱንና ግንባታውም በእምነቱ ተከታዮች፣ በሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ በማኅበረ ካህናቱ፣ በሰንበት ት/ቤቶች ተማሪዎችና በአምስቱ ብሔረሰብ ተወላጆች ትብብር እየተከናወነ መኾኑን አቶ ጋቱሉዋክ ቱት ጠቅሰው፤ ለመንበረ ጵጵስናው የሚያገለግል የቤት መኪናም መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት፣ በአኙዋና በኑዌር ዞኖች በሚነሣው ግጭት፣ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ለክልሉ ሰላም በመታገል ሰላምን አረጋግጠዋል፤ ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፣ ይህም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ባሉበት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ምስክርነት የተሰጠበትና በፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር “የሰላም ጀግና” ተብለው የነሐስ ሜዳልያ የተሸለሙበት፤ በክልሉም “የሰላም እና የልማት አምባሳደር” ተብለው የተሠየሙበት እንደኾነ በደብዳቤአቸው አስፍረዋል ‐ “በአኙዋሃ ዞንና በኑዌር ዞን በሚነሣው ጦርነት መሀል ገብተው ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ኮሾሮ በመብላት የክልላችንን ሰላም ያረጋገጡ በመኾኑ የሰላምና የልማት አምባሳደር በማለት ሠይመናል፡፡”

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ባለፈው ግንቦት አጋማሽ ክልሉን በጎበኙበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በክልሉ ልማት፣ መልካም አስተዳደርና የሰላም ግንባታ ዙሪያ “ወደር የለሽ ሥራ እየሠራች ነው፤” ያሉት ርእሰ መስተዳድሩ፤ “ይህን ለማስቀጠል እንዲቻል፣ የአባ ተክለ ሃይማኖት ከእኛ ጋር መኖር አስፈላጊ ነው፤” ማለታቸውን ዜና ቤተ ክርስቲያን ጋዜጣ በወርኃ ግንቦት እትሙ ዘግቧል ‐ “ክልላችን በተለያዩ ጊዜአት ቅዱስ ሲኖዶስን የጠየቀው ጥያቄ ተግባራዊ እንዲያደርግልን በክልላችን መንግሥት ስም አኹንም ጥያቄ እያቀረብኹ ቅዱስነትዎ እንዲያስብበት እጠይቃለኹ፡፡”

Gambella Regional State to the Patriarch1
መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖትን፣ ለኤጲስ ቆጶስነት ያበቋቸዋል ያሉትን ምስክርነት፣ በ22 ነጥቦች ዘርዝረዋል፤ ርእሰ መስተዳድሩ በደብዳቤአቸው፡፡

ከምስክርነቱም መካከል፤ የቀድሞውን የክልሉን ፕሬዝዳንት አቶ ኡሞድ ኡቦንግንና በርካታ የክልሉን ባለሥልጣናት ጨምሮ ከ7ሺሕ637 በላይ የአምስቱ ብሔረሰብ አባላት ማስጠመቃቸውን፤ 53 አብያተ ክርስቲያናትን ማሳነፃቸውንና ገዳማዊ ሕይወትን ማስፋፋታቸውን፤ “የመናፍቃን መዶሻ” የሚል ቅጽል የተሰጣቸው ጸሎተኛና ወንጌላዊ መኾናቸውን፤ 13 ባለፎቅ ት/ቤቶችን ማስፋፋታቸውን፤ የክልሉን ብሔረሰብ ልጆች ሰብስበው በገዳም የሚኖሩ፤ በእምነቱ ተከታይና ከእምነቱ ውጭ ባሉት ተወዳጅ ከመኾናቸው በቀር አንድም የሥጋ ዘመድ የሌላቸው፤ ዘረኝነት፣ ሙስና፣ ኪራይ ሰብሳቢነት የማያውቃቸው፤ ለአገልግሎት ሲወጡ በየመቃብር ቤቱና በቤተ ክርስቲያን የሚያድሩ እንጂ በሆቴል የማያድሩና በሴት የማይታሙ ናቸው፤ የሚሉት ይገኙባቸዋል፡፡

ኾኖም ርእሰ መስተዳድሩ፣ የሥራ አስኪያጁን አገልግሎትና ብቃት መዘርዘሩ በኤጲስ ቆጶስነት ለማሾም በቂ ኾኖ ያገኙትና የተማመኑበት አይመስልም፤ ከበድ ያለ ማሳሰቢያም መስጠታቸው አልቀረም፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በቅርቡ እንደሚያካሒድ በሚጠበቀው የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት፣ ከሥራ አስኪያጁ መጋቤ አእላፍ አባ ተክለ ሃይማኖት ውጭ ሌላ አባት መመደቡን እንደ ጫና እንደሚቆጥሩትና እንደማይፈልጉ ርእሰ መስተዳድሩ በግልጽ አስፍረዋል፤ ከመንበረ ፓትርያርኩ ጋር ያለው የግንኙነት መሥመር እንደሚበጠስም አስጠንቅቀዋል፤ “ተመድቦ ቢመጣም ከባሮ ቆላ ከኤርፖርት አናሳልፍም፤ አንቀበልም፤” ሲሉም ዝተዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችን ቀኖና÷ በመኳንንት አማላጅነት ሢመተ ጵጵስናን መፈጸምን ያወግዛል፤ ኤጲስ ቆጶስ፣ በእምነቱና በእግዚአብሔር እንዲጸና እንጂ በዚኽ ዓለም መኳንንት ርዳታ እንዳይቆም ያዝዛል፤(ፍትሐ ነገሥት 176፤ ረስጠብ 21)፡፡ ኤጲስ ቆጶሳት የሚሾሙት፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ታምኖበት ሲወሰን እንደኾነ የሚደነግገው ሕገ ቤተ ክርስቲያናችን፤ ለሢመቱ የሚለዩትም፣ ለዕጩነት የሚያበቋቸውን መስፈርቶች አሟልተው ሲገኙ እንደኾነ በግልጽ አስቀምጧል፡፡

በተጨማሪም፣ ኤጲስ ቆጶስ የሚሾመው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ምርጫ እንደኾነ በሥርዓታችን የተደነባ ሲኾን፤ ስለ ደግነቱና ትሩፋቱ፤ ስለ ንጽሕናውና ከነውር የራቀ ስለመኾኑ የማረጋገጫ ምስክርነት የመስጠቱ ድርሻ የሚሾምበት ሀገር ካህናትና ምእመናን እንደኾነ፤ ሹመቱ ሲፈጸምም፣ ካህናቱም ሕዝቡም ተገኝተው እየመሰከሩለት እንደሚሾም የተቀነነ ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 5፣ አብጥሊስ 2፤ ረስጠብ 52)

ዕጩ ቆሞሳት ወይ መነኰሳት፣ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና በግብረ ገብነታቸው፤ በአስተዳደር የሥራ ልምዳቸውና በሥራ አመራራቸው ያላቸው ችሎታና ብቃት የሚጣራው፣ በነበሩበት አካባቢ/የሥራ ቦታ/ ሲኾን፤ ይህም በክፍሉ/በሀገረ ስብከቱ/ ሊቀ ጳጳስ ርእሰ መንበርነት በሚሰበሰቡ ካህናትና ምእመናን ምስክርነት እንደሚረጋገጥ በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን የኤጲስ ቆጶሳት የምርጫ ማስፈጸሚያ ደንብ፣ 2007(ቁ.8) ተገልጧል፡፡

በዚኽም መሠረት፣ የኤጲስ ቆጶሳት ሰማያዊና ክህነታዊ ሹመት እንደ ሕዝባውያን ምድራዊና ዓለማዊ ሹመት በ“ድምፃችን ይከበር” ዓይነት ውትወታ(lobby) ብቻ የማይወሰን ቀኖናዊ መለኪያዎችና አፈጻጸሞች እንዳሉት እንረዳለን፤ ፈቃደ እግዚአብሔር የሚጠየቅበትና በጸሎት የሚታገዝ መንፈሳዊ በመኾኑም ዛቻና ማስፈራራቱ አግባብነት እንደሌለው እናስተውላለን፡፡ በመኾኑም፣ በቀኖናው፣ በሕጉና በማስፈጸሚያ ደንቡ ዓይን፤ ርእሰ መስተዳደሩ የጠቀሷቸው የሥራ አስኪያጁ የሥራ ፍሬዎችና የድጋፍ መሠረቶች፣ በአህጉረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት ተረጋግጦ ጥቆማውም በዚኹ መሠረት መከናወን እንዳለበት እናምናለን፡፡  

ርእሰ መስተዳድሩ፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጻፉትን ደብዳቤ በሰፊ ልቡና ለመውሰድ ብንሞክርና የዘረዘሯቸውንም የመጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት አገልግሎትና ብቃት ብናምንበት እንኳ፤ በዛቻና በማስፈራሪያ መልክ መቅረባቸው ኢ-ሕገ መንግሥታዊና ኢ-ቀኖናዊ ብቻ ሳይኾን፤ የቤተ ክርስቲያናችንን ሉዓላዊነትና ብሔራዊነት የሚገዳደር በመኾኑ ያለማመንታት መታረም ይኖርበታል፡፡

ይህንንም በማድረግ ቤተ ክርስቲያናችንን የማስከበሩ ቅድሚያ፣ ከራሳቸው ከሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መጀመር ይገባዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ “ይደልዎ፤ ይደልዎ” ተብሎ ለመሾም የሐቅ ምስክርነቱና የዓመታት ሥራቸው ብቻ በቂ ነውና! አልያ፣ በመለካዊ እጅ ጥምዘዛ አስገዳጅ ኹኔታ በመፍጠር ሹመቱን ለመሸመት በእጅ አዙር የቀረበ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ስላለመኾኑ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?

የጋምቤላ እና የደቡብ ሱዳን አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመኾን ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት፣ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት፤ ከመቱ – ኢሉ አባ ቦራ የተገኙ፣ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የዲፕሎማ ምሩቅ ናቸው፡፡ የቀድሞው ዲያቆን አምሳሉ ንጉሤ፣ አባ ተክለ ሃይማኖት ተብለው ምንኵስና የተቀበሉት በደብረ ሊባኖስ ገዳም እንደኾነ የተገለጸ ሲኾን፤ ከክልላዊ መንግሥቱ ባለሥልጣናት ጋር ባላቸው ጥብቅ ግንኙነት ጎልተው ይታወቃሉ፡፡

Advertisements

20 thoughts on “የጋምቤላ ፕሬዝዳንት: የሀ/ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጵጵስና እንዲሾሙላቸው ፓትርያርኩን ጠየቁ፤ ሌላ አባት ቢመደብ ክልሉ እንደማይቀበል አስጠነቀቁ

 1. Anonymous June 23, 2016 at 5:11 pm Reply

  Aba Teklehaymanot baytsafilachewum yideliwo libalu yigebal yetignawum agelgay ersachew yarefubeten ye agelegilot menged yalefe yelem bizowochu agelgayoch ketema tekor behonubet ke 15 amet belay geter magelgel yikebdal. Prezidantu silalu sayho yigebachewl bay negn

 2. giontimes June 23, 2016 at 9:21 pm Reply

  Reblogged this on ghion times.

 3. Anonymous June 24, 2016 at 2:50 am Reply

  ይህን አይነት ነገር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አትቀበለውም። ቅዱስ ሲኖዶስ እና ፓትርያርኩ ሳይመድቡ ሌላ አንቀበልም ማለት በውስጡ ሌላ ጉድ እንዳለ ይቆጠራል። አባ ተክለ ሃማኖት ጥሩ ከሰሩ በሌላውም ጥሩ እንዲሰሩ ይፈለጋል። ስለዚህ ስራውን ለቅዱስ ሲኖዶስ ስጡና አባት እንፈልጋለን በሉ። ቅዱስ ሲኖዶስ የመረጠውን አንቀበልም እናባርራለን ካላችሁ ማን የመረጠውን ልትሾሙ ነውን? ይህ ነገር ጤነኛ አይመስለኝም። እርሳቸውም ጥሩ ከሆኑ የሚቀየሙ አይመስለኝም። ስለዚህ መታዘዝ ከሰነፍ መስዋእት ይበልጣል አይደል የሚባለው። አባቶች በዚህ ዙሪያ ብዙ ጥናት ያስፈልገዋልና በደንብ መታየት አለበት። If the higher power order, we have to do. If there is a problem, you should tell for Sinodos. We have to respect our true fathers. We have to make a zeal for our church, but not our relatives. Because God think for your relatives.

 4. Anonymous June 24, 2016 at 6:34 am Reply

  ye presedentu mastenkekiya kalat mekelakel yeqalat gidfet new. presdentu Amakari kalacew letenagerut mastenkekiya kalat patriyarkunna sinodosun yikrta teykew qalatun yetenagerut le agelgayu yalachewn adnakotna degaf lemasayet yahl enji mastenkekiya metsaf endemaygebachew endemigenezebu geltsew endiyarmut bimekeru tiru new. le emnetu lasayut tenkara degaf degmo ejg limesegenu yigebal. yekell presdentn le betekrstyan agelglot yabeka ye agelgayu tigatm yemidenek new. ene balakacewm kanbebkut tenesche talak abat endehunu megemet chiyalehu. sew kemiyayew beteleye eyta westn mermro yemiyay amlak egziabher fitsamiachewn yasamrew.

 5. tsigemariam June 24, 2016 at 6:48 am Reply

  Egziabherin medafer ayhonim. Woniz anashagirim new yalut. Erso degimo me 2008 wede 2009 ayishagerum.

 6. Anonymous June 24, 2016 at 11:13 am Reply

  Gud sayisema meskerm ayitebam alu

 7. wagaw June 24, 2016 at 2:32 pm Reply

  በመለካዊ እጅ ጥምዘዛ አስገዳጅ ኹኔታ በመፍጠር ሹመቱን ለመሸመት በእጅ አዙር የቀረበ ጥያቄና ማስጠንቀቂያ ስላለመኾኑ እንዴት ማረጋገጥ ይቻላል?

 8. seneshaw June 24, 2016 at 2:33 pm Reply

  ere sewyew eko emebelet new qedasie ayqedesem ayaqorbem

 9. Anonymous June 24, 2016 at 11:48 pm Reply

  ሌባ ላለመሆኑ ማረጋገጫ የለንም።

 10. Anonymous June 25, 2016 at 6:45 am Reply

  አባታችን እግዚአብሔር ሆይ ለእናትህ አስራት አድርህ ሰጥተኸናልና ስለድንግል ማሪያም ብለህ ስማን እኛ ወደ አንተ ተማፅነናልና፡፡

 11. mana June 26, 2016 at 7:23 pm Reply

  የጋምቤላ ሀገረ ሰብከት ሥራ አስኪያጅ መጋቤ አእላፍ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ጉዳይ ፡-
  1. መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባት እንደማይችል እየታወቀ ቆሞሱ ግን የክልሉ መንግስት ፕሬዝደንት ያለግባብ በማሳመን የካህናት ድምፅ በማስመሰል በፕሬዝደንቱ ፊርማ ቆሞሱ ጳጰስ ሆነው እንዲሾሙ ደብዳቤ ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ሲያጽፉ ሌላ ጳጰስ ከተመረጠ ከባሮ ቀላና ከኤርፖርት የማናሳልፍ የማንቀበል መሆኑን ብለው ደብዳቤ ማስጻፋቸው፣ይህ አፃፃፍ አግባብ ባለመሆኑ የተለያዩ አካላት በኢንተርኔት ለቀውት ሀገር ጉድ ያስባለና የጠቅላይ ቤተ- ክህነቱንም የመሾም ስልጣን፣የሚገፋ፣ አፃፃፍ መሆኑ፣
  2. ምዕመናን፣ካህናት ፣ዲያቆናት፣ሥርዓት -ቤተ ክርስቲያን ሲፈርስ ሲያዩ ይህ ቢስተካከል ብለው ለቆሞሱ ጥቆማ ሲሰጡና ሲያማክሩ ካለመቀበላቸውም በላይ ጠቋሚውን ይህንን ካላቆምክ ለክልሉ ፕሬዝደንት፣ነግሬ አሳስርሀለሁ በማለት በማስፈራራታቸው ሁሉም ይህንን ዛቻና እስራት ፈርቶ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሲበላሽ ዝም ብሎ እንዲያይ መገደዱን፣
  3. ቆሞሱ በቃል አዋዲ የማይመሩ ስለሆነ የሰበካ ጉባኤ በሁሉም አድባራት በእሳቸው መዳቢነት ብቻ እንዲሠራ መደረጉን ምዕመናኑ የራሱን ተወካይ እንዳመርጥ መደረጉን መብቱን ያለአግባብብ ከሀገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ መገደቡን
  4. የሰንበት ትምህርት ቤት አባላት ባላመኑበት የሰበካው ጉባኤ ባልተሰፈበት ራሳቸው ቆሞስ አባ- ተክለ- ሃይማኖት የሰንበት ትምህርት ቤት ኮምቴ ሰብሳቢ ም/ሰብሳቢ ፀሐፊ ገንዘብ ያዥ ለመምረጣቸው፣ በጋምቤላ ከተማ የነበረው የሦስቱ ሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት ጉባኤ መበተናቸውንና በሰሞኑ በጠቅላይ ቤተ ክህነት ተካይዶ የነበረው የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት ጉባኤ ላይ የተላኩ የሀገረ ሰብከት ሰራተኞች መሆናቸውና አንድ ሰው ከሰንበት ትምህርት የተሳተፈ ሰንበት ተማሪ አለመኖሩን፡፡
  5. ከቃለ ዓወዲ ውጭ ከመኮይ ወረዳ፣ መታር ወረዳ ጋምቤላ ከተማ የወረዳ የወረዳ አስተዳዳርዎች ለቀበሌ ሊቃነ መናብርት የመንግስት ተሽዋሚ ሆነው ደመወዝ ከመንግስት የሚከፈላቸው ባለስልጣናት ከአጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን ደመወዝ እንዲከፋለቸው ማድረጋቸውን እና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰበካ መፈሳሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በመገኘት ሀገረ ስብከት ያቀረቡት ሪፖርት ዙራያ ላይ ምስክርነት እንዲሰጡ በማድረግ ማረጋገጥ የሚቻል መሆኑን
  6. ትንሳኤ ዘጋምቤላ ተብሎ ባሳተሙት መጽሔት በጋምቤላ ሀገረ ስብከት ለውጥ፣ እኔ ከመጣው ነው፣ የመጣው ማለታቸው ምዕመናኑ የዘወትር ሃይመኖታዊ ግዴታውን ይወጣል፣በታቃራኒው ግን እሳቸው ከመጡ ወዲህ ግን የሚቆርቡ እና አሥራት በኩራት የሚያወጣው ምዕመናን ቁጥር መቀነሱ ሥርዓተ -ቤተ-ክርስቲያንም መበላሸቱ፣ በድብቅ የተድሶ ሥራ መሠራቱ በቃል ግን እኛ ተሀድሶ አንከተልም ብሎ ማስወራታቸው፡፡
  7. ተጠመቁ በተባሉት የክልሉ ባለሥልጠናት በተመለከተ አጠመኩኝ የተባለው የውሸት መሆኑን ከተጠመቁ ባለሥልጠናት አንደበት መስማት የሚቻለው ፣እኛ ጥምቄቱን አልተጠመቅንም፣ገንዘብ ስለምሠጡን ለማለታቸውንና ለትክክለኝነቱ በቂ መረጃ መኖሩ ስያጠምቁና በሀማይኖቱ ያላመኑትን የሀሰት ምስክርነት ይህንን ሠራሁ ብሎ ማቅረባቸው፡፡
  8. በዓመቱ በሚከበረው የሆሳዕና ክብረ በዓል ዕለት በጋምቤላ ከተማ ያሉት ቤተ -ክርሲቲያናት እንዲዘጉ በማድረግ በገዳም ብቻ ላይ በግሉእንዲከበር በማድረግ ሥርዓቱን እዲፋለስ ማድረጋቸው፡፡
  9. ቆሞስ አባ- ተክለ ሃይማኖት ጋምቤላ ከገቡ ወዲህ በህዝብ የተመረጠ ሰበካ ጉባኤ ያለመኖሩ በእሳቸው ብቻ በተመረጡ ሰበካ ተብዬዎች እሳቸው እንዲፈለጉት፣ የሚሆኑ፣እንዲሁም ፣በበዓላት ቀንም ሆነ በስጦታ ለቤተ-ክርስቲያን የሚገባው ከሙዳይ ምፅአት የሚገኝ ገንዘብ ጨርሶ ሪፖርት አለመቅረብ በገንዘብ የሚመዘበር ላለመሆኑ ምን ማስረጃ ያቀርባሉ ፣አይሆንም (ስለሆነም ምዕመናን ለቤተ ክርስቲያን ሰጥቶ ለግል ጥቅም የዋለ ሊኖር ስለሚችል ጥብቅ ክትትል ቢደረግ?
  10. ቤተ ክርስቲያን ሕዝብ ምዕመኑ ፀሎት ለሚድረስ ወንጌልን ለመስማት ለመማር ሲመጡ ሰባኪው ስለክርስቶስ መስበክና ወንጌል ማስተማር ትቶ የቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ሥልጣን እና ይህን ሠሩ ያን አደረጉ ብሎ ካልሰበከ ሰባኪው፣በበነጊገታው ይባረል ፡፡ በዚህ የተነሳ ንፁህ ወንጌል ሲሰብኩ የነበሩት ሰባኪያን ተባርረዋል፡፡ታዲያ ይህን የሚሰሩ አባት አንዴት ነው ዝም የተባሉት?
  11. በየደረጃው የሚሰጡት የክህነት ሥልጣናት የሚሰጡት ፣በተሟላ የክህነት ብቃትና ችሎታ ብሎም በሚሰጡት፣ ብቁ አገልግሎት ስራው ታይቶ በህገ ቤተ ክርስቲያን መሰረት ባለው የሥልጣን አካል ተመርመሮ፣ተጠንቶ፣ ተመስክሮ ሆኖ ሳለ ቆሞስ አባ ተክለ ሃማኖት ጋምቤላ ከገቡ ጀምሮ ፊላጎታቸው ስልጣን ማግኘት ነው፡ ለዚህም የውሸት የህዝብ ጥያቄ ነው መሾም አለብኝ ማለታቸው ግልጽ ነው የሚያስጠይቁ ደብዳቤዎችን ዘንድሮ በቀጥታ ለጠቅላይ ቤቱ ክህነት መድረሱ ከዚህ በፊት የተፃፉትን ስምዓ ጽድቅ ዘጋምቤላ ተብሎ ከታተመው መጽሔት ከገጽ 62 ጀምሮ ማይት ይቻላል፡፡
  12. የጋምቤላ ሀገረ ሰብከት ከየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ከህዝብ የተሰበሰበው የልማት ገንዘብ አምጡ ብሎ ያለአግባቢ ከደሀ ቤተ ክርስቲያን መውስዳቸው
  13. ያፈረሰ ቄስ እና ታራ ምዕመን ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አድርጎ በመሾማቸው በርካታ ምዕመን ቤተ ክርስቲያን ከመሄድ ማቋረጣቸው ይህ አዝማሚያ ወዴት ያመራናል ; ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይህንን ተግባር እያዩ እየሰማ ቆሞስ አባ ተክለ ሃይማኖት ይሾማል ወይ?
  14. የጋምቤላ ትንሳኤ መጽሔት ብሎ ባሳተሙት ላይ ቃለ መጠየቅ ሲያደርጉ ንባብ ጀምሮ ዳዊትና ቅዳሴ ተምሬያለሁ ያሉት ሁሉም የሚያውቀው የአደባባይ ሚስጢር የሆነውን አይደለም ቅዳሴ ይቀርና የቤተ ክርስቲያን ትምህርት መጀመሪያ የሆነው ውዳሴ ማርያም መች ተምረው ያውቃሉ?መች በቃላቸው ይደግማሉ?ኧረ ለመሆኑ መች ቅዳሴ ቀድሰው ያውቃሉ? ;አይደለም ለመቀደስ በክብረ በዓላት ቀን በተገኙበት የቤተክርስቲያን ግፃዌ በሚያዝዘው መሠረት እንዳይቀደስ በክብረ በዓላት”ወንጌል እንሰብካለን” በማለት መቼ ቅዳሴ ሲያልቅ ውዳሴ ማሪያም ፣ውዳሴ ማሪያም፣መልክዐ ማርያም እና መልክዐ ኢየሱስ ደግመውና አስደግመው ያውቃሉ? ጠቅላይ ቤተ ክህነት ይህንን እያየ እየሰማ ቆማስ አባ ተክለ ሃይማኖት ይሾማል ወይ?
  15. ያሬዳዊ ዜማ የሆነው ማህሌት እንዳይቆም በመከልከል መርጌቶች እንዳይኖሩ አድርገዋል፡፡
  16. ጽላት ስያዝገቡ ቀይሮ ወይም ሌላ ጽላት ማስገባት ለምሳሌ ኢታንግ ወረዳ ተርፋም ቀበሌ መጥቀስ ይቻላል በቤተመቅደስ ያስገቡት ጽላት የአባ ሊባኖስ ሲሆን የጊወርጊስ ጽላት ነው በማለት ምዕመኑን አታለዋል፡፡

 12. wagaww June 27, 2016 at 7:27 am Reply

  ግልጥ ደብዳቤ ለእጩ ኮሚቴ
  ግልጽደብዳቤ ለ አቶ ጋት ሉዋክ ቱት
  ቤተ ክርስቲያን ከመቸውም ጊዜ በላይ ልትነቃ ይገባታል
  አንድ መንግስት በተዘዋዋሪ መልኩ ካለሆነ እንዴት በግልጽ እገሌ ካልተሸመ ይላል
  አቶ ጋት ሉዋክ የጻፉትን ደብዳቤ ባነበብኩ ጊዜ አፈርኩቦት፣ ለነገሩ ተክለሀይማኖት የተባለው መነኩሴ እንዳሳሳትዎት እሙን ነው
  ምናልባት በሙስና ተሳስረው ይሆናል አልያም በወሬ አወዛግቦት ይሆናል፣፣ የእርስዎ ሃላፊነት ምን ድረስ ነው፣ ለነገሩ እርስዎ ስላልተጠመቁ እና ትምህርተ ሃይማኖት ስላልተማሩ ጳጳስ እንዴት ተብሎ እንደሚመረጥ እውቀቱ ስለሌለዎት አልፈርድቦትም፣፣
  ተሳስቶም ያሳሳተዎት መሃይሙ አባት ሳይሆን እንደማይቀር እገምታለሁ፣፣
  የቤተክርስቲያን ውርደት የጀመረው መቼ ነበር፣ ኢጥሙቅ ግን ለጳጳስነት ሲያጭ ፣ከ ባሮ ቆላ እያለ ሲዝት፣የሰውየውን መሃይምነት ግን እርስዎ እያስቀጠሉት እንደሆነ ይገባዎታል ፣፣አባት ተብዬውስ አያፍርም;፣ ምናለ ሰኔ ጎልጎታ ብቻ ሳይሆን ድድስቅልያ ቢያነብ፣፣ፍትሃነገስቱን ቢያየው፣፣ከትምህርት ትምህርት ፣ከጽድቅ ጽድቅ የለው ሮብ አርብ የሚበላ ሰው ሊሾም፣፣ሃሃሃሀሀሃሃሃሃ እንዲያማ ከሆነ ለሹመት እኔ መች አንሼ
  ከሚገርመኝ ነገር የመነኮሰው እዛው ኮሌጅ እያለ ነበር ወይ ብር ሸለቆ ገዳም ይብላኝ ላንቺ አኛን አስረጅተሸ ላመነኮስሽን
  መስፈርቱ በረሃ መቀመጥ ከሆነ፣፣፣፣፣በረሃ እኮ አኔም አቀመጣለው ሙሉ በሙሉ የባንክ አካውንቱን በቁጥጥሬ ስር አውዬ
  በተክርስቲያን ሰራ ሰው አጠመቀ፣፣ ምናምን ሲስተሙ እንደሆነ አያውቅም ፣አንድ ጥያቄ አለኝ ጥሙቃኑ የት ናቸው አይቶአቸው ያውቃል ፣እንዲያ ከሆነማ የማህበረ ቅዱሳኑዋ ወይዘሮ ዘውዴ እኮ ተክሌ ካጠመቀው የበለጠ በሽናሻ በአሶሳ በ ጂንካ ወዘተ አጥምቃለች ሊያውም በገዛ ብሩዋ ፣መቅደስ አሳንጻለች፣ ካህናት ከየብሄረሰቡ አስተምራለች፣እና ለሱዋስ ዐይጽፉላትም ደብዳቤ ፣ለሴትነቱና ለ አሉባለታ ተክሌ መች አነሰ ፣ለነገሩ የስልጣን ጥሙ አዙሮ ሳይደፋው አንድ ነገር መደረግ አለበት፣
  አባ ገብርኤል የተማሩት ትምህረት ለሹመት ያበቃዋል ብሎ የህሊና ምስክርነት ይሰጥዎታል ወይስ አይሰድዎትም
  አባ ሳዊሮስ እርስዎ በቀደሱበት መቃድስ ቆመው ይህ የወንድ ነው ወይስ የሴት መግቢያ ብለው ይጠይቁት
  አባ ሳሙኤል ስለ ማናጅመንት ይጠይቁት፣ስላሳሰራቸው ሰራተኞችም
  ድሮ ቢሆን አንድ 300000 ቢያቀርብ ይባላል፣ ዘንድሮ ግን ይከብዳል
  ወደ ጋት ሉዋክ ልመለስ ደብዳቤዎን ከ ሃራ ላይ ሳነብ ገረመኝ

  ቀሚስ አሳምሮ መኩነስነስ ብቻ ለጵጵስና ካስመረጠ ከኔ የበለጠ ስለሌለ ለኔም የሎቢ ስራዎትን ይስሩ፣፣ አቶ ጋትሉዋክ ምንም እንኩዋ የሰቨን ደይ አድቬንቲስት ተከታይ ቢሆኑም የ ደንቆሮውን ሰውዬ የስልጣን ጥም ሳያዩ አይቀርም፣፣ ከ ኦሮሞ ጋር የተወለድኩት፣፣፣ መቱ ነው ሲል፣፣፣ ደግሞ ለአቡነ ጳውሎስ ሀገሬ አድዋ ነው በእናቴ በኩል ይላቸው ነበር አቤት ዉሸት፣፣ ደግሞ ለአሜሪካው ሲኖዶስ አባቴ ከጎንደር ተሰዶ ወጣ እንጂ ደሜ ልክ እንደ እናንተ ነው እዚህ እንደማይሾሙኝ አውቃለው እያለ በኢንተርኔት የሚደውል ሰው እንደሆነ ያውቃሉ፣፣
  አንድ ነገር ልበልዎት አብሬው ኮሌጅ ስማር ፊላታዎስ እንለው ነበር ኤፉን ሲደረድር ታድያ ምናለ ስኮላር ሺፕ ሰጥተው ቢያስተምሩት
  እመበለቱም እንለው ነበር ዳዊት ገልብጦ ሲደግም ታድያ አስተምራችሁ ሹሙት ምናለ ቢሉ፣፣፣፣ በእጅጉ ግን መቅደሱዋን አልደፈርኩም ይላሉ፣፣

 13. Anonymous June 29, 2016 at 1:05 pm Reply

  (መንፈስ ቅዱስ በርናባስንና ሳውልን እኔ ለፈለግኋቸው ሥራ ለዩልኝ ሐዋ13፥2)ባለው መሠረት የቤተክርስቲያን መሪ እግዚአብሔር እና ሹመት ሰጭ እግዚአብሔር መሆኑ ቢታወቅም ለሹመት ብቁ ነው የሚባለውን ሰው የመለየት ሥራ ግን የሰዎች ድርሻ ነው በመሆኑም በዚህ የኤጲስቆጶሳት እጩ ውስጥ በተራ ቁጥር 75 ላይ የሚገኙት አባ ገብረ ማርያም የተባሉት አባት በአስተዳዳሪነት ከሰሩባቸው ቦታዎች መካከል ጥቂቶቹ በድሬዳዋ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ከርስቲያን ፣በታላቁ ቦታ በደብረ ብርሃን ሥላሴ ቤተ ከርስቲያን ፣ በኳታር ጽርሀ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ከርስቲያን በአሁኑ ሰአት ደግሞ በዱባይ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በአንዱ ቦታ በአስተዳደር የሚገኙ ሲሆን በሥራቸው ታታሪ እግዚአብሔርን ፈሪ ሰውን አክባሪ አንደበተ ርቱዕ እና ለቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ሲሆኑ ለተባለው ሲመት ከፍጻሜ ቢደርሱ ለቤተክርስቲያን ጠቃሚ መሆናቸውን አምናለሁ ።

 14. Bete Zewudu July 2, 2016 at 10:10 am Reply

  Bete Zewudu
  28. Juni um 17:38 ·
  አባ ኃይለ መለኰት ተስፋ ማርያም/ጀርመን/ ከዚህ በፊት ያላቸው የኋላ ታሪክ ምን ይመስላል የሚለውን ምዕመናን እንዲያውቁትና አስመራጭ ኮሚቴው በራሱ መንገድ ማጣራት ያካሂድ ዘንድ ፤ ለቤተክርስቲያን ያለፉት አመታት የተከናወኑት ድርጊቶች ዳግም እንዳንመለከታቸው አሁን ላይ ሆነን ሃላፊነታችንን ከመወጣት ምዕመኑን ከማንቃት አንጻር እንዲህ አቅርበነዋል፡፡
  Gefällt mirWeitere Reaktionen anzeigenKommentierenTeilen

 15. Bete Zewudu July 4, 2016 at 11:51 am Reply

  ስራ ባለቤቴ በድንገት መስሬቤት ትቀነሳች እንዲህ ከሆነገች አስር ይበቃናል ብለን መክፈል ስንጀምር
  አንድቀን እድቀን እደአባት ሰላም ብሎየማያውቀው የስም መነኩሴ ተብየ አባ ሲራክ እንዴት አስሩን ትቀንሣላችሁ እየተመካከራችሁ አይደል ስብሰባ ገብታችሁ ለመናገር እንዲያመቻችሁ ብላችሁ እንጂ እስካሁን ጨርሶ ትወጡነበር
  እኔን ለመበጥበጥ ነው ከዚህ የምትመጡ ብሎሰደባት ባለቤን ተመልከቱ
  አባ ሐይለመለኮት ተስፋማርያም የሗላታሬኩ እደሜስረደው ከአርባምንጪ ገብርኤል ወደቅዱስሜካኤል
  በምን ምክንያት እደተዛወረ አርባምንጪ አገርስብከት መረዳት አዲስ አበባቅድስትማርያም ምንይሰራእንደነር
  በአጭሩ መረዳት ይቻላል ቆቡን አውልቆ በየሴታዳሬወች ሲዞር
  እንዲሁም ባለትዳሮችን ለማስቀደስ ፈተና እስከሚሆንባቸው ድረስ
  ሌላው በጫት ሱስ እና በሲጋራ አጫሽነት ሀገርቤት ይታወቃል
  ከዚህ ፋንክፈርት ጀርመን ህይወቱ ተመሣሣይ
  ነው በተለምዶ ፋራንክፈርት ካይዘር እስትራሰ እየተባለ በሜጠራው ሴታዳሬወች ቦታ
  ሲመላለስ ሁሉም ሰውያገኝዋል ክርስቲያኑ ቀርቶ አስላች ያውቁታል
  በዝሙቱ ይህንን ስእፅፋ ልዮጥላቻ ለእሱ ኑሮኝ ሣይሆን ካህን ስላይደለነው
  ገዳም ነበርኩኝ ይላል አወገዳም ነበረ ፈተነውን መቇቇም አቅቶት ይህንን ሁሉ
  ሐጤያት የሚያሠረው ከገዳም ያወጣው ሰይጣን ነው አንዴ አባ ሲራክ
  አንዴ አባ ሐይለመለኮት መልም ሰራእንጄ ሰም በመቀየር ሹመት አይገኝም
  ጉልቻ መቀየር ወጥ አያጣፍጥም ይባላል
  የያዘው ሰይጣን ክርስቴያኖችን ማሳደድ አስር ጌዜየ ማህበረቅዱሳን እረበቨኝ
  በነጻ እየረዱት ሄኖክ ወንድወን
  እባክህ ብለን ብንለመነው ማህበረቅዱሣን ይውጣልኝ ብሎ ከፈላችው
  ይህ ኖለት ጳጳስ ቢሆን ጥሩይሰራይሆን እውነቱን እናጋልጥ አለም አዲትመንደር ሁናለች
  እና እውነትወታ በሲራክ ሴራ ከሁለት የተከፈለው የፍራንክፈርት ቅድስትማርያም ምመናን አንድመሆን
  አለበት እንላለን እውነቱን ስንናገር እኔ ትግሬስለሆንኩኝ ነው እያለ በየዋህ ክርስቴያኖች ቤት ማልቀሱ የማይቀርነው
  ግን ትግሬ በመሆኑሣይሆን ሐጤያተኞ የመቤታን ካዝና በአዶ ያስቀረ ህዝብ የበተነ ዛሬየተናገረውን ነገ የማይደግም
  ትግሬኮሜቴ ካልተመረጠ ብሎ ተመረጠለት ግን የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማድ ነውና
  ትክክል እንስራ ሲሉት ሲቆጣጠሩት ስም መጥራት ጀመረ ቴዎድሮ እላሠራኝ አለ ሰለተቆጣጠረው እኮነው
  ሰለዚህ ገንዘብ ያላግባብ ሲዘርፋ እና ሲዘሙት እያየ ዘምያላለሰው ለአባ ሲራችክ ጥሩ አይደለም
  ኮሦኮሦም ቢይላቸው አባ ሲራክ ተብየው እውነት እንናገራለን ለድንግልርያም ብለንከፋል ኑረን
  Gefällt mir · Antworten · 2. Juli um 13:33

 16. […] ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፣ ከክልሉ መንግሥት ለፓትርያርኩ በተጻፈ ትእዛዝ በብቸኝነት መቅረባቸው፦ በዓለማዊ መኳንንት ምልጃ ክህነት […]

 17. […] መለካዊነት የተጠናወታቸው ተሿሚው አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፥ “አቶ ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን፤” እያሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትን ሲወተውቱና በማኅበሩ ላይ ሲያሳድሙ ሰነበቱ፤ […]

 18. […] መለካዊነት የተጠናወታቸው ተሿሚው አባ ተክለ ሃይማኖት ንጉሤ፥ “አቶ ካሳ ይጠራልን፤ መመሪያም ይስጠን፤” እያሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤትን ሲወተውቱና በማኅበሩ ላይ ሲያሳድሙ ሰነበቱ፤ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: