የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት የሙከራ ስርጭት መጀመር በፓትርያርኩ ቡራኬ ይፋ ይደረጋል

pat blessing to EOTC tv
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቴሌቭዥን አገልግሎት(EOTC tv) የሙከራ ስርጭት መጀመር፣ ዛሬ፣ ሰኔ 16 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቡራኬ ይፋ ይደረጋል፡፡

ቅዱስነታቸው፣ የሙከራ ስርጭቱን መጀመር አስመልክቶ፣ የቋሚ ሲኖዶስ አባላት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የመምሪያ ሓላፊዎችና የብዙኃን መገናኛ ስርጭት ድርጅቱ የቦርድ አባላት በተገኙበት በጽ/ቤታቸው ለብዙኃን መገናኛ መግለጫ እንደሚሰጡ ታውቋል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሎጎ/መለዮ/ በመጠቀም የሙከራ ስርጭቱን(logo display) የጀመረው አገልግሎቱ፣ በቀጣይ ልዩ ተልእኮውን የሚገልጽ የራሱ ሎጎ ይኖረዋል፤ ለዚኽም ግልጽ የውድድር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ተጠቁሟል፡፡ አጠቃላይ የሰው ኃይሉን(በይዘት ዝግጅት እና በኤዲቶሪያል ኮሚቴዎች) ለማዋቀርም፤ ባወጣው ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ መሠረት በሠራተኞች ቅጥር ሒደት ላይ ይገኛል፡፡

ቢሮውን በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት አድርጎ፣ ለስርጭት የሚኾኑትን ማናቸውንም ፕሮግራሞች በሀገር ውስጥ የሚያዘጋጀው አገልግሎቱ፤ በውሉ መሠረት በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ጋር በተደረገ ስምምነትና ገዳሙ ካለበት ከኢየሩሳሌም በሚገኝ የሳተላይት ድርጅቱ ቢሮ አማካይነት ስርጭቱን ያከናውናል፡፡

ለምሥራቅና ሰሜን አፍሪቃ እንዲኹም ለመካከለኛው ምሥራቅና ደቡብ አውሮጳ በናይል ሳት፤ ለሰሜን አሜሪካ (ካናዳ በተወሰነ መልኩ) እና ካሪቢያን አገሮች በጋላክሲ 19 የሚሰራጭ ሲኾን፤ ዋናው የስርጭት አገልግሎት ሲጀምርም በኢንተርኔት ላይቭ ስትሪሚንግ እንደሚቀርብ ተገልጧል፡፡

 Satellite name =Nilesat
 Frequency = 11353
 Symbol Rate = 27500
 Polarity = Vertical
 channal Name = EOTC


 

Advertisements

2 thoughts on “የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት የሙከራ ስርጭት መጀመር በፓትርያርኩ ቡራኬ ይፋ ይደረጋል

  1. ገ/ጊዮርጊስ ይግዛው June 23, 2016 at 8:54 am Reply

    እግዚአብሔር ይመስገን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: