ሳይመረምር በፖለቲካና በጎጠኝነት የሚሾም፥ በክፉ ሥራ ይሳተፋል፤ በእግዚአብሔርም ይጠየቃል፤ በሀገረ አሜሪካ የሚስተዋለው እውነታ

the Patriarchate in the diaspora ordained six new bishops

 • ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ” የሚለው የጵጵስናቸው ተቀዳሚ አደራ ተዘንግቷቸው ነውር ነቀፋ፣ ኑፋቄና ክሕደት አለበት፤ እያሉ ምእመናን እየጮኹ፣ ለጩኸቱ ተገቢውን ምላሽ እንደ መስጠት በምን ታመጣላችኹ ዓይነት አካሔድ፥ ዲቁና፣ ቅስናና ኤጲስ ቆጶስነት እስከ መሾም ደርሰው ኀዘናችንን አብሰውታል።
 • ጎጠኝነቱ፣ ከፖለቲካው አልፎ በቤተ ክርስቲያናችን ጭምር ዙፋኑን ዘርግቶ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ አስተምህሮ ምን ይላል፤ ሳይኾን የእኛ ወገንና ዘር የምንላቸው ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳት ምንም ይናገሩ፤ ምንም ያጥፉ፤ በጎጠኝነቱ አተላ ሰክረን በጭፍን እንድንደግፋቸው እያደረገን ነው። ጎበዝ፥ ወዴት እየሔድን ይኾን?
 • በምድረ አሜሪካ ስደተኛ ሲኖዶስብለው የሚጠሩት፣ ነገ ከነገ ወዲያ አንድነቱን ሊያመጣ የሚችል ኹኔታ ቢከሠትስ፤ በዚኽ ምርትና ግርዱ በተቀላቀለበት ሒደታቸው እንዴት ነው ተፈላጊው አንድነት ሊመጣ የሚችለው? የሰሞኑ አሠራራቸው ልዩነቱን አጥብቆ ለማስፋት የተደረገ ሤራስ አይኾንም? በያለንበት ኾነን አደብ ግዙ እንበላቸው

*                *               *

ቀሲስ ስንታየሁ አባተ

/ደቡብ አውስትራልያ/

Kesis Sintayehu Abateእግዚአብሔር እንደ ሰው አይቸኩልም። ዝምታውም ነገሮችን ፈቅዶና ወድዶ የመቀበሉ ምልክት አይደለም። ወደ አሜሪካ ያሉት “አባቶች”፣ በቤተ ክርስቲያናችንና በሕዝባችን ላይ እየፈጸሙት ያሉትን ግፍ የቤተ ክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር ያያል። አይቶም ዝም አይልም፤ ይፈርዳል። ርስቱና ጉልቱ የኾነችውን ቤተ ክርስቲያን የነኩ የተዳፈሩ ኹሉ የት ነው ያሉት? የቆዩትንስ ትውልዱ በምን ታሪካቸው ነው ዛሬ የሚያስታውሳቸው? እኛም ከቅዱስ ዳዊት ጋር በአንድነት፣ አቤቱ አሕዛብ ወደ ርስትኽ ቤትኽ ገቡ፤ ርስትኽንም አረከስዋት እያልን እናለቅሳለን። እርሱም ልመናችንን ይሰማናል። ከሥጋዊ ከደማዊ አእምሮ በራቀ ሕሊናም እንባችንን ወደ እርሱ እናፈሳለን። እርሱም እንባችንን ያብስልናል። እግዚአብሔር ሆይ፣ በምሕረትኽ አስበን፤ ወደ ጽድቅኽም መልሰን፤ ፍርድንም ለሕዝብኽና ለቤትኽ ስጥ። አሜን።


ሰሞኑን ከወደ አሜሪካ የተሰማው ዜና ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች የመወያያ ርእስ ኾኗል። በመሠረቱ እነአባ መልከ ጼዴቅ ይህን ሠሩ ብሎ መደነቁ ብዙም አይገርምም፤ ምክንያቱም ከጥንት ጀምሮ ምን ዓይነት ዓላማ እንዳላቸው በቅርበት የሚያውቋቸው አባቶች ሲናገሩ፣ ሲያሳስቡ የኖሩት ጉዳይ ነውና። ይልቅ በቅርቡ የሰማዕያኑን ጆሮ ጭው የሚያደርግ ነገር ሊሠሩ እንደሚችሉ አስቦ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያናችንን ይታደጋት ዘንድ እግዚኦ ማለቱ ሳይሻል አይቀርም። ዐውቀው ለሚያጠፉቱ፣ እግዚአብሔር ምሕረቱን ይላክ ከማለት በስተቀር የሚባል ነገር የለም። ይልቁንስ ምእመናንን ከክፉዎች ለመጠበቅ የሚበጀውን ብንነጋገር ይሻላል።

ክርስትና፣ ጌታችን በወንጌል እንደተናገረው፣ በጠበበው በር መግባትን የምትጠይቅ እምነት ናት። ክርስትና ራስን ስንኳ ሳይቀር መክዳትን አጥብቃ የምታስተምር ሰማያዊት መንገድ ናት። በክርስትና ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን አካሔድና አስተሳሰብ ቀላቅለን እንያዝ ብንል ፍጻሜአችን የከፋ ይኾናል። አኹን ለተፈጠረው ችግርም መሠረታዊው ምክንያት እኒኽን ኹለት የማይገናኙ ነገሮችን ቀላቅለው መያዝ የሚሹ አካላት ወደ ሥልጣን መውጣታቸው ነው። የአምልኮ መልክ ያላቸው ኀይሉን ግን የካዱ ሰዎች በቤተ ክርስቲያናችን እንዲፈነጩባት መግቢያ ቀዳዳ ያገኙበትን ምክንያት በጥንቃቄ ስንመረምረው፣ ኹለት ዐበይት ምክንያቶችን እናገኛለን።

ከኹሉ በፊት፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በዘመናችን ለክህነት አሰጣጥ ያላት ትኩረት ቁጥጥር አልባ መኾኑ ነው። ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መፈጸም ካህናት አስፈላጊ ብቻ ሳይኾኑ ወሳኞችም ናቸው። ካህናት ከሌሉ አፍኣዊውን አገልግሎት እንጂ ተልዕኮ ምሥጢራትን ማከናወን አይቻልም። ማስተማር፣ ማጥመቅ፣ ማቁረብ፣ መቀደስ፣ መባረክ፣ መናዘዝ፣ ማንጻት የመሳሰሉት ያለካህናት የማይታሰቡ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችን አገልግሎቶች ናቸው። ይህ ደግሞ ካህናት የግድ የሚያስፈልጉ መኾናቸውን ያስረዳል። ይኹን እንጂ አንድ ኤጲስ ቆጶስ እጁን በአንድ ደቀ መዝሙር ወይም ተማሪ ወይም በአንድ ዲያቆን ወይም በአንድ መነኩሴ ላይ ከመጫኑ በፊት በጥልቀት ሊያስተውላቸው የሚገቡት መሠረታዊ ነገሮች አሉ።

የመጀመርያው፣ ሊካን(ክህነት ሊቀበል የቀረበው) ሰው፣ የቀናች የጸናች ሐዋርያዊት ሃይማኖት እንዳለው መመርመር ይገባዋል፤ ምክንያቱም፣ ሲሞን እንደ ተመኘው ክህነቱን ገንዘብ አድርገው የክርስቶስን ያይደለ የራሳቸውን ሥጋዊ ፍላጎት ለማሟላት እንጂ የጠፋውን ስለመፈለግ፣ የተሰበረውን ስለመጠገን፣ የታመመውን ስለመፈወስ ዓላማ የሌላቸው በርካቶች ስላሉ ነው።

ከዚኹም ጋር የምግባር ጉዳይም ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። ክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር በአንድ ወቅት በምናሳየው መላላክ፣ አገልግሎት፣ የአባቶችን ጉልበት በመሳም ወይም ለቤተ ክርስቲያን በምናበረክተው የዕውቀትና የገንዘብ ልግሥና ብቻ የሚለካ አይደለም። እንደዚህማ ቢኾን ኖሮ በዘመናችን ባለነው አገልጋዮች ዘንድ የሚታየው በመንፈሳዊነት የተሸፈነ ፍጹም ሥጋዊነት ሀገራችንንም ኾነ ቤተ ክርስቲያናችንን ባላስቸገራት ነበር። አኹን አኹን በሚዘገንን ኹኔታ በሌላ ቦታ የሌለና የማይሰማ ከቶም የማይታወቅ ኀጢአትና ክፋት፣ ተንኮልና ምቀኝነት፣ ሥጋዊነትና ዓለማዊነት አካል ነስቶና ገዝፎ የሚታየው በእኛ መንፈሳውያን አገልጋዮች በምንባለው ነገር ግን ከክፉ ሥራችን የተነሣ የእግዚአብሔርን ኀይል በካድን አስመሳዮች ነው።

ኤጲስ ቆጶሱ ለሢመት እጁን ከማንሣቱ በፊት ተሠያሚው ለዚኽች ቅድስናን ለምትጠይቅ፣ ምድራውያን ሰዎችን መላእክት ለምታስመስል ሥልጣነ ክህነት የሚያበቃው ሥነ ምግባር እንዳለው ከቀደመ ክፉ ምግባሩ ተለይቶ ከእግዚአብሔር ጋር እንደ ፈቃዱ መኖሩን መመርመር ግዴታው ነበር። ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ ልጁ ጢሞቴዎስን፣ በማንም ላይ ፈጥነኽ እጅኽን አታንሣ በማለት ያስጠነቀቀው። ሐዋርያው፣ ሳይመረምር ለሢመት እጁን የሚያነሣ ኤጲስ ቆጶስ በክፉ ሥራቸው የሚሳተፍና በኋላም በእግዚአብሔር የሚጠየቅ መኾኑን ተናግሯል። ይህ ሐዋርያዊ ምክር ሰሚ ባለማግኘቱ እግዚአብሔርን የማያውቁ አገልጋዮች በቤተ እግዚአብሔር ሊበራከቱ ችለዋል።

በአንድ አጋጣሚ ደብረ ሊባኖስ ሊሳለም ወርዶ፣ ሌሎች ሲመነኩሱ አይቶ ወይም ዓለም ውስጥ ያለውን መከራ ተሠቅቆ ወይም እጁን አለስልሶ የምዕመናንን ገንዘብ “በክህነት ዋሻ” ተሸሽጎ ለመብላት እንዲመቸው ለሚቀርበው ሥልጣነ ክህነትን እንደ ካባ ቢደርቡለት፣ ሊጸድቅበት ሊያጸድቅብት ሳይኾን ለበጎች ማጥመጃ እንደ በግ ለምድ ስለሚጠቀምበት ኤጲስ ቆጶሳቱ ቢያስቡበት ዛሬ መከራችንን የሚያበዙብን ባልበዙብን ነበር፤ ቤተ ክርስቲያንም መከራዋ ከውስጥ ባልኾነ ነበር።

ይኹን እንጂ ዛሬ ዛሬ አንዳንድ ኤጲስ ቆጶሳት ቤተ ክርስቲያንን መጠበቅ የሚለው የጵጵስናቸው ተቀዳሚ አደራ ተዘንግቷቸው ይኹን በሌላ ምክንያት፥ ነውር ነቀፋ፣ ኑፋቄና ክሕደት አለበት እያሉ ምእመናን እየጮኹ ለጩኸቱ ተገቢውን ምላሽ እንደ መስጠት በምን ታመጣላችኹ ዓይነት አካሔድ ዲቁና፣ ቅስናና ኤጲስ ቆጶስነት እስከ መሾም ደርሰው ኀዘናችንን አብሰውታል

'Aba' Wolde Tinsae Ayaleneh
አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ፤ በኑፋቄአቸውና በክሕደታቸው፣ “አይገባቸውም” እየተባሉ ከተሾሙት ፀረ አንድነትና ፀረ ቤተ ክርስቲያን አንዱ፤

“ ቤተ ክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ የጸጋው ግምጃ ቤት ናት። ዛሬ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋና ክብር የማይታይባቸው አስመሳይ የሐራ ጥቃ መናፍቃን በመንፈሳዊቷ ቤተ ክርስቲያን ሲሣልቁ ከመመልከት በላይ ልብን የሚያሳዝን ነገር የለም። ዛሬ ላይ፣ በተለይም በቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን፣ የቅዱስ አቡነ መቃርስን አስኬማ፤ የቅዱስ አቡነ አትናቴዎስን ካባ ለአርዮስ ሲሰጡት ተመልክተናል። እግዚአብሔር የሚዘበትበት አምላክ አይደለም። ሰው ኹሉ የዘራውን ያጭዳል። ዛሬ ቤተ ክርስቲያን እንደ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ጽሕሙን የሚነጭላት ጥርሱን የሚነቀልላት እንጂ በሥጋ ሐሳብ እንደ ኤልያብ የሚኩነሰነሰውን ቤተ ክርስቲያን አትፈልግም።” (መ/ር ዳንኤል ግርማ፤ በ፴፱ኛው የሰሜን አሜሪካ ፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጥምረት የስልክ ጉባኤ ላይ ከሰጡት ትምህርት)


አንድ ኤጲስ ቆጶስ ብፁዓት እጆቹን ለሢመት በአንድ ሰው ራስ ላይ ከማኖሩ በፊት ያ ተሿሚ ክህነትን መቀበሉ፥ ለምን፣ ለየትኛው አጥቢያ፣ በምን አገልግሎት፣ በምን ደመወዝ እንደሚመደብ በጥሞና ሊመረምር ይገባዋል። ይህ ማለት በኣት አልባ መነኩሴ፣ ደብር አልባ ቄስ አይኖርም ማለት ነው። አንዳንድ ኤጲስ ቆጶሳት ጵጵስናቸው በሾሟቸው ዲያቆናትና ቀሳውስት ብዛት የሚለካ ይመስል በሔዱበት ቅዱሱንና ሰማያውያን መላእክት የሚያስመስለንን ክህነት ለአላፊ ለአግዳሚው ሲናኙ ይስተዋላሉ።

ይህ የክህነቱን ክብር ይቀንሳል። ካህናቱ የሚያገለግሉበት ደብር ሲያጡ ወደ አንዱ እንዲፈልሱ፣ በሔዱበትም የሚያስጠጋቸው ለማግኘት ሲሉ በሓላፊነት ወንበር ያለውን ሕሊናቸው እየወቀሳቸውም ቢኾን እያወደሱ፤ የልብ ትርታውን እያጤኑ እግዚአብሔር የሚወደውን ሳይኾን “አለቃው” የሚወድደውን እየተናገሩና እየሠሩ እንጀራን እንዲበሉ በሒደትም ቤተ ክርስቲያኒቷን መልሰው “እንዲበሏት” ያደርጋቸዋል። በሀገረ አሜሪካ በአኹኑ ጊዜ እየተስተዋለ ያለው እውነታም ይኸው ነው።

በሐዋርያቱ ቀኖና በፍትሐ ነገሥቱም እንደተደነገገው፣ ካህናቱ ኹሉም ቦታ ተሰጥቷቸው እንዲያገለግሉ ቢደረግ፣ ኤጲስ ቆጶሳቱም በየአህጉረ ስብከታቸው የካህናት እጥረት አለብን ይሹምልን፤ በዚኽ በዚኽ መልኩ እናስተዳድረዋለን የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው ብቻ ቢሾሙ ከላይ የተገለጡት በኣት አልባ መነኮሳት፣ ደብር ኣልባ ቀሳውስት አይበዙም ነበር። ከዚኽ በተጨማሪም “ገለልተኛ” ለሚባለው ወገን መፈጠር በር ባልተከፈተም ነበር።

ኹለተኛው ዐቢይ ምክንያት ደግሞ፤ ከምዕመናን ጋር የሚገናኝ ነው። በዓለማችን ላይ ምንጊዜም ቢኾን መንፈሳዊውና ሥጋዊው አስተዳደር ጎን ለጎን መሔዳቸው አይቀርም። እነዚኽ ኹለቱም አካላት አገልግሎታቸውም ግባቸውም ይለያይ እንጂ ተፈጻሚነታቸው በሕዝብ ላይ ነው። መንግሥት ያለሕዝብ አይኖርም። አካለ ክርስቶስ የኾነችው ቤተ ክርስቲያንም ሕዝብ ከሌለ በሰማያውያን ኅብረት ብቻ ትወሰናለች። ስለዚህ ኹለቱም አካላት ሕዝብን ይፈልጋሉ። በዚህ ሒደትም አንዳንድ ጊዜ አንዱ በሌላኛው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ አይቀርም።

በ313 ዓ.ም ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ የቤተ ክርስቲያንን ነፃነት ካወጀ ጊዜ ጀምሮ እውነቱን ብንነጋግር ቤተ ክርስቲያን በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ ከመንግሥታት ተጽዕኖ ነፃ ኾና አታውቅም። የተነሡትና የሚነሡት ነገሥታትና መሪዎች ይፈልጓታል። ለበጎና ለመልካም ግን አይደለም። እርሷን እንደ መረብነት ተጠቅመው በጉያዋ የተሰበሰቡ ምዕመናንን ለማጥመድ እንጂ። እነዚህ ሰዎች ከልካቸው አልፈው እጃቸውን እስከ መቀደሱ ድረስ ያስገቡበት ዘመንም ነበር። መለካውያን ጳጳሳት ማለት የነገሥታቱን ፈቃድ የሚፈጽሙ ጳጳሳት በክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ላይ መሾማቸውን የአራተኛውና የአምስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል።

ሕዝቡ እዚህ ላይ መሠረታዊ የኾነ ግንዛቤ ሊይዝ ይገባል። ማንኛውም ሕዝብ አንድን መንግሥት መቃወምም ኾነ መደገፍ መብቱ ነው። ከመንግሥታት ተጽዕኖ ተላቅቃ የማታውቀውን ቤተ ክርስቲያንን ደግሞ ከመንግሥታቱ ወይም ከመራሔው ቡድን ጋር አንድ አድርጎ መፈረጅ ደግሞ ጤናማነት አይኾንም። አባቶች በግልጥ መንግሥትን ተቃውመው ለምን ሰማዕትነትን አልተቀበሉም ማለትም ፍትሐዊነት አይደለም። በተለይ ከሀገር ውጭ በምንኖር ሰዎች ይህ ቃል ሲነገር ስንሰማ፤ እኛስ ለምን ሀገራችንን ተትን ወጣን የሚል ጥያቄ ያስነሣል፤ ወይስ ሰማዕትነት የተሰጠው ለጳጳሳቱ ብቻ ነው? የሚል ጥያቄም እንዲነሣ ያደርጋል።

አሜሪካ ያሉት አባቶች ይህቺን የሕዝቡን ጉርምርምታ ለዓላማቸው በሚገባ ነው የተጠቀሙባት። በኢትዮጵያ ምድር ያሉ አባቶች በሙሉ የገዢው ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እንደኾኑ በማስመሰል በመንግሥት ላይ ጥያቄና ጥላቻ ያለው ኢትዮጵያዊ ኹሉ በሀገር ቤት ባሉ አባቶች ላይ ጥላቻና ነቀፌታ እንዲኖረው፣ ቢመርረውም የእነርሱን ጥፋት እንዲቀበል እያደረጉት ነው። እንዲኽማ ባይኾን ኖሮ ኑፋቄአቸውና ክሕደታቸው ከዳር ዳር የወጣ ሰዎች ወደ ከፍተኛው የቤተ ክርስቲያን ሥልጣነ ክህነት ሲመጡ ዝም ብሎ ባላያቸው ነበር።

ውድ ምዕመናን፣ ሃይማኖተኝነት ከማስተዋል ጋር ሲኾን ነው ፍሬያማ የሚኾነው። የጠላነውም ኾነ የደገፍነው፣ ፖለቲካ እና ፖለቲከኞች ኀላፍያን ናቸው፤ ደግሞም ምድራውያን ናቸው። በፖለቲካው ዓለም የነበሩ መሪዎች ቤተ ክርስቲያንን ፈርጣማ ክንዳቸውን አሳርፈውባት ሊያደቋት በብዙ ሞክረው ነበር፤ ነገር ግን ኹሉም እንደየአመጣጣቸው አልፈዋል፤ አኹን ያሉትም እንደዚያው ያልፋሉ። ቤተ ክርስቲያን ግን ትኖራለች።

ፖለቲካውን ተጠግቶ ጥላቻንና መለያየትን እየዘራ ያለው ክፉው መንፈስ፣ ማስተዋላችንን ነሥቶን የሰላም፣ የዕርቅና ወደ ሰማዩ ርስታችን መግቢያ ደጅ ከኾነችው እናት ቤተ ክርስቲያን እየለየን በጥምቀተ ክርስትና የተቀዳጀነውን ክብር፤ ያገኘነውን ሰማያዊ ልጅነትና የማይጠፋ ዘር ሳይኾን ጎጥና መንደር እያስቆጠረን ነው። ጎጠኝነቱ ከፖለቲካው አልፎ በቤተ ክርስቲያናችን ጭምር ዙፋኑን ዘርግቶ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷ አስተምህሮ ምን ይላል፤ ሳይኾን የእኛ ወገንና ዘር የምንላቸው ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳት ምንም ይናገሩ፤ ምንም ያጥፉ፤ በዘረኝነቱ አተላ ሰክረን በጭፍን እንድንደግፋቸው እያደረገን ነው። ጎበዝ ወዴት እየሔድን ይኾን?

በጎጠኝነትና በፖለቲካ ደጋፊነትም ሆነ ተቃዋሚነት ጽንፍ ይዘን ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን በቀጥታም ይኹን በተዘዋዋሪ በማፍረስ ላይ የምንገኝ ምዕመናን፣ ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ ጳጳሳት በሙሉ፤ ኹሉን ያሳልፍ ዘንድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ቀን ባላሰብንበት ሰዓት በክብር ይገለጣል። በርግጠኝነት በዚያን ዕለት ፖለቲካውም ኾነ ጎጠኝነቱ አይታደገንም። በእግዚአብሔር መንግሥት ለዘረኞችና ለጎጠኞች ዕድል ፈንታ ጽዋ ተርታ የላቸውም። ይህ የእግዚአብሔር እውነት ነው።

በመኾኑም ምዕመናን አንድ ነገር በውል ልናጤንና ለተግባራዊ መፍትሔው መፋጠን አለብን። በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ የቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እግዚአብሔር በሰጠን አእምሮ በጥልቀት አስበን እንወያይ። የትላንትናው የአባቶች መከፋፈል እነማንን ነው የጠቀመው? ማንንስ ነው ያስደሰተው? ሀገር ውስጥ ያሉትና በውጭ ያሉት አባቶች የልዩነቱን ድልድይ ሰብረው ወደ አንድነት ይመጣሉ ብለን ተስፋ እያደረግን ባለንበት ወቅትስ ኤጲስ ቆጶሳት መሾም፤ ለዚያውም በኑፋቄያቸው ሀገር ያወቃቸውን ፀሐይ የሞቃቸውን ሰዎች ሳይቀር ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሥልጣን ማምጣት ትርፉ ምን ይኾን?

በምድረ አሜሪካ የሚገኙና ራሳቸውን ስደተኛ ሲኖዶስ ብለው የሚጠሩት ነገ ከነገ ወዲያ አንድነቱን ሊያመጣ የሚችል ኹኔታ ቢከሠትስ ከዚኽ ምርትና ግርዱ በተቀላቀለበት ሒደታቸው እንዴት ነው ተፈላጊው አንድነት ሊመጣ የሚችለው? ይህ የሰሞኑ አሠራራቸው ልዩነቱን አጥብቆ ለማስፋት የተደረገ ሤራስ አይኾንም?

በያለንበት ኾነን የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት አደጋ ውስጥ ሊያስገቡ ቀን ከሌሊት የሚሮጡ አካላትን አደብ ግዙ እንበላቸው። በማወቅም ይኹን ባለማወቅ የቤተ ክርስቲያናችንን መሠረተ ሃይማኖት ለመናድና የመናፍቃኑን የዘመናት ምኞት ለመፈጸም ከሚተጉት ራሳችንን እናርቅ። እኛ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ከቅዱሳን አበው ተቀበልናት እንጂ አልመሠረትናትም። የተቀበልናትን ደግሞ ከነሙሉ ክብሯ ለቀጣዩ ትውልድ የማስረከብ ሰማያዊ አደራና ግዴታ አለብን።

በመኾኑም በተለያዩ የምድር ማዕዘናት የምንገኝ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት፤ በኢትዮጵያም በአሜሪካም ያሉት፣ በየዓመቱ በመግለጫቸው፥ የሰላም ውይይቱ እንዲቀጥል ብለው ያሰሙንን የመግለጫ ቃል አክብረው ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ይፋዊ ጥያቄያችንን እናቅርብ። በያለንበትም ተሰባስበን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት ከመጸለይ በተጨማሪ ዓላማ ያለው አንድነት ፈጥረን፣ ያዕቆብ ካልባረከኝ ብሎ እስኪነጋ እግዚአብሔርን እንደታገለ፣ እኛም አንድ ካልኾናችሁ፤ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅምና ክብር ስትሉ የጥል ግድግዳውን ካላፈረሳችኹ አንለቃችኹም እንበላቸው። ከኹሉ በፊት ግን እኛ ራሳችን የጉዳዩ አሳሳቢነት ይሰማን። ይቆጨን። ለኹሉም እግዚአብሔር ይርዳን።

Advertisements

23 thoughts on “ሳይመረምር በፖለቲካና በጎጠኝነት የሚሾም፥ በክፉ ሥራ ይሳተፋል፤ በእግዚአብሔርም ይጠየቃል፤ በሀገረ አሜሪካ የሚስተዋለው እውነታ

 1. Asmamaw June 22, 2016 at 10:20 am Reply

  እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንን የሚጠብቅ ጠበቃ ከአሕዛብ እንኳን ሳይቀር ያስነሳል፡፡ ነገር ግን እኛ እንድንጠብቃት እርሱ ይርዳን!!!

  • Anonymous June 22, 2016 at 12:35 pm Reply

   ብቻ እግዚኦ ነዉ

 2. Anonymous June 22, 2016 at 1:15 pm Reply

  አንዳንድ ጊዜ “የተሰደደው” ሲኖዶስ ባይኖርና እንዲህ ባይበዛ ሀገር ቤት ያሉት አባቶች እንዴት አድርገው ዲያስፖራውን ያገለግሉ ነበር ብዬ ሳስብ ግርም ይለኛል፡፡ በሀገር ቤት ያሉት እኮ አሁን እንኳን የሚያስቡት ስለ ሥልጣን (እንደራሴ) እንጂ ስለ አገልግሎት መች ያወሩና፡፡ ቀሲስዬ እንዲህ ዓይነት ነገር አይስማማዎትም

 3. Anonymous June 22, 2016 at 1:48 pm Reply

  ተሳቆ ማለቅ ሆነብን

  /Mebrud Tsige/

  እንዳንተቻችሁ አገባባችን አይደለም ብለን
  እንዳንናገራችሁ እኛስ ከእናንተ ምን የተሻለ ነገር አለን ብለን
  እንዳንኮንናችሁ እኛስ የሥጋ ፍላጎታችንን መች ገታን ብለን
  እንጂ
  አሜሪካ ተኮኖ የሚደረገው ነገር አሸማቆ ሊገለን እንደሆነ እወቁት

  ፓትርያርክ ይሰደዳል ብትሉ እንደእናንተ አመክንዮ በክፉ ጊዜ መሰደድ በደጋግ አባቶች እንደደረሰ ጠፍቶን ሳይሆን አገር ቤቱ አሳዳጅ አይደለም ብለን የምንልበት ሞራል ብናጣ እየጨነቀን ዝም!! ደግሞስ አገርቤት ያሉትስ ፕትርያርክ(ያለፉትም ተከታዩም) መች በምእመናን ቅቡል የሚያደርጋችው መንፈሳዊ አስተዳደር ተገበሩ ? ብለን ዝም!!
  ሲኖዶስ እናቋቁም ስትሉ ሲኖዶስ እንደማይሰደድ አታቁም ብለን ሳይሆን መቼስ መመለሻው ጭንቅ ቢሆንባቸው ይሆን ? ብለን ዝም
  ጳጳሳት ስትሾሙ ይደልዎ ብለን ሳይሆን ለእርቅ እንቅፋት እንዳይሆን ብለን እያዘንን ዝም!!
  አሁን ጭራሽ እርቁ እንኳን ቢፈጠር ለአንድነት ሲባል ብለን ልንቀበላቸው የማንችላቸውን እንደ አባ ወልደትንሳኤ ያሉትን ሾማችሁ ፡፡እልህ ምላጭ ያስውጣል ካልሆነ በቀር ምን ሊባል ይችላል? አሁንስ ዝም ይባል ?

  ሌላውን በምትኮንኑበት ግብር ዘረኝነቱንም ሆነ ሕግ አፍራሽነቱን ምንፍቅናዉን ሆነ አማሳኝነቱን በአሜሪካ ስታንዳርድ አሻሽላችሁ አደረጋችሁት እንጂ ከአገር ቤቱ የተሻለ መንፈሳዊ አስተዳደር ያሳያችሁት ነገር የለም ፡፡
  ደግሞ በዚህስ መች ትቆማላችሁ፡፡ ሲኖዶሳችሁን ማስፋትና ማጠንከር ካለባችሁ ቀጥ ያለ ስታጡ ጎባጣውን እየሾማች ከድጡ ወደማጡ መገስገሳችሁ አይቀር፡፡ ደጋጎች መነኮሳት መቼስ ለስጋ ፍላጎትና ለፍትፍት ብለው አሜሪካ አይሰደዱ!! ፊቴ ይቅላ ደረቴ ይሙላ ያለና ያኮረፈ ነው ሄዶ ጵጵስና ከሞቀበት አሜሪካ የሚሾመው፡፡ የተሐድሶ መናፍቅ ዘማሪና ሰባኪ እዚ አገርቤት ሲጨንቀው እየሾለከ እየመጣ ነው በሉ በየሀገረ ስብከቱ ጵጵስና ሹሙ፡፡

  እንዲህ ደፍሮ መናገር የሚያስችለን ነገር ደግሞ አለ፡፡ ይኸውም የአሜሪካ ስደት ፍቅርና ምኞት በሁላችን ልቡና ውስጥ አለና እናንተን ብቻ ኮንነን ራሳችንን ጻድቅ አናደርግም፡፡ ምናልባትም ስላልተሳካልን ብቻ አገር ቤት የቀረንና አሜሪካን የምናክፋፋ ልንኖር እንቻላላን፡፡ ግን ይቺ የስጋ ፍላጎታችንን አምነን እንኮንናታለን እንጀ ምክንያት እያበጀን ለድክመታችን ሌሎችን ብቻ ተጠያቂ እያደረግን እናመልጥም፡፡ ለነፍሳቸው ያደሩትማ እንኳን አሜሪካ አዲስአባንም ይንቋታል ይመንኗታልም፡፡በየገዳማቱና አብነት ትምህርት ቤቱ ወንበራቸውን ላላማጠፍ ጉባኤ ላለመስታጉል ምዕመናን እንዳይበተኑ በአት አጽንተው ችግሩን ተቋቁመው ያሉ ስንት አሉ፡፡ይህ ሲባል ባህር ማዶ ያለውን አገልግሎትና አገልጋይ መናቅም ማጣጣልም አይደለም፡፡ በተገባና በሥርዓት አለመሆኑ እያሳዘነን እንጂ፡፡አርአያ ክህነታቸውን እንደጠበቁ አሜሪካን በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ሊቃኟት የሚጋደሉ እንዳሉ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ለአገርቤቱም ተስፋ የምናደርጋቸው አሉ ዋጋቸውን አያስቀርባቸው፡፡

  ስንጠቀልለው እንግዲህ ምን እንላለን ያሳዝናል ያስለቅሳል ለሁላችንም ልቡና ይስጠን ከማለት ውጪ ምን ይባላል ?ለእርቅ ለሰላምና ለአንድነት ያለንን የቀጠነ ተስፋ ቆርጦ ለመበጠስ ሰይጣን እያቻኮለንና እየገፋን እንዳለ እንዳናስተውል አዚም ተደርጎብናል፡፡
  እንዲህ ልባችንን እንዳደነደንን እስከመቼ? እግዚአብሔር ይቀጣል አይተናልም ግን እድሜ ለንስሐችንን ብንጠቀምበት ምናለ፡፡እያቻኮለንና እየገፋን እንዳለ እንዳናስተውል አዚም ተደርጎብናል፡፡
  እንዲህ ልባችንን እንዳደነደንን እስከመቼ? እግዚአብሔር ይቀጣል አይተናልም ግን እድሜ ለንስሐችንን ብንጠቀምበት ምናለ፡፡

 4. Anonymous June 22, 2016 at 2:08 pm Reply

  የማንታወቅ ይመስለን እንጂ ብዙዎች ያውቁናል።
  2ኛ ቆሮ 6:9

  ጵጵስና መንፈሳዊ ክብርን የሚያጎናፅፍ ከፍተኛ መንፈሳዊ ማዕረግ ቢሆንም አስተዋይነትን፣ ብልኅነትን፣ ቅንነትን፣ ቅድስናን እና ንፅህናን አጣምሮ መያዝን የሚጠይቅና ከሥልጣን ይልቅ ለእግዚአብሔር ታዛዥና ተገዥ ሆኖ በመገኘት ከብዙ ውጣ ውረድና ፈተና በኋላ የሚገኝ ከባድ ኃላፊነት ነው።

  ብልኅ እና አርቆ አስተዋይ የሆኑ ሰዎች ለሹመትና ለሥልጣን የማይሽቀዳደሙትም ለዚሁ ነው። በዚህ በኩል ቤተክርስቲያናችን አኩሪ ታሪክ አላት። ይህ አኩሪ ታሪክ ከሐዋርያት የተወረሰ ባህል ነው። ሐዋርያት ተተኪዎቻቸውን የሚመርጡበት ራሱን የቻለ መንፈሳዊ ሥርዓት ነበራቸው። ይህ የሐዋርያት ሥርዓት በዓለም ላይ ከሚታየው “የዲሞክራሲያዊ አሠራር” በእጅጉ የተሻለ ነበር።

  ለምሳሌ ያህል አንድ ሁለት ማስረጃዎችን እንመልከት። በሐዋርያት ዘመን ስብከተ ወንጌሉ እየተስፋፋ መጥቶ የክርስቲያኖች ቁጥር እየበዛ በመጣበት ጊዜ መንፈሳዊ ተልእኮውን በሚገባ ማከናወን ይቻል ዘንድ ከአበው ሐዋርያት ጋር በመሆን የሚያገለግሉ ተጨማሪ ዲያቆናት(ደቀ መዛሙርት) መሾም እንዳለባቸው ታመነበት። በወቅቱ ሐዋርያት ራሳቸው “እገሌ” ብለው ለመምረጥ የሚያስችል መንፈሳዊ ብቃት ነበራቸው ነገር ግን አሠራሩ ፍትሐዊ እንዲሆንና ከሁሉም በላይ ሕዝቡ ያመነባቸውን ለማስመረጥ በመፈለግ ተከታዮቻቸውን:–
  “ከእናንተ ወገን በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብ የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ምረጡ ለዚህ ሥራም እንሾማቸዋለን” ሐዋ 6:3 ባሏቸው መሰረት እስጢፋኖስን ጨምሮ ሰባት ዲያቆናት ተመርጠው ተሾሙ።

  ሐዋርያት ከቀጥታ ምርጫ ሌላ የአመራረጥ ዘዴም ይጠቀሙ ነበር። ይህም በጸሎት የሚከናወን ሥርዓት ነበር። ለምሳሌ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል ይሁዳ በገዛ ክፉ ስራው ጌታውን በመሸጡና በመጥፎ አሟሟት ከሞተ በኋላ ሐዋርያት ተሰባስበው በምትኩ ሌላ ሐዋርያ ሊተኩ ፈለጉ። በእነርሱ እምነት ይሁዳን ሊተኩ ይችላሉ ወይም ደግሞ ከባዱን የሐዋርያነት ቀንበር ሊሸከሙ ይችላሉ ያሉዋቸውን ሁለት ደቀ መዛሙርት (ዮሴፍንና ማትያስ) ነበሩ። ይሁንና ከሁለቱ መካከል እገሌ ብለን ከምንመርጥ የሁሉን ልብ የሚያውቅ መንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ሁኔታውን ይገልጽልን ዘንድ ሱባኤ እንግባ ብለው የጋራ ጸሎት ጀመሩ።

  በመጨረሻም እግዚአብሔር በገለጠላቸው አሠራር መሠረት በሁለቱም ላይ ዕጣ አጣጣሉ። በወጣው ዕጣ መሠረትም ማትያስ ዐሥራ ሁለተኛ ሐዋርያ ሆኖ ተመረጠ (ሐዋ 1:22–26)።

  ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው አበው ኢትዮጵያውያንም ከመካከላቸው አበምኔት አልያም ኤጲስ ቆጶስ ለመምረጥ ሲፈልጉ ከላይ የተጠቀሱትን የምርጫ ዘዴዎች ነበር የሚጠቀሙት።
  ለሹመት የሚታጨው አባትም ቢሆን ለምርጫ (ለውድድር) ከመቅረቡ በፊት መጽሐፍ ቅዱስ በሚያዘውና አበው በደነገጉት ሕግ መሠረት:–
  *ጭምት
  *ቃሉ የማይለወጥ
  *የወይን ጠጅ መጠጣት የማያበዛ
  *ከንቱ ትርፍ የማይወድ
  *የሃይማኖት ምሥጢር የሚጠብቅ
  *የማይኮራ
  *የማይቆጣ
  *የማይጨቃጨቅ
  *እንግዳ የሚቀበል
  *ጻድቅና ቅዱስ የሆነ
  *ራሱ ተምሮ ሌሎችን ማስታማር የሚችል
  የመሳሰሉትን መስፈርቶችን ያሟላ መሆን ነበረበት (1ኛጢሞ 3:7–8 ፣ ቲቶ 1:7–9)።

  ለኃላፊነት የታጨው አባት በበኩሉ “ትሾማለህ” ሲባል “እኔ ለዚህ ኃላፊነት ብቁ አይደለሁም” ሲል በትሕትና ይመልሳል። ይሁን እንጂ አባቶች በጋራ ሱባኤ ይዘው እግዚአብሔር ሲገልጽላቸው ወይም ደግሞ በጋራ ሆነው በሚጸልዩበት ፣ በሚሰበሰቡበት ሰዓት እርግብ መጥታ ከታጩት መካከል ካረፈች ሹመቱ ከእግዚአብሔር የመጣ ጥሪ መሆኑ ስለሚታወቅ የተመረጠው አባት ኃላፊነቱን በትጋት ለመወጣት ቃል ገብቶ ሥራውን ይጀምራል።

  ዛሬ ግን የጥንቱ የአበው ሥርዓት ተረስቶ (ሆን ብሎ ተዘሎ) የአበው ምርጫ ዓለማዊ ቅርጽና ይዘት እየያዘ መጥቷል።
  በግላጭ “እኔን ምረጡ፣ እኔ እንድመረጥ አርዱኝ፣ አግዙኝ” እያሉ ግልፅና ስውር ዘመቻ የሚያካሂዱ “መነኮሳት” በተደጋጋሚ እያየን እያስተዋልንና እየታዘብን ነው።

  ትሾማለህ ሲባሉም ዛፎች ተሰብስበው እሾህን
  “መጥተሽ በላያችን ንገሺ” ሲልዋት
  “በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሳችሁኝ እሳት ከእሾህ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ” እንዳለች ሁሉ ውስጣቸውን ሳይፈትሹ ለሥልጣን በመጓጓት ብቻ በፍጥነት እንደ እሾህ እሺ የሚሉ፣ ከተሾሙ በኋላም የደስ ደስ ድግስ የሚደግሱ ሆነዋል።

  በተቃራኒው ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬም የጥንቱን የአበው መንገድ ተከትለው ወይንነታቸውን ሳያስደፍሩ፣ በወይራነታቸው እንደኮሩ፣ የበለስ ጣፋጭነታቸውን እንዳስከበሩ የሚገኙ አባቶች አሏት።

  ይሁን እንጂ ከጊዜ ወደጊዜ የዶጎቹ (እሾሆቹ) ቁጥር እየበዛ በመምጣቱ አሁን አሁን እያየነው እንዳለ ከዶግ የሚወጣ እሳት ዝግባዎችን ማቃጠል ጀምሯል ፤ የምናምንቴዎች የዶግ(የእሾህ) ዘመን ደርሷል እንበል ይሆን?

  “እሾህ በወጋኝ ጊዜ ወደ ጉስቁልና ተመለስኩ”
  መዝ 31:4/Miheret Yaregal/

 5. Anonymous June 22, 2016 at 2:13 pm Reply

  ቄሱ ምን ነካዎት እንኳንስ እነኚህን የመሰሉ በቃለ እግዚአብሔር የበሰሉ አባቶች ቀርቶ እርስዎ አንድ ቀን እንኳን ሳይቀድሱ ባልተማሩትና በሌለዎት ቅድስና ቄስ ተብለው የለም እንዴ እኔ አባቶችን ብሆን መጀመሪያ የርስዎን የምእመኑን ስልጣን ነበር የምነጥቀው አሁን እርስዎ እነ አባ ወልደ ትንሳኤን(አቡነ በርናባስን) የመሳሰሉ አራት አይና ሲተቹ አያፍሩም ማፈሪያ ነዎት።

 6. Anonymous June 22, 2016 at 7:52 pm Reply

  ሐራዎች አናንተ የደገፈ ፃድቅ ያልደገፈ ኃጢአተኛ አረተው

 7. Anonymous June 22, 2016 at 9:04 pm Reply

  አናዝናለን ስደቱ የሚቆመው መለያየቱ የሚበቃው ወረኞች ንስሀ ሲገቡ ነው የተለያየነው ከእግዝአብሔር ሰለተለያየን ነው !!!!!!!!!!

  ንስሐ እንግባ

 8. Anonymous June 23, 2016 at 4:13 am Reply

  ቀሲስ ስንታየሁ ፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን።

  አባቶችን የንስሐ ዘመን ይስጥልን።

 9. ሳምሶን June 23, 2016 at 7:50 am Reply

  ይህን የፃፍክ ከውሻ አትሻልም።

 10. Samson June 23, 2016 at 7:56 am Reply

  ውሻ ነህ አባቶችን ባለማክበርህ

 11. petros June 23, 2016 at 10:21 am Reply

  Kissis, your are nonsense. Please, stop your negative attitude from Orthodox fathers. Aba Wolde, now his holiness Abune Barnabas is a true Christian living by Christ of Jesus.

 12. Anonymous June 23, 2016 at 11:19 am Reply

  ካካካ… አቦ እናንተ ክርስቲያኖች… ታስቁኛላችሁ፡፡

 13. Anonymous June 23, 2016 at 12:02 pm Reply

  ቀሲስ ስንታየሁ በመጀመርያ ስም ያወጡልህ አናትህን ሳላመሰግግን አላልፍም ስንት አየን ካየናቸው ነገሮች አንዱ አንተ ነህ ቆርጦ ቀጥል ዉሸታም የሚያውቅ ያውቅሃል ለማያውቅህ ግን ለቤት ክርስትያን ሕግና ሥርዓት የተቆረቆርክ ለኣአመሰል ሞክረሃል ይሁን ዘመኑ አንዳንተ ዓይነት ቀዳዳ ስሚ የሚያገኝበት ዘመን ስለሆነ የብዙዎቻችሁ ችግር ዘረኝነት አንደሆነ በደንብ መረዳት ይቻላል በኢትይዮጵያ ዉስጥ ለሃያ አምስት አመታት ጎንደሬው አንደ ኢትዮጵያዊ ሳሆን ከዜግነት በታች ወርዶ በየአጥብያ አብያተ ክርስቲያናት ማሳደድ ማጥፋት ጎንደሬነት አንደወንጀል አድርጋችሁ ደከማችሁ በዚህ ምክንይት ስደት አማራጭ የሌለው መፍትሔ በመሆኑ አድል ያገኙት ትንሽ የማይባሉ ካህናት በሀገራቸው የሚደርስባቸውን ግፍና መከራ ለመሸሽ ከናንተ አጂ አግዚአብሔር አውጥቶቸው በሰው ሀገር ክብር አንዲያገኙ ያደረገው አምላክ ክብር ምሥጋና ይግባው አናንተማ የዉጭውን ሲኖዶስ ሽባ ለማድግ ደከማችሁ ግን ምንም አድርጉ ምን አትችሉም ምክንያቱም አግዚአብሔር ጸጋውን አብዝቶ ባርኮቸዋል የማታፍሩ ጉድች ለ25ዓመትት ብዙ ኤጲስቆጶሳት ሲሾሙ አናንተ ከምትጠሉት ብዙ ሊቃውንት መንኮሳት ሀገር ሰው ጠፍቶ ነው ያልሾማችሁት ነው የምትናፍቋቸው የጥንት ግብጾች አንዳሉት ከሊቃውንቶቻቸው ውስጥ ጎንደሬዎች አንዳይሾሙ ብላችሁ ወስናችኋል ?
  ጎጠኞች አናንተ ናችሁ አናንተን በመፍራት ያላችሁን ጸረ ጎንድር ሕዝብ ብዙ ሊቃውንት የተወለዱበትን ቦታ በመቀየር ወሎ ጎጃም ሸዋ ትግሬ አያሉ አንደሆነ ልንገርህ ታዲያ ዘረኞች አሳዳጆች ስትሆኑ አንዴት ሌላውን በኢትዮጵያዊነቱ የሚያምነው ሕዝብና አባቶቹን በዘረኝነት ልትከሱ ፈለጋችሁ ?
  አናንተ አኮ አቡነ ጳውሎስንም ሆነ አቡነ ማትያስን አንዴት ለምን አንደተቀበላችሁ ሁሉም ያውቀዋል ምድረ ፈሪ ሁሉ ወንድ ከሆንክ የወጡት አባቶች ፈሪ ስጋዊ ሆኑ ትላለህ አስቲ አንተ ሃይማኖተኛው ትክክል ያልሆነውን ነገር ተቃወም አና ሰማዕት ሁን ከዝያ በኋላ አንከተልህ ኣለቅላቂ ሁሉ ኣታለቅልቅ ምንም አታመጣም

 14. Gebre Hiwot G June 23, 2016 at 12:32 pm Reply

  see things in detail before say something

 15. Seife June 23, 2016 at 3:24 pm Reply

  Hi kisses Sentayehu this is seife from Hanna Mariam Sunday school. Now I live in Canada calgary Alberta. I need your sprtual advice and pray. Can you cantac me please.

 16. Anonymous June 23, 2016 at 5:58 pm Reply

  Sentyhu tegrmalhi selmawkhi bedbe Anit endhi.yemetlbet semit yelhme.meknyatum Abatchi hoy begzi matl.demo metchi yekbedal kewskam Awkhi Alhu erdat kisis hune.enkuane beyt endmewta.tawkalhi gene anetme.kahne negi belhi Abatchne settchi yegermal kzhi yedrsku beyt arghi edhone takalhi yeshi dnzhi belhi tekekel negi elalhu fetar fekdo Etho betmta eskagihi nafkogal yshi gene

 17. Anonymous June 23, 2016 at 7:31 pm Reply

  ይሉሽን ብትሰሚ ገበያ ባልወጣሽ።

  ሰውን ለማሳሳት ብትጽፉ ብትገጥሙ፣
  ውሸት እውነት ላይሆን በከንቱ አትድከሙ፣
  እውነትን ለማወቅ ከተዘጋጀላችሁ፣
  ረጋ በሉና አስቡ እባካችሁ።

  ገሃድ የሆነውን ግልፅ የሆነ ሥራ፣
  እናት ቤ/ክርስቲያን መልምላ አበጥራ፣
  ሊቃውንት ልጆቿን ስትሾም አክብራ፣
  ማመስገን ሲገባን የፈጣሪን ሦራ፣
  ለምን አይቀፈንም ሀሰት ስናወራ።

  ይልቅስ እናስብ ሃይማኖት ካለን፣
  እውነት እንናገር ስም ማጥፋቱን ትተን።

  አስበን ከሆነ እንደማንታወቅ፣
  እንወቅ በቅድሚያ የለም የሚደበቅ፣
  አንዱ ሰው ስላንዱ ቀድሞ ከመናገር፣
  እኔን ማን ይሉኛል ብሎ ነው መጠርጠር።

  ዘረኛው ያወራል ዘረኞች እያለ፣
  ሁሉ እያወቀበት በዘር የታለለ፣
  ዘረኛ እንደሌለ እርሱን የመሰለ።

  ብርሃኑን ጨለማ ጨለማውን ብርሃን፣
  ለምን ትላላችሁ ክዳችሁ እውነቱን፣
  መመስከር ሲገባ እውነት የሆነውን።

  ልቡና ይስጣችሁ ኃያሉ ፈጣሪ፣
  መሆን እንድትችሉ እውነት ተናጋሪ፣
  ጽድቅ የለውምና ለነገረ ሠሪ።

 18. Anonymous June 24, 2016 at 12:39 am Reply

  Betam new yemiasazinew andu yandun hatiat kemiwera esti hulachin hatiatachin eyasebin nisiha engiba eskemeche dires bemenekakef eninur Egziabher yikir ybelen yewuket melekia aydelem zimbilo sewun mewengel erasachin enyew megemeria ebakachihu betecristianitun asalifen ansitat lebaedan hulachin wedr Rgziabher binichoh erasu yastekakilatal chigiru man gar endale yemiawuk esu bicha new

 19. Temesgen June 24, 2016 at 12:43 pm Reply

  ቀሲስ ስንታየሁ፤ ለመሆኑ ላንተ የፍርድ ስልጣን የሰጠህ ማን ነው ሲኖዶስ አይሰደድም እያልክ ስትዘባርቅ አልነበረም ወይ! አረ ለመሆኑ አንተ ውሸት ተናጋሪ የዲያብሎስ ልጅ (ዮሐንስ ፰፤፵፬) አባ ወልደ ተንሣኤን የመሰለ የወንጌል አርበኛ በክርስቶስ ወንጌል ከስሜን አሜሪካ እስከ ደቡብ አፍሪካ፤ከአወሮፓ እስከ አውስትራሊያና እስከ ኒውዚላንድ የወንጌል ብርሃንን ያበሩ ወደፊትም የሚያበሩ አባትን ኑፋቄአቸውን ሳትናገር ወይም የሊቃውንት ጉባኤም ሆነ የሃገር ቤቱም ሆነ የውጭው ቅዱስ ሲኖዶስ አቅርቦ ሳይጠይቃቸው ያለፍርድ የምትናገር አንተ የምትቀድስው ቅዳሴ ምን አይነት ቅዳሴ ነው፤ሲኖዶስ አይሰድድም ያለው አንድ ሲኖዶስ ነው ካልክ በውጭ ያሉት አባቶች ቢያጰጵሱ ባያጰጵሱ ምን አገባህ አረ ጉደኛ ነህ ! ለመሆኑ እነ አርዮስ እነ ንስጥሮስ እነ መቅዶንዮስ ሲወገዙ አባቶች ተሰብስበው ኑፋቄአቸው ተነግⶂቸው አሻፈረን ብለው አይደለም ወይ አንተ መስቀል የያዝክ ጨለማ ያለፍትህ ሰው ላይ ትፈርዳለህ ‘አንተ በኖራ የተለስንክ ግድግዳ እግዚአብሔር አንተን ይመታ ዘንድ አለው በሕግ ልትፈርድ ተቀምጠህ ሳለህ ያለሕግ እመታ ዘንድ ታዛለህን(የሐዋርያት ሥራ፤፳፫፡፫) አንተ የዘመናችን ሐናንያ ያለ ፍትህ አባታችን ላይ እንዴት ልትፈርድ ቻልክ የድፍረት ሐጢያት የገዛህ።ደግሞ ተሾሙ ብለህ ፍራሽ ጎዝጉዘህ ተቀምጠሃል፡በመጀመሪያ ደረጃ ይህንን እኔ ሹመት አልለውም የበለጠ ፈተና የበለጠ ሃላፊነት ነው የበለጠ እረኝነትና ሸክም ነው እንጂ በዚህ አንተ ምን አስቆጣህ አንተ ጳጳስ አትሆን በዚህ ድፍርትህና ጥላⶫህ ቅስናህንም መጠበቅህ አጠያያቂ ነው።ከታሰርክበት የጥላቻና የቅናት መንፈስ እግዚአብሔር ያላቅህ፤ሁለቱም የስጋ ፍሬዎች ናቸው፡ስተሳደብ ምናለበት መስቀሉን እንኳን ብትደብቀው መስቀል እኮ ጌታችን ወርቀ ደሙን አፍስሶ የባረከውና የቀደስው መባረኪያ እንጂ ለስድብ የምናሳየው መዘበቻ አይደለም።አንተ ምን ቸገረህ አንድ እግርህ ወያኔ ጋ አንድ እግርህ ተቃዋሚዎች ጋ፡ሁለት ባላ ትከል አንዱ ቢሰበር በሁለተኛው ተንጠልጠል።መጀመሪያ ጓዳህንና ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን ብለህ ኡራዔልን ከፋፍለህ ያቆምከውን ቤተክርስቲያን በስርዓት አስተዳድር።ከዚያ በኋላ ሃገር ቤት የወያኔ ባለስልጣናት እየገቡ አመራር የሚስጡትን ሲኖዶስ ውቀስ።ከዚያ በኋላ ስለ ውጭ አባቶች ጉዳይ ትነጋገራለህ ያውም ደግሞ ከተጠየክ።
  ደግሞ ስለእርቅ ታነሳለህ! እርቁንማ አንተና ጓደኞችህ ከወያኔ ጋር ሆናችሁ አይደለም እንዴ ያበላሻችሁት!ደግሞ እንዳንታረቅ እንኳን የማይፈለጉ መናፍቅ ተሾሙ አልክ፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም መናፍቅ ተብሏል።”የአባቶቼን አምላክ እነርሱ ኑፋቄ ብለው እንደሚጠሩት መንገድ አመልካለሁ”የሐዋርያት ሥራ፤፳፬፡፲፬)ያንተና የመሰሎችህ ስድብ ለአባታችን አባ ወልደ ትንሣኤ ለአሁኑ ብፁዕ አቡነ በርናባስ ተጨማሪ ፀጋ ነው የስድብ አፍ ተሰጥቶሃልና እስኪዘጋ ድረስ ስድቡን ቀጥል”አመ ይመጽ ወልድኪ መንፈቀ ሌሊት በስልጣን አሜሃ ይበⷍዩ ኃጥአን ወይትፌስሑ ጻድቃን ትብህም አፍ ወትትአሰር ልሳን”(እሴብህ ጸጋኪ ሰዓታት)ደግሞ እግዚአብሔር ዝም አይልም እያልክ ታስፈራራለህ አዎ እግዚአብሔርማ ዝም አይልም ዝም አለማለቱንማ የቤተ መንግስቱንም የቤተ ክህነቱንም በኩራት አባቶችህን በአንድ ሰሞን ጠራርጎ ወስዶልናል፡አዎ አምላክነ ኢያረምም ዝምም አይልም።

  እመለስበታለሁ

  እግዚአብሔር የንስሐን ሕይወት ይስጠን

 20. Gessess June 25, 2016 at 1:14 pm Reply

  How dar Mahibere Rekusan against our father in exile, MK must learn from our father how to say NO! Musie was said NO! to FERON, our father said NO to woyane illegaly involvement in EOTC. NO any more when ever the government changed the Patririch got killed and elected the supporeter one, it is great lesson for you to learn, our fathers in exil doing great job curgiousely

 21. Solomon June 26, 2016 at 10:11 pm Reply

  አሁንማ ዝም ብዬ ሳስበው እኛ ሰዎች ስራችንን ዘንግተናል። ስራውን ያልዘንውጋው ሰይጣን ብቻ ነው። ኧረ እንደውም የሱን ስራ በደንብ እየሰራንለት ነው። ወገኖቼ ይሰይጣንን ካልኩሌሽን (calculation) ቀድመን እንንቃበት። የመጀመሪያው አባቶችን ማለያየት ነው። እረኞቹ ከተጣሉ በጎችን መበተን ወይም መስረቅ ቀላል እንደሆነ በደንብ የተረዳው እሱ ነው። ኣላማውን ደግሞ እኛው እራሳችን እንድንፈጽም እያደረገን ይገኛል። ግድ የላችሁም ወገኖቼ ይሄን መንፈስ በሕብረት ሆነን በጸሎት እንዋጋው። ፈጣሪ ይርዳን።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: