ስለድንግል ማርያም ፍቅር የተመተረውን የእናት ወሰን የለሽ ፈቃዱን እጅ ዐየኹት፤ የሰማዕትነት ቋጠሮ ነው፤ ንሥኡ ፍሬ ሃይማኖት!

the jihadist victim of Jimma

 • እናታችን፣ በቀዶ ሕክምና የማይመለሰውን የግራ እጃቸውን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም ላይመለስላቸው ዐጡት፤
 • የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር ከሚሰብከው ማንነት እንማር፡፡ ይህ አረንጓዴ ሰማዕትነት አይደለም፤ ነጭ ሰማዕትነትም አይደለም፤ ይህ ቀይ የደም ሰማዕትነት ነው
 • ለምን ኾነ ሳይኾን፣ በኾነው ነገር ኹሉ ስለሚሰጠን ትምህርት፣ ጽናት እና ዋጋ ልንጨነቅ ይገባል፡፡

(ዶ/ር አክሊሉ ደበላ)

Dr. Aklilu Debela FB

ዶ/ር አክሊሉ ደበላ

ዛሬ፣ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት፣ በጅማ ዞን የም ወረዳ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከጠዋቱ 12 ሰዓት ገደማ በክርስቲያኖች ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ መጨፍጨፍ አሳዛኝ ነው፡፡ ተራኪዋ በደራረቁ የእንባ ዘለላዎች ውስጥ ፍጹም ሰላምተኛነትን ታሳያለች፡፡ አደጋው የደረሰባቸው እናት በሚሰማቸው ከፍተኛ የሕመም ስሜት ውስጥ ኾነው ጉዳታቸውን አቅልለው ለማየት የሚያደርጉት ጥረት ያስታውቃል፡፡

የግራ እጃቸው፣ ከትልቁ የእጅ ጣት በስተቀር፣ አራቱ ጣቶች ከመነሻ መገጣጠሚያቸው አንሥቶ ተቆርጠዋል፡፡ ተቆርጦ የተነሣው የግራ እጅ ክፍል ለብቻው በሌላ መያዣ ተቀምጧል፡፡ ይህን የተቆረጠ እጅ ስመለከት፣ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ትዝ አለኝ፡፡ የተነጨው ጽሕሙና የተነቀለው ጥርሱ!! “ንሥኡ፤ ይህ የክርስትና ፍሬ፤ የሃይማኖት ፍሬ ነው ብሎ ለእስክንድርያ ክርስቲያኖች አክብሮ የላከላቸው ያ የሰማዕትነት ቋጠሮ ትዝ አለኝ፡፡

የእናታችን የተቆረጠ እጅ በማንኛውም የሪኮንስትራክቲቭ ቀዶ ጥገና የማይመለስ ስለኾነ እናታችን የግራ እጃቸውን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም ዳግም ላይመለስላቸው ዐጡት፡፡ “ኹሉን ትተን ተከተልንኽ…፤ ማለት ይህ ስለኾነ፡፡

በአፋቸው መናገር አይችሉም፡፡ አፋቸውንና አፍንጫቸውን ጨምሮ የላይኛው ፊታቸው ከዓይናቸው በታች ዙሪያውን ታሽጓል፡፡ የማጅራት አጥንት ጉዳት መኖር አለመኖሩ ስላልተረጋገጠ አንገታቸው ከጀርባቸው በኩል በኮላር ተያይዟል፡፡ ፊታቸውን የሸፈነው መሸፈኛ ሲነሣ የገጀራው መሥመር ግራ እጃቸውን ከፊታቸው ጋር አድርጎ እንደ መተረው ያመለክታል፡፡ የላይኛው ከንፈር እና የላይኛው መንጋጋ አጥንት በምን ያኽል ጥልቀት እንደ ተጎዳ ለማረጋገጥ የፊት Facial CT-SCAN መነሣት ይኖርባቸዋል፡፡ የጭንቅላት እና አከርካሪ ሲቲ ስካን ውጤቱ እየተጠበቀ ነው፡፡

the martyr mother of Jimma

ሰኔ 8 ቀን ማለዳ ከታናሽ እኅታቸው ጋር ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው እና ስለ ድንግል ማርያም ስም የጅሐዲስቶችን ሰይፍ የተቀበሉት የ60 ዓመቷ እናትና የ10 ልጆች እናት የኾኑት ወ/ሮ ወሰን የለሽ ፈቃዱ፤… በዚኽ ኹሉ መሀል የሕመመተኛዋ ርጋታና ምንም አልኾንኩም ዓይነት ስሜት ግን የሚደነቅ ነው፡፡

አኹን ለሚሰማቸው ሕማም፣ በመርፌ በሚወሰዱ ኹለት መድኃኒቶች ሕክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ግሉኮስም ተገጥሞላቸዋል፤ ጠያቂዎችም ብቅ ብቅ እያሉ የጥቁር አንበሳ ድንገተኛ ክፍልን ከበዋል፡፡ ወደ አጥንት ቀዶ ጥገና ክፍል ገብተው Correctional Amputation እስከሚያደርጉ ድረስ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩም እንደሚደርሱ እየተጠበቀ ነው፡፡ በዚኽ ኹሉ መሀል የሕመመተኛዋ ርጋታና ምንም አልኾንኩም ዓይነት ስሜት የሚደነቅ ነው፡፡

ኹለት ክርስቲያኖች፣ አምስት ሙስሊሞች እንደ ተጎዱ ሲዘገብ ነበር፡፡ ሌላዋም ክርስቲያን የእኚኽ እናት ታናሽ እኅት ናቸው፡፡ ጠዋት ቤተ ክርስቲያን ለመሔድና ኪዳን ለማድረስ እንደ ተሰናዱ ነው፤ መስጊዱም ኾነ ቤተ ክርስቲያኑ ከቤታቸው በጣም ሩቅ የሚባል አይደለም፡፡ ከቤታቸው ወጥተው እየሔዱ ሳሉ፣ ከአራቱ አክራሪ ጅሐዲስቶች አንዱ ድንገት ከተሸሸገበት ወጥቶ ድንገተኛ ጥያቄ ይጠይቃቸዋል፡፡ ማርያምን ትወጂያታለሽ?አላቸው፡፡ በከፍተኛ መገረም፣ አዎበጣም እወዳታለኹ ብለው ይመልሳሉ፡፡ ከዚያ “አሏህአክበር በይ” ይባላሉ፡፡ እምቢታቸውን ይገልጣሉ፡፡ በዚኽ ጊዜ በያዘው ገጀራ ከላይ የተገለጹትን የአካላቸውን ክፍሎች በጭካኔ ይመታቸዋል፡፡ ቀጥሎም አጠገባቸው የነበሩትን ታናሽ እኅታቸውን ከኋላ አንገቷ አካባቢ በዚያው ገጀራ ይመታቸዋል፡፡ ወዲያው ግን ከመስጊድ እየወጡ ያሉ ሰዎች ያዩአቸዋል፡፡ እየሮጡ ሔደው ሲገላግሉአቸው፣ ለእነርሱም የገጀራው ጽዋ ይደርሳቸዋል፡፡

ሕያው መጽሐፍ/ትምህርት ነው፡-

መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ የሚቸግረው፣ ወይም የማይገባው፣ ወይም ጊዜ ያጣ ቢኖር ይኽን ሕያው መጽሐፍ ያንብብ፡፡ አምና ሊቢያ የነበረው በርቀት ምክንያት አልፎት ቢኾን፣ ከዚኽ በፊት ደግሞ 1999 ዓ.ም.፣ በዚኹ በጅማ የተፈጸመው መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሕይወት ዐውደ ርእይ በተለያዩ ምክንያቶች ተላልፎትም ከኾነ ይምጣና ይህ የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር ከሚሰብከው ማንነት ይማር፡፡ ይህ አረንጓዴ ሰማዕትነት አይደለም፣ ነጭ ሰማዕትነትም አይደለም፡፡ ይህ ቀይ የደም ሰማዕትነት ነው፡፡

ክርስቲያኖች ሆይ:- ኹሌ ስለ ኑሮ ውድነትና በየዕለቱ ስለሚከሠቱ የዓለም ክፋቶች ብቻ መስማት አለብን? ወይስ ስጋችንን ስለሚያስደስት ነገር ብቻ መስማት እንሻለን? ስለ ቤተ ክርስቲያን ችግር፣ ስለ ፈታኞቿ መናፍቃንና የተሐድሶ መናፍቃንስ መስማት አይገባንምን? ተግተው ስለሚሰብኩን እንዲኽ ዓይነት ማንነቶችም አንዳንዴ መስማት ያስፈልገን ይኾናል፡፡ ለምን ኾነ ሳይኾን፣ በኾነው ነገር ኹሉ ስለሚሰጠን ትምህርት፣ ጽናት እና ዋጋ ልንጨነቅ ይገባል፡፡

His Holiness visiting the victim
ቤተ ክርስቲያን
እንደ ተቋም፡– ቅዱስ ፓትርያርኩ ጥቁር አንበሳ ድረስ መጥተው ለመጠየቅ መትጋታቸው መልካም ነው፡፡ ከጅማ አንሥቶ እስከ መጨረሻው ድረስ እነዚኽን ወገኖች ካሉበት ድረስ ሔደው በመርዳት የተዋሕዶ አለኝታነታቸውን የገለጹ የማኅበረ ቅዱሳን ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን በእውነት ዋጋቸውን የቅዱሳን አምላክ አያጓድልባቸው፡፡ ኾኖም፣ ነገሮች እየኾኑ ያሉት ለምንና እንዴት ነው የሚለውን ጥያቄ ከነመፍትሔዎቻቸው በየልቡናችን ማመላስ ይኖርብናል፡፡

መንግሥት፡ መንግሥትም እስከ አኹን ቤተ ክርስቲያን ስትበደል ስትደማ ዓይን ዓይኗን እያየ በደሟ ከመሣቅ ያልተናነሰ ቸልተኝነትን ሲያሳይ ቆይቷል፡፡ ምናልባት ሌላው ቢቀር፣ የኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች ንጹሕ ደም እንደ ዜጋ መጠን ሊያሳስበው ይገባልና አድበስብሶ ከማለፍ ቢያስብበት!!

ሌሎች አብያተ እምነቶች፡ በርግጥ ለእነዚኽና ለሌሎችም በብዙ የሚቆጠሩ ነፍሳት ማለፍ ከክርስቲያኑ ጋር በመከባበርና በመገናዘብ የሚኖሩት ሙስሊሞች ተጠያቂዎች አይኾኑም፤ ዛሬ ሳይቀር ከእኛ ጋር መከራ ሲቀበሉ አይተናልና፤ ነገር ግን እምነቱን መሠረት ያደረገና መጠየቅ ያለበት አስተምህሮ የለም ለማለት አንችልም፡፡ ይህ ኹሉ የነፍስ እልቂት ያለአንዳች መነሻ የሚኾን ነው ለማለት ይከብዳል፡፡

የተሐድሶ መናፍቃንና መናፍቃን ሆይ፡ ለሃይማኖት የሚከፈለው ዋጋ ይህን በመሰለው ሰማዕትነት የሚገለጽ መኾኑን ለመማር ባትችሉ እንኳ፣ እስኪ ለትንሽ ወራት እንኳ ስለ አምላክ ፍቅር ረኀብን በመታገሥ ለመጾም ተለማመዱ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ሰኔ 2008 ዓ.ም.

Advertisements

8 thoughts on “ስለድንግል ማርያም ፍቅር የተመተረውን የእናት ወሰን የለሽ ፈቃዱን እጅ ዐየኹት፤ የሰማዕትነት ቋጠሮ ነው፤ ንሥኡ ፍሬ ሃይማኖት!

 1. Desalegn Dosa June 16, 2016 at 1:32 pm Reply

  እግዚአብሔር የጻድቃንን ያስድርብን!!!!!!

  2016-06-15 23:26 GMT-12:00 “ሐራ ዘተዋሕዶ” :

  > haratewahido posted: ” እናታችን፣ በቀዶ ሕክምና የማይመለሰውን የግራ እጃቸውን ስለ ተዋሕዶ ሃይማኖታቸው
  > እና ስለ ድንግል ማርያም ስም ላይመለስላቸው ዐጡት፤ የድንግል ማርያምን ልዩ ፍቅር ከሚሰብከው ማንነት እንማር፡፡ ይህ
  > አረንጓዴ ሰማዕትነት አይደለም፣ ነጭ ሰማዕትነትም አይደለም፡፡ ይህ ቀይ የደም ሰማዕትነት ነው፤ ለምን ኾነ ሳይኾን፣
  > በኾነው ነገር ኹሉ ስለሚሰጠን ትምህርት፣ ጽናት እና ዋጋ ል”
  >

 2. Anonymous June 16, 2016 at 2:00 pm Reply

  በረከታቸው ይድረሰን የናታችን በእውነት!!!

 3. Seife Gebrel June 16, 2016 at 4:34 pm Reply

  Sileteseten timihirt Egziabher yimesgen! Ye Enatachinin himem ena sikay Egziabher yastagsilin. Dingil Maryam Tiketelilin!!! Amen

 4. Anonymous June 16, 2016 at 4:47 pm Reply

  ሰማእትነት ካገኙ በኋላ ደስ ይላል። ነገር ግን በትክክል የምትራመዱ አባቶች ቀሳውስት፥ዲያቆናት፥በተለይ ለኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ብላችሁ ጠበቃ የቆማችሁ ጳጳሳት እባካችሁ ተጠንቀቁልን። እናንተ ብታልፉ ጽድቅ ነው። የበለጠ ጽድቅ የሚሆነው ግን መንጋውን ስትጠብቁ ነው። እናንተን ጠብቆ ለመምታትና ከተቻለም ለመግደል ተሀድሶ መናፍቅ አጀንዳውና እቅዱ አድርጎ የያዘው ይመስለኛልና ተጠንቀቁልን። በፍርሃት ኑሩ አይደለም። ተሃድሶ መናፍቅ በገንዘብ አልታለልም ያሉትን አባቶቻችን መግደል እቅዱ ነው።

 5. Anonymous June 17, 2016 at 8:48 am Reply

  እመቤታችን ታበርታችሁ፡፡ ክርስቶስ አጽናኙን መንፈስ ቅዱስ ጲራቅሊጦስን በሐምሳኛው ቀን ይላክላችሁ፡፡

 6. birukgmariam June 17, 2016 at 8:49 am Reply

  እመቤታችን ታበርታችሁ፡፡ ክርስቶስ አጽናኙን መንፈስ ቅዱስ ጲራቅሊጦስን በሐምሳኛው ቀን ይላክላችሁ፡፡

 7. Anonymous June 29, 2016 at 1:40 pm Reply

  እግዚአብሔር ለእሳቸውም ዋጋውን ይክፈላቸው ድንግል ማርያም ትዳብሳቸው፡፡ ወገን እባካችሁ በእንባ ወደአምላክ እንፀልይ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: