ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት: የጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል የአክራሪዎች ተጠቂዋንና ቤተ ሰዎቻቸውን አጽናኑ

 • ሦስት ጉዳተኞች በወሊሶ ሆስፒታል በሕክምና ላይ ናቸው

his-holiness-abune-mathias

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ዛሬ ማለዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት ከፍተኛ ጉዳት ከደረሰባቸውአንዷ የኾኑትንና በጥቁር አንበሳ ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን ምእመንት ጎበኙ፤ ቤተ ሰዎቻቸውንም አጽናኑ፡፡

ቅዱስነታቸው፣ ከቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ከምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ከስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ጋር በመኾን ነው፣ ዛሬ ማምሻውን በሆስፒታሉ የተገኙት፡፡

ለጉዳተኞች ጸሎተ ማርያም ከደረሰ በኋላ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትያርኩ ባሰሙት ቃል፤ “ለሃይማኖታችኹ የከፈላችኹት ዋጋ ነው፤ ይህ መከራ አባቶቻችን የተቀበሉት ነው፤ አዲስ አይደለም፤ አባቶች ብለን የምንጠራቸው እንዲኽ ባለው ግፍ በእምነታቸው ጸንተው ስላለፉ ነው፤” በማለት ቤተ ሰዎቻቸውንም አጽናንተዋል፡፡

ጥቃቱ ዛሬ ማለዳ ከተፈጸመ በኋላ፣ ረፋድ 4፡30 ገደማ ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ሆስፒታሉ የደረሱት ምእመኗ፣ በ40ዎቹ የዕድሜ ክልል የሚገመቱ ሲኾን፤ ከአንድ እጃቸው አውራ ጣታቸው ሲቀር የተቀሩት አራት ጣቶች ከመዳፋቸው በጥቃቱ መቆረጡን፤ ከከንፈሮቻቸው መገጣጠሚያከአፍንጫቸውም አካባቢ ወደ ጆሯቸው አቅጣጫ በጥልቀት በስለት መታረዳቸውን የሆስፒታሉ ምንጮች ተናግረዋል፡፡

His Holiness Aba Mathias visiting the victim
ሌሎች ሦስት ታካሚዎች፣ በወሊሶ ሆስፒታል የሕክምና ርዳታ እየተደረገላቸው እንዳለም ታውቋል፡፡ ለአካባቢው ፀጉረ ልውጥ ናቸው የተባሉት አራቱ ጥቃት አድራሾ
ች፣ ከወደ አዲስ አበባ አቅጣጫ በመኪና እንደመጡና ጥቃቱን ካደረሱ በኋላ አንዱ ሲያዝ የተቀሩት ሦስቱ ወደ ጅማ አቅጣጫ መሸሻቸው በቀደመው ዘገባ ተገልጧል፡፡

the patriarch consoling the victim

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ጉዳተኛዋን እናትና ቤተሰዎቻቸውን ባጽናኑበት ወቅት(ፎቶ: ሶምሶን እደግልኝ)

ጥቃት ያደረሱባቸውን የስለት መሣርያዎች ጨምሮ ሌሎችም አመላካቾች፣ ይህንኑ እንደሚያረጋግጡ በቁጥጥር ሥር በዋለው ግለሰብ ላይ የሚካሔዱ ምርመራዎች ቢጠቁሙም፤ በዛቻና ማስፈራሪያ ቃል አዘውትረው የሚያሸብሯቸው ግለሰቦች እንዳሉም ነው፣ የወረዳዋ ክርስቲያኖች የሚናገሩት “[በየእምነታችን ተከባብረን በመኖር] ቀበሌዋ ደኅና ነች፤ አንድ ቀን እንዲኽ ትኾናላችኁ፤ ራት እናድርጋችኋለን እያሉ የሚዝቱብን ግን አሉ፤ [ጥቃት አድራሾቹ] መንገደኞች ናቸው፤ አናውቃቸውም በሚል ለመሸፋፈንና ለማጠፋፋት የሚነገረው በጥንቃቄ ሊታይ ይገባዋል፤” ብለዋል፡፡

መንበረ ፓትርያርኩ፣ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስና በጽ/ቤታቸው አማካይነት ኹኔታውን እየተከታተለ ሲኾን፣ በጥቃቱና በዘላቂ መፍትሔው ላይም፤ በመንበረ ፓትርያርኩ ደረጃ ከመንግሥት ጋር ንግግር እንደሚደረግበት ተጠቁሟል፡፡

 

Advertisements

5 thoughts on “ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት: የጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል የአክራሪዎች ተጠቂዋንና ቤተ ሰዎቻቸውን አጽናኑ

  • Angile June 15, 2016 at 10:48 pm Reply

   በዛቻና ማስፈራሪያ ቃል አዘውትረው የሚያሸብሯቸው ግለሰቦች እንዳሉም ነው፣ የወረዳዋ ክርስቲያኖች የሚናገሩት – “[በየእምነታችን ተከባብረን በመኖር] ቀበሌዋ ደኅና ነች፤ አንድ ቀን እንዲኽ ትኾናላችኁ፤ ራት እናድርጋችኋለን እያሉ የሚዝቱብን ግን አሉ፤ [ጥቃት አድራሾቹ] መንገደኞች ናቸው፤ አናውቃቸውም በሚል ለመሸፋፈንና ለማጠፋፋት የሚነገረው በጥንቃቄ ሊታይ ይገባዋል፤” ብለዋል፡፡

 1. Angile June 15, 2016 at 10:47 pm Reply

  በዛቻና ማስፈራሪያ ቃል አዘውትረው የሚያሸብሯቸው ግለሰቦች እንዳሉም ነው፣ የወረዳዋ ክርስቲያኖች የሚናገሩት – “[በየእምነታችን ተከባብረን በመኖር] ቀበሌዋ ደኅና ነች፤ አንድ ቀን እንዲኽ ትኾናላችኁ፤ ራት እናድርጋችኋለን እያሉ የሚዝቱብን ግን አሉ፤ [ጥቃት አድራሾቹ] መንገደኞች ናቸው፤ አናውቃቸውም በሚል ለመሸፋፈንና ለማጠፋፋት የሚነገረው በጥንቃቄ ሊታይ ይገባዋል፤” ብለዋል፡፡

 2. Anonymous June 17, 2016 at 9:42 am Reply

  ega betachen be seamy new!!!!!!!!!!!!! le ahzab anferam egzihabeher alena!!!!!!!!!!!!!!!

 3. Anonymous August 3, 2016 at 7:03 pm Reply

  iwunetenga mengad ti ketnalech ing atibetesim

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: