ሰበር ዜና – በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

eotc patriarchate edd

 • 2 ኦርቶዶክሳውያን እና 5 ሙስሊሞች መጎዳታቸው እየተገለጸ ነው
 • ከ4ቱ የጥቃቱ አድራሾች አንዱ ተይዟል፤ 3ቱ አምልጠዋል፤ ተብሏል
 • ሀ/ስብከቱ ከወረዳው የአስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር እየሠራ ነው

(UPDATES) በጅማ ሀገረ ስብከት የም ልዩ ወረዳ ቁንቢ ቀበሌ፣ በቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሰበካ የሚገኙ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች፣ ዛሬ፣ ሰኔ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ማለዳ በአክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተሰማ፤ በነዋሪ ሙስሊሞችም ላይ ጉዳት አድርሰዋል፡፡

ምእመናኑ ጥቃቱ የተፈጸመባቸው፣ በቤተ ክርስቲያኑ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በሚመለሱበት ወቅት ነው፤ ተብሏል፡፡

በጥቁር አልባሳት ፊታቸውን የሸፈኑ አራት የጥቃቱ አድራሽ አክራሪዎች፣ ወደ አካባቢው በመኪና እንደ ደረሱ ጥቃታቸውን የጀመሩት፣ በቀጥታ በአካባቢው ወደሚገኝ አንድ መስጊድ በመግባት እንደኾነ ተገልጧል፡፡

“ግንባር፣ አንገት፣ እጅ እየመቱ ያገኙትን በስለት ጨፈጨፉ፤” ያለው የስፍራው ምንጭ፣ በጭፍጨፋው አምስት ሙስሊሞች(አክራሪዎቹ እንደ ከሐዲ/ካፊር የሚቆጥሯቸው ነዋሪዎች) ክፉኛ መቁሰላቸውን ተናግሯል፡፡

ከመስጊዱ እንደወጡ ወደ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አቅጣጫ በማምራት፣ የኪዳን ጸሎት አድርሰው በመመለስ ላይ በነበሩ ምእመናን ላይም በቀጠሉት ጥቃት፤ ኹለት ምእመናንን ክፉኛ አቁስለዋል፤ ከቆሰሉት የአንዷ እጇ በጥቃቱ ተቆርጦ ከቆይታ በኋላ መገኘቱ ተጠቅሷል፡፡ 

ከጥቃቱ አድራሾች ሦስቱ በመጡበት መኪና ከአካባቢው በመሰወር ያመለጡ ሲኾን፣ አንዱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል፡፡ “ወደ ጅማ አቅጣጫ ነው የነዱት፤ ቅስቀሳቸውንና ጥቃታቸውን ከማስፋፋታቸው በፊት በተጠናከረ ክትትልና አሠሣ ሊያዙ ይገባል፤” ይላል አንድ የአካባቢው ነዋሪ፡፡

በጥቃቱ ከተጎዱት ምእመናን፣ ለሕክምና ወደ አዲስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የደረሱ መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

የቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሚገኝባት የም ልዩ ወረዳ፣ በሰኩሩ እና ናትሪን መካከል ያለችና አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ምእመናን፣ ከሚበዙት የእስልምና እምነት ተከታዮች ጋር በመከባበርና በመገናዘብ የሚኖሩባት ወረዳ እንደ ኾነች ተመልክቷል፡፡

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ጽ/ቤታቸው፣ የተጎዱትን ምእመናን ለመርዳትና ጥቃት አድራሾቹን ለመቆጣጠር ከወረዳው አስተዳደርና የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ መኾኑ ተገልጧል፡፡

በጅማና በኢሉባቦር አህጉረ ስብከት ዴዴሳ ወረዳ፣ ክርስቲያኖች፣ የጦር መሣርያና ገጀራ በያዙ አክራሪዎች ተደጋጋሚ ጥቃት(ግድያ፣ ዘረፋ፣ የቤትና የንብረት ውድመት፣ መፈናቀልና ፆታዊ መደፈር) ሲፈጸምባቸው ቆይቷል፡፡ ከመስከረም 16 ቀን 1999 ዓ.ም. ጀምሮ በነበሩት ተከታታይ ቀናት፥ በጎማ፣ በማና እና በቶባ 12 ክርስቲያኖችን ገድለው፣ ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን (የጨጎ ቅዱስ ገብርኤል፣ ቦሬ ቅዱስ ገብርኤል እና በሻሻ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ) አቃጥለው ንዋያተ ቅድሳቱን ከመዝረፋቸውም በላይ፤ ከ800 በላይ የአባ ወራ ቤቶችን በማቃጠል ከቀዬአቸው ማፈናቀላቸውና በግዳጅም ማስለማቸው ይታወሳል፡፡

ማረሚያ፡- በቀደመው የሰበር ዘገባ፣ “ሰኮሮ ወረዳ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል” የሚለው “የም ልዩ ወረዳ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል” ተብሎ እንዲታረም እንጠይቃለን፡፡  

Advertisements

14 thoughts on “ሰበር ዜና – በጅማ ቁንቢ ቅዱስ ሚካኤል አክራሪ ሙስሊሞች ጥቃት አደረሱ

 1. Abrha June 15, 2016 at 9:56 am Reply

  Harawoch bertu!

 2. Aytalnew Newzendro June 15, 2016 at 10:03 am Reply

  TPLF fascists are the root cause no ethnic or religious problem prior the occupation of Ethiopia by the fascists from TIGRAI.

 3. kinfae Gebreale June 15, 2016 at 10:13 am Reply

  EGZIABEHARE Alen

 4. teddy June 15, 2016 at 10:48 am Reply

  ሰማዕት በእንቲአከ ሐሙ
  ሕማሞሙ ትፍስሕተ ኮኖሙ
  ክብር ይደልዎሙ!!!

  • Anonymous June 15, 2016 at 1:28 pm Reply

   AMAN MENENU SEMAET TSAMA LEZA ALEM WO KEAW DEMPMU/…..

 5. biruk June 15, 2016 at 1:37 pm Reply

  yihe yeminisemaw hulu betinibit yetenegere silehone metseleyi bicha new

 6. Anonymous June 15, 2016 at 1:48 pm Reply

  አቤቱ ጌታ ሆይ ህዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ

 7. Anonymous June 15, 2016 at 2:07 pm Reply

  Enanten KIDIST SELASSIE Yabzachihu

 8. Abebe June 15, 2016 at 3:42 pm Reply

  Mini Feligew new terrist Ethiopia wist Ayiseram

 9. Anonymous June 15, 2016 at 11:15 pm Reply

  መንግሥት ባለበት አገር እንዲህ አይነት አረመኔያዊ ተግባር መፈፀሙ እጅግ ያሳዝናል

 10. Anonymous June 16, 2016 at 1:02 am Reply

  በአክራሪዎች አደጋ ለደረሰባችሁ ለቁንብ ቅ/ምካኤል ቤ/ያን የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮቸና እንድሁም የአካባቢዉ ሙስልም ወንድሞችና እህቶች ለእናንቴ መፅናናትን ተመኘሁ::የአገሬ ህዝብ ሆይ አገራችን ኢ/ያ የተለያዩ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ተቻችለንና ተከባብረን ለብዙ አመታት የኖርንና አሁንም እየኖርን ያለን ነን ነገር ግን ይህ የህዝባችን በፍቅር መኖር ያስቀናቸው አንዳንድ የሰይጣን መልእክተኞች የሚፈፅሙትን እኩይ ተግባራትን እጅ ለእጅ ተያይዘን መታገል አለብን::የጥፋት ተልእኮ ይዘው የሚንቀሳቀሱ ሻቢያና አልሸባብ መጨረሻቸው ከምድር ይጠፋሉ በዝህ አትጠራጠሩ

 11. Anonymous June 16, 2016 at 9:27 pm Reply

  ፆም ምናምን እየፆምን ሲሉ ነበር ከምኔው ወደግድያ ዞሩ? ምን እያሉ ይሆን የሚፀልዩት?

 12. […] Muslims  attack Christians and moderate Muslims. According to Amharic religious-focused website HARA ZETEWAHIDO, four extreme Muslim attackers covered their face, when they entered to the local Mosque and then […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: