በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ: “በጐች በበጐች ላይ እንዳይሰማሩ”:-ካህናቱንና ምእመናኑን ማሳተፍ፤ ከኹሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ መጸለይ ይገባል/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

consecration of bishops by Abune Baslios, Abune Theoplos and Abune Paulosበአባቶች እግር አባቶችን የመተካት አስፈላጊነት፡-
 • ብዙ ጠንካሮች አባቶቻችን በተከታታይ አንቀላፍተዋልበሕመምና በዕርግና ከቤት የዋሉም አሉ
 • እግዚአብሔር አልባነት፣ አምልኮ ባዕድ፣ የመንጋ ቅሠጣና የአህጉረ ስብከት ብዛት ጉዳዮች ናቸው
 • ለቤተ ክርስቲያን ያሰቡ መስለው ጥቅሟን ለመቦጥቦጥ የተነሡ ውስጠ ተኩላዎች ተበራክተዋል
 • ቤተ ክርስቲያን፥ “ከወዳጅ ጠላቴ ጠብቀኝ” ብላ ጸሎት የምታቀርብበት ጊዜ ላይ ደርሳለች፤
በአባቶች እግር አባቶችን መተካት ግዴታ ቢኾንም፡-
 • ከነጣቂ ተኩላዎች የሚያድኑ፣ የሕዝብ መብራትና ቸር እረኛ የኾኑት ሊለዩና ሊመረጡ ይገባል
 • በጐች በበጐች ላይ የሚሰማሩበትና ጠባቂዎች ተጠባቂዎች እንዳይኾኑ ካለፈው ተሞክሮ ይወሰድ
 • ለቤተሰብ የማያዳሉ፣ ለዓለም የማይገዙና ቅድስናቸውን ያረጋገጡ በውስጥም በውጭም ይታሠሡ
 • ትክክለኛ የኤጲስቆጶሳት ምርጫና ሹመት ቤተ ክርስቲያንን ከወቅቱ አደጋ የመታደግ ጥያቄ ነው
ካህናቱንና ሕዝበ ክርስቲያኑን የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ፡-
 • በሰውና በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦ መምረጥ የቅዱስ ሲኖዶስ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ነው
 • የዕጩዎች ዕውቀት፣ አገልግሎትና ቅድስና ሳይጋነንና ሳይንኳሰስ ያለአድልዎ ለመመርመር
 • በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ የሚወረወረውን ትችት ካህናቱም፣ ምእመናኑም እንዲጋሩት ያስችላል
 • ከካህናቱ እና ከሕዝቡ ምስክርነት ጋር መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ ኹሉም ሊጸልይ ይገባል፡፡

*           *          *

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ ርእሰ አንቀጽ፤ ፷፪ኛ ዓመት ቁጥር ፸፩፤ ግንቦት ፳፻፰ ዓ.ም.)

zena-bete-kirstian-gazetta-editorial edከባሕር ወዲኽም ኾነ ከባሕር ማዶ፣ ለነጩም ለጥቁሩም ቀን ከሌሊት አስተምረውና ቀድሰው ከማይጠግቡት ከዓለም አቀፋዊው አባት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ጀምሮ አንቱ የተባሉ ብዙዎች ጠንካሮች አባቶቻችን፣ ሐዋርያዊ ተልእኮአቸውን በሚገባ አከናውነው በተከታታይ አንቀላፍተዋል፡፡ በሕመምና በዕርግና ምክንያት ደክሟቸው ከቤት የዋሉትም አባቶች ጥቂት አይደሉም፡፡

ባለንበት ዘመን በትምህርተ ወንጌል እንጂ እንደ ቀድሞው በዐዋጅ ብቻ የሚከበር ሃይማኖት የለም፤ በጸሎተ ቅዳሴው፣ በሰዓታቱ፣ በማሕሌቱ፣ በተኣምሩ እና በገድላቱ ብቻ የሚያምነውም ትውልድ እያረጀ እያፈጀ ሔዷል፡፡ የተዘረዘረው ኹሉ ተደማምሮ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ጸሎት እና ምስጋና ነው፡፡ ጸሎቱ እና ምስጋናው ውስጡ ስብከት አዘል ቢኾንም፣ አገልግሎቱ የሚፈጸመው በግእዝ ቋንቋ ስለኾነ ሕዝበ ክርስቲያኑ ትርጉሙንና ምሥጢሩን አይረዱትም፡፡ እንኳን ሕዝበ ክርስቲያኑ ካህናቱም ቢኾኑ ጥሬ ቃሉን ከማንበብና ከማዜም ያለፈ ትርጉሙንና ምሥጢሩን ከሚረዱት ይልቅ የማይረዱት ያመዝናሉ፡፡ ቅኔው በግእዝም፣ በአማርኛም ቢዥጎደጎድም ከማስገረምና ከማስደነቅ ብሎም ከፍልስፍና አልፎ አንድ አማኝ ሊያስገኝ አይችልም፡፡

ከስድሳ ስድስት ዓመተ ምሕረት ወዲኽ፣ “እግዚአብሔር የለም” ተብሎ የተሰበከለት ትውልድ እስከ አኹን ድረስ በእግዚአብሔር አልባነቱ ጸንቶ በግማሽ ምእት ዓመት የዕድሜ ክልል(ደረጃ) ላይ ይገኛል፡፡ በአኹኑ ጊዜም ያለው ትውልድ በተሰጠው ገደብ የለሽ የሃይማኖት ነፃነት መሠረት÷ በዛፉ፣ በቅጠሉ፣ በወንዙ፣ በሣሩ፣ በጨሌው፣ በቦረንትቻው ሲያመልክ ይስተዋላል፡፡ የፈለጉትን ሃይማኖት መከተልና ጨርሶ አለማመንም መብት ኾኖ ተፈቅዷል፡፡ ይህንንም የአምልኮ ባዕድ ተግባር ቤተ ክርስቲያን ዝም ብላ የምትመለከት ከኾነ፣ የክርስትና ሕይወት የሚያዘውን ግዴታ ልትወጣ ያልቻለች ትርጉም አልባ ተቋም ልትባል ትችላለች፡፡

እንደዚያም ኾኖ በአኹኑ ጊዜ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር፣ ማለት በአፍሪቃ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ በዐረብ አገሮችም ጭምር የቤተ ክርስቲያናችን አህጉረ ስብከት እየተበራከቱ ሔደዋል፡፡ የውስጦችም የውጮችም የእምነቷ ተከታዮች የአባቶች ያለኽ እያሉ ነው፡፡ በዚያው ላይ “ከአባ ቁፍር እሸት ተበልቶላት” እንዲሉ በውጭ ያሉ የአባቶቿ መከፋፈል እንዳለ ኾኖ ነው፡፡

ይህ በእንዲኽ እንዳለ፣ አንዱ የእምነት ተቋም ከሌላው የእምነት ተቋም በረት ገብቶ በጎችን እንዳይቀስጥ የተላለፈው ዓለም አቀፍ ድንጋጌ ተጥሶ፣ በአኹኑ ጊዜ የተለመዱት የውጭ ተኩላዎች በክፍተቱ ተጠቅመው ከበረቷ ውስጥ በመግባት በጐቿን እየተቀራመቱባት ነው፡፡ የውጭ ተኩላዎች ብቻ ሳይኾኑ የውስጥ ተኩላዎችም ለሃይማኖት መስፋፋት አስበው ሳይኾን ጥቅሟን ለመቦጥቦጥ ሲሉ እጅግ ተበራክተዋል፡፡ የስም አባሎቿ ኹሉ እንዳሉ ተኩላዎች ኾነው ተነሥተውባታል፡፡ ቤተ ክርስቲያን፣ ፈላስፋው፥ “የማውቀውን ጠላቴን እኔ እጠብቀዋለኹ፤ አንተ ግን እኔ ከማላውቀው ከወዳጅ ጠላቴ ጠብቀኝ” በማለት ለፈጣሪ ያቀረበውን ጸሎት ከምታቀርብበት ጊዜ ላይ ደርሳለች፡፡

ታዲያ በዚኽ ጊዜ፣ በአባቶች እግር አባቶችን መተካት ግዴታ ቢኾንም በጐች በበጐች ላይ እንዳይሰማሩ ማለት ጠባቂዎችም ተጠባቂዎችም አንድ ዓይነት እንዳይኾኑ ከአለፈው ተሞክሮ በመውሰድ፣ “እንደ በጐች በተኩላዎች መካከል አሰማራችኋለኹ” በተባለው መሠረት፣ በትምህርት ብቃታቸው ከተኩላዎች ጋር ግብግብ በመግጠም፣ በጐችን ከነጣቂ ተኩላዎች ማዳን የሚችሉትን፤ “ብርሃናችኹ በሰው ፊት ይብራ” በተባለው መሠረት፣ ዕውቀት ቢኖራቸውም የጋን መብራት ሳይኾኑ የሕዝብ መብራት የኾኑትንና፤ “ቸር እረኛ ነፍሱን ለበጐቹ አሳልፎ ይሰጣል” የተባለውን ቃል ተግባራዊ በማድረግ ነፍሳቸውን ለበጐቻቸው አሳልፈው የሚሰጡትን፣ ለይቶ ማየትና መምረጥ ያስፈልጋል፡፡

ከዚኽም በቀር፣ ራሳቸው ከሕዝቦች ጋር የሚጋጩትን ሳይኾን “ብፁዓን ገባርያነ ሰላም፤ ሰላምን የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው፤” የተባለውን ቃል በተግባር በመተርጎም በተጋጩት ሕዝቦች መካከል እየተገኙ የሚያስታርቁትን፤ ማዕተብ የሚያስበጥሱትን ሳይኾን ማሳሰር የሚችሉትን፤ “አባቱንና እናቱን በጠቅላላው ቤተሰቡን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም” የተባለውን አምላካዊ ቃል በመተግበር፣ ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ለቤተሰብ የማያዳሉትን፤ ቅድስናቸውንና የሕዝብ ተደራሽነታቸውን በተግባር ያረጋገጡትን በጠቅላላው ለወዲያኛው ዓለም እንጂ ለዚኽ ዓለም የማይገዙትን ቆሞሳት በውስጥም በውጭም አስሶ፣ ያለአንዳች አድልዎ አጣርቶና መርምሮ ዕውቀታቸውን አገልግሎታቸውንና ቅድስናቸውን ሳያጋንኑም፣ ሳያኮስሱም በሰውና በእግዚአብሔር ፊት አቅርቦ በመምረጥ ቤተ ክርስቲያን ከደረሰባት አደጋ መታደግ የወቅቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ሓላፊነትና ተጠያቂነት ነው፡፡

ለዚኽ ኹሉ አንዱ መፍትሔም፣ የቀድሞው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ስለ ጳጳሳት ምርጫ ባወጣው መስፈርት መጠቀምና እንደ ቀድሞው ካህናቱንና ሕዝበ ክርስቲያኑን የምርጫው ተሳታፊ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ሲኾን ብቻ ነው፣ በጐች በበጐች ላይ እንዳሰማሩ ማድረግ የሚቻለውና በቅዱስ ሲኖዶስ ላይ ብቻ የሚወረወረውን ትችት ካህናቱም፣ ሕዝበ ክርስቲያኑም ሊጋሩት የሚችሉት፤ ከኹሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ ኹሉም ሊጸልይ ይገባል፡፡

Advertisements

6 thoughts on “በኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ: “በጐች በበጐች ላይ እንዳይሰማሩ”:-ካህናቱንና ምእመናኑን ማሳተፍ፤ ከኹሉም በላይ መንፈስ ቅዱስ እንዲመርጥ መጸለይ ይገባል/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

 1. girum June 12, 2016 at 6:43 pm Reply

  ለታላቁ ሊቅ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ቃለ ዓዋዲ ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እድሜ ጤና እመኝለው።

 2. teddy June 13, 2016 at 8:25 am Reply

  አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አምላከ ቅዱስ ያሬድ አምላከ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ይጨመርበት!!!

 3. Tourist Dilla June 13, 2016 at 9:27 am Reply

  Yemenafkan shemparara lisan tebye sianbarkbet “amen Eyesus geta new” yemil yemenafkan lisan “Ge’ez metekemia yelebachihum” lemalet yemoral bikat yelewum

 4. Anonymous June 13, 2016 at 10:56 am Reply

  ለታላቁ ሊቅ መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ቃለ ዓዋዲ ዘኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እድሜ ጤና እመኝለው

 5. Habte Yohanes June 14, 2016 at 2:23 pm Reply

  look at the editorial of ZENA BETECHRISTIAN!
  we are not old to accept:-
  -mahelet
  -kidase
  -tamer
  -gedle
  -satat

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: