ቅ/ሲኖዶስ: ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፥አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ ዳንኤልና አቡነ ኄኖክ ተጨማሪ ምደባዎች ሰጠ

 • ጁባ፣ ካርቱም፣ ግብጽ፣ እንግሊዝና አውስትራልያ ይገኙበታል
 • በእጥረቱ መነሻነት በጊዜያዊነት የተደረጉ ምደባዎች ናቸው
additional placements of their graces the archbishops

በምልዓተ ጉባኤው ተጨማሪ ምደባዎች የተሰጧቸው ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት(ከግራ ወደ ቀኝ)፡- ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፣ ብፁዕ አቡነ ዳንኤልና ብፁዕ አቡነ ኄኖክ

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ በዛሬው፣ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው፣ ለአምስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተጨማሪ አህጉረ ስብከት ምደባዎችን ሰጥቷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ “በውጭ ያሉ አህጉረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት በሌሉባቸው ተደርበው እንዲሠሩ” በሚል በተ.ቁ(18) በያዘው አጀንዳ መሠረት፣ የሰጣቸው ተጨማሪ ምደባዎች፣ ባለው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት እጥረት ሳቢያ በጊዜአዊነትና በፈቃደኛነት ላይ ተመሥርቶ የተደረገ መኾኑ ተገልጧል፡፡

በዚኽም መሠረት፡-

 • በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፡- የትንሣኤ ዘጉባኤ ማተሚያ ቤት የበላይ ሓላፊ፤ የሰሜን ሱዳን(ካርቱም) እና ግብጽ አህጉረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ፤
 • የጅማ፣ ኢሉ አባ ቦራ እና ጋምቤላ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፡- የደቡብ ሱዳን(ጁባ) ሀገረ ስብከት ደርበው ይመራሉ፤
 • የደቡብ፣ ደቡብ ምሥራቅና ደቡብ ምዕራብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሙሴ፡- የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ አህጉረ ስብከት ደርበው ይመራሉ፤
 • የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል፡- የምሥራቅ አፍሪቃን ማለትም የጅቡቲ እና ኬንያ አህጉረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ፤
 • የአሶሳ፣ ምዕራብ ወለጋ እና ቄለም ወለጋ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኄኖክ፡- የአውስትራልያ አህጉረ ስብከትን ደርበው ይመራሉ፤

ምልአተ ጉባኤው በተጨማሪም፣ ከጥቂት ወራት በኋላ እንደሚያካሒደው በሚጠበቀው የአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ላይ መክሮ በጥቆማውና በምርጫው ጉዳይም ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል፡፡

ለብፁዓን አባቶቻችን፣ መልካም የአገልግሎት ጊዜ እንመኝላቸዋለን፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ይከታተሉ

 

Advertisements

4 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ: ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፥አቡነ ሉቃስ፣ አቡነ እስጢፋኖስ፣ አቡነ ሙሴ፣ አቡነ ዳንኤልና አቡነ ኄኖክ ተጨማሪ ምደባዎች ሰጠ

 1. Anonymous June 6, 2016 at 3:52 pm Reply

  የተጠቆሙ መነኮሳትንና ቆሞሳትን አሳውቁን

  • Anonymous June 7, 2016 at 8:29 am Reply

   እነማናቸዉ የተጠቆሙ

 2. Anonymous November 2, 2016 at 7:00 am Reply

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: