ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፤ ዕጩዎች በሠሩባቸው ቦታዎች ካህናትንና የሰንበት ት/ቤቶችን ያነጋግራል

 • በሃይማኖት አቋም፣ በሥነ ምግባር፣ በሥራ አመራር እና አፈጻጸም ይገመገማሉ
 • ካህናትና ምእመናን ከሢመቱ በፊት “ይገባዋል” ሲሉ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል
 • በተሐድሶ ኑፋቄ ቅጥረኝነትና በሲሞናዊነት ለመሸመት ካሰፈሰፉት እንጠብቀው

*               *               *   

Synod Tik2008

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ

የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤውን እያጠናቀቀ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በዛሬው፣ ግንቦት 29 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በፊት ውሎው፣ ተጨማሪ ኤጲስ ቆጶሳት አስፈላጊ መኾናቸውን በማመን አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፤ ለሹመቱ በሚጠቆሙና በሚመረጡ መነኰሳትና ቆሞሳት ጉዳይም መመሪያ ሰጠ፡፡

በመመሪያው መሠረት ቆማው፥ የማኅበረ ካህናትን፣ የሰንበት ት/ቤቶችንና የማኅበረ ምእመናንን ተሳትፎ ባረጋገጠ ግልጽነት እንዲፈጸም ያሳሰበው ምልዓተ ጉባኤው፤ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት የሚገኙበት፣ ሰባት አባላት ያሉበት የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አስመራጭ ኮሚቴ መሠየሙ ታውቋል፡፡

በዚኽም መሠረት በአስመራጭነት የተሠየሙት ብፁዓን አባቶች፡-

 1. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ
 2. ብፁዕ አቡነ ገሪማ
 3. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
 4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
 5. ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
 6. ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
 7. ብፁዕ አቡነ አብርሃም
 8. የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በአስረጅነት ናቸው፡፡

የኮሚቴው አባላት፣ ተጠቋሚ ዕጩዎች በሠሩባቸው አህጉረ ስብከት፣ አጥቢያዎች፣ ድርጅቶችና ተቋማት እየተገኙ፣ አስፈላጊውን ማጣራት የሚያካሒዱ ሲኾን፤ ከሃይማኖት ሕፀፅ፣ ከሥነ ምግባር ጉድለት፣ ከሥራ አመራርና አፈጻጸም አኳያ ጥብቅ ማጣራት እንዲደረግ መመሪያ ተሰጥቷል፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት፣ በኤጲስ ቆጶስነት የሚሾሙት፣ ካህናት እና ምእመናን ይገባዋል ብለው የመሰክሩላቸው መነኰሳትና ቆሞሳት በመኾናቸው፣ ከሢመቱ በኋላ እርባናና ተቀባይነት የሌለው ሐሜትና ተቃውሞ ከማንሣት፣ በጥቆማው ሒደት በሚደረግ ግምገማ እና ምዘና ከምር የኾነ ንቁ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

የመዓርግ ክህነት የመጨረሻ ደረጃ የኾነው የኤጲስ ቆጶሳት ሹመት፣ በከፍተኛ መስፈርትና ጥንቃቄ እንዲኾን መደረጉ፡- ተሿሚዎች ከተጣለባቸው አደራና ከሚሰጣቸው ሓላፊነትና ታላቅነት የተነሣ ነው፡፡

ኤጲስ ቆጶሳት፡-
 • እግዚአብሔር በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን ይጠብቃሉ(የሐዋ ሥራ 20፥28)
 • የእግዚአብሔር ምሥጢር መጋቢዎች ናቸው(1ቆሮ.4፥1)
 • የቤተ ክርስቲያን ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ጠባቂዎች ናቸው((2ተሰ.3፥6)
 • ምእመናንን ከመናፍቃን ቅሰጣ የሚጠብቁ ናቸው(ዮሐ.21፥15-17)

ለመኾኑ ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት፣ ፍትሐ ነገሥቱ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንና ሕጉን መሠረት አድርጎ በቅዱስ ሲኖዶስ የወጣው መስፈርትና የምርጫ ሥርዓት ደንብ ምን ይላል? በሲሞናዊነትና በጎጣዊ መሳሳብ ሹመቱን ለመሸመትና በቤተ ክርስቲያን ላይ እንደ መዥገር ለመጣበቅ፤ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ቅጥረኝነት የቤተ ክርስቲያንን ማንነትና ማዕከላዊ አንድነት ለማናጋት ያሰፈሰፉትንስ እንዴት እናጋልጣቸው?

 

 

 

Advertisements

10 thoughts on “ሰበር ዜና – ቅ/ሲኖዶስ: የኤጲስ ቆጶሳት አስመራጭ ኮሚቴ ሠየመ፤ ዕጩዎች በሠሩባቸው ቦታዎች ካህናትንና የሰንበት ት/ቤቶችን ያነጋግራል

 1. teddy June 6, 2016 at 1:40 pm Reply

  ከሁሉ በላይ ማዕምረ ኅቡዓት የሆነ የእረኞች አለቃ ጌታ መድኃኔዓለም እሱ የወደደውንና የፈቀደውን መልካሙን እረኛ ይምረጥልን!!!

 2. Anonymous June 6, 2016 at 2:50 pm Reply

  ምን ቀራችሁ? ሁለንም ተሐድሶ ብላችሁ ፈርጃችኋል ተሐድሶ ያልተባሉት መሿሚያና ፀናፅል ብቻ ናቸው ጳጳሳቱን መነኮሳቱን መምህራኑን ቀሳውስቱን ሁሉ ተሐድሶ ናቸው ካላችሁ ማን ቀረ? አሁን እኮ ግንቡና ማቴርያሉ ብቻ ነው የቀራችሁ በእርግጥ አንዳንድ ድንኳን ሰባሪ ለፍርፋሪ ብሎ የተጠጋችሁ ወይባ ለባሽ አታጡም እንደው አሁንማ ተሐድሶ ብላችሁ ልትሞቱ ነው ይልቁኑ ከክፉ ሥራችሁ ብትታደሱ ይሻላችሁ ነበር ቅራቅምቦ ከምታራግቡ።

  • ዳሞት June 7, 2016 at 6:06 pm Reply

   ለanonymous Jun 6,2016 at 2:50pm

   በመጀመሪያ የግንዛቤ አድማስህን አስተካክለው። ለመናገርና ለመውደቅ ከመጣደፍህ በፊት ተረጋግተህ ሥለሚነገረው( እየተባለ) ሥላለው አድምጥ(ሥማ)። በልቅ ንግግርህና ሥሜትህ ተደነቃቅፈህ ከመውደቅህ በፊት የምትናገረውን አሥተውለው። በስንዴው መካከል እንክርዳድ ተገኘ ማለት ሥንዴውም እንክርዳድ ነው ማለት አይደለም። ማንነትህ ባዶ ሥላሥቀረህ ሁሉም ተሐድሶ ተብሏል እያልክ ከመስማት ይልቅ ያልተገነዘብኸውን ለመናገርና ተደነቃቅፈህ ለመውደቅ ትማስናለህ። ከእውነት የተጣላና ለወሬ የሚሮጥ ወደቀ ሲባል ተሰባበረ፣ ታመመ ከተባለ ሞተ ነውና የሚሉ አንተም አንዱ ነህ።
   ወንድም፦ አይነልቦናህ በምትሐት ታውሮ አይንህን ጨፍን ሥትባል የምትጨፍን ፤ እጅ ለእጅ ተያያዝ ካለበለዛ መንፈሱ አይወጣም ሥትባል የምትያያዝ መንፈስን መመርመር የማትችል ሆነህ ሳለ በሌሎች ቤተ እምነት ምን ጥልቅ አደረገህ የወተት ዝንብ ካልሆንክ በስተቀር። ቤተ መቅደሱ ግንብ ብለህ የምታቃል ባዶ ቆርቆሮ መሆንህን ያሳብቅብሃል።

 3. fkremarkos stotawu June 6, 2016 at 10:13 pm Reply

  ብዙዎቻችን አባ ሰላማ ከተሳደበ እየተረዳን ያለነው አሁን ያ ስሙ የጠፋው አካል በትክክል ቤተክርስቲያንን ጠቅሟል መለት ነው ለዘህ ደግሞ ማሳያ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ናቸው ገና ሳይሾሙ ጀምሮ በሬ ወለደ ዘመቻወን ተያይዞታል በጣም የሚያሳዝነው በዚህ ብሎግ እንደህ ተባለ ብሎ የሚያራግብ አንዳንድ ሰው መነሳቱ ነው ይህ ደግሞ እራሱ ሰውየው የተሃድሶ መንፈስ አለበት ማለት ይቻላል አንዱም ማሳያ ነው አቡነ ሳዊሮስ መበርታት አለባቸው ስራቸው ፍሬ ማፍራቱን ተረድተናል

  • Anonymous June 7, 2016 at 11:18 am Reply

   Leortodox tewahido lijoch hulu BEAHUNU YEKIDUS Raguel Astedadari aba zeradagut bole EYALU yebeteserategna huge kmiserabet yepailet bet mistin yegbre sign tsifetsimu aychalehu yemiyazaznew eswanymtakyi Canada hida beneberechibet seat Bet endtitebik yemetach talak Ehitm betebel amakagnitw Wesib Fetsemubat keza ken jemiro behaymanote Tritare adrobignal addera papas endayhon adrgi we let maryima

   • Anonymous June 8, 2016 at 11:47 am

    ምርጥ አለቅላቂ ወሬኛ አሉባልተኛ አነካኪ የጦም እቃ ነህ ማንነትህ የማይታወቅ ወንበዴ ስለሆንክ ምን ብታወራ አናምንህም የሆንክ ባዶ ቅል እራስ፡፡

  • Anonymous June 7, 2016 at 3:10 pm Reply

   ስለ ኣባ ሳዊሮስ ንጽህና ሙሉ ልሙሉ አርግጠኛ ነህ ? ወይስ ማህብሩ ለምን ተነካ ነው?
   ንጹህ ከሆኑ አሰይ።

 4. Anonymous June 7, 2016 at 5:35 am Reply

  ቅዱስ መንፈስ ጰራቅሊጦስ መልካሙን እረኛ ይሹምልን

 5. Anonymous June 7, 2016 at 9:56 am Reply

  እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያን የሚበጃትን ያድርግ ምክንያቱም እኛ ሰዎች ዛሬ የመረቅነውንና ያፀደቅነውን ነገ እንረግመዋለን እናዋርደዋለን እንኮንነዋለን እሱ ግን የመረጠውን ያፀድቃል እስከመጨረሻውም ከሱ ጋር ይሆናል ወረት በባህሪው የለበትምና

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: