ፓትርያርኩ: የምልዓተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ ለዋና ሥራ አስኪያጅነትና ለዋና ጸሐፊነት ያቀረባቸውን ዕጩዎች አልቀበልም በማለታቸው ሒደቱ ተስተጓጎለ

Aba Mathias

 • ሕግ አፍራሽነት፣ የአማሳኞችና የጨለማ ቡድን አስፈጻሚነትና ቂመኝነት መርሓቸው ኾኗል
 • ከአመራራቸው ጋር በተያያዙ ወሳኝ አጀንዳዎች በተቿቸው አባቶች ላይ ቂማቸውን አሳይተዋል
 • ከቀረቡት ዕጩዎች፣ አቡነ ዲዮስቆሮስንና አቡነ ሳዊሮስን “ይውጡልኝ” ሲሉ ሒደቱን አውከዋል
 • ምልዓተ ጉባኤው መርጦ ለሚሠይማቸው የሹመት ደብዳቤ መስጠት እንጂ መቃወም አይችሉም
 • ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴን የበላይ ጠባቂነት ተመድበዋል

*                *                *

በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን እንደተደነገገው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኾነው የሚመረጡት ብፁዓን አባቶች የአገልግሎት ዘመን ለሦስት ዓመታት ነው – በአንቀጽ 24/4 እና አንቀጽ 43/3 እንደተደነገገው፡፡

በየሦስት ዓመቱ ለሚካሔደው ምርጫ፣ በምልዓተ ጉባኤው የሚሠየም አስመራጭ ኮሚቴ፣ የሥራ አመራር ልምድንና ችሎታን መሠረት አድርጎ ሦስት ተወዳዳሪዎች በጉባኤው እንዲጠቆሙ ካደረገ በኋላ፣ ምርጫው በምስጢር ድምፅ አሰጣጥ ሥርዓት ተከናውኖ ከፍተኛ ድምፅ ያገኘው ብፁዕ አባት በዋና ጸሐፊነት እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት ይሠየማል፡፡ ይህም ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ፈርመው በሚሰጧቸው የሹመት ደብዳቤ ይገለጻል፡፡

በዋና ጸሐፊነት እና በዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት ብፁዓን አባቶች የአገልግሎት ዘመን ለሦስት ዓመታት ብቻ ይኹን እንጂ፤ አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘ ለአንድ ተጨማሪ የሥራ ዘመን ብቻ እንደገና እንዲያገለግሉ ሊመረጡ ይችላሉ፡፡

his grace the gen sec abune lukas and his grace the gen mgr. abune mathewos
በጥቅምት 2006 ዓ.ም. በቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊነት የተመረጡት፣ በክልል ትግራይ የምዕራብ ሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ለዋና ሥራ አስኪያጅነት የተመረጡት የወላይታ ኮንታና ዳውሮ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፤ የአገልግሎት ዘመን የሚያበቃው በዘንድሮው ዓመት በመኾኑ፣ የተተኪዎቹ ምርጫ ከምልዓተ ጉባኤው አጀንዳዎች አንዱ ኾኗል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ በዛሬ፣ ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. የቀትር በኋላ ውሎው፣ በተ.ቁ(20) ለተቀመጠው የምርጫ አጀንዳ አፈጻጸም አምስት አባላት ያሉበት አስመራጭ ኮሚቴ የሠየመ ሲኾን፤ ኮሚቴውም ለዋና ጸሐፊ ሦስት፣ ለዋና ሥራ አስኪያጅ ሦስት ዕጩዎችን በጥቆማ በመለየት ለምልዓተ ጉባኤው አቅርቧል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገብርኤልን፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስን፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስንና ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን በአስመራጭነት የያዘው ኮሚቴው ለዋና ሥራ አስኪያጅነት በዕጩነት ያቀረባቸው ብፁዓን አባቶች፡-

the three nominees to the gen mgr position

 • ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፤ የደቡብ ትግራይ – ማይጨው እና የምሥራቅ ትግራይ – ዓዲ ግራት አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
 • ብፁዕ አቡነ አብርሃም፤ የባሕር ዳር፣ ምዕራብ ጎጃም፣ አዊ እና መተከል አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤
 • ብፁዕ አቡነ ያሬድ፤ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ እና የሱማሌ እና የአርሲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ኮሚቴው ለዋና ጸሐፊነት በዕጩነት ያቀረባቸው ሦስት ብፁዓን አባቶች ደግሞ፡-

their graces the nominees for the gen sec position

 • ብፁዕ አቡነ ኤልያስ – የሰሜን ኦሞ እና ደቡብ ኦሞ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
 • ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ – የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወሊሶ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
 • ብፁዕ አቡነ ኄኖክ – የምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋና አሶሳ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ አንቀጽ 17 ንኡስ አንቀጽ 14 መሠረት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ከዕጩዎቹ የመምረጥና የመሠየም ተግባርና ሓላፊነት ያለው ቢኾንም፤ ምልዓተ ጉባኤውን በርእሰ መንበርነት የሚመሩት ፓትርያርኩ፣ ኹለት ዕጩዎችን ካላስወጣችኹልኝ በማለታቸው ለዕለቱ የተያዘው የምርጫ ሒደት መስተጓጎሉ ተገልጧል፡፡

ፓትርያርኩ “ከምርጫ ውድድሩ ይውጡልኝ” ያሏቸው፣ ለዋና ሥራ አስኪያጅነት ከቀረቡት ዕጩዎች ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስን ፤ ለዋና ጸሐፊነት ከቀረቡትም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስን እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ “አስመራጭ ኮሚቴው በሕጉ መሠረት ያቀረባቸው ናቸው፤ አይወጡም” በሚል ቢቃወማቸውም ፓትርያርኩ አቋማቸውን ባለማለዘባቸው ወደ ድምፅ አሰጣጡ ለመቀጠል ሳይቻል ጉዳዩ በይደር ለነገ ተላልፏል፡፡

ፓትርያርኩ እንደ ርእሰ መንበርነታቸው፣ ጉባኤውን ከመምራት ባለፈ ተቃውሟቸውን/ልዩነታቸውን በምርጫው ሥርዓት መሠረት በሚሰጡት ድምፅ መግለጥ ሲገባቸው፣ ካልወጡልኝ በሚል ሒደቱን በቂመኝነት ማወካቸውና ማስተጓጎላቸው፤ ሕገ አፍራሽነትንና ቂመኛነትን መርሓቸው አድርገው መቀጠላቸውንና ከኹሉም በላይ ደግሞ፣ አማሳኞችና የጨለማው ቡድን ከምርጫው አንፃር በሚያካሒዱት እንቅስቃሴ ተጽዕኖ ውስጥ እንደወደቁ ማረጋገጫ ተደርጎ ተወስዷል፡፡

በየደረጃው ከሚካሔድ የሓላፊዎች ምርጫና ምደባ ጋር በተያያዘ፣ ፓትርያርኩ የሚፈጽሟቸው መተላለፎች እየተበራከቱ ሲኾን፣ ለአብነትም፡- ቀደም ሲል ለአዲስ አበባ ሀ/ስብከት በቅ/ሲኖዶሱ የተመደቡትን ረዳት ሊቀ ጳጳስ ሓላፊነት በመጋፋት የሥራ አስኪያጆችና የዋና ክፍል ሓላፊዎች ሹም ሽር ማድረጋቸው፤ ይባስ ብለው በቅ/ሲኖዶሱ ከተመደቡት ይልቅ ሌላ ሊቀ ጳጳስ ለሒሳቡ እንቅስቃሴ ፈራሚ ማድረጋቸው፤ ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ዕውቅና ውጭና የዋና ሥራ አስኪያጁን ሥልጣንና ተግባር በመጋፋት ሓላፊዎችን ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ማዘዋወራቸውና ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ያነሧቸውን በጠቅላይ ጽ/ቤቱ መምሪያዎች ላይ መመደባቸው በጉልሕ ይጠቀሳሉ፡፡

በዛሬውም የጉባኤው ውሎ ፓትርያርኩ፣ ከዕጩነት ይውጡልኝ ያሏቸው ብፁዓን አባቶች ከቂመኛነትም በላይ፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጅ ብሎጎችም የጥቃት ዒላማ መኾናቸው ሲታይ(የአገልግሎት ዘመናቸውን ባገባደዱት ብፁዕ አቡነ ሉቃስ እና ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ላይ ሲፈጸሙ እንደነበረው)አማሳኞችና የጨለማው ቡድን ከኑፋቄው ወኪሎች ጋር ተሳስረውና ተመጋግበው በዙሪያቸው ለፈጠሩት የተጽዕኖ ክበብ ማደራቸውን ከጥርጣሬም በላይ ያደርገዋል – “እንኳን እነዚኽን ሾመን አባ ሉቃስ እና አባ ማቴዎስም ሦስት ዓመት ሙሉ አላሠራ ብለውኛል፡፡”

ብፁዕ አቡነ እንድርያስ

ፁዕ አቡነ እንድርያስ፤ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ እና የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ

በተያያዘ ዜና፣ ምልዓተ ጉባኤው በዛሬው ውሎው፣ የሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ሓላፊ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፣ ከቀድሞው የደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከታቸው በተነሡበት ኹኔታ ያቀረቡትን ጥያቄ የተመለከተ ሲኾን፤ ጉዳዩ የመጨረሻ ምላሽ እስኪሰጠው ድረስ፣ ብፁዕነታቸው ከያዙት ሓላፊነት ጋር፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ በነበሩበት የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የበላይ ጠባቂ አድርጎ እንደመደባቸው ታውቋል፡፡

*                *                *

ማረሚያ፡- በዚኹ ዘገባ በምልዓተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ ለዕጩነት የቀረቡት ብፁዓን አባቶች ስም ሲዘረዘርና ሲጠቀስ፣ ለዋና ጸሐፊነት፥ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ እንደተጠቆሙ፤ ለዋና ሥራ አስኪያጅነት፥ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እንደተጠቆሙ ቀደም ሲል ተገልጧል፡፡

ይኹንና ዕጩዎቹ የቀረቡበት ሓላፊነት ሲዘረዘርና ሲጠቀስ በመዘዋወሩ፥ ለዋና ሥራ አስኪያጅነት የተጠቆሙት፥ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም እና ብፁዕ አቡነ ያሬድ እንደኾኑ፤ ለዋና ጸሐፊነት የተጠቆሙትም፤ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ አቡነ ኄኖክ እንደኾኑ እየገለጽን በአቀማመጡ መዘዋወር ለተፈጠረው ስሕተት ከፍ ያለ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡  

 

Advertisements

15 thoughts on “ፓትርያርኩ: የምልዓተ ጉባኤው አስመራጭ ኮሚቴ ለዋና ሥራ አስኪያጅነትና ለዋና ጸሐፊነት ያቀረባቸውን ዕጩዎች አልቀበልም በማለታቸው ሒደቱ ተስተጓጎለ

 1. Anonymous June 3, 2016 at 4:13 am Reply

  ኧረ ጉድ ነው ኧነኚ ሰዎች ጨርቃቸውን ሊጥሉ ነው

 2. g June 3, 2016 at 4:39 am Reply

  እኔ የሚገርመኝ እኝህን ሰው ለምንድነው ቅዱስ ሲኖዶሱ ከፓትርያሪክነት የማያነሣቸው? ከአንድ ፓትርያሪክና ከቤተ ክርስቲያን ማን ይበልጣል? ሕገ ቤተ ክርስቲያንን እየጣሱ፤ ከሲኖዶስ በላይ ነኝ እያሉ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ በጠቃሚ አጀንዳዎች ላይ እንዳይወያይ በየጊዜው ንትርክ እየፈጠሩ፣ የኦርቶዶክሳውያንን ሳይሆን የመናፍቃንንና የአማሳኞችን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተጉ ይኖሩ ዘንድ የሚፈቀድላቸው እስከመቼ ነው? በሕጉ መሠረት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ህልውና ሲባል ለምን እንዲገለሉ አይደረግም? ቅዱስ ሲኖዶሱስ እስከመቼ ነው ጥርስ የሌለው አንበሳ ሆኖ የሚዘልቀው?

 3. Anonymous June 3, 2016 at 5:56 am Reply

  እኚህ ሰው የቀበሌ ምርጫ አደረጉት እንዴ ነው እርሳቸውም ተሀድሶ ናቸው

 4. Anonymous June 3, 2016 at 7:12 am Reply

  muach ke memotu befit yinkejekej Neber….

 5. Anonymous June 3, 2016 at 8:28 am Reply

  ሲነቃም እኮ ቀራል

 6. bishsite June 3, 2016 at 9:21 am Reply

  በመንፈስ ቅዱስ መመራት ቀርቶ የራስንና የአፍራሾችን ሃሳብ ማራመድ ለአለም ሙት ከሆነ መንጎቹን ሊጠብቅ ከተሾመ ፓትርያሪክ አይጠበቅም።እግዚአብሔር ተዋጊ ነው።ከማን ጋር ውጊያ እንደጀመሩ ያወቁ አይመስለኝም።ተዋህዶ ሁሌም በእግዚአብሔር ጥላ ስር ናት ተቃውሞአቸውን ከቀጠሉ ከእግዚአብሔር ቁጣ አያመልጡም።

 7. TEWAHIDO KIDIST June 3, 2016 at 9:49 am Reply

  I THINK THE PATRIARICH IS GETTING CRAZY – we should pray foe him – he is not above the synod

 8. Anonymous June 3, 2016 at 10:39 am Reply

  God with us

 9. Abebe Bizuye June 3, 2016 at 10:55 am Reply

  Good news

  Sent from Yahoo Mail on Android

 10. Anonymous June 3, 2016 at 11:25 am Reply

  እግዚአብሔር ቀን አለው ፣ ሁሉንም ዋጋ ይሰጣል፡፡ ዝም አይልም ይፈርዳል ፣ ያጸዳል ፣ጅፉን ሲያነሳ አያድርስ ነው፡፡ ብዙ ብዙ ነገር አይተናል እኛ ግን ቅዱሳን ፣ሰማዕታት ፣ሐዋርያት ደማቸውን ያፈሰሱባት ፣ አጥታቸውን የከሰከሱባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመሆኑዋ በጸሎት እንበርታ፡፡

 11. Anonymous June 3, 2016 at 2:01 pm Reply

  please believe in Jesus, He is the way, the truth and the life. and መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።

  And there is salvation in no one else, for there is no other name under heaven given among men by which we must be saved Jhon 14,6 and acts 4:12.

  please leave other things just follow Jesus, He is enough

 12. Anonymous June 3, 2016 at 9:25 pm Reply

  Jesus is the lord and the saints angels are his ministers. and the quin is our blessed mother of God vergin Mary. All of them are with us!!! Our Orthodox church is lucky so do we

 13. Senait Aregawi June 4, 2016 at 9:32 am Reply

  እንደኔ ይህን የመእመኑን ልብ የሚያሳዝን እንዲሁም ልብ የሚያሸፍት ዘገባ ሳአነብ ውስጤ ነው የአዘነው ከዛበተፃራሪ ደግሞ ጮቤ የሚረግጡም አሉ የዝች ጥንታዊት ቤተ -ከርስቲያን የመበታትን ህልም የሚያልሙ በከፍተኛ የትጥቅ ትግል ዘመቻ ድፋቀና የሚሉ እንዳሉ ግምት ውስጥ በማስገባት ግጭት ሊኖር ግድ ነው። ምክንያቱም ግጭት እና ስላም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው እና ከሹመት ወይም ከወንበር ነፋቄ እንዲሁም ከዘረኝነት ካንስር ከቂምበቀል የፀዳችሁ ብትሆኑ ተከታዮቻችሁንም እያበዛችሁ ትሄዳላችሁ ካልሆነ ቤተ-በክርስቲያኗን እረኛ የሌለው መንጋ እንዳታድርጔት ከዘገባ በፊት እርስ በርሳችሁ ግለሂስ አደርጉ ተወቃቀሱ በድያለሁ ይቅር በለኝ በድለህኝ ነበር ይቅር ብየኃለው ተባባሉ ሶስተኛ ወገንም በመጨመር ከመሿሿማችሁ በፊት ፆም ይዞ ፀሎት ቂም ይዞ ፅድቅ የለም እያላችሁ እባታዊ አስተምህሮ አልስበካችሁንም አንድ ወግ ልንገራችሁ እንዲህ ነው ዘመናዊ ት/ት ነው አስተማሪ አንዲት ተማሪያቸው ከተማሪ አለባበስ
  ወጣ ያአለ አለባብስ ስለለብሰች ወላጅ እንድታመጣ ይነግራታል በማግስቱ እናት ሽክ ብላ ከልጅቱ አለባበስ ወጣ ያአለ አለባበስ ለብሳ
  ወደ ት/ት አስተማሪም የልጅቱን ወላጅ አለባበስ እንዳየ ትቸዋለሁኝ ወደ ቤተዎ ይመለሱ አላቸው አሉ ምን ለማለት ፈልጌ ነው እርስ በርሳችሁ የሐጥያት መረብ ውስጥ እየተርመሰመሳችሁ መርባችሁ ውስጥ ማን ሊገባ ይችላል ለምሳሌ በስደት በምኖርበት አገር ቤተክርስቲያን መሄድ ልቤ አልፈቅድ አለ የዘረኝነት ነቀርሳው በስፋት ሰለሚስተዋል በአገር ላይ ስትመለከት ደግሞ በጣም ያማል ባይታወር ትሆናለህ ለማንኛውም
  እግዚአብሔር በኦርቶዶክስ መእመናን መካከል ፍቅርን ሰላምን ያብዛልን ለሐይማኖት አባቶቻችንም የምድሩን ሳይሆን የሰማዩን ሹመት በማሰብ መእመኑን እንዲታደጉት የእግዚአብሔር
  ፍቃድ ይሁን። አሜን አሜን አሜን

 14. Anonymous June 4, 2016 at 3:57 pm Reply

  kadirewin ke betchirstiyan nekilen yeminawetabet ken derswal beritu

 15. Anonymous June 6, 2016 at 3:53 pm Reply

  Egzyabern feru beza egzyaber ferdun ysetote kalfewu ymaymaru not baset ymifrdut mdanemyalme ewnt newn elalewgn wlo sayder yfrdbote antupatrhrek syono wyane note astgn btkrstnahn atfrsem alne embthen antu tdso note bdnb gbtnal almwut egzyaber yfrdbte

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: