ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጰስ ኾነው ተመደቡ

 • እስከ መጪው ዓመት ጥቅምት በዚኹ ሓላፊነታቸው ይቆያሉ
his grace abune hizkiel

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፤በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳትና የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ

የካፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ሓላፊ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ፡፡

የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ዛሬ፣ ግንቦት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ብፁዕነታቸውን የመደበው፣ በሥራ ላይ በሚገኘው ሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጥቆማ በመቀበል ነው፡፡

አዲስ አበባ በ2005 ዓ.ም. ለአራት አህጉረ ስብከት ተከፍሎ በነበረበት ወቅት፣ ብፁዕነታቸው የደቡብ እና ምዕራብ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው የሠሩ ሲኾን፤ አኹን በያዙት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስነት ምደባ፣ እስከ መጪው ጥቅምት፣ 2009 ዓ.ም. ድረስ እንደሚቆዩ ተገልጧል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ አዲስ አበባን የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሚያደርገው የሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ ተጠንቶ እንዲሻሻልና ራሱን ችሎ ለቅዱስ ሲኖዶሱ ተጠሪ በኾነ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ በትላንቱ ስብሰባው መወሰኑ ተዘግቧል፡፡

Advertisements

11 thoughts on “ሰበር ዜና – ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጰስ ኾነው ተመደቡ

 1. Anonymous June 2, 2016 at 9:32 am Reply

  ፓትርያልኩ አቡነ ሕዝቅኤልን ቢጠቁሙም የፈለጉት ቢመረጥላቸውም ከዚህ በፊት አቡነ እስጢፋኖስንና አቡነ ቀለሜንጦስን በራሳቸው ጥቆማ ተመርጠው ከሁለቱም ጋር ተግባብተው መስራት ስላልቻሉ ተለያይተዋል፡፡ዛሬስ ከአቡነ ሕዝቄል ጋር ተስማምተው መስራት ይችሉ ይሆን ? በሦስት ዓመት ውስጥ እንዴት ሦስት ጳጳሳትን ይቀያይራሉ?እመኑኝ ፓትርያልኩ አቡነ ሕዝቅኤል ሙስናንና ዘረኝነት አጥብቀው የሚጠሉ በመሆናቸው መጣላታቸው አይቀርም ፡፡

 2. Anonymous June 2, 2016 at 9:32 am Reply

  የተሐድሶ መናፍቃን አራማጆች ጉድ ፈላባችሁ፡፡አቡነ ሕዝቅኤል ለኑፋቄ ያላቸውን ጥላቻ ኑፋቄን እንዲያጣራ የተሰየመው ኮሚቴ ሰብሳቢ በሆኑ በጥቂት ቀናት ውስጥ የሰሩትን መቼስ አትረሱም ?

  • Bini June 2, 2016 at 11:17 am Reply

   Hulum leboch nachew zeregnoch nachew bemanm melkam sera yiseral biye alamnm egziabher betunena mengawn eskaltebeke dres

 3. Amlak Yimesgen June 2, 2016 at 2:04 pm Reply

  Mechem Amlak yihen yakil tiwuldun yitewal balilem, ahunem betachin metrat alebat. Yihe lihon yemichilew degmo and ena and patriarku kezeregninet betseda melik meguwaz kechalu bicha new!!!

 4. Anonymous June 2, 2016 at 2:05 pm Reply

  ድሮውንም ፓትርያርኩ ላይወጡት የእነ የማነን የጨለመ ምክር ሰምተው ጳጳሳትን ከሀገረ ስብከቱ አገለሉ ሀገረ ስብከቱን በየማነ ሲያዘርፉት ከረሙ እነ የማነም ቢሆኑ ከጳጳሳት ጋር መጋጯቸው እንጂ አልጠቀሟቸውም ሲጀመር ፓትርያርኩ ርዕሰ መንበር ሆነው እንዴት ወደ ታች ወርደው የአንድ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ይሆናሉ ይህ ሁሉ ስልጣን ወዳድነት ነው ለማንኛውም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዲህ በቀላሉ የሚፀዳ አይደለም።

 5. Anonymous June 2, 2016 at 4:38 pm Reply

  ye welo minchet giba…

 6. ፍቅረ June 2, 2016 at 7:41 pm Reply

  ዘረኛ ናቸው ምንም ድርድር የለውም ገንዘብም ይወዳሉ ምን አልባች ሃይማኖት አላቸው እሱንም ቢሆን ከቅርብ ጊዜ ወድህ አድር ባይ ሆነዋል መካሪአቸውም ኑእረእዱ ነው ገደል የሚገቡበትን ይፈልጋል

 7. Anonymous June 2, 2016 at 11:30 pm Reply

  በቤተክርስትያናችን ታሪክ እንዲህ አይነት የክፍፍሎሽ የስድብ የጥላቻ የመለያየት አለመደማመጥ…የስልጣን ሽኩቻ …የፓለቲካ…መማስፋፊያ…የኑፋቄ መዝርያ መድረክ ሆና አታውቅም ነበር እግዚአብሄር ስለ እኛ አይደለም …ስሙን አክብረው ስሙን አስከብረው ስለ አለፍት ስለ ቅዱሳን ሰማዕታት ሲል ቤተክርስትያናችንን ይጎብኝልን…

 8. Anonymous June 3, 2016 at 8:00 am Reply

  may God bless ETHIOPIA

 9. Anonymous June 8, 2016 at 8:51 am Reply

  እግዝህ አብሄር ሆይ ኢትዮጶያን ባርክ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: