ለቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት ቴሌቭዥን አገልግሎት የቅጥር ማስታወቂያ ወጣ፤ የቤተ ክርስቲያን አባልነት አንዱ መስፈርት ነው

 • በተለያዩ የሥራ መደቦች 15 ባለሞያዎች እና 6 ድጋፍ ሰጪዎች ይፈለጋሉ
 • ከአብነት ጉባኤ ቤትና የማስተርስ ዲግሪ እስከ 2ኛ ደረጃ ዝግጅት ይጠይቃል
 • ለአዘጋጆችና ዘጋቢዎች የግእዝና የእንግሊዝኛ ቋንቋዎች በቂ ዕውቀት ያሻል
 • ማመልከቻውን የማቅረቢያ ጊዜ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ነው
 • ኦርቶዶክሳውያን ጋዜጠኞች፣ ጸሐፊዎችና የቴክኖሎጂ ሞያተኞች አመልክቱ!

  *                *                *

eotc patriarchate eddበቀናት ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭት የሚጀምረውን፣ የቤተ ክርስቲያናችንን የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት የሚመራው፣ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የብዙኃን መገናኛ አገልግሎት ስርጭት ድርጅት ቢሮ የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ አወጣ፡፡

የሥራ ቦታውን፣ በአዲስ አበባ የመንበረ ፓትርያርኩ የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሕንፃ አንደኛ ፎቅ ያደረገው ቢሮው ባወጣው ማስታወቂያ፤ በተለያዩ ሞያዎችና የሥራ ዘርፎች 21 ሠራተኞችን እንደሚቀጥር ተጠቅሷል፡፡

የቤተ ክርስቲያን አባልነት ማስረጃን ጨምሮ መሥፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች፣ እስከ ሰኔ 3 ቀን 2008 ዓ.ም. ለቢሮው ማመልከት የሚጠበቅባቸው ሲኾን፤ የቅጥሩ ኹኔታ፣ ለውጭ ተወዳዳሪዎች በኮንትራት፣ ለውስጥ ተወዳዳሪዎች ደግሞ በዝውውር መኾኑ ተገልጧል፡፡

በተጠቀሱት የሞያ እና የሥራ ዘርፎች የሚካሔደው ቅጥር÷ ለቦታው የሚመጥኑ ወገኖች የቤተ ክርስቲያናቸውን ድምፅ እስከ አጽናፈ ዓለም ለማሰማት በትጋት የሚያገለግሉበትና ከሰርጎ ገቦች የተጠበቀ ይኾን ዘንድ ቢሮው የሚቻለውን ጥንቃቄ ኹሉ እንደሚያደርግ ተስፋችንን እየገለጽን፤ ተፈላጊው የትምህርትና ሥልጠና ዝግጅት እንዲኹም የሥራ ልምድ ያላችኹ ኦርቶዶክሳውያን ኹሉ ዕድሉን እንድትጠቀሙበት እንጠይቃለን፡፡ 

ድርጅቱ፣ የቅጥር ሒደቱን እስኪያጠናቅቅ ድረስ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በሚሰጡ የቤተ ክርስቲያን ልጆች በኾኑ ባለሞያዎች ከቀናት በኋላ የሙከራ ሥርጭቱን እንደሚጀምር ታውቋል፡፡ መቀመጫው እንግሊዝ ሎንዶን ከኾነው European Communication Service UK LTD Co. የተሰኘ የሳተላይት ስርጭት ኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ የእስራኤል ቢሮ ጋር በተፈጸመው ውል መሠረት፤ እ.አ.አ ከትላንት ጁን 1 ቀን አንሥቶ የሙከራ ስርጭቱ መጀመር የነበረበት ቢኾንም፣ የዘገየው በክፍያ መጓተት ሳቢያ እንደኾነ ተሰምቷል፡፡

ክፍያው በተከታዮቹ አጭር ቀናት ውስጥ እንደተጠናቀቀ፣ ኩባንያው በሚሰጠው የስርጭት ፍሪኴንሲ መሠረት የሙከራ አገልግሎቱን የመለያ ሎጎውን በማስተዋወቅና የመንበረ ፓትርያርኩን የዓመታት የፊልም ክምችቶች በመጠቀም እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

የ24 ሰዓት የቴሌቭዥን አገልግሎት ክፍት የሥራ ቦታ የውስጥ ማስታወቂያeotc mass media service adverteotc mass media service advert02eotc mass media service advert03

Advertisements

3 thoughts on “ለቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት ቴሌቭዥን አገልግሎት የቅጥር ማስታወቂያ ወጣ፤ የቤተ ክርስቲያን አባልነት አንዱ መስፈርት ነው

 1. bezawit degeu June 2, 2016 at 3:51 pm Reply

  በጣም ደስ የሚል ዜና ነው።
  ግን ተሀድሶዎች እንዳይሳተፋ
  ትልቅጥንቃቄ ስፈልገዋል።

 2. Anonymous June 3, 2016 at 10:17 am Reply

  የተሃድሶ አራማጅ አለመሆናቸውን ቢያንስ የቅርብ የሚያውቁዋቸው የቤተክርስቲያን አባቶች ምስክርነት ቢኖርበት ወይም ተደውሎላቸው የሚጠየቁ አባቶች ቢኖሩ ጥሩ ነው ሃላፊነቱንም እንዲወስዱ ይደረጋልና፡፡ ይህ አዲስ አሰራ ሳይሆን ሪፈረንስ ተብሎ የሚጠቀስ ነገር በሲቪ ስለሚኖር ነው፡፡ ሲቪያቸውን በደንብ ማየት፡፡ ህዝቡም አይቶ ወደፊት አስተያየት መስጠት ይችላል ቤተክርስቲያንም እርምጃ ለመውሰድ ወደሁዋላ ማለት የለባትም፡፡ ቢቻል ከአብነት ትምህርት ቤት የቀመሱ ቢሆኑ ጥሩ ነው ለገንዘብ የማይገዙ ለምን ቢባል መዝሙር እያሉ ዘፋኞቻን የዘፈኑትን የነዘርፌን የነ ትዝታውን የነ ምርትነሽን የነ እዝራን የነ አሸናፊን የነ ዳግማዊን የነ ሃብታሙን ዘፈን በገንዘብ እየተደለሉ ሊያቀርቡዋቸው ይችላሉና ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ መዝሙር ነው ያሉትን ሁሉ ማሰማት በገንዘብ ለሚገዙ ቀላል ነው፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: