በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

Ato kassa teklebirhan; holy synod gin2008በምልዓተ ጉባኤው ውሎ በተደረሰው መግባባት፤
 • የእንደራሴው መመዘኛ፣ ፓትርያርኩን የማገዝ ተግባሩና ሓላፊነት ደንቡ በቀጣዩ ጉባኤ ይታያል፤
 • በልዩ ጽ/ቤቱ፣ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች ተነሥተው፣ እንዲስተካከልና እንዲረጋጋ ይደረጋል፤
 • የገዘፈ ችግር ያለበት የአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ በረዳት ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ሕጉ የሚሻሻል ይኾናል፤
 • ፓትርያርኩ፣ ስለወቅታዊ ኹኔታዎች ያላቸው አረዳድ ውስንነት ምደባውን አስፈላጊ አድርጎታል፤
 • ተግባር የሚሻው የልዩ ጸሐፊውና የጨለማ አማካሪዎች ግፍና አውዳሚነት አጽንዖት አግኝቷል፡፡
ሚኒስትሩ ስለአጀንዳዎቹና በውሏቸው እንደታዘቡት፡-
 • ከጥቅማጥቅም ጋር ሳይገናኙና ራስን ማዕከል ሳያደርጉ ጤናማ ውይይት ሊካሔድባቸው ይገባል፤
 • ጠንካራ ቅ/ሲኖዶስ፤ ጠንካራ አደረጃጀትና ፖሊሲ፤ አስፈጻሚና ፈጻሚ የሰው ኃይል ያስፈልጋል፤
 • እናንተ ናችሁ እኛን መደገፍ ያለባችሁ፤ ቤቱ ተኣማኒነቱና ተጽዕኖ ፈጣሪነቱን ማጣት የለበትም፤
 • በጨለማ የሚያማክሩት እነማን ናቸው? በእምነት፣ በምግባርና በዕውቀትስ ለቤቱ ይመጥናሉ?
 • አለመተማመን ይታያል፤ ይህ ፍጹም ክፍተት አምጥቷል፤ በጋራ መሥራት ይጠበቅባችኋል፡፡
የሚኒስትሩ እንደታዛቢ መጠራት፡-
 • ከቅዱስ ሲኖዶስ ልዕልና፣ ከቀኖና ቤተ ክርስቲያንና ከሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች አንፃር መነጋገርያ ኾኗል፤
 • የፓትርያርኩ ግትርነት ዋናው መንሥኤ ቢኾንም፣ ምልዓተ ጉባኤው በጥሪው መስማማቱ አስቆጥቷል፤
 • ጥሪው፥ “ኃይል አለኝ” ሲሉ የዛቱት ፓትርያርኩ፥ ለማስፈራሪያ በሚጠቅሱትና አዘውትረው ለርምጃ በሚማፀኑት አካል ፊት፣ ችግራቸውን የማስረዳትና ምልዓተ ጉባኤው በመጨረሻ የሚወስደውን አቋም ጠብቆ የግንቦት 2001 ዓ.ም. ዓይነቱ ግርግር ለመፍጠር የተዘጋጀውን የጨለማ ቡድን የማጋለጥ ዓላማ እንደነበረው ተጠቁሟል፤
 • በጥሪው፥ በእምነቶች የሰላምና የመግባባት ጉዳዮች እንዲሠራ ተልእኮ የተሰጠው ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን፤ በሃይማኖታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ጉዳዮችም ያላቸው ቅርበት ከግምት መግባቱ የተጠቀሰ ሲኾን፤ ትላንት፣ ተሲዓት በኋላ ከ9፡00 እስከ 12፡45 በዘለቀው ስብሰባ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ሥልጣንና ተግባር ከፓትርያርኩ ሥልጣንና ተግባር ጋር እየተነፃፀረ በብፁዕ ዋና ጸሐፊው ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፤

 • የምልዓተ ጉባኤው አባላትም፣ ፓትርያርኩ ከሢመታቸው ጀምሮ የሀገሪቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ወቅታዊ ጉዳዮች ለመረዳት አሉባቸው ያሏቸውን ውስንነቶች፤ አማሳኞችን መቃወም ይቅርና የክፋታቸውና የምክራቸው ሰለባ መኾናቸውን፣ በአ/አበባ ሀ/ስብከትና በልዩ ጽ/ቤቱ ማሳያነት በስፋት አስረድተዋል፤ መፍትሔውንም ጠቁመዋል፤
 •  ፓትርያርኩ በበኩላቸው፣ የእንደራሴ ሹመት በሕጉ የሌለና አላስፈላጊ ቡድናዊ ሐሳብ መኾኑን፤ ሊመረጥና ሊሾም የሚችለው ሲፈቅዱ ብቻና ከዚኽ ውጭ የሥልጣን ቅሚያ እንደኾነ እየመላለሱ አልፎ አልፎም የተናገሩትን እየተቃረኑ ጭምር ሲናገሩ ተደምጠዋል፤
 • የእንደራሴ ሹመት በተሞክሮ የነበረና አኹንም በሕግ የመደንገግ ሥልጣኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ ነው፤ ያለው ምልዓተ ጉባኤው፣ “ለዓመታት በውጭ ነው የኖሩት፤ ቤተ ክርስቲያኒቷንና ሀገሪቱን በደንብ ሳያውቋት ነው የተሾሙት፤ ለዚኽም ረዳት ያስፈልጎታል፤ በእርስዎ የተከለሉ፣ እዚኽ ግቡ የማይባሉ ወሮበሎች ቤተ ክርስቲያኒቷን እንዳሻቸው ሲያደርጓት፤ መሬቷን እየሸጡ፣ ገንዘቧን እየዘረፉ ሲያማስኗት፤ አገልጋዩና ምእመኑ በፍትሕ ዕጦት ሲንገላታ፤ በልዩ ጽ/ቤቱና በጨለማው ቡድን ጳጳሳቷ ክብራቸው ሳይጠበቅ እንደ ሕፃን እየተሸቆጠቆጡ እንዲገቡና እንዲወጡ እየተደረገ መጫዎቻ ሲኾኑ፤ ሕይወታችን ያልፋል እንጂ ዝም አንልም፤” ሲል ከፓትርያርኩ ጋር በለዘብታ እንዲያም ሲል በኃይለ ቃል ሲመላለስ አምሽቷል፡፡
 • “ለምን ተጠራን አንልም፤ እምነታችን ነው፤ ቤታችን ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ ቤተ ክርስቲያን ለሀገር ያደረገችውን አስተዋፅኦ በመዘርዘር፤ ተኣማኒነቷንና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን እንዳታጣ፣ “ወቅቱን የጠበቁ ናቸው” ባሏቸው አጀንዳዎች ላይ በአንዳችም ነገር ሳይታወኩና በመተማመን፣ ጤናማ ውይይት ማካሔድ እንደሚያስፈልግ ሐሳብ ሰጥተዋል፤
 • “ሕዝቡ ከእናንተ ብዙ ይጠብቃል፤ እናንተም ለብዙ ትበቃላችኹ፤ ቤተ ክርስቲያኒቷ ከላይ እስከ ታች መጠናከር እንዳለባት ይገባኛል፤” ያሉት ሚኒስትሩ፣ አጀንዳዎቹም የተቀረፁት ከዚኽ አንፃር እንደሚመስላቸው ጠቅሰው፣ የእንደራሴ ምደባው ደንብና አፈጻጸሙ አስቀድሞ ተጠንቶና ከዋናው ሕግ ጋር ተጣጥሞ ለቀጣዩ ምልዓተ ጉባኤ ቢቀርብ፤
 • የአ/አበባ ሀገረ ስብከት የከበደና የገዘፈ ችግር እንዳለበትና መንግሥትም በቅርበት እንደሚያውቀው፤ ችግሩ፥ ለጊዜው፣ ባለው ሕግ ሰንሰለቱ ተጠብቆ እንዲፈታና በቀጣይም ከተጠሪነት አኳያ[የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት የሚለው] በማገናዘብ ቢታይ፤
 • በልዩ ጽ/ቤቱ ለሥራ ዕንቅፋት የኾኑ ሰዎች እንዲነሡ ቀድሞም ከፓትርያርኩ ጋር ተነጋግረውበት እንደነበርና በአጀንዳ መካተቱ ትክክል እንደኾነ፤ መወሰንና በጎ ተጽዕኖ መፍጠር በሚችል የአስተዳደር ሰው ቢደራጅና ቢጠናከር የሚሉ ሐሳቦችን ሰጥተዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ በእነዚኽ ጉዳዮች ላይ ተስማምቶና ወስኖ ካልወጣ፣ “ለሕዝቡም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ሲሉም መክረዋል፡፡  

 

 

 

Advertisements

8 thoughts on “በፓትርያርኩ እንደራሴ አስፈላጊነት ከስምምነት ተደረሰ፤ “ወቅቱን የጠበቀ ነው” ያሉት ሚኒስትሩ፣ “ቅ/ሲኖዶሱ ተስማምቶ ካልወጣ ለሕዝብም ለሀገርም ጥሩ አይኾንም” ብለዋል

 1. Anonymous June 1, 2016 at 5:55 am Reply

  አምላከ ሓዋርያት ካባቶቻችን ጋር ይሁን!!

 2. Anonymous June 1, 2016 at 7:52 am Reply

  ፓትርያሪኩ አሳፋሪ ስራ ነው የሰሩት ሚንስትሩ ትክክለኛ አስተያየት ነው የሰጡት ቀድሞም ሲኖዶስን ቢቀበሉስ አሁንም አማሳኝ ሌቦች መናፍቃን አማካሪዎቻቸውን ቢተው ጥሩ ነው፡፡ ገና ውርደት ይከተላቸዋል አርፈው ቢከበሩ ይሻሎታል፡፡ ካድሬነት አይሰራም፡፡

 3. Anonymous June 1, 2016 at 8:16 am Reply

  ፓትርያርኩ ለቤተክርስቲያኗ የማይሰሩ ክሆነ ለምን ምልዓተ ጉባኤው አያነሳቸውም?
  ስልጣናቸውን የመጠበቅ ሳይሆን ቤተክርስቲያንን የመታደግ ጉዳይ ነው መሆን ያለበት::

 4. Anonymous June 1, 2016 at 11:36 am Reply

  dirom bilen neber yichi betchirstiyan be asitedaderwa lay abiyot yasifeligal

 5. Anonymous June 1, 2016 at 1:03 pm Reply

  Betam yasazinal yebetekirstiyan gebena endih adebabay lay endiseta mikniyat yehonutinina kibrwan sedbo lesedabi yesetutin yebetekirstiyan amlak yifred

 6. Anonymous June 2, 2016 at 10:03 am Reply

  እግዚአብሔር ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን። አጽራረ ቤተክርስቲያኖችንንም ያስታግስልን።

 7. Anonymous June 2, 2016 at 4:54 pm Reply

  ሌባ ጳጳስ አውቀው መርጠው አመንዛሪ ፓትርያርክ አውቀው መርጠው ህግ ሲጣ ዝም ብለው አሀን እመር አመሩ ለምንድ ነውነው

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: