ቅዱስ ሲኖዶስ ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጠ

በመክፈቻ ጸሎት ከተጀመረ፣ ዛሬ፣ ግንቦት 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ስምንተኛ ቀኑን ያስቆጠረው፣ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጠ፡፡

His grace abune yaco(left) and his grace abune Entones(right)

የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪቃ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ(በግራ)፤ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ(በቀኝ)

ለቅዱስ ሲኖዶስ ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት በዛሬው የቀትር በኋላ የምልዓተ ጉባኤው ውሎ ምደባ የተሰጣቸው፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እና ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ናቸው፡፡

በምደባው መሠረት፣ የምሥራቅ አፍሪቃ ሊቀ ጳጳስ የኾኑት ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ፣ ቀደም ሲል የነበሩበትን የደቡብ አፍሪቃ ሀገረ ስብከት ደርበው ይመራሉ፡፡ የሰሜን ምዕራብ አውሮጳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ፣ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲኾኑ መመደባቸው ታውቋል፡፡

የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት፣ የድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዳንኤል በመደረብ እየመሩት እንደነበር ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ ኹኔታ፣ የሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የኾኑት የብፁዕ አቡነ እንድርያስ ጥያቄም ምልዓተ ጉባኤው የሚነጋገርበት ሲኾን፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫና ምደባም ለነገ አድሯል፡፡

በአኹኑ ወቅት በቅዱስ ሲኖዶስ የምልዓተ ጉባኤያት ስብሰባዎች የሚሳተፉና በሥራ ላይ የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ቁጥር ከ40 ያልበለጠ ሲኾን፤ በመንግሥት ዞናዊ መዋቅር በትይዩ ምደባ ከሚያስፈልጋቸው አጠቃላይ የአህጉረ ስብከት ቁጥር ሢሦው ተደርበው የተያዙ ናቸው፡፡ ራስን የመቻል ጥያቄ የቀረበበት የምዕራብ አርሲ ዞን – ሻሸመኔ እና በአርሲ – አሰላ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ ምደባ ጉዳይ የቀረቡ ጥያቄዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ለአዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ኮሚቴ መሠየምን በአጀንዳነት የያዘው ምልዓተ ጉባኤው፣ ለክፍተቱ እንደ ጊዜያዊ መፍትሔ የወሰደው፣ ሊቃነ ጳጳሳቱን እየደረበ ማሠራትን ነው፡፡

በኹለቱ አህጉረ ስብከት ለተመደቡት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ መልካም የሥራ እና የውጤት ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡

 

Advertisements

4 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጠ

  1. ከሻሸመኔ ሕዝበ ምዕመን June 2, 2016 at 4:13 am Reply

    የሻሸመኔ ሕዝበ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያኖቹ ግቢ ውስጥ እያደረ በጉጉት የሚጠባበቀውን የምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከትነትን ጥያቄ እንዳይዘነጋ በእግዚአብሔር ስም ይማፀናል ::

  2. […] Source: ቅዱስ ሲኖዶስ ለኹለት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ምደባ ሰጠ […]

  3. Anonymous June 2, 2016 at 8:04 am Reply

    gene eliyas Techane guday tedbesbiso mekiret alneberebetim

    masirejawoch yisebasebu bizu yemitebaber ale.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: