ቅ/ሲኖዶስ የእንደራሴ ምደባ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ ሠየመ፤ ልዩ ጸሐፊው እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊው በአጭር ጊዜ እንዲነሡ አሳሰበ

 • ኮሚቴው፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኑን የአ/አበባ ሀ/ስብከት ድንጋጌዎችንም ያጠናል
 • ከቀትር በኋላ ለአ/አበባ ሀ/ስብከት፣ የረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫና ምደባ ያካሒዳል
 • “[ልዩ ጸሐፊውን ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን] በቅርብ ቀን አነሣዋለኹ፤”
 • “በውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ ማስረጃ እፈልጋለኹ፡፡”

/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ/

*               *                *

Holy Synod2008Tikmit
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፥ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ከቤተ ክርስቲያን የተሰጣቸውን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ እንዲያከናውኑ የሚያግዛቸውን እንደራሴ ለመመደብ የሚያሰችለውን ደንብ የሚያረቅ ኮሚቴ ሠየመ፡፡

የምደባ ደንቡ፥ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ ቤተ ክርስቲያኑን መሠረት በማድረግ፣ የእንደራሴውን አመራረጥና ማሟላት የሚጠበቅበትን መመዘኛ፤ ተግባርና ሓላፊነቱን፤ እንዲኹም ተጠሪነቱንና የአገልግሎት ዘመኑን ያካተተ እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡

ሦስት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ ሰባት አባላት ያሉት ይኸው ኮሚቴ፣ የምደባ ደንብ ረቂቁን ለመጪው ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ እንዲያቀርብም የተወሰነ ሲኾን፤ የምልዓተ ጉባኤው አባላትም፡-

 • ብፁዕ አቡነ ገብርኤል(የሐዋሳ እና ነገሌ ቦረና አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ)
 • ብፁዕ አቡነ አብርሃም(የባሕር ዳር፣ ምዕ.ጎጃም፣ መተከልና አዊ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ )
 • ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ(የከምባታ ሐዲያ ጉራጌና ስልጤ የሰ/ት/ቤቶች ማ/መ የበላይ ሓላፊ)
 • ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጩ (የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሓላፊ)
 • መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም (የካህናት አስተዳደር መምሪያ ዋና ሓላፊ)
 • አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌታሁን (የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና ሓላፊ) እና
  ከውጭ አንድ የሕግ ባለሞያ ናቸው፡፡

ረቂቁ፣ በኮሚቴው ቀርቦ በምልዓተ ጉባኤው ከጸደቀ በኋላ፣ ትላንት በምልዓተ ጉባኤው በተደረሰበት መግባባትና በመመዘኛው መሠረት የእንደራሴው ምርጫና ምደባ እንደሚካሔድ ተገልጧል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ የእንደራሴ ምደባ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ፣ በጥቅምት 2007 ዓ.ም. ተሻሽሎ በጸደቀው ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት፣ የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት እንደኾነ ከሚገልጸው አንቀጽ 50 ንኡስ አንቀጽ 1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ድንጋጌዎች ከተጨባጭ ኹኔታዎችና መኾን ከሚገባው አኳያ በማጥናት የማሻሻያ ሓሳብ እንዲያቀርብም በጉባኤው ተወስኗል፡፡

ማሻሻያው፣ የሀገሪቱ መዲና፣ የመንበረ ፓትርያርኩ መቀመጫና የአህጉረ ስብከት ማዕከል የኾነው አዲስ አበባ፣ ከመናገሻ ከተማነቱ(metropolitan) አንፃር፣ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ኾኖ ራሱን በቻለ ሊቀ ጳጳስ ለመመራት እንደሚያስችለው ተነግሯል፡፡

እስከዚያው ድረስ፣ በሥራ ላይ ባለው ሕግ መሠረት፣ በፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እየተመራ ይቆያል፡፡ ለዚኽም በዛሬው ከቀትር በኋላ ውሎ፣ በፓትርያርኩ አልያም በምልዓተ ጉባኤው ሦስት ብፁዓን አባቶችን በመጠቆም በአብላጫ ድምፅ የሚመረጠው ብፁዕ አባት እንደሚመደብበት ተጠቅሷል፡፡

eotc patriarchate
ከዚኹ ጋር በተያያዘ፣ ምልዓተ ጉባኤው፣ በዛሬው የቀትር በፊት ውሎው፣ በአጀንዳው ተራ ቁጥር 10፣ “በልዩ ጽ/ቤት እና በውጭ ግንኙነት ያሉ ሠራተኞች ወደ ሌላ ተዛውረው በሊቃነ ጳጳሳት እንዲመሩ” የሚለውን አጀንዳ በተመለከተ፣ በትላንቱ ምክክር የተደረሰበትን መግባባት መነሻ በማድረግ በአጭር ጊዜ ተፈጻሚ እንዲኾን ለርእሰ መንበሩ ተጨማሪ ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡

ቀድሞም ቢኾን ኹለቱም ሓላፊዎች(ልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው የካሊፎርኒያው ነውረኛ መናፍቅ መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅ) የተመደቡት፣ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ቀጥተኛ ትእዛዝ ሲኾን፤ በራሳቸው በፓትርያርኩ በአጭር ቀናት ውስጥ እንዲነሡ ነው፤ ስምምነት የተደረሰው፡፡ 

በስምምነቱና በምልዓተ ጉባኤው ጥብቅ ማሳሰቢያ መሠረት፣ “ጉዳዩን ለእኔ ስጡኝ” ያሉት ፓትርያርኩ፣ ልዩ ጸሐፊውን በአጭር ቀን እንደሚያነሡ ዛሬም ቢያረጋግጡም፤ የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊ መልአከ ሰላም አባ ቃለ ጽድቅን በተመለከተ ግን “ተጨማሪ ማስረጃዎችን ስጡኝ፤ እወስናለኹ” ነው ያሉት፡፡ ኹለቱም ሓላፊዎች ከቦታቸው ከተወገዱ በኋላ፣ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ እንደሚመደቡ ቢጠቆምም፤ ስለሕግ ተጠያቂነት አልያም ዲስፕሊናዊ ርምጃዎች ጉዳይ በምልዓተ ጉባኤው ማሳሰቢያ የተመለከተ ነገር የለም፡፡

በኑፋቄአዊ ልምዱና በነውረኛ ተግባሩ የሚታወቀው አባ ቃለ ጽድቅ፣ አኹን ለያዘው ሓላፊነት ሊበቃ የቻለው፣ በዚያው በአሜሪካ – ኒውዮርክ ሀገረ ስብከት በከፍተኛ ሓላፊነት ከሚሠሩና ለፓትርያርኩ ቅርበት ባላቸው ሰው ጥቆማ እድጋፍ እንደኾነ ታውቋል፡፡

ልዩ ጽ/ቤቱ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የተሰጡትን ተግባራት እና ሓላፊነቶች በማገናዘብ፣ ክህነታዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ተለይተው በመስኩ በሠለጠነ የሰው ኃይል የሚደራጅበትና በሊቀ ጳጳስ የሚመራበት አሠራር፤ የሚሻሻለው ሕገ ቤተ ክርስቲያን አካል እንደሚኾን ተጠቁሟል፡፡ በአኹኑ ወቅት ልዩ ጽ/ቤቱንና የውጭ ጉዳይ መምሪያውን በበላይ ሓላፊነት እየመሩ ያሉት አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ገሪማ ሲኾኑ፤ በዚኹ ሓላፊነታቸው እስከ መጪው ጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ ይቆያሉ፤ ተብሏል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ ያለፉትን ቅዳሜና እሑድ ሳይጨምር አምስት ተከታታይ ቀናትን የወሰደባቸውን፡- የእንደራሴ ምደባ፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሊቀ ጳጳስ ምደባ፣ የልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊዎች ጉዳይ በዚኹ የቋጨ መስሎ ይታያል፡፡ ውይይቱ፣ በተ.ቁ(5) በተቀመጠው፣ የአየሩሳሌም ገዳማት የመሬት ጥያቄና የዮርዳኖስ ቅድስት ሥላሴ ገዳም ጉዳይና በቀሪ 20 አጀንዳዎች ላይ ቀጥሏል፡፡

Advertisements

10 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ የእንደራሴ ምደባ ደንብ አርቃቂ ኮሚቴ ሠየመ፤ ልዩ ጸሐፊው እና የውጭ ጉዳይ መምሪያ ሓላፊው በአጭር ጊዜ እንዲነሡ አሳሰበ

 1. Anonymous June 1, 2016 at 12:23 pm Reply

  እስከመቼ ነው ሲኖዶስ በተደረገ ጊዜ ሁሉ ሰውነታችን በሁከት የሚያልቅ?

  ይሄ ሁሉ ሁካታና ቱማታ የተደረገበት ውሳኔ ላይፈጸም ይሄን ይህል አተካሮ ፈጥሮ መንግሥት መጋበዝ ራስን ማቃለል፣እኛንም አንገት ማስደፋት ነው፡፡

  እሺ ጥቅምትና ግንቦት ሲደርስ የት እንደበቅ የሲኖዶስ አስፈሪ ዜናዎች ላለመስማት?

  በጣም ይሰለቻል በእናታችሁ፡፡

 2. Anonymous June 1, 2016 at 2:17 pm Reply

  ያሳዝናል ያሳፍራል አይ ጵጵስና ቱሪናፋ ሁሉ ጨርቅ ብቻ

 3. Anonymous June 1, 2016 at 6:16 pm Reply

  የደቡብ አፍሪካ ምእመኖችን ያጋደለ ነውረኛው ቃለፅድቅ ይነሳ

 4. Anonymous June 4, 2016 at 1:38 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ይርዳቸው ብፁአን አባቶቻችንን!
  አባ ቃለ ጽድቅ ይህ ሰው በጣም መጥፎ የሆነ ሰው ነው መድሀኒአለም ማስተዋሉን ይስጠው
  እዚህ Austria(Vienna) ልክ እንደ South Africa አይነት ከፍተኛ ችግር እየፈጠረብን ነው
  በኪዳነምህረት ጥበቃ ነው ያለነው ጸሎታችሁ አይለየን ወገኖቼ

 5. Anonymous June 4, 2016 at 2:04 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ይርዳቸው ብፁአን አባቶቻችንን!
  ይህ ሰው (የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ)
  በጣም መጥፎ የሆነ ሰው ነው መድሀኒአለም ማስተዋሉን ይስጠው
  እዚህ Austria(Vienna) ልክ እንደ South Africa አይነት ከፍተኛ ችግር እየፈጠረብን ነው
  በኪዳነምህረት ጥበቃ ነው ያለነው! ጸሎታችሁ አይለየን ወገኖቼ

 6. Bsrat Yohannes (@Bsrat19) June 4, 2016 at 2:10 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ይርዳቸው ብፁአን አባቶቻችንን!
  ይህ ሰው (የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ)
  በጣም መጥፎ የሆነ ሰው ነው መድሀኒአለም ማስተዋሉን ይስጠው
  እዚህ Austria(Vienna) ልክ እንደ South Africa አይነት ከፍተኛ ችግር እየፈጠረብን ነው
  በኪዳነምህረት ጥበቃ ነው ያለነው! ጸሎታችሁ አይለየን ወገኖቼ

 7. Bisrat June 4, 2016 at 3:53 am Reply

  እግዚአብሔር አምላክ ይርዳቸው ብፁዐን አባቶቻችንን!
  ይህ ሰው (የውጭ ጉዳይ መምሪያ ዋና ሓላፊው አባ ቃለ ጽድቅ) በጣም መጥፎ የሆነ ሰው ነው መድሀኒአለም ማስተዋሉን ይስጠው
  እዚህ Austria(Vienna) ልክ እንደ South Africa አይነት ከፍተኛ የሆነ ችግር እየፈጠረብን ነው በኪዳነምህረት ጥበቃ ነው ያለነው
  ጸሎታችሁ አይለየን ወገኖቼ

 8. […] ሲኖዶስ፣ ባለፈው ዓመት የርክበ ካህናት ምልአተ ጉባኤው፣ አሁን በቦታው ላይ ያሉትና የውጭ ግንኙነቱን የሚያቃውስ […]

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: