ሰበር ዜና – የእንደራሴ ምደባ አጀንዳ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት እንዲታይ ተወሰነ፤ ፓትርያርኩ በተቃውሟቸው እንደቀጠሉ ናቸው

 • ዛሬ ከቀትር በኋላ አልያም ነገ ታዛቢ ባለበት ለመቀጠል ከስምምነት ላይ ተደርሷል

holy synod vs. pat aba mathias
በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን ውይይቱን የቀጠለው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ በፓትርያርኩ ተቃውሞ ምክንያት ከስምምነት ለመድረስ ባለመቻሉ፣ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት ለመነጋገር ወሰነ፡፡

ፓትርያርኩ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን የመጨረሻ አቋም እንዲያሳውቁ፣ ምልዓተ ጉባኤው በትላንቱ የቀትር በኋላ ውሎው፣ እስከ ዛሬ ጠዋት የማሰላሰያ ጊዜ ሰጥቷቸው የነበረ ቢኾንም፣ ምደባውን፥ ቤተ ክርስቲያን ህልውና አንፃር ከማሰብ ይልቅ  ከሥልጣን ተጋሪነትና ከጥቅም ጋር ብቻ በማገናኘት በተቃውሟቸው መቀጠላቸው የታዛቢውን መገኘት አስፈላጊ አድርጎታል፤ ተብሏል፡፡

ስብሰባውን በጸሎት ዘግቶ ምልዓተ ጉባኤውን ማሰናበት አልያም፣ ሌላ ሰብሳቢ ሠይሞ በእንደራሴ ምደባው ላይ በአብላጫ ድምፅ በመወሰን ወደ ሌሎች አጀንዳዎች መቀጠልጉባኤው ለተከታታይ ሦስተኛ ቀን በአንድ አጀንዳ ተወስኖ ለገባበት እግዳት በአማራጭነት የተያዙ እንደነበሩ ተጠቅሷል፡፡

በስብሰባው ላይ ይገኛሉ የተባሉት የመንግሥት ታዛቢ፣ የፌዴራልና አርብቶ አደር ልማት ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትሩ አቶ ካሳ ተክለ ብርሃን ሲኾኑ፣ በፓትርያርኩ በኩል ጥሪው እንዲደርሳቸው መወሰኑ ተጠቁሟል፡፡ ምልዓተ ጉባኤው፣ ታዛቢው እንደተገኙ፣ ዛሬውኑ ከቀትር በኋላ አልያም ነገ በአጀንዳው ላይ ተወያይቶ እንደሚወስን ተነግሯል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶሱን ውሳኔ የሚጥሱና የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና የሚያስደፍሩ የፓትርያርኩ እንቅስቃሴዎች መበራከታቸው፤ ሙስናንና የፍትሕ ዕጦትን በማስወገድ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን በየጊዜው ከሚያደርጓቸው ንግግሮች በተፃራሪ ችግሩ እየተባባሰ መምጣቱ፤ ከዚኽም አልፎ ራሳቸው ፓትርያርኩ በአማሳኞቹና ችግሩን እንደ ከለላ(safe heaven) ተጠቅመው ኅቡእ ዓላማቸውን በሚያራምዱ የተሐድሶ ኑፋቄ ወኪሎች ተጽዕኖ ሥር መውደቃቸው፤ ይህም በሒደት የቤተ ክርስቲያንን ህልውና ለከፋ አደጋ ማጋለጡ የእንደራሴ ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው እንደታመነበት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡

በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የመላው ካህናትና ምእመናን አባት ፓትርያርኩ፣ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት በመኾናቸው የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ሰብሳቢ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ርእሰ መንበር እና የቤተ ክርስቲያን የበላይ ጠባቂ ቢኾኑም፤ መንፈሳዊ እንቅስቃሴአቸው እና የአመራር ብቃታቸው ለቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮ ያለውን ሥምረት ከግንዛቤ በማስገባት ሊመዘኑና ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡

Advertisements

18 thoughts on “ሰበር ዜና – የእንደራሴ ምደባ አጀንዳ የመንግሥት ታዛቢ ባለበት እንዲታይ ተወሰነ፤ ፓትርያርኩ በተቃውሟቸው እንደቀጠሉ ናቸው

 1. Anonymous May 31, 2016 at 11:02 am Reply

  Aba matiyas is drop down the loyalty of Holy synod on history the first father.

 2. Anonymous May 31, 2016 at 11:07 am Reply

  በመንፈሳዊ ህይወት ትልቁ ችግር መንፈሳዊ ሥራዎች መንፈሳዊ ባልሆኑ ሰዎች ሲሰሩ ነው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መንፈሳዊ አገልግሎት ነው ስራውም መሰራት ያለበት በመንፈሳውያን ሰዎች ነው መንፈሳዊ መሆን የሚቻለው ደግሞ ለመንፈስ ቅዱስ ማደሪያነት እራስን በማዘጋጀት ነው በአጠቃላይ ካሣ ተክለብርሃን መንፈሳዊ ሰው አይደለም የፖለቲካ ሰው እንጂ

 3. Anonymous May 31, 2016 at 11:17 am Reply

  በተደጋጋሚ ፓትርያርክ ስለማውገዝ፣ስለመሻር፣እሳቸው አስወጥቶ ጉባኤ ስለመቀጠል፣የሁሉ ደካማነት ምንጭ ከሳቸው ብቻ እንደሆነ ነው ያለ የምታስተላልፉት፡፡በሰላም ነው? በጣም በዛ ብዬ ነው እሳቸው ላይ ያላቹ ቦጎ ያልሆነ ኣመለካከት፡፡

 4. anonymous May 31, 2016 at 11:21 am Reply

  shame, the last shame! Yebetekiristian Amlak yifred!!!!!!!!

 5. Anonymous May 31, 2016 at 11:45 am Reply

  በጣም አሳዛኝ ሰው ናቸው ሰው የሚላቸውን የማይሰሙ ለቤተክርስቲያን የማይጠቅሙ እውነቱን ነው ዲያቆን ዳንኤል ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ለምእመኑ ድህነት ጸር ናቸው ያለው

 6. Anonymous May 31, 2016 at 11:46 am Reply

  አንድ ሰው ይበልጣል ሲኖዶስ መንግስት ይግባበት ያሉት ፖለቲከኞች ናቸው ለማስባል ይሆን

 7. mesele May 31, 2016 at 12:34 pm Reply

  እናንተ ትክክለኛ የቤተክርስቲያን ጠላቶች ናችሁ። በጣም ነው የምታሳፍሩት። እውነት የለውም።ጳጳሳቱን የምታደራጁት እናንተ አይደላችሁ እንዴ

 8. Anonymous May 31, 2016 at 1:18 pm Reply

  ያሳዝናል ፣ያሳዝናል ፣ያሳዝናል ፣ያሳዝናል

  የመጀመሪያው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ከፓትርያልክ በላይ ስልጣን ያለው ሆኖ ሳለ ከሃምሳ በላይ ጳጳሳት አንድን ጳጳስ ማስታገስ አቅቶአቸው እዚህ መድረሳቸው፡፡
  ሁለተኛው በጊዜ የተገደበው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከአምስት ቀን በላይ በአንድ አጀንዳ መክረሙ፡፡
  ሦስተኛው ደግሞ እጅግ የሚያሳዝነው ከራሱ ከሕዝቡ ከጎረቤቶቹ እንዲሁም ከአለም ሕዝብ ጋር የተጣላ መንግስት አለምን ሰላም ያደርጋሉ የተባሉ አባቶችን ለማስማማት መቀመጡ በእውነት በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጠፍተወቅ ነው ? በእውነት እነዚህ አባቶች በሰውነታቸው ክሳትና በልብሳቸው ጥራት ካል ሆ አስታራቂ ከተባለው ሰው በምን ያንሳሉ ?…. ‹‹ 1ቆሮ 6፤1-5 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመጸኞች ፊት ሊፈርድ ይደፍራልን ? ቅዱሳን በዓለም ላይ እምዲፈርዱ አታውቁምን በዓለምስ ላ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ሽለሚኆን ነገር ልጽፈርዱ አትበቁምን ? የትዳር ጉዳይ ይቅርና (የእንደራሴ ጉዳይ ይቅርና) በመላዕክት እንኳን እንድንፈርድ አታውቁምን ?እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ (የእንደራሴ ጉዳይ ) ፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ(ፖለቲከኞች ቢያስፈልጋችሁ) በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች (ዓላውያን ነገሥታትን) ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ፡፡እንደዚህ ነውን ?በወንድሞች መካከል ሽማግሌ (ከቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ሽማግሌ) ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን ?
   ………….

 9. davavisky May 31, 2016 at 1:19 pm Reply

  ያሳዝናል ፣ያሳዝናል ፣ያሳዝናል ፣ያሳዝናል

   የመጀመሪያው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባዔ ከፓትርያልክ በላይ ስልጣን ያለው ሆኖ ሳለ ከሃምሳ በላይ ጳጳሳት አንድን ጳጳስ ማስታገስ አቅቶአቸው እዚህ መድረሳቸው፡፡

   ሁለተኛው በጊዜ የተገደበው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከአምስት ቀን በላይ በአንድ አጀንዳ መክረሙ፡፡

   ሦስተኛው ደግሞ እጅግ የሚያሳዝነው ከራሱ ከሕዝቡ ከጎረቤቶቹ እንዲሁም ከአለም ሕዝብ ጋር የተጣላ መንግስት አለምን ሰላም ያደርጋሉ የተባሉ አባቶችን ለማስማማት መቀመጡ በእውነት በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌዎች ጠፍተው ነው? በእውነት እነዚህ አባቶች በሰውነታቸው ክሳትና በልብሳቸው ጥራት ካልሆነ አስታራቂ ከተባለው ሰው በምን ያንሳሉ ?…. ‹‹ 1ቆሮ 6፤1-5 ከእናንተ አንዱ ከባልንጀራው ጋር ሙግት ቢኖረው በቅዱሳን ፊት በመፋረድ ፋንታ በዓመጸኞች ፊት ሊፈርድ ይደፍራልን ? ቅዱሳን በዓለም ላይ እምዲፈርዱ አታውቁምን በዓለምስ ላ ብትፈርዱ ከሁሉ ይልቅ ትንሽ ሽለሚኆን ነገር ልጽፈርዱ አትበቁምን ? የትዳር ጉዳይ ይቅርና (የእንደራሴ ጉዳይ ይቅርና) በመላዕክት እንኳን እንድንፈርድ አታውቁምን ?እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ (የእንደራሴ ጉዳይ ) ፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ(ፖለቲከኞች ቢያስፈልጋችሁ) በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች (ዓላውያን ነገሥታትን) ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን?አሳፍራችሁ ዘንድ ይህን እላለሁ፡፡እንደዚህ ነውን ?በወንድሞች መካከል ሽማግሌ (ከቤተክርስቲያን አባቶች መካከል ሽማግሌ) ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው በእናንተ ዘንድ አይገኝምን ?
   ………….

 10. ቃበታ May 31, 2016 at 2:52 pm Reply

  ይህ አባት ነኝ ብለው በቅዱሳን አባቶች ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት መንበር ላይ የተቀመጡ አባት የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ለመጠበቅ፣ ሥርዓቷን እና ትሩፋቷን ለልጅ ልጅ ለማስተላለፍ ሳይሆን፤ እምነቷን ለመበረዝ ብሎም ቀስ በቀስ ውስጥ ውስጧን ንዶ ለጠላት ለማስጠት እንደሆነ ከተሃድሶ መናፍቃን ጋር ሌት ተቀን ደፋ ቀና ለማለቻቸው በላይ ማስረጃ የለም።

  ለቅዲስት ቤተክርስቲያ ህግ እና ሥርዓት ለማስጠበቅ አይደለም ነገሩ እንድ ነው ለአቦይ ፀሐይ፣ለእነ ቴዎድሮስ አዳኑ ፤ ለነ ስባት ነጋ ምዕመንን በሀገር ቤት ሆነ በውጭ ሀገር ለመሰለል እንዲያመቻቸው መረብ ዘርግተው የተቀመጡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ውስጥ የወያኔ አምባሳደር ናችው። ካድሬው ማትያስ የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስን ለማጥፋት የተቀመጡ በጉቦ እና በመስና የተጨማለቁ ፣ ከክርስቶስ ፍቅር በዘረኝነት እንደ ጧፍ የነዳዱ ምህረትን የማያውቁ ፣ ሁሌም በስኖዶሱ ስብሰባ ላይ ከተቀበላችሁ ተቀበሉ እምቢ ካላችሁ ግን የፈለኩትን አደርግ ዘንድ ማንም አይከለክለኝም እነ እከሌ ፣ እነ እከሌ ደግ አደረግህ እኛ ክጉንህ ነን ብለውኛልና እያሉ የሚያስፈራሩ ከመሆናቸው ሌላ ማህበረ ቅዱሳን መናፍቃን እና ቤተክርስቲያንን ቀኝ ግዛት ይዘዋል ብለው ደፍራው የተናገሩ ሰው ናቸው።

  ከዛም ሌላ ህዝባችን ያለህግ ፣ስገደል ፥ስታሰር፣ ስታፈን፣አሰቃቂ መከራ በወያኔ ስደርስባቸው እንደ አባት ፍርደ እግዚአብሔር ተጒዲሏል፤ ደሃ ተበድሏል ብለው ድምፃቸውን እንኳን አላሰሙም፤ የሚገደለው ፣ የሚታሰረው፤ ከቤቱ ከንብረቱ የሚባረረው የሚፈናቀለው ኢትዮጵያዊ አይደለን?

  በሰፈሩበት ቁና መሰር የግድ ነው
  ለሁሉም ጊዜ አለው።

  • ምን፡ልሁን June 1, 2016 at 12:26 am Reply

   ጌታ፡በምድር፡ላይ፡ሳለ፡የሰዎችን፡ፈቃደኝነት፡ይጠይቅ፡ነበረ፡መዳን፡ትፈልጋለክ፡ልትከተለኝ፡ተወዳለክ፡ሊያውም፡ትህትና፡በተሞላበት፡አጠያየቅ፡ይመስለኛል፡ቃሉን፡ማወቅ፡ብቻ፡ሳይሆን፡ሰምተውት፡የሚያውቁም፡አይመስልም፡፡

 11. Tamagn May 31, 2016 at 9:12 pm Reply

  ይህ ሁኔታ ለእርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችም ሆነ ለአገር አደገኛ ሁኔታ ነው። ይህ ነገር እንኳንስ ከሃይማኖት አባት ይቅርና ከማናቸውም ማሰብ ከሚችል ግለሰብ የሚጠበቅ ነገር አይደለም። ፍቅረ-ሹመት ሴጣን የወለዳት ደዌ ናት ይላል መጽሃፍ። እርሳቸውም ለማይረባ እና ስጋዊ ለሆነ ነገር መሸነፍ አልነበረባቸውም። ዋናው መልእክቴ መንግስት በዚህ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባት የለበትም። የመንግስት ሚና በህገ-*መንግስቱም የተገደበ ነው። የትኛውንም ወገን ደግፎ የመንግስት ኃላፊ አስተያየትም ሆነ መመሪያ ቢሰጥ ችግሩን ከመፍታት ይልቀ የበለጠ እንዲባባስ ያደርገዋል የሚል እምነት አለኝ። ሲኖዶሱ የቤተክርስቲያኗ የመጨረሻው የስልጣን አካል በመሆኑ ችግሩ መፈታት ያለበት በራሱ በሲኖዶሱ ነው። ውሳኔውም በተቀመጠው አሰራር መሰረት መከናወን አለበት። መንግስት እጁን ከዚህ ማስገባት የለበትም። ፓትርያርኩም ታሪክ ይቅር የማይለው ጥፋት እየሰሩ ነው የሚገኙት። እግ/ር ልቦና እንዲሰጣቸውም እንፀልያለን።

 12. Anonymous June 1, 2016 at 7:10 am Reply

  አቤቱ ጌታ ሆይ ተነስ፤ ሰለ ቤትህ ክንድህ ይድረስ፤ አንተ ድንቅ መካር ሃያል አምላክ ሆይ ምክርህ የሴረኞችን ምክር ያፍርስ፤ ለአባቶቻችን የክህነታቸዉን አላማና ምክንያት እንዲሁም ግብ ግለፅላቸዉ፡ ዘላለማዉ የሆንከዉን አንተን ማወቅ ከሰማይ በታች ስላለዉ ስልጣንና ዝና ስፍራ እንዳይኖረን ያደርገናልና አንተን ማወቅን በልቦናቸዉ በጎ አምልኮትን በህሊናቸዉ ጨምር፤ ህዝብህን የበረታና ከጳጳሳት አሻግሮ አንተን በማየት ተስፋ እንዲሞላ እርዳዉ፤ ጌታ ሆይ የጠላታችን መሳለቅያ አታድረግ፤ ራስ ለሆንካት ቤት ቅና፤፤ ለዘላለማዊነት ክብር ይሁን፡፡

  • ጌታሁን June 2, 2016 at 2:04 pm Reply

   ፓትሪያርኩን ስታወግዙ ሰማኻችስሁ። ለመሆኑ ከሲናዶስ አባላት ውስጥ ምን ስው። አለና ነው። ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ናቸው አሁን የአሉት ጳጳስት በሙሉ። ፓትሪያርክ በፓትርያርክ ላይ ሲሾም ዝም እሺ የእሉ ናቸው። የምቱት ጳጳስ ህግ ሲጥሱ ዝም የአሉ ናቸው ቤተክርስቲያን ለመከፍፈል ምክናያት ናችውይህ ማለቴ ፓትርያርኩ የአሁኑም የምቱትም ጥሩ ናቸው ማልቴ አይደልም ዋና ተጠያቂዎች ጵጵሳት ናቸው አባቶቻችን ለሃማናታቸው መስዋዕትነትን ከፈሉ ብለው የአስትማሩን እነሱ ግን መስዋእትነትን የፈሩ ተዋህዶ እንድትበን የፈርዱ። ንብሳችሁን እይማረው

 13. Anonymous June 2, 2016 at 2:06 pm Reply

  Abune Matyas is member of illuminati

 14. dejene June 2, 2016 at 6:16 pm Reply

  ለኢትዮጵያ ኢርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ
  “ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርሰቲያን ቅድስት ጉባኤ እንተ ዘሐዋሪያት ርትዕት በእግዚአብሔር“ ፤ “ሐዋርያት ስለሰበሰቧት አንዲት የምትሆን ቤተክርሰቲያን ሰላም ፀልዩ“
  የተከበራችሁ ውድ የቤተክርስቲያን ልጆች ሆይ መናፍቃን የራሳቸውን አገልጋዮች በቤተ ክርሰቲያን አሰራጭተው የሚሰሩትን ታያላችሁ፡፡
  በጣም የሚገርመው ከብዙ እኩይ ምግባራቸው ሚያሳዝነው በታቦት (በታቦት አጠገብ) መቀደስ ከልክለውናል ሌላው ያስገረመኝ ያለታዛቢ ያለመንግስት ተወካይ መሰብሰብ አትችሉም ተብሎ ይህው ቅዱስ ሲኖዶስ ታግዷል፡፡
  ውድ የቤተክርስቲያን ልጂች ሆያ ታዲያ እናንተ ምን እንደምትሉ አላውቅም ወንድሞቼ እኔ ግን አንድ ነገር ልላችሁ አሰብኩ በቅድሚያ ቅዱስ ሲኖዶሱን ይቅርታ እየጠየኩ በየግላችን ምህላ እንድንይዝ ነው፡፡
  ከፈቀዳእሁልኝ
  የምህላ ቀን ፡- ከ ግንቦት 27 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ
  ሰዓት ፡- ጥዋት 12፡00 እስከ 3፡00
  ፡- ማታ 10፡፡00 እስከ 11፡00
  የፀሎት ቦታ ፡- በሚቀርበን አጥቢያ ቤተክርስቲያን
  የፀሎት ዓይነት ፡-
  1. ፀሎተ ችግዝዕትነ ማርያም ፀሎተ ማርያም 64 ግዜ
  2. አቡነ ዘበሰማያት አናታችን ሆይ 12 ግዜ
  3. እግዚኦ ማርነ ክርስቶስ 41 ግዜ
  4. በእንተ እግዝዕትነ ማርያም ማርነ ክርስቶስ 41 ግዜ

  ማሳሰቢያ ፡- ማንም ይህንን ምህላ መሳተፍ ይችላል ፡፡ በየግላችን እንጂ አብሮ መፀለዩ ለግዜው ይቆየን
  ፀሎቱን ከጨረሱ ፤ ሰዓት ሳያበቃም ወደየግል ተግባራችን መሰማራት ችንችላለን
  እግዚአብሔር ፀሎታችንን ይስማን፡፡
  አባ እፁብ ሣህለ ስላሴ

 15. Anonymous June 6, 2016 at 10:48 pm Reply

  የቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዐት የተጣሰው አሁን አይደለም፡ቤተክርስቲያን የምትመራው በመንግስት ባለስልጣን ስለሆነ እግዚያብሔር እንደፈቀደ።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: