በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ: ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው

Abune Mathias perplexed

 • ከንግግራቸው በተፃራሪ በአማሳኞችና በተሐድሶ መናፍቃን ተጽዕኖ ውስጥ ወድቀዋል
 • የተጽዕኖው አስጊነት ምደባውን አስፈላጊ እንዳደረገው በምልዓተ ጉባኤው ታምኖበታል
 • ፓትርያርኩ፣ “ሌላ አለቃ ልታስቀምጡብኝ ነው ወይ?” በሚለው ተቃውሟቸው ውለዋል
 • በተቃውሞ ከጸኑ፣ ጉባኤው በአብላጫ ድምፅ ወስኖበት ሌላ ሰብሳቢ በመምረጥ ይቀጥላል

*           *           *

 • ቅ/ሲኖዶስ፣ የመጨረሻው መንፈሳዊ እና አስተዳደራዊ ሕግ አውጭ እና ወሳኝ አካል ነው
 • ሕጎችን ያወጣል፤ ያሻሽላል፤ ይሽራል፤ የአስተዳደር መዋቅርን ደረጃና ተጠሪነት ይወስናል
 • በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ የሚያሳልፈው ውሳኔም፣ የሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ አካል ይኾናል
 • ፓትርያርኩን በአመራር ለማገዝ ለሚሾመው እንደራሴ ምደባ፣ ዝርዝር ደንብ ይወጣል

*           *           *

 • ፓትርያርክ የሚባሉት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን አባት ናቸው
 • የፓትርያርክነት/ርእሰ ሊቃነ ጳጳስነት ሥልጣናቸው የአመራር እንጂ የክህነት ደረጃ አይደለም
 • ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቀው ያለአድልዎ የማስተዳደር እና የመምራት ሓላፊነት አለባቸው
 • ቤተ ክርስቲያንን ማስነቀፋቸውና ታማኝነት ማጣታቸው ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው ይወርዳሉ

*           *           *

በዛሬ፣ ግንቦት ፳፪ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ከምደባው ጋር በተያያዘ ከምልዓተ ጉባኤው ውይይት የሚጠቀሱ፡-

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፡-
 • “በሕጉ እንደራሴ ይመደብ የሚል ሕግ የለም፤ ከሕጉ ውጭ ነው፤ ሕጉ ይከበር፤ እኔስ ምን አደረግኋችኹ? እየሠራኹ አይደለም ወይ? ከእኔ በላይ ሌላ አለቃ፣ ሌላ ባለሥልጣን ልታስቀምጡ ነው ወይ?”
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡-
 • “ምልዓተ ጉባኤው÷ ሕግ የማውጣት፣ የወጣውን የማሻሻልና የመሻር ከፍተኛ ሥልጣን አለው፤ ውሳኔውም እንደ ሕግ ይሠራል፤ የቅዱስነትዎም ተጠሪነት ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው፤ ሓላፊነትዎ ከባድና ክፍተቱ ብዙ ቢኾንም የተሰጠዎትን ከመናገር በቀር ምንም አልሠሩም፤ ምክርዎም ከአማሳኞችና ከመናፍቃን ጋር ነው፤ ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ እስከ ሀገረ ስብከትና አጥቢያ ድረስ ወርደው ሥራ አስኪያጅ፣ ጸሐፊ እና ሒሳብ ሹም ይመድባሉ፤ የምንሾመው የሚያግዝ እንደራሴ ነው፤ አንድ ብቻ ሳይኾን ብዙ ሊያስፈልግ ይችላል፤ ከዚኽ በፊትም በየዘመነ ፕትርክናው ሠርተንበታል፤”
 • እንደ ጉባኤው ሕግና ደንብ፣ አጀንዳው በድምፅ ብልጫ ሊወሰንበት ይገባል፤ ምልዓተ ጉባኤው 50 ለ1 ኾኖ መቀጠል የለበትም፤
 • ፕትርክናዎን ከቅዱስ ሲኖዶስ እና ለቤተ ክርስቲያን ከሚያስቡ ጋር ሊሠሩበት እንጂ ከማይመለከታቸውና ከሚያበጣብጡን ጋር ሊመክሩበት አይገባም፤ ካልኾነ ሥልጣኑ የቅዱስ ሲኖዶስ ነው
 • ከቅዱስ ሲኖዶስ ጋር መሥራትዎ ግድ ነው፤ ሕዝብ ይግባ፤ መንግሥት ይግባ ማለት ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ሕገ መንግሥቱን አለማወቅ ነው፤ ማንም በማንም መግባት አይችልም፤ እኛም አንፈልግም፤
 • ቤተ ክርስቲያን በሕዝብ መካከል ኾና ኹሉንም በአንድነት የምትጠብቅ ችግር ፈቺና አስታራቂ ተቋም ናት፤ እነእገሌ ይግቡ፤ እነእገሌ ይምጡ የሚለው አስተሳሰብ የመከፋፈል አጀንዳ ያላቸው ሰዎች ከውጭ የሚረጩት ነው፤
 • ለረጅም ጊዜ በቤተ ክርስቲያንና በብፁዓን አባቶች ላይ ሲዘምቱ የቆዩ መናፍቃን፣ ስለአጀንዳው የሚያሰራጯቸው አሉባልታዎች፣ ፍጹም ሐሰትና ኾነ ተብሎ የጉባኤውን አቅጣጫ ለማስለወጥ የሚያናፍሷቸው ናቸው፡፡
Advertisements

12 thoughts on “በእንደራሴ ምደባ ጉዳይ: ፓትርያርኩ እስከ ነገ አቋማቸውን የሚያሳውቁበት የማሰላሰያ ጊዜ ተሰጣቸው

 1. ድልነሳ ደባሱ May 30, 2016 at 6:52 pm Reply

  እኒህ ሰው ከመጡ ከወሬ ውጭ ምን ፈየዱ??? የባሰ መከራ ነው የሆኑባት ለቤተ ክርስቲያን

 2. Anonymous May 30, 2016 at 9:03 pm Reply

  Egizabher keabatoch gar endHon tselyu.
  Betelaym yeadisabeba mimenan kegonachw
  Bert item yemikomubet gize Ahun new.
  Yebetekirstiyan tinsa en yasyen.

  • Anonymous May 30, 2016 at 10:44 pm Reply

   Egzeabeher Amlak kenante gar yehun .Ahun Abatoch endalachehun asmesekerachehu .edmena tenant labatochachen !

 3. sintayehu tsegaye May 31, 2016 at 4:31 am Reply

  E/r yirdachihu

 4. Anonymous May 31, 2016 at 6:15 am Reply

  እንደራሴ ሕግ ሳይወጣለት ዝምብለህ ካልተሸመ ብሎ ድርቅና ይገርማል፡፡ጥቅሙና ጉዳቱ፣የሥልጣንና ተጠሪነት ኣድማሱ ሳታጣራ ፓትርያርኩ ለማጨናነቅና ለመገደብ ስትል ብዙ ትርፍ ወሬ ማውራት ይደብራል፡፡ከጥላቻ ውጡና ሰፋ አርጋቹ አስቡ፡፡

  • Anonymous May 31, 2016 at 9:22 am Reply

   you can use your own language; it is clear who you could be. Go out of the church; the church is not a market place!

 5. Anonymous May 31, 2016 at 8:36 am Reply

  MEGEMERYA GEDEB AWKEW ENDISERU PATRIYAKUN MEKRAHACHEW BITHON TIRU NEBER PATRYARKU EKO SIRA CHEW AYAWKUM SYESIRA ASKIYAG SIRA KESERU ENDESIRA ASKIYAG LIKES ESU LIKES YEGD NEW

  • Anonymous May 31, 2016 at 12:54 pm Reply

   እኝ አባት ዘመናቸውን ከአማሳኞች ከሀራ ጥቃ ጋር ጨረሱት ሲይሳዝኑ እልና ግትርነታቸውን ሳይ ደግሞ ድብቅ አጀንዳስ እንዳላቸው ማን ያውቃል እግዚአብሔር ብቻ ነውነው ሁሉን የሚያውቅ የሰው ሆዱ የወፍ ወንዱ አይታወቅምይባል የለ አባታችን እባክዎ በኢትዬጽያ በቤተክርስቲያን አምላክ ጳጳሳቱን ያድምጡዋቸው ምድራዊ ስልጣን ሳይሆን ሰማያዊውን ያስቡ ቢቻላቸው የተመረጡትን ያስታሉ አይደል የሚለው ቅዱስ መጽሀፍ እነዚእ የጥፋት መልእክተኞችን እግዚአብሔር አምላክ ከቤተክርስቲያናችን ላይ እጃቸውንም አይናቸውንም ያንሳልን አሜን አሜን አሜን!!!

 6. Anonymous May 31, 2016 at 12:38 pm Reply

  ስለቤተክርስቲያናችን ግድ ይለናል።
  እንደ ዓይን ብሌንም እንጠብቃታለን!!

 7. Anonymous May 31, 2016 at 3:30 pm Reply

  eko min lisera new cadre kabatoch gar yemisebesebew…betekedesew gubae….yih difiret new ezaw kemiwashibet parliamet …yigermal mech yihon gin yih mengist kebetekrstian lay ejun yemianesaw…yih betezewawari yemiseraw sera new

 8. አማኑኡል ከከናዳ June 2, 2016 at 12:03 am Reply

  በፁአን ሊቂነ ጳጳሳት በዘመናችሁ የመንፈስ ቅዱሱን ጉባኤ የፖለቲካ መድረክ ለማድረግ እየተፋጠናችሁ መሆኑን ምእመናንሁሉ አውቀዋል ምንም ማለት ስለማይችሉ ማስተዋል እዲሰጣችሁ ወደአምልክ መጮሀችንን እንቀጥላለን እናንተ ቤተክርስቲያንን ብትረሷት” የሚጠብቃት አያቀላፋም”በእውነት ያለሐሰት።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: