ቅ/ሲኖዶስ: የፓትርያርኩን አመራር ውጤታማ በሚያደርጉ አሠራሮች ላይ መምከር ጀመረ

 • የመንበረ ፓትርያርኩ እንደራሴ ምደባና የጽ/ቤቱ አደረጃጀት ትኩረት ተሰጥቶታል
 • ቅዱስ ፓትርያርኩ፥ “ሊያሠራኝ ስለማይችል አልቀበለውም” በሚል እየተቃወሙ ነው
 • የቃለ ዓዋዲው ማሻሻያ ረቂቅ ለብዙኃን ውይይት እስከ አጥቢያ እንደሚወርድ ተጠቆመ

*                *                *

pat 3rd yearብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤ በ፫ኛ ዓመት በዓለ ሢመት

ሦስተኛ ቀኑን የያዘው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን አመራር ውጤታማ ያደርጋሉ ባላቸው አሠራሮች ላይ መምከር ጀመረ፡፡

ከዚኹ ጋር በተገናኘ፣ ምልዓተ ጉባኤው የሠየመውና በብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ሊቀ መንበርነት የሚመራው ስምንት አባላት ያሉት የአጀንዳ አዘጋጅ ኮሚቴ፣ ሦስት ዐበይት ጉዳዮችን የለየ ሲኾን፤ ለምልዓተ ጉባኤው ቀርበው ከጸደቁት 24 የመነጋገርያ ነጥቦች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡

እኒኽም፣ በተ.ቁ(4) የእንደራሴ ምርጫ፤ በተ.ቁ(7) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቅዱስ ሲኖዶስ የሊቀ ጳጳስ ምደባ፤ በተ.ቁ(10) የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት መምሪያ አደረጃጀት እና በሊቃነ ጳጳሳት መመራት እንደኾኑ ተጠቅሷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው፣ በትላንት፣ ግንቦት 18 ቀን ኹለተኛ ቀን የቀትር በኋላ ውሎው፣ በእንደራሴ ምደባ አስፈላጊነት ላይ መምከር እንደ ጀመረ ተሰምቷል፡፡ የሚበዙት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የምደባውን አስፈላጊነት ከፓትርያርኩ አፈጻጸም እየተነሡ በማስረዳት ሲደግፉ፤ ርእሰ መንበሩ በበኩላቸው፣ በአጀንዳነት መያዙን ከመቃወም ጀምሮ “ሊያሠራኝ ስለማይችል አልቀበለውም” ማለታቸው ተነግሯል፡፡ ይኹንና የምልዓተ ጉባኤው አባላት ጠንካራ አቋም በመያዛቸው ለተጨማሪ ምክክር አድሯል፤ ተብሏል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ ተመርጦ የሚመደበው የቅዱስ ፓትርያርኩ እንደራሴ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከቤተ ክርስቲያን የተጣለባቸውን ሓላፊነትና መንፈሳዊ አመራር በሚጠበቀው ብቃትና ደረጃ ለማከናወን እንደሚያስችላቸው በሰፊው ታምኖበታል፡፡

ከዚኽ ሓላፊነት አኳያ፣ በእንደራሴነት የሚመደበው ብፁዕ አባት፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ እንደሚወጡ የሚጠበቁ መመዘኛዎችን ማሟላት ይኖርበታል፡፡ በመመዘኛው፥ የአስተዳደር ችሎታና የመንፈሳዊ አመራር ልምድ፤ መንፈሳዊውንና ዘመናዊውን ዕውቀት አጣምሮ መያዝ እንዲኹም ዕድሜ ቀዳሚዎቹ መኾናቸው ተጠቁሟል፡፡ ምርጫው፣ አስቀድሞ በፓትርያርኩ አልያም በምልዓተ ጉባኤው አባላት ጥቆማ ላይ ተመሥርቶ ሊካሔድ እንደሚችል ተመልክቷል፡፡

እንደራሴው፣ ቅዱስ ፓትርያርኩን በዕለት ተዕለት አስተዳደራዊ ሥራቸውና በመንፈሳዊ አገልግሎታቸው የሚያግዝ እንጂ የሚጋፋ እንዳልኾነ የሚገልጹ አካላት ለዚኽም ካለፉት ዘመነ ፕትርክናዎች በቂ ተሞክሮ መኖሩን አስታውሰዋል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ፣ ከፕትርክናቸው በፊት፣ ከየካቲት 11 ቀን 1942 ዓ.ም. ጀምሮ ለኻያ ዓመታት የመጀመሪያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ እንደራሴ ኾነው ሠርተዋል፡፡ ቅዱስነታቸው፣ የቅኔ መምህር፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትንና ፍትሐ ነገሥትን የጠነቀቁ ከመኾናቸውም በላይ ዘመኑን በዋጀ አርቆ አሳቢ አስተዳደራቸውም ይታወሳሉ፡፡ በተመሳሳይ መልኩ፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ የሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የአራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ፤ ብፁዕ አቡነ ባስልዮስ የአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እንደራሴዎች/በመሰል ሓላፊነት የሠሩ/ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡

ከእንደራሴ ምደባ በተጨማሪ፣ ከሓላፊነቱ መብዛት የተነሣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ከሚያስነቅፉና የቤተ ክርስቲያንን ልዕልና ከሚጎዱ የአስተዳደር በደሎች እና የአመራር ጉድለቶች ለመጠበቅ“የፓትርያርኩ ልዩ ሀገረ ስብከት” በሚል ስለ አዲስ አበባ በሕገ ቤተ ክርስቲያን የሰፈረውን ድንጋጌ ምልዓተ ጉባኤው በአፈጻጸም ገምግሞበፓትርያርኩ ምርጫ አስቀድሞ የመደባቸው ረዳት ሊቀ ጳጳስ እንዲመለሱ አልያም ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ የኾነ ሊቀ ጳጳስ ሊመደብበት እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎችን በመተላለፍና የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣን በጣልቃ ገብነት በመጋፋት ፓትርያርኩን ለግጭትና ነቀፋ ሲዳርግ የቆየው ልዩ ጽ/ቤት፤ ከደረጃው አኳያ በሊቀ ጳጳስ እንደሚመራና በአደረጃጀቱ እንደሚጠናከር በአጀንዳው ተጠቁሟል፡፡ “ልዩ” የሚለው ቅጽል የጽ/ቤቱን ህልውና ጊዜያዊ በማድረግ መዋቅራዊነቱን ጥያቄ ውስጥ እንደሚያስገባው የሚተቹ ወገኖች፤ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ደረጃ ሊታዩ የሚችሉና የሚገባቸው ክህነታዊ እና አስተዳደራዊ ተግባራቱ በውል ተዘርዝረው፤ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እና ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ ጋር ሊኖረው የሚገባው ግንኙነት በግልጽ ተለይቶ መቀመጥ ይኖርበታል፤ ይላሉ፡፡

በተለይ በሰው ኃይል አደረጃጀቱ፥ ቢያንስ በሥልጣን የሚሠራ የፕሮቶኮል ሹም/የጽ/ቤት ሓላፊ/ እና ጸሐፊ የሚያስፈልገው ሲኾን፤ የፕሮቶኮል ሹሙ፥ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ፣ ሥርዓትና ወቅታዊ ኹኔታ ጠንቅቆ የተረዳ፤ ስለ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ ያለው፤ በዓለም አቀፍ ቋንቋዎች(ቢያንስ በእንግሊዝኛ) በቅጡ መግባባትየሚችል(reasonable language proficiency)፤ ለዘመኑ የኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቅርብ ትውውቅና ክሂል ያለው እንዲኾን ይታሰባል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በዛሬው ስብሰባው፣ ስለ እንደራሴው ምደባና ተያያዥ ጉዳዮች ያሳደረውን አጀንዳ ቀጥሎበት እንደሚውልና የፓትርያርኩን መንፈሳዊ አመራር ከማገዝና ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ዜና፣ ምልዓተ ጉባኤው በትላንቱ ውሎ፣ በቀረበለት የ1991 ዓ.ም. ቃለ ዓዋዲ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ በዐቢይ ኮሚቴውና በሰበካ ጉባኤው ማደራጃ መምሪያ ሓላፊዎች አስረጅነት ሲወያይ ከዋለ በኋላ፣ እርማትና አስተያየት በማከል ለቀጣዩ የጥቅምት ምልዓተ ጉባኤ የመጨረሻ መልኩን ይዞ እንዲቀርብ ወስኗል፡፡

በውሳኔው መሠረት፣ የማሻሻያ ረቂቁ እስከ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ድረስ ወርዶ በሰፊ የብዙኃን ማኅበረ ካህናት እና ማኅበረ ምእመናን ውይይት እንደሚዳብር ይጠበቃል፡፡

Advertisements

6 thoughts on “ቅ/ሲኖዶስ: የፓትርያርኩን አመራር ውጤታማ በሚያደርጉ አሠራሮች ላይ መምከር ጀመረ

 1. Anonymous May 27, 2016 at 8:01 am Reply

  የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት ሥልጣንና ኃላፊነት በሕግ የተደነነ ማድረግና በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ማጠናከር ጥሩ ሐሳብ ነው፡፡እንደራሴ ግን ከተንሰራፋው ቡድናዊ አስተሳሰብ አንጻር ውሎ አድሮ ‹‹የፓትርያርኩ ቡድን›› እና ‹‹የእንደራሴው ቡድን›› የሚል ክፍፍል ያመጣል፡፡እናንተም ይህን ያህል የእንደራሴ ሹመት እንዲኖር የምትገፉት ፓትርያርኩ ላይ ካላችሁ ቅሬታ አንጻር እንጂ ችግሩ ጠፍቷችሁ አይደለም፡፡
  እንደራሴነት ቢጸድቅ እንኳ ዝርዝር ውይይትና መመሪያ የሚፈልግ ነው፡፡ያለበለዚያ በዚህ የተበላና የተጠጣው ሁሉ ያለምንም ቅንጣት የቅንነትና የመንፈሳዊነት ሽታ በየሚዲያው በሚዘራበት ዘመን በሁለቱ መካከል የሚነሳ ክፍተት ተቋማዊ አንድነትንም ሊያናጋ ይችላል፡፡

 2. girum May 27, 2016 at 9:10 am Reply

  ተመስገን እግዝአብሔር በምህረቱ ቤተክርስቲያናችንን ያስባት አባቶች ጥበቡን ያብዛላቸው ቤተክርስናችንን ይጠብቅልን

 3. Zagoi Lalibela May 27, 2016 at 9:33 pm Reply

  Ayie mahibere agannt endeabatachu diyablos sbseba bemeta kutr tagesalachu. keingdih behuala betecristianachin bewerye atmeram mknyatum ya zemen tekebrwal. ahun yesra zemen new yewerye aydelem::

 4. Michael May 27, 2016 at 10:10 pm Reply

  Sinodose should discuss and pass a resolution on our Father the God blessed Memhir Girma’s banned from casting the demons and evils from the suffered people of Ethiopia and others in writing by Abune Mathias and his fellows unfairly. Memhir Girma, instead of rewarding honor and respect for his restlessly good work in healing the people by using his God given blessing, the Orthodox Church leaders are attempting to defame his name and his wholesome work by fabricated lies and accusation. Therefore, Sinodose should not ignore the issue. This is a big issue and important to we all Orthodox Christians. God bless Ethiopia.

 5. Abrham Habtom August 31, 2016 at 3:20 pm Reply

  selam nakum ykun ahwat eshi kem fqad amlak hto alatni yfqed dyu

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: