ሕዝቡ፥ ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ ደራሽና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፤ እሰየው የሚያሰኝ አሠራር ማረጋገጥ አለብን – ፓትርያርኩ

Pat Aba Mathias Holy Synod Opening speech Gin2008

ሕዝበ ክርስቲያኑ፡-
 • ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና ለሃይማኖት መጠበቂያ ብሎ በእምነት የሚለግሰው ገንዘብ እና ንብረት ከምዝበራ ተጠብቆ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል፤
 • መልካም አስተዳደር ሰፍኖ፤ አድልዎ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ መለያየት፣ በአጠቃላይ ከሃይማኖቱ መርሕ ጋር የማይጣጣም ኋላ ቀር አሠራር እና አሰተሳሰብ ተወግዶ፣ የተስተካከለ ሥርዐትን ማየት፤
 • ስለ ሃይማኖት ክብር እና ህልውና ከልብ የሚቆረቆሩ፣ መልካም ሥነ ምግባርና የተስተካከለ ሰብእና ያላቸው፣ በኑሯቸው ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንደ ሞዴል የሚጠቀሱ ውሉደ ክህነትና ሠራተኞች እንዲመሩት፤
 • ቤተ ክርስቲያን÷ በኹሉም መስክ ጠንካራ አቅም ገንብታ፣ እንዲኹም ለሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ችግር ደራሽ እና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፡፡
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፡-
 • የሕዝበ ክርስቲያኑን ጥያቄ በጽሞና አዳምጠው እና ተቀብለው፣ በቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማዕከልነት የማስተናገድ ክርስቶሳዊ ግዴታ አለብን፤ ከሕግ የወጣ አሠራር ሲኖርም፣ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በወቅቱ ማረም ያስፈልጋል፡፡

/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የመክፈቻ ንግግር/

*               *               *

በሃይማኖት እና በሃይማኖተኝነት ላይ ከባድ ተጽዕኖ በመፍጠር ቤተ ክርስቲያንን እየወጋ ያለውን ሥጋዊ ፍልስፍና እና ቁሳዊ አምሮት በመቋቋም ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመታደግ፣ በመልካም አስተዳደር እሰየው የሚያሰኝ አሠራር ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስታወቁ፡፡

በዓለ ትንሣኤውን ካከበርን በኋላ፣ በቀኖና ሐዋርያት ድንጋጌ መሠረት፣ ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ለመነጋገር፣ በርክበ ካህናት የሚካሔደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ በርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የመክፈቻ ንግግር፣ ዛሬ፣ ግንቦት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም. ጠዋት ተጀምሯል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ የተጀመረው ምልአተ ጉባኤ፣ ቤተ ክርስቲያንን  ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በአደራነት የተረከበና ገደብ የለሽ መንፈሳዊ ሥልጣን የተሰጠው/ድንበር የሌለው መኾኑን/ የገለጹት ቅዱስነታቸው፤ ሥራው እና ሓላፊነቱም ዓለም አቀፋዊ ይዘት እንዳለው በንግግራቸው አሥምረውበታል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልእኮዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ የምታካሒድበት ይህ የኻያ አንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን፤ የሴኩላሪዝም አስተሳሰብ ያየለበት፣ የዓለም ሉላዊነት የበረታበት፣ የጽንፈኝነትና የሽብርተኝነት መንፈስ የተስፋፋበት፤ እኒኽም ኹሉ በየፊናቸው በሃይማኖት እና በሃይማኖተኝነት ላይ ከባድ ተጽዕኖ የፈጠሩበት ዘመን መኾኑን ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ አስረድተዋል፡፡ አያይዘውም፣ ዓለም በዚኽ ፍልስፍና እና ቁሳዊ አምሮት ቤተ ክርስቲያንን ለመውጋት ስትዘጋጅ፣ እኛ የክርስቶስ ወኪሎች ዝም ብለን የምናይበት ኅሊና ሊኖረን አይችልም፤ ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

የዓለም ጥበብ በክርስቶስ ጥበብ ለመቋቋም እየኾነ ያለውን ነገር ኹሉ መከታተል እና ማወቅ፤ ለወደፊትም ሊያስከትል የሚችለውን ሃይማኖታዊ፣ ማኅበራዊ፣ ሰብአዊ እና ባህላዊ ቀውስ አስቀድሞ በመተንበይ፣ ሕዝቡን በእግዚአብሔር ቃል ኃይል መጠበቅና መንከባከብ ከእኛ እንደሚጠበቅ ቅዱስነታቸው ጠቁመዋል፡፡

በተጠቀሱት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዎች፣ የአገራችን ሕዝብ ምርጫ እግዚአብሔር እና የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን እንደኾነ የጠቀሱት ፓትርያርኩ፤ ይህን ሕዝብ በሚገባ ማገልገል ከተቻለ፣ ችግሩን በሚገባ መቋቋም ይቻላል፤ ብለዋል፡፡

እንደ ቅዱስነታቸው፣ ሕዝቡን በሚገባ ለማገልገል እና ለመጠበቅ፣ ከኹሉም በፊት የሕዝቡን ጥያቄ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ቀጥሎም ለጥያቄው ተገቢ መልስ በመስጠት ፍጹም መግባባት መፍጠር ይገባል፤ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከሃይማኖት መሪዎች እና ከአገልጋይ ካህናት የሚጠብቀውን ኹለንተናዊ አገልግሎት በሚገባ ካገኘና በሃይማኖቱ እንዲኮራ የሚያስችል ኹኔታ ከተመቻቸለት፤ ለተጠቀሱት ዓለም አቀፍ ተጽዕኖዎች አይንበረከክምስለኾነም የእኛ የጥበቃ ስልት መቀየስ ያለበት በዚኹ መንፈስ እና አቅጣጫ ነው፡፡

ሕዝበ ክርስቲያኑ በአኹኑ ወቅት ከሚጠይቃቸው ነገሮች የሚከተሉትን ነገሮች በቤተ ክርስቲያኑ ማየት እንደሚፈልግ ርእሰ መንበሩ በመክፈቻ ንግግራቸው ዘርዝረዋል፡-

 • ሕዝቡ፣ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት እና ለሃይማኖት መጠበቂያ ብሎ በእምነት የሚለግሰው ገንዘብ እና ንብረት ከምዝበራ ተጠብቆ ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል፤
 • በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መልካም አስተዳደር ሰፍኖ፤ አድልዎ፣ ጭቅጭቅ፣ ንትርክ፣ መለያየት፣ በአጠቃላይ ከሃይማኖቱ መርሕ ጋር የማይጣጣም ኋላ ቀር አሠራር እና አሰተሳሰብ ተወግዶ፣ የተስተካከለ ሥርዐትን ማየት፤
 • ስለ ሃይማኖት ክብር እና ህልውና ከልብ የሚቆረቆሩ፣ መልካም ሥነ ምግባር እና የተስተካከለ ሰብእና ያላቸው፣ በኑሯቸው ኹሉ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንደ ሞዴል የሚጠቀሱ ውሉደ ክህነት እና ሠራተኞች እንዲመሩት፤
 • ቤተ ክርስቲያን÷ በኹሉም መስክ ጠንካራ አቅም ገንብታ፣ እንዲኹም ለሕዝበ ክርስቲያኑ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ ችግር ደራሽና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ተልእኮ፣ እግዚአብሔርንና ሕዝብን ማገልገል በመኾኑም፣ አባላቱም በተሰጣቸው አደራ እና ሓላፊነት መሠረት ይህንኑ የሕዝበ ክርስቲያኑን ጥያቄ በጽሞና አዳምጠው እና ተቀብለው፣ በቅዱስ መጽሐፍ አስተምህሮ፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን ድንጋጌ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያን ማዕከልነት የማስተናገድ ክርስቶሳዊ ግዴታ አለብን፤ ከሕግ የወጣ አሠራር ሲኖርም፣ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ በወቅቱ ማረም ያስፈልጋል፤ ብለዋል ቅዱስነታቸው፡፡

በዚኽ ረገድ ክርስቶሳዊ እና ሐዋርያዊ የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ከልዩ ልዩ የቤተ ክርስቲያናችን አካላት እና ከጉባኤው የሚቀርቡትን ሃይማኖታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች በጥልቀት በመፈተሽ እና በመርመር፤ ሕጋዊ እና ቀኖናዊ መፍትሔ በማስቀመጥ የተሳካ ውጤት እንደሚያስመዘግብ ርእሰ መንበሩ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ተስፋቸውን ገልጸው፤ የ፳፻፰ ዓ.ም. የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መከፈቱን በማብሠር ንግግራቸውን አጠቃለዋል፡፡

በቅዱስነታቸው የመክፈቻ ንግግር እንደተመለከተው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ለምልአተ ጉባኤው 14 የመነጋገርያ ጉዳዮችን የለየ ሲኾን፤ በምልአተ ጉባኤው የሚሠየመው አርቃቂ ኮሚቴም የጽ/ቤቱን ነጥቦች መነሻ አድርጎ የሚያቀርባቸውን ዝርዝር አጀንዳዎች በማጽደቅ ቅዱስ ሲኖዶሱ መወያየቱን ይቀጥላል፡፡

*          *          *

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ መክፈቻ ንግግር ሙሉ ቃልHoly Synod OpeningGin2008Holy Synod OpeningGin2008b
Advertisements

11 thoughts on “ሕዝቡ፥ ቤተ ክርስቲያን ለችግሩ ደራሽና አለሁላችኹ ባይ ኾና ማየት ይፈልጋል፤ እሰየው የሚያሰኝ አሠራር ማረጋገጥ አለብን – ፓትርያርኩ

 1. Anonymous May 25, 2016 at 10:17 am Reply

  ካወሩ አይበቃም ሁሌም ወሬ

 2. Anonymous May 25, 2016 at 10:56 am Reply

  Kirstos betekirstianachinin yitebkiln yeselamna yemeregagat yewengel zeme yadirgiln lemekefafel yemirotutin makin yastagisln yenisha edme yistachew kirstosin kemitela menfes e r yitebken

 3. Anonymous May 25, 2016 at 10:57 am Reply

  ይህን ለማየት ያብቃን!! ቃል ከስራ ያስምርልን ከፓትርያርኩ ጽሕፈት ቤት ይጀመርልን!!

 4. yene May 25, 2016 at 11:41 am Reply

  how many TIMES the patriarch insist on very POSITIVE and ENCOURAGING statements in words but execute NOTHING! corruption, narrow mindness, and nufake have become more and more spreading even worse than before. the IMPORTANT THING IS TO IMPLEMENT THE WORDS OF HOPE IN THE GROUND NOT VOID HOPE IN THE AIR

 5. zeleke May 25, 2016 at 1:26 pm Reply

  Kalwotin Yasimir Fetari Yasebutn Yasfetsimwot. wugzetunm yatsina.

 6. Anonymous May 25, 2016 at 2:43 pm Reply

  ወሬ ወሬ ወሬ ምንድነው ወሬ!!! ይኽን አቅደን ይኽን አከናውነናል ለምን አይሉም… ሁሌ ወሬ.. በየቦታው ወሬ እውነት ሰለቸኝ! ለምንም የማይጋብዝ ወሬ፡፡ ይሰበሰባሉ፣ ይወያያሉ ይወስናሉ፣ ግን ተግባራዊነት ላይ ወገቤን ይላሉ፡፡ ቃላትን ማሳመር ብቻ፡፡ ይቅርታ አድርጉልኝና በእግአብሔር የሚተማመኑም አይመስለኝም፡፡ ወሬ ብቻ፡፡ ዝርፊያ ብቻ፡፡ በጎጥ መቧደን፣ መወልሰት፣ መጠቃቀም፣ የአዳም ልጅነትን መርሳት… ለምን? ሰው በልቶ፣ በልቶ ገንዘቡን ሰብስቦ ሰብስቦ የት ነው ሚሄደው? ካህናት ምሳሌዎቻችን ናቸው፡፡ ከእነሱ በላይ ማንን ነው ምሳሌ የሚሆነን? እባካችሁ ወገኖቼ መዝሙር ምዕራፍ ፬፣ ቁ ፱ አንብቡት፡፡ ሰው ግራ ተጋብቷል፡፡ ስንት ቅዱሳን ያሉባት ተዋሕዶ ሃይማኖት የወስላቶች ከሆነች ቆች፡፡ ለምን? ስለዚህ ከወሬ በላይ ተግባራዊ ድርጊት በጥቂት ጊዜ ውስጥ መታየት አለበት አለበለዚያ…

 7. Anonymous May 25, 2016 at 4:37 pm Reply

  ፓትርያርኩ ካድሬ እንጂ መንፈሳዊነት የለባቸውም ሁልጊዜ ወሬ ማውራት የሚሰሩትን ማደናቀፍ እንጂ ሥራ የት ያውቃሉ ?መልካም ስራን ማደናቀፍ ስራቸው ነው ::

 8. Tewodros Gidey May 25, 2016 at 4:44 pm Reply

  መልክቶችን በሰዓቱ አድርሱልን በጣም ደስየ ይላል፣
  እግዚአብሔር ተዋህዶን ይጠብቅ አባቶችንም ልቦና ይስጥ

 9. Anonymous May 25, 2016 at 10:05 pm Reply

  enante mahbere kidusan sorry erkusan ye bete krstiyan zerafiwoch enagzal blachihu ahun ye church lela tigegna hunachihu abatoch masadeb hone sirachihu and ken meatu aykerlachihum

 10. Zagoi Lalibela May 25, 2016 at 10:43 pm Reply

  Yih setan mahiber endegbreabatu diyablos ye sinodos sbseba bemeta kutr merz mertset lmadu new mkniyatum bekidusan sme yemeta ye setan meliktegna slehone new beyeametu yeabatochachin kidus sbseba eyetelefe yehuket, yekrkr, yemekefafel, beatekalay yih merz mahiber yekidus sinodosachin sbseba kealemawi sbseba yebase yekrkr medrek endihon let ke ken eyesera yemigegnow. neger gn yih be ethiopia ” branch of mason” maletm yesetan melektegna yehone bekdusan sme yeminegd yehuket mahiber betekiristiyanachnn ayafersatm. Mknyatum, betekrisitiyanachin be krstos dem, be hawariyat astemhro, be semaetat ena be kdussan tegadlo new yetemeseretechu! Egziabher tewahdo emnetachin ke huket, krikr, meleyayet ena kezih merzam bekdusan sme yeminegd mahiber yitebkln. Amen!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: