በርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎት: በጎጥና በሙስና መሾም ተወገዘ፤ ሕግ እንዲከበርና ፍትሕ እንዲሰፍን ተጠየቀ፤ “ፖሊቲካ ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ”/ብፁዕ አቡነ እንድርያስ/

ምልዓተ ጉባኤው ከሚነጋገርባቸው አጀንዳዎች መካከል፡-

 • የቅ/ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅ/ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ምደባ
 • በአ/አበባ ሀገረ ስብከት የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ እና ምደባ
 • ካህናት እና ምእመናን በጥቆማ ያልተሳተፉበት የኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ እና ሢመት ጉዳይ
 • ሙስናንና ኑፋቄን ጨምሮ ኹለተናዊ ችግሮች የተጠኑበት የዐቢይ ኮሚቴ ሪፖርት ተጠቅሰዋል
 • ጉበኞች እንዲወጡ፤ በዝባዦች እንዲጋለጡ፤ ምርጫ እና ምደባ በሞያ እንዲኾን ተጠይቋል

 *               *               *

his grace abune Endryas

አራቱ ጉባኤያት ተጠያቂ፤ መምህር ወመገሥጽ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንድርያስ፤ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በዓለ ትንሣኤ በዋለ በአራተኛው ሱባኤ/፳፭ኛ ቀን/፣ የሚያካሒደው የምልዓተ ጉባኤ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባ የመክፈቻ ጸሎት ሥነ ሥርዓት፣ ዛሬ፣ ግንቦት ፲፮ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ተከናውኗል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናትና ምእመናን በተገኙበት በዚኹ ሥነ ሥርዓት፤ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢው ብፁዕ አቡነ እንድርያስ የመርሐ ግብሩን ትምህርት ሰጥተዋል፡፡

ብፁዕነታቸው÷ የቤተ ክርስቲያንን ዐበይት ወቅታዊ ችግሮችና ተግዳሮቶች የዳሠሡበትና ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ከነገ ጀምሮ በሚያካሒደው የምልዓተ ጉባኤው ስብሰባው እንዲያተኩርባቸው ያሳሰቡበት ትምህርታቸው፤ በተጠቃሽ ኃይለ ቃላት የተሞላ፤ ሰማዕያኑን ያስደመመ እና ጥቂት የማይባሉትንም ባልተለመደ አኳኋን ያስጨበጨበ ነበር፡፡

“ስምዐነ አምላክነ ወመድኃኒነ ተስፋሆሙ ለኵሎሙ አጽናፈ ምድር፤ አምላካችንና መድኀኒታችን  ሆይ÷ ስማን፤  በምድር ዳርቻ ኹሉ ላሉ ተስፋቸው የኾንክ“/መዝ. 64(65)÷6/ በሚል የተነሣው የብፁዕነታቸው ትምህርት፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያን መሸርሸሩን በመጥቀስ ሰዎችን ከማለዋወጥ ይልቅ ሕጉን ማወቅና ማክበር ቅድሚያ እንዲሰጠው አሳስበዋል፤ ቤተ ክርስቲያን የሕግ እና የመላእክት ቦታ፤ የእግዚአብሔር የሥራው መገለጫ እና የምሕረቱ መገኛ መኾኗን በማስገንዘብ፤ “በምእመናን ምጽዋት የከበሩ፤ የምጽዋት ጌቶች” ያሏቸውንና በምዝበራቸው ጎጆ መውጫ ያደረጓትን አማሳኞች ገሥጸዋል፡፡

“ቤተ ክርስቲያን መናገጃ አይደለችም! ሌቦች ይውጡ! ጉበኞች ይውጡ! ሠርተው ይብሉ! በቤተ ክርስቲያን አውደልዳይ አይብዛ፤ ቦታ ይሰጠው፤” ያሉት ብፁዕነታቸው፤ ከምእመናን ይልቅ በአስተዳደር መዋቅሯ ውስጥ የተሰገሰጉ አማሳኞች ችግር እንደኾኑባት በግልጽ አመልክተዋል – ቢሮው የማን ነው? በጉቦ የገባ ማን ነው? ወንጌሉ የሚሰበከው ለማን ነው? ሕዝቡ ተሰብኮ፣ ተሰብኮ ዐውቆታል፤ ከቢሮ ውስጥ ነው ችግሩ፤ ጥያቄው ሲጎርፍ አለመመለስ ነው ችግሩ፤ በዚኽ ዓለም ያልታመነ በእግዚአብሔር መንግሥትስ ቦታ አለው እንዴ? ትምህርቱ የጆሮ ቀለብ ኾኗል፤ ውስጥ ገብተው ሲያዩት ያስለቅሳል፡፡”

የቀጣይ ሦስት ዓመታት፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ምርጫ እና ምደባ ጨምሮ፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ረዳት ሊቀ ጳጳስ ምርጫ እና ምደባ እንዲኹም፤ በቀኖና ቤተ ክርስቲያንና በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ ድንጋጌ መሠረት ማኅበረ ካህናት፣ ማኅበረ ምእመናንና የሰንበት ት/ቤቶች በየአህጉረ ስብከታቸው በጥቆማ ያልተሳተፉበት የኤጲስ ቆጶሳት፣ ምርጫ እና ሹመት፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአጀንዳው ከሚነጋገርባቸው መካከል ዋነኞቹ እንደኾኑ ተጠቁሟል፡፡ ብፁዕነታቸውም፣ “በጎጥ እና በቋንቋ የምንመራው እስከ መቼ ድረስ ነው?” ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ፣ በእኒኽ አጀንዳዎች ረገድ አይሎ የሚሰማውን ውስጣዊ መሳሳብ የጠቆመ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ 

ምርጫ በሞያ ይኹን፤ በጎጥ አይደለም፤ ሲጠየቅ መልስ የሚሰጥ የሕዝብ አባት ይኹን፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው? መሰብሰባችንም ምንም በቈዔት የለውም” ሲሉ ብፁዕነታቸው የምልዓተ ጉባኤውን አባላት በአጽንዖት አሳስበዋል፡፡

የአራቱ ጉባኤያት ተጠያቂ አራት ዓይናው መምህር ወመገሥጽ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ÷ በአኹኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያን በአራቱም ማዕዝናት በበርካታ ጥያቄዎች መከበባቧን ጠቁመው፣ ከፖሊቲከኛነት ይልቅ ሕጉን በመመልከት፣ እውነቱን በመግለጥ እና ስለ እውነት በመቆም በብቃት ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል መንፈሳዊ፣ ፍትሐዊ እና መዋቅራዊ ቁመና ይዘን እንድንገኝ በጽኑ መክረዋል፡፡

“አእምሯችን ሳይገራ፣ ለሕጉ ተገዥ ሳንኾን ከየትም ከየትም መጥተን እግዚአብሔርን የምናስቀይም ነው የምንኾነው፤ ያልተቀጣ ልጅ ኹልጊዜ እንደሰረቀ ይኖራል፤ ልቡናው በእግዚአብሔር ቃል እና ምስጢር ያልተቀጣ ሰው ኹልጊዜ እንደበጠበጠ ይኖራል፤ ፖሊቲካ ከቤተ ክርስቲያን ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ ቅዱስ አባታችን፤ ስለእውነት እንቁም፤ በአራቱ ማዕዝን ጥያቄ ተቀስሯል፤ ስለ ሃይማኖት ጥያቄ እየተነሣ ነው፤ ጥያቄውን የሚመልሰው ማን ነው? ብዙ ችግሮች ቀርበዋል፤ የሚፈታቸው ማን ነው? አእምሮ ያስባል፤ ጆሮ ይሰማል፤ ድኻ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ፤ የሚል አባት ከሌለ ትርጉሙ ምንድን ነው? ዙሪያውን ሰይፍ ተመዞ እየተብለጨለጨ የደነዘዘውን አእምሮ እናስወግደው፤ ቃሉን እንጠይቀው፡፡”

በመጨረሻም፤ ምልዓተ ጉባኤው በቤተ ክርስቲያን ዐበይት ጉዳዮች ላይ የሚመክርበት ይህ ወቅት፣ ዓመታዊ በዓል መኾኑንና መሰብሰቡም ለእውነት እንዲኾን በመጠየቅ ትምህርታቸውን በሚከተለው ማመልከቻቸው ደምድመዋል፤ 

ዓመታዊ በዓል ነው፤ ለጉባኤው የማመለክተው፡- ሕጉ ይከበር፤ ስም ብቻ አንያዝ፤ ሕጉን ወደ ኋላ አሽቀንጥረን ትተን እንዴት መምራት እንችላለን? ተንኰል ይቅር፤ በውሸት አንመን፤ በዝባዥ ይጋለጥ፤ ጨርሻለኹ፡፡”

 

Advertisements

19 thoughts on “በርክበ ካህናት ቅ/ሲኖዶስ መክፈቻ ጸሎት: በጎጥና በሙስና መሾም ተወገዘ፤ ሕግ እንዲከበርና ፍትሕ እንዲሰፍን ተጠየቀ፤ “ፖሊቲካ ይውጣ፤ እውነት ይገለጥ”/ብፁዕ አቡነ እንድርያስ/

 1. Abebe Bizuye May 24, 2016 at 10:07 pm Reply

  አታችንን ቃለህይወት ያስማልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ያርዝምልን። እውነተኛ ና ለ ቤተክርስቲያናችን የሚቆረቆሩ አባቶችን አያሳጣን።

  Sent from Yahoo Mail on Android

 2. Anonymous May 25, 2016 at 12:59 am Reply

  አባታችን “ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤” በረከትዎ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብን፡፡

 3. Zelalem Jaleta May 25, 2016 at 1:00 am Reply

  አባታችን “ቃለ ሕይወት ያሰማልን፤” በረከትዎ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርብን፡፡

 4. Anonymous May 25, 2016 at 5:26 am Reply

  አባታችን ቃለሕይወት ያሰማልን በረከትዎ ይደርብን አምላከ ቅዱሣን እድሜ እና ጤና ይስጥልን አሜን፡፡

 5. Alemtsehay Belachew May 25, 2016 at 5:39 am Reply

  አባታችን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ በረከትዎ ይደርብን የቅዱሣን አምላክ ልኡል እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን፡፡

 6. Ashager May 25, 2016 at 5:42 am Reply

  አባታችን”ቃለ ሕይወትያሰማዎት”እድሜና ጤና ይስጠዎት በረከተዎት ይድረሰን

 7. Anonymous May 25, 2016 at 6:44 am Reply

  ብፁዕ አባታችን አምላከ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አምላከ ቅዱስ ያሬድ አምላከ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ ጸጋውን ክብሩን አብዝቶ ይስጥልን፤በእድሜ በጸጋ ይጠብቅልን፣ያኑርልን!!!

 8. Anonymous May 25, 2016 at 8:34 am Reply

  TSIONENE BASEBNAT GIZE ALEKESEN

 9. Anonymos May 25, 2016 at 8:36 am Reply

  “Tsionen Basebinat Gize Alekesin… ” Bereketewo Yiderben O Aba Abune

 10. sara May 25, 2016 at 8:47 am Reply

  እድሜና ጤና ይስጥዎ፡፡ሙስና፣ ዘረኝነት፣….. ለማጥፋ የሁላችንም ድጋፍ ያስፈልጋል፡፡ እውነትን ሣንፈራ እንናገር ታሸንፋለችና

 11. Anonymous May 25, 2016 at 9:00 am Reply

  ለአባታችን፡እድሜ፡ ይስጥልን፡፡

 12. Anonymous May 25, 2016 at 9:08 am Reply

  ተመስገን አባት አያሳጣን

 13. Anonymous May 25, 2016 at 10:37 am Reply

  ቃለ ህይወትን ያሰማልን ቅዱስ አባታችን

 14. solomon asratie May 25, 2016 at 11:44 am Reply

  አታችንን ቃለህይወት ያስማልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ያርዝምልን። እውነተኛ ና ለ ቤተክርስቲያናችን የሚቆረቆሩ አባቶችን አያሳጣን።

 15. Anonymous May 26, 2016 at 9:52 am Reply

  kalehiwot yasemalin

 16. Anonymous May 30, 2016 at 5:33 am Reply

  አታችንን ቃለህይወት ያስማልን የአገልግሎት ዘመናቸውን ያርዝምልን። እውነተኛ ና ለ ቤተክርስቲያናችን የሚቆረቆሩ አባቶችን አያሳጣን።

 17. Anonymous May 30, 2016 at 8:07 am Reply

  አባታችን !!! ቸሩ መድኃኔ ዓለም እድሜና ጤናዎን ሰጥቶ የአገልገሎት ዘመንዎን ያርዝምልን በአባቶች እግር ተተክተው እናት ቤተ ክርስቲያናችን በእውነትና በቅንነት የሚያገለገሉ ደጋግ መምህራንን በቸርነቱ እንዲያስነሳልንና ስለ እኛ ስለምእመናን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን ? በረከትዎ በሁላችን አድሮ እያንዳንዳችን ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን !!!
  ሥምረተ ማርያም

  አባታችን !!! ቸሩ መድኃኔ ዓለም እድሜና ጤናዎን ሰጥቶ የአገልገሎት ዘመንዎን ያርዝምልን በአባቶች እግር ተተክተው እናት ቤተ ክርስቲያናችን በእውነትና በቅንነት የሚያገለገሉ ደጋግ መምህራንን በቸርነቱ እንዲያስነሳልንና ስለ እኛ ስለምእመናን ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልን ? በረከትዎ በሁላችን አድሮ እያንዳንዳችን ለንስሐ ሞት ያብቃን አሜን !!!
  ሥምረተ ማርያም

 18. solomon May 30, 2016 at 7:25 pm Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: