በምዕራብ አርሲ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በደቡብ ክልል ዞኖች የሚተዳደሩ 13 ወረዳዎች በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ አቀረቡ

Shashemene

 • ሻሸመኔን ዋና ከተማው ያደረገው የምዕራብ አርሲ ዞን ከተቋቋመ 11 ዓመታት ተቆጥረዋል
 • የዞኑ ምእመናን፣ በአዳማ ሀገረ ስብከት ሥር መጠቃለላቸው እንግልት እያደረሰባቸው ነው
 • ከሰኔ 2007 ዓ.ም. አንሥቶ እስከ መንበረ ፓትርያርኩ ጥያቄአቸውን ሲያቀርቡ ቆይተዋል
 • የመልካም አስተዳደር ችግሩ፣ በአንድነት የነበሩትን የሻሸመኔን 6 አጥቢያዎች ሰላም ነስቷል
 • ውዝግቡ ሠርግና ምላሽ የኾነላቸው አማሳኞችና የተሐድሶ መናፍቃን ጥምረት ፈጥረውበታል

ዛሬ፣ ግንቦት 16 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም በተካሔደው፣ የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ የመክፈቻ ጸሎት፤ በምዕራብ አርሲ ዞን የሻሸመኔ ምእመናን፣ በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ አቅርበዋል፤ ሊቀ ጳጳስ እንዲመደብላቸውም ጠይቀዋል፡፡

በአራት መኪኖች ተጭነው የመጡ ከ150 በላይ ምእመናን፣ በመክፈቻ ጸሎቱ ፍጻሜ፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ከእንባ እና ከፍተኛ ተማኅፅኖ ጋር በንባብ ባሰሙት አስተዳደራዊ ጥያቄ፤ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማግኘት እና መንፈሳዊ ግዴታቸውን ለመፈጸም ወደ አራት የተለያዩ አህጉረ ስብከት ለመሔድ በመገደዳቸው፣ ለእንግልት እየተዳረጉ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ምእመናኑ በጽሑፍ ያቀረቧቸውን ጥያቄዎች፣ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እና ለብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት አሰራጭተዋል፡፡በአኹኑ ወቅት፣ የምዕራብ አርሲ ዞን – ሻሸመኔን ጨምሮ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጳጳስነት እየመሩ የሚገኙት፣ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ናቸው፡፡

Shashemene01 Shashemene03

የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ቅዱስ ሲኖዶስ እና የዞናችን እስተዳደር በሚያወጣው የልማት እና የዕድገት ጎዳና ላይ በንቃት መሳተፍ እንድንችል፤

በከተማችን ሰላማችንን ለማስጠበቅ እና የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ለሚያቀርብልን ማንኛውም የመንፈሳዊ አገልግሎት ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት እንድንችል፤

በርቀት በአዳማ ከተማ ጽ/ቤቱን አድርጎ እያስተዳደረን ካለው የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ይልቅ ዞን እንደመኾናችን መጠን በርእሰ ከተማችን ሊቀ ጳጳስ ቢመደብልን፤


 

Advertisements

4 thoughts on “በምዕራብ አርሲ፣ በባሌ፣ በአርሲ እና በደቡብ ክልል ዞኖች የሚተዳደሩ 13 ወረዳዎች በሀገረ ስብከት ራስን የመቻል ጥያቄ አቀረቡ

 1. ገነት ተገኔ May 24, 2016 at 8:11 pm Reply

  ቅዱሳን አባቶቻችን በረከታችሁ ይደርብን!!! ድረሱልን ጥሪ። በደቡብ አፍሪካ የጆሀንስብርግ ጽርሀ ጽዩን መድሀንያለም ቤተ ክርስትያን ጉዳይ አረ ህዝብ ሳይጫረስ ከፊታችን እሁድ 21/9/2008 በፊት ስለ ህያው እግዝአብሄር ብላችሁ ድረሱልን።

 2. ተስፋዓለም ገ/ጊዮርጊስ May 25, 2016 at 9:17 am Reply

  በጎ የሆነውን ሃሳብ ለመፈፀምና ለማስፈፀም እግዚኣብሄር ይርዳን።

 3. Anonymous May 27, 2016 at 6:46 am Reply

  hager sibket megentelim tifeligalachu ayidel makoch ayi mahiber kesashoch

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: