ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በፓትርያርኩ ተነገራቸው፤ የአያሌ አባቶች እንባና እርግማን አለባቸው

 • ቤተ ክርስቲያንን “የተደረተች”፤ፓትርያርኩን“ብቃት የሌላቸው”፤ ጳጳሳቱን“ማይሞች እና ደደቦች” እያሉ መዝለፍ አዘውትረዋል፤
 • ራሳቸውን የመንግሥት ታማኝ አድርገው ስም እየጠሩና “እገሌ ደወለልኝ” እያሉ በፓትርያርኩም ላይ ጫና ሲፈጥሩ ቆይተዋል፤
 • ጥላ ወጊ አለኝ፤ በጥላ ወጊ እሸበልለዋለኹ!” የሚለው ከንቱ የጥንቆላ፣ የመተት እና የመርዝ ማስፈራሪያቸውም አይዘነጋም!
 • ምደባቸው፥ ከሹመት ቦታዎች ውጭ እንዲኾን በተደጋጋሚ ቢጠቆምም፤ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የድርጅት ሓላፊነት እየተፈለገላቸው ነው
 • በበኬ ከተማ ባለ6 ፎቅ ሕንፃ እያስገነቡ ነው፤ የተለያዩ ይዞታዎች ባለቤት በኾኑበት በየረር ሰፈራ ባለ5 ፎቅ ሊገነቡ ይንቀሳቀሳሉ

*          *          *

NebureEd Elias Abreha deposed
የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንደተነገራቸው ተሰማ፡፡

ፓትርያርኩ ውሳኔአቸውን ያሳወቋቸው፣ ለኢየሩሳሌም ጉብኝት ከመነሣታቸው አራት ቀናት በፊት እንደነበር የተናገሩት ምንጮቹ፤ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ከልዩ ጸሐፊነታቸው መነሣታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ሳይደርሳቸው እንዳልቀረ ጠቁመዋል፡፡

በሓላፊነት በተቀመጡባቸው ቦታዎች ኹሉ፥ በምዝበራ ሰንሰለታቸው የሙስና ገበያውን እያጧጧፉ ሕገ ወጥ ሀብት በማካበት፤ የጎጥ እና የመንደር ቡድን እያቋቋሙ በመከፋፈል፤ የቀድሞውንም ይኹን የወቅቱን ፓትርያርክ ክፉ እየመከሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ እና ለቤተ ክርስቲያን ደግ ከሚያስቡ አካላት በማራራቅ፤ ለጥቅሜ እና ለሥልጣኔ ያሰጋሉ ያሏቸውን የሥራ መሪዎች እና አገልጋዮች በማሳደድ፤ ከኹሉም በላይ፣ ሓላፊነታቸውን ተገን በማድረግ ለሚያገኟቸው ዓላውያን፥ ቤተ ክርስቲያንን በአድርብዬ ፖሊቲከኛነት እያሳጡ የተቋማዊ ለውጥ ጥረቷን በማሰናከል በሚገባ የሚታወቁ የአማሳኞች አለቃ እንደኾኑ ሲዘገብ ቆይቷል፡፡

ከዚኽም አኳያ ምደባቸው ከሹመት ቦታዎች ውጭ እንዲኾን በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ሳይቀር በተደጋጋሚ ሲጠቆም ቢቆይም፤ ከልዩ ጸሐፊነታቸው ከተነሡ በኋላ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአንድ ድርጅት ዋና ሓላፊ ኾነው ሊመደቡ እንደሚችሉ እየተነገረ ይገኛል፡፡

በ1986 ዓ.ም ከጎንደር ወደ አዲስ አበባ መጥተው በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በመዘምርነት ሥራ የጀመሩት ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፤ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤት አስተዳደር ዲን ኾነው የሠሩ ሲኾን በርእሰ ገዳማት ወአድባራት አኵስም ጽዮን ንቡረ እድነት ተሹመውም ነበር፤ ነገር ግን በጽዮን ንብረቶች ላይ በፈጸሙት ከፍተኛ ሙስና ከተማውን በ24 ሰዓት ለቀው እንዲወጡ ኾነው መባረራቸውን ተከትሎ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው በሠሩባቸው ዘጠኝ ዓመታት ሦስት ብፁዓን ዋና ሥራ አስኪያጆችን አፈራርቀዋል፡፡

በዕሥራ ምእቱ መባቻ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ለማስከበር በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የተመራ ሲኖዶሳዊ መንቀሳቀስ በተደረገበት ወቅት፤ “መፈንቅለ ፓትርያርክ ነው እንጂ የሕገ ቤተ ክርስቲያን ጥያቄ አይደለም” በማለት ከጊዜው የውስጥና የውጭ ግብረ አበሮቻቸው ጋር ጥረቱን በማሰናከል ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የሕገ ቤተ ክርስቲያንን የበላይነት በማስከበር ጥረቱ ተጠቃሽ አስተዋፅኦ የነበራቸው ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ከሓላፊነታቸው እንዲነሡም በብዙ ደክመዋል፡፡

ለዚኽ ክፋታቸው የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅነት በወቅቱ ቢመኙትም አላገኙትም ነበር፡፡ ይኹንና የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራን ጨምሮ የንብረት አሰባሰቡን በካህናቱ ተሳትፎ በማሻሻል እንባቸውን ያበሱት ፀረ አማሳኙ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም መዛወራቸውን ተከትለው በ2003 ዓ.ም. ሲመደቡበት ግና፤ በዋና ዋና አድባራት በዘረጉት የምዝበራ ሰንሰለታቸው አማካይነት አዲስ አበባን የደራ የሙስና ገበያ አድርገው ራሳቸውን በከፍተኛ ደረጃ አበልጽገውባታል፡፡

ቅጥር፣ ዕድገት፣ ዝውውር የሚጠይቁ የአድባራት ሠራተኞች፥ ድንጋይና አሸዋ እንዲደፉ፤ ሲሚንቶ እንዲያወርዱ በአቀባባይ አማሳኞች እየታዘዙ፣ በሰንዳፋ በብር 600 ሺሕ መኖርያ ቤት ሠርተዋል፡፡ ለቅጥር፣ ዕድገት እና ዝውውር ኮሚቴ ተሠይሟል ይሉ የነበረ ቢኾንም፤ ለስም ካልኾነ በስተቀር ምንም የማይፈጸምባቸው፣ በትንሹም እስከ 30 ሺሕ ብር ጉቦ የሚጠይቅባቸው ነበሩ፡፡ የልማት ጉብኝት” እያሉ በደላሎቻቸው አመቻችነት በሚሔዱባቸው አጥቢያዎች ከ30 ሺሕ እስከ 50 ሺሕ ብር እጅ መንሻ(የኮቴ) ይቀበሉም ነበር፡፡

NeBureEd Elias Abreha Mesfin
የረር በር(ሰፈራ) እየተባለ በሚጠራው በወረዳ 28 ቦሌ – ኮተቤ ቀበሌ ገበሬ ማኅበር ውስጥ፣ በ1988 ዓ.ም. በባለቤታቸው ስም በገዙት 480 ካሬ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ ባለአምስት ፎቅ ሕንፃ በማስገንባት ለድርጅት ለማከራየት እየተሯሯጡ ሲኾን፤ በዚኹ አካባቢ በባለቤታቸው እናት ስም የገዙትን ስፋቱ 300 ካሬ ሜትር የኾነ ሌላ ይዞታ ለብሎኬት ማምረቻ ማከራየታቸው ተገልጿል፤ ቆይተው ኹለቱንም ይዞታዎች በራሳቸው ስም ማዞራቸው ተጠቅሷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ፣ በበኬ ከተማ ከፍተኛ ውሳኔዎች እየሰጡ በሌላ ስም የሚያስገነቡት ባለስድስት ፎቅ ሕንፃ እንዳላቸውም የታወቀ ሲኾን፤ ከቀድሞው የሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ ጋር ፍጥጫና ፉክክር ውስጥ የከተታቸው፤ በዚኽ መልኩ በየቦታው የጀማመሯቸውን ሥራዎች የሚያስጨርሱበት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ፍለጋ እንደነበር የዐደባባይ ሐቅ ኾኗል፡፡ በልዩ ጸሐፊነታቸውም፤ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ፣ በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት እና በአዲስ አበባ የታላላቅ አድባራትንና ገዳማትን አስተዳዳሪዎችንና ሠራኞችን እየጠሩ በማስፈራራት፤ የመንግሥት ውክልና አለኝ እያሉ ጉቦ በመጠየቅ ተጠቅመዋል፡፡ የየረር በር ጽርሐ አርኣያም ቅድስት ሥላሴ ደብር አስተዳዳሪን በፓትርያርኩ ማኅተም ያለደረጃቸው በማገድ ወደ ቦታቸው ለመመለስ ብር 300.000 ጉቦ መጠየቃቸውም ይጠቀሳል፡፡

በ2005 ዓ.ም. ለመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በቀረበ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሒሳብ ሪፖርት ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ጉድለት መኖሩን ተከትሎ ከሥራ አስኪያጅነታቸው የተነሡት ንቡረ እዱ፤ መንፈሳዊ ዘርፍ በሚል በጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅነት ሲመደቡም፤ የዜና ቤተ ክርስቲያን ርእሰ አንቀጽ እንደተቸው፣ “የምክትል ሥራ አስኪያጆች ጋጋታ” ከመኾን ባለማለፉ፣ ብዙ ተንኰል የሠሩበትን የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት፣ በልዩ ጸሐፊነት ተቆጣጥረው፤ ከተማሪ ቤት ጀምሮ የተከተላቸው የደጋግ አባቶችንና ሊቃውንትን እንባ እና እርግማን ያተረፉበትን ክፋታቸውን በሽፋን እየፈጸሙ ቤተ ክርስቲያንን ሲያምሱበት ቆይተዋል፡፡

ከሓላፊነታቸው እንደሚነሡ ካወቁበት ጊዜ ጀምሮ፣ ፓትርያርኩን፥ “የአመራር ብቃት የላቸውም፤ ይረሳሉ፤ እኔ ጽፌ ከምሰጣቸው ደብዳቤ ላይ ከመፈረም ውጪ አንዳች ክህሎት የላቸውም፤ መቼም ቢኾን አይነኩኝም፤ ያለእኔ አይኾንላቸውም” እያሉ ማሳጣት የያዙ ሲኾን፤ ፓትርያርኩ ያራመዷቸውን አወዛጋቢ አቋሞች በጀብደኝነት እየጠቀሱ፣ ለዚኽ ያበቋቸው እርሳቸው እንደኾኑ አፍ አውጥተው እስከ መናገር መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

“ጭቁን ካህናት” በሚል ባደራጇቸው ግለሰቦች፣ አራተኛው ፓትርያርክ ከሥልጣን እንዲወርዱ ሲቀሰቅሱ ከነበሩት አንዱ እንደነበሩ የሚያስታውሱ፤ ጳጳሳቱንም“ማይሞችና ደደቦች” እያሉ ከመዝለፍ አልፈው፣ “ሰው አጥተው እንጂ እንደ ሉተር የሚነሣባቸው ቢኖር ጉዳቸው ይወጣ ነበር” በሚል ገና በተማሪነት የተለከፉበትን መንፈቀ – ሉተራዊነት፣ የተደረተች በሚሏት ቤተ ክርስቲያን ላይ አዘውትረው እንደሚያውጁ ያስረዳሉ፡፡

ከተማሪ ቤት አንሥቶ ለጥቅም ያደሩ እንጂ እምነት እንዳልነበራቸው የሚያውቋቸው ይናገራሉ፡፡ በተማሪነታቸው፣ ለልደት እና ለትንሣኤ በዓላት ገንዘብ በፖስታ እያሸጉ ከሚሰጡ ሚስዮናውያን መቀበል በማዘውተራቸው፣ የጎንደር በዓታው የአቋቋም ምስክር ዬኔታ ኄኖክ ወልደ ሚካኤል፣ “እዚያ ሔዳችኹ ብር የተቀበላችኹ ኹሉ ቃለ እግዚአብሔር እሳት ኾኖ ያቃጥላችኹ!” ብለው ረግመዋቸዋል፡፡ የመጻሕፍት እና የቅዳሴ ዐዋቂው የፊት አቦ አለቃ፣ “መድኃኔዓለም ያንከራትህ!”፤ ሊቀ አእላፍ በላይ “ብንን ያድርግህ!” ብለው አልቅሰውባቸዋል፡፡ ገና ተራ መዘምር ኾነው ቃለ እግዚአብሔር እያበላሹ እኔ ነኝ የማውቀው እያሉ በዓምባገነንት በማስቸገራቸው የአቋቋሙ ሊቅ ዬኔታ ሐረገ ወይን ክፉኛ አዝነውባቸዋል፡፡ የቅኔ እና የመጻሕፍት መምህሩ መጋቤ ስብሐት ኃይለ ማርያም፣ “ይኼ ምስጥ አርዮስ” ይሏቸው ነበር፡፡

ስለ ሊቅነታቸው ብዙ ቢነገርም፣ “በጽሕም እና በፈረጅያ የተሸፈነ፤ በማሕሌት ያልተፈተነ ነው፤” ይላሉ የቅርቦቻቸው፡፡ ቀስ ብለው ማርቀቁን ከሚያውቁበት የነገር መጣጥፍ በቀር፣ በቅኔው ሳይደክሙ መጽሐፍ ቤት ገብተው ከማቴዎስ መቅድም መዝለቅ ስለተሳናቸውና በክፋታቸውም በመጣላታቸው በሊቀ ሊቃውንት መንክር ከባድ ተገሣጽ እስከመባረር ደርሰዋል፡፡ በዚኽ ዓመት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በማታው መርሐ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን የሚያጠናቅቁ ቢኾንም፤ ቀደም ሲል “በከፍተኛ ማዕርግ” ተብሎ የተቀበሉት ዲፕሎማም ባልደከሙበት በዋዛ ያገኙት ሥላቅ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

ሬሳ በዝምታው ይፈራል እንዲሉ በከባድ ጸጥታቸውና ጽሕማቸው ለብዙ ቢገመቱም፤ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል መዘምር ሳሉ፣ “ረድእ ናት” እያሉ በማስተዋወቅ በቤታቸው ያቆዩአትን በኋላ የሕግ ሚስት ቢያደርጓቸውም፤ ከጋብቻው በፊት በተደጋጋሚ እንዲያስወርዱ ያስገድዷቸው እንደነበር ብዙዎች ያውቃሉ፡፡ እኒኹ የልጆቻቸው እናት ባለቤታቸው፣ መውለድ እንደተከለከሉ በሐኪም እንደተነገራቸው እያወቁ፣ በጭካኔአቸው ሳቢያ ለኅልፈት ካበቋቸው በኋላ ዓመታት ቢያልፉም፣ ቄስ ይኹኑ መነኵሴ ሳይታወቁ ወደ መቅደሱ ሲወጡና ሲገቡ ይታያሉ፡፡

 


NebureEd Elias Abreha Mesfin02በቅርቡም ለጡመራ መድረኩ የደረሰው ጥቆማ የሚከተለውን ይላል፡-

ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ፤ የሕግ ሚስቱን በድብደባ ገድሎ ሴተኛ አዳሪ እየጎተተ የቤተ ክርስቲያንን ክብር ያዋረደ ሃይማኖት የለሽ ሰው ነው፡፡ ይህ ሰው፣ ብዙ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንትንና የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን በጥንቆላ፣ በመተት እና በመርዝ መቃብር በማውረድ በርካታ ልጆችን ያለአሳዳጊ ያስቀረ፤ ብዙ ቤተሰብን ያለጥፋታቸው በሐዘን የቀጣ የዲያብሎስ ጭፍራ ነው፡፡

ዛሬ ንቡረ እዱ ሚስቱን ገድሎ ሬሳ ያወጣበትን ቤት አፍርሶ ወደ ፎቅ ለመቀየር ግንባታ የጀመረ ሲኾን ጊዜያዊ ቤት ጎሮ አካባቢ ተከራይቶ የተቀማጠለ ኑሮ በመኖር ላይ ነው፡፡ በሰፈራ አካበቢም ሌላ 1000 ካሬ ሕገ ወጥ መሬት ገዝቶ ግንባታ ለማከናወን በፓትርያርኩ ስም እየነገደ፣ ባልተሰጠው ሥልጣን ደብዳቤ እየፈረመና ፓትርያርኩ በማይመጥናቸው ደረጃ የአድባራት አለቆችን እንዲያግዱ እያስደረገ፤ በዚኽም ከፍተኛ ጉቦ እየተቀበለ ቤተ ክርስቲያኒቱን እያተራመሰ ቤቱን ለመገንባት እየሠራ ይገኛል፡፡

ንበረ እዱ፣ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ እንቅስቃሴ በስውር ከሚሠሩ ድርጅቶች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በመቀበል አቅሙንና ጉልበቱን አስተባብሮ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የዘመተ ሲኾን፤ የዚኹ ዘመቻ አካል የኾኑ የየመንፈሳዊ ኮሌጆች አንዳንድ ሓላፊዎችን በጥቅም እና በሥልጣን በማባበል የዘመቻው አካል አድርጎዋቸዋል፡፡


“ነጠላ ለባሾች፤ ማይሞች” እያሉ የሚሣለቁበትን ማኅበረ ቅዱሳንን፣ በመፈንቅለ መንግሥት በመክሠሥ የሚታወቁት የመዝባሪዎች አለቃ ንቡረ እድ ኤልያስ፣ “መንግሥት ማኅበረ ቅዱሳንን እንዳፈርስ ነው በቦታው ያስቀመጠኝ፤ ከመንግሥት ጋር ኾኖ መዝጋት ነው!” በሚል ውስጥ ውስጡንና አልፎ አልፎም በተገኙት መድረኰች ‹ብርቱ› ተፋላሚ ኾነው ቆይተዋል፡፡ የራሳቸውንና የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቡድኖችን ሐሳብ የመንግሥት በማስመሰል ብፁዓን አባቶችን ለማስፈራራት፤ በደኅንነት ስም ያደራጇቸውን ግለሰቦች ወደ ፓትርያርኩና አንዳንድ ጳጳሳት በመላክ ማኅበረ ቅዱሳንን የማፍረስ ሐሳብ የመንግሥት አቋም ነው፤ እያሉ ተጽዕኖ ለመፍጠርም በብዙ ሞክረዋል፡፡

በዚኹ አጀንዳና በሓላፊነታቸው ተገን ለተዋወቋቸው አፅራረ ቤተ ክርስቲያን ባለሥልጣናት፣ ራሳቸውን የመንግሥት ታማኝ አድርገው በማቅረብ፤ ስማቸውን እየጠሩና “እገሌ ደወለልኝ” እያሉ በፓትርያርኩ ላይ ሳይቀር ጫና በማሳደር ተቀባይነት ለማግኘት በአያሌው ሲጣጣሩ ቆይተዋል፤ “ጥላ ወጊ አለኝ፤ በጥላ ወጊ እሸበልለዋለኹ!” የሚለው ከንቱ የጥንቆላ፣ የመተት እና የመርዝ ማስፈራሪያቸውም የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ኾኖም፣ በመጨረሻ፤ ኹሉም ፊታቸውን አዙረውባቸዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በ2007 ዓ.ም ግንቦት ወር የምልዓተ ጉባኤው ስብሳባ፣ በአማሳኝነታቸውና በእምነት የለሽ ክፉ ምክራቸው ከመንበረ ፓትርያርኩ አካባቢ እንዲርቁ ለፓትርያርኩ ቢያሳስባቸውም፤ ፓትርያርኩ፥ “አብራችኹ አንሡኝ” ብለው ባደረጉላቸው መከላከል ወራትን የገዙበት ዕድሜ ከእንግዲኽ አይቀጥልም፡፡ ይህ ዘገባ ሲጠናቀር በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በአንድ ድርጅት በዋና ሓላፊነት እንደተመደቡ ቢሰማም፣ ርግጡ ግን፤ በልዩ ጸሐፊነታቸው እንደማይዘልቁ ፓትርያርኩ ያሳወቋቸው መኾኑ ነው፡፡

Advertisements

10 thoughts on “ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ በሓላፊነታቸው እንደማይቀጥሉ በፓትርያርኩ ተነገራቸው፤ የአያሌ አባቶች እንባና እርግማን አለባቸው

 1. w May 20, 2016 at 10:46 am Reply

  sera leseriw eshoh latariw endilu Egziabher yferdal!!!

 2. Anonymous May 20, 2016 at 2:25 pm Reply

  ‹‹ የተንኮሉን ጉድጓድ አትቆፍረው ከቆፈርከው አታርቀው የሚገባበት አይታወቅምና ››

 3. Anonymous May 20, 2016 at 3:23 pm Reply

  Now the Patriarch will get enough time to think about his Tewahido Church……..Nuredin will go to hell.

 4. Anonymous May 20, 2016 at 4:47 pm Reply

  ነጠላ ለባሾች፤ ማይሞች እያሉ የሚሣለቁበትን ማኅበረ ቅዱሳንን

 5. Anonymous May 20, 2016 at 10:07 pm Reply

  ትንሽ ከሃይማኖት የወጣችሁ አልመሰላችሁም

 6. Anonymous May 22, 2016 at 10:19 am Reply

  This is yemane’s dream. He paid for this article to you and you posted it. I see that both hara and aba SELAMA do not work for truth. I am sorry to see this.

 7. Mikayeil Geberekidan May 25, 2016 at 10:33 am Reply

  yasaznaley papas wede poletika tegeb megezim waga yelewem

 8. yesion May 30, 2016 at 8:38 am Reply

  የ ”አባት“ እርግማኖች
  የ”ምሁራን” ጠላቶች
  የ”ትልቅ” አንከርቶች
  የ”ሊቃውንት” ሐፍረቶች
  የወንጌሉ እንቅፋቶች
  የመንፈሰ ቅዱስ ሞጋቾች
  ለመዳኑ ሀይል ተጋርጠው
  ከመቅደሱ መሃል ቆመው
  ከሞት ጭፍሮች ጋር አብረው
  ነውራቸውን ስድባቸውን ንቀታቸውን እያጓሩ
  ከጭንጫው መሃል ዘርዘሩን እየመረጡ ሲያበጥሩ
  ጎተራውን በገለባ በብቅ በንክርዳድ ሲሰፍሩ….
  አትዝረፉ ባይ ዘራፊዎች
  አትዋሹ ባይ ቀጣፊዎች
  የስሙ ጠላት ጠምጣሚዎች
  አናንት የዘመን መርገምቶች
  ብትጥሉን እንቆማለን
  ብታውሩን እናያለን
  ብታመክኑን እንወልዳለን
  ሞትም ቢሆን ብትገሉን
  በሱ …
  ትንሳኤውን ባወጀልን
  መዳን በሞቱ በሰጠን
  ሀይሉን በፍቅሩ ባደለን
  የብርሀን ልብስ ለብሰን
  የጽዮን ልጆች በምስጋና ከዙፋኑ ስር ለዘላለም ስሉስ እያልነው እንከብራለን
  በወደደን በክርስቶስ … ዘላለም እና ለዘላለም ካሸናፊዎች እንበልጣለን

 9. Anonymous May 24, 2018 at 10:15 am Reply

  it is amazing.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: