የዴር ሡልጣን ጉዳይ ከዋነኛ ተግባራችን አንዱና በየደረስንበት የምናስረዳው አጀንዳ ነው – በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ

Der sultan

  • “ግብፃውያን እንዳያድሱ ርስትነቱ የእነርሱ አይደለም፡፡ እኛም ከተከለከልን ማደስ ያለበት፣ መንግሥት ነው፡፡ ችግሩ የእስራኤልንም መንግሥት የሚያስነቅፍ ነው፡፡”/ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ/
  • “በኤምባሲው ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ፣ ከዋነኛ ተግባራት አንዱ ኾኖ ተቀምጦ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱም ክትትል የሚያደርግበት ነው፡፡” /በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዌ ዮሴፍ/
  • “ምንም ቢኾን መነጋገር የማይፈታው ነገር የለምና እንነጋገርበታለን፤ ጉዳዩን እንፈታዋለን፡፡”/የእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሩቨን ሩቭሊን/

    *               *               *

“ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በተጓዝን ቁጥር የንግሥት ሳባን ፈለግ መከተላችንን እናስባለን፤” ያሉት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል ያለው ዝምድና፣ በዓለም ሃይማኖታዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ታሪክ እጅግ ጥንታዊው መኾኑን ለእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ነግረዋቸዋል፤ ይላል የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ድረ ገጽ ዘገባ፡፡

ይኹንና ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የዴር ሡልጣን ገዳማችን አለመታደሱ አግባብ አለመኾኑን የገለጹት ፓትርያርኩ፤ በእግዳት ውስጥ እስካለ ድረስ ሓላፊነቱ የመንግሥት መኾኑን ለፕሬዝዳንቱ አስረድተዋቸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱም በምላሻቸው፣ “መነጋገር የማይፈታው ነገር የለምና እንነጋገርበታለን፤ ጉዳዩን እንፈታዋለን፤” እንዳሏቸው ኢቢሲ፣ በትላንት፣ ግንቦት 10 ቀን ምሽት ዜናው ገልጿል፡፡

የፓትርያርኩ ሐዋርያዊ ጉብኝት የኹለቱን ሀገሮች ግንኙነት ከማጠናከር ባሻገር የገዳማቱ ችግሮች ትኩረት እንዲያገኙ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፤ ያሉት በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዌ ዮሴፍ በበኩላቸው፣ “የዴር ሡልጣን ጉዳይ፣ በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ፣ ከዋነኛ ተግባራት አንዱ ኾኖ ተቀምጦ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱም ክትትል የሚያደርግበት ነው፤ እኛም በየደረስንበት ቦታ የምናስረዳው አጀንዳ ነው፡፡” ብለዋል፡፡


(ኢ.ቢ.ሲ፤ ቡሩክ ተስፋዬ፤ ግንቦት ፲ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

በኢትዮጵያ እና በእስራኤል መካከል ለሦስት ሺሕ ዓመታት የዘለቀው የባህል፣ የሃይማኖትና ማኅበራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳሰቡ፡፡

ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ በእስራኤል በነበራቸው ሐዋርያዊ ጉብኝት በኢየሩሳሌም ጎልጎታ ይዞታ ካላቸው የኦርየንታል፣ የግሪክ እና የላቲን አብያተ ክርስቲያናት ፓትርያርኮች እና መሪዎች ጋር ተገናኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታ የኾነውን የዴር ሡልጣን ገዳምንም ጎብኝተዋል፡፡

Presidentr Rivlin with the Ethiopian Orthodox Patriarch in Jerusalem

ፓትርያርኩ ከዚኽም በተጨማሪ፣ ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሩቨን ሩቭሊን ጋር ባደረጉት ውይይት፤ ኢትዮጵያ እና እስራኤል ከንግሥት ሳባ እና ከንጉሥ ሰሎሞን ጀምሮ ከሦስት ሺሕ ዓመታት በላይ የቆየ የሃይማኖት፣ የባህል፣ የማኅበራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

ይኹን እንጂ እንደ ዴር ሡልጣን ባሉ ጥንታውያን ገዳማት ይዞታዎች ላይ እየደረሰ ያለው የቆየ ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ ጠይቀዋል፤ ቦታው እስከ አኹን አለመታደሱ አላግባብ መኾኑን በመጠቆም፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፣ ከፕሬዝዳንት ሩቭሊን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ፕሬዝዳንት ሩቨን በዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ገዳም ዙሪያ ያሉ ችግሮችን ፍትሐዊ በኾነ መልኩ እንደሚያዩት እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

ግብፃውያን እንዳያድሱ፥ ቦታው፣ ርስትነቱ የእነርሱ አይደለም፡፡ እኛም ከተከለከልን እነርሱም የማያድሱት ከኾነ፣ ማን ነው ማደስ ያለበት፣ መንግሥት ነው፡፡ ማደስ ያለበት መንግሥት ነውና በእኛ ላይ ያለው ችግር ብቻ ሳይኾን የእስራኤልንም መንግሥት የሚያስነቅፍ ነው፡፡ ምንም ቢኾን መነጋገር የማይፈታው ነገር የለምና እንነጋገርበታለን፤ ጉዳዩን እንፈታዋለን ነው፤ ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

Ambassador Hilawe Yosef
በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ህላዌ ዮሴፍ በበኩላቸው፤ የፓትርያርኩ የእስራኤል ሐዋርያዊ ጉብኝት፣ በኢትዮጵያ እና እስራኤል መካከል ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክርና በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ይዞታዎች አካባቢ ያሉ ችግሮች ከፍተኛ ትኩረት እንዲያገኙ የሚያደርግ መኾኑን ነው የገለጹት፡፡ በእስራኤል የኢትዮጵያ መንግሥት ኤምባሲም፣ በዴር ሡልጣን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ ጠንክሮ እንደሚሠራም አስታውቀዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት በማጠናከር ረገድ ከቀረበው ጥያቄ አኳያ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ኹለተኛው፣ በገዳማችን አካባቢ ስላሉ ችግሮች መፍትሔ በማግኘትም ረገድ እንደዚኹ ከፍተኛ ፋይዳ አለው፡፡ የዴር ሡልጣን ጉዳይ፣ በእስራኤል የኢፌዴሪ ኤምባሲ ዓመታዊ ዕቅድ ውስጥ፣ ከዋነኛ ተግባራት አንዱ ኾኖ ተቀምጦ፣ ዋና መሥሪያ ቤቱም ክትትል የሚያደርግበት ነው፤ እኛም በየደረስንበት ቦታ የምናስረዳው አጀንዳ ነው፡፡

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የተመራው ልኡክ በእስራኤል የነበረውን ጉብኝት አጠናቅቆ ተመልሷል፡፡

Advertisements

4 thoughts on “የዴር ሡልጣን ጉዳይ ከዋነኛ ተግባራችን አንዱና በየደረስንበት የምናስረዳው አጀንዳ ነው – በእስራኤል የኢትዮጵያ ኤምባሲ

  1. Wogene May 19, 2016 at 2:44 pm Reply

    ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርኩ ግብጽም እሥራኤልም በመጓዝ የሚመለከታቸውን መንግሥታዊና መንፈሳዊ ባለሥልጣኖችን ኢየሩሳሌም ስለሚገኘው ታሪካዊ የኢትዮጵያ ቅርስ፤ “ዴር ሡልጣን” ገዳም ማነጋገራቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። ያስገኙት ውጤትም የተጨበጠ ተግባር የሚያስገኝ እንጂ ዲፕሎማሲያዊ የሆነ ባዶ ተስፋ እንዳልነበረ የሚያረጋግጥ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተደገፍ መግለጫ በቅርቡ በይፋ እንደሚወጣ ይጠበቃል።

    ከዚህ ጋር የተያያዘው ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ግን ቅዱስ ፓትሪያርኩ እሥራኤል ድረስ ተጉዘው አንገብጋቢ የሆነውን እጅግ ከባድ ጉዳይ ማንሳት አለማንሳታቸውን ምንም ዓይነት መግለጫ አለመውጣቱ ነው። ይኸውም የሚመለከተው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በ34 ዓ/ም በተጠመቀበት፤ ወደ ጋዛ በሚወስደው መንገድ ኣጠገብ የሚገኘው ሥፍራ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ገዳም እና/ወይም ደብር እንዲቋቋምበት የማመቻቸቱ ተግባር ነው። እንደቅሚታወቀው፤ በመጽሓፍ ቅዱስ፤ በሐዋርያት ሥራ፤ በምእራፍ 8 ቁ. 26-39 እንደ ተገለጸው፤ በዘመናዊው አጠራር የገንዘብ ሚኒስትር የነበረው ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ፤ በፊልጶስ አማካኝነት እዚያ ሥፍራ ተጠምቋል። በቤተ ክርስቲያን ትውፊትም የተጠመቀበት ዓመትም 34 ዓ/ም መሆኑ ተገልጿል። ያ ጥምቀት፤ ኢትዮጵያ ክርስትናን በመቀበል ቅድሚያ እንዳላት የሚያረጋግጥ ከፍተኛ ቅርስ በመሆኑ ተገቢ የሆነ መታሰቢያ ሊቋቋምለት ይገባል።

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: