የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከቀናት በኋላ የሙከራ ስርጭት ይጀምራል

 • መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፣ አገልግሎቱን በዋና ዳይሬክተርነት ይመራሉ
 • በፓትርያርኩ የኢየሩሳሌም ጉብኝት ከኮሚዩኒኬሽን ኩባንያው ጋር ውል ተፈጽሟል
 • ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ለሥርጭቱ የ30,050 ዶላር ወርኃዊ ክፍያ ለኩባንያው ይፈጽማል
 • ፓትርያርኩ የኹለት ሳምንት ጉብኝታቸውን አጠናቀው ዛሬ ከቀትር በኋላ ይመለሳሉ

ethiopianorthodoxበጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በተወሰነው መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያናችን፣ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ምእመናን ድምፅዋን የምታሰማበት እና መረጃ የምትሰጥበት የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከኹለት ሳምንት ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭቱን እንደሚጀመር ተገለጸ፡፡

የስርጭት አገልግሎቱን ለመስጠት ለወድድር ከቀረቡት ሦስት ኩባንያዎች መካከል በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የብዙኃን መገናኛ ድርጅት ቦርድ ከተመረጠውና በእስራኤል ከሚገኘው የኮሚዩኒኬሽን ኩባንያ ጋር የሥርጭት ስምምነት ውሉ ፓትርያርኩ ኢየሩሳሌምን እየጎበኙ በነበሩበት በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ መፈጸሙም ታውቋል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ለአገልግሎቱ 12 ሚሊዮን ብር የአንድ ዓመት በጀት ያጸደቀ ሲኾን፤ በዚኽ ሳምንት በተፈረመው የስምምነት ውል መሠረት ቤተ ክርስቲያናችን፣ 30,050 ዶላር(ከ660ሺሕ ብር በላይ) በየወሩ ለኩባንያው እንደምትከፍል ተጠቁሟል፡፡

የብዙኃን መገናኛ ድርጅቱን በዋና ዳይሬክተርነት እንዲመሩ በቦርዱ የተመደቡት እና ስምምነቱን ከኩባንያው ጋር የተፈራረሙት መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል ናቸው፡፡ በኹለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ የሙከራ ስርጭቱን ይጀምራል የተባለው አገልግሎቱ፤ የድርጅቱን ሎጎ(መለዮ) ከማስተዋወቅ ባሻገር ቀደም ሲል ተቀርጸው ከቆዩ የምስል ወድምፅ ክምችቶች የተመረጡ ትዕይንቶች፣ ትምህርቶችና መዝሙራት እየቀርቡበት የሚቆይ ሲኾን፤ መደበኛ ዝግጅቱ ከሦስት ወራት በኋላ መተላለፍ ይቀጥላል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

ቀረፃውንና ዝግጅቱን በሀገር ውስጥ በማከናወን መካከለኛው ምሥራቅን፣ ደቡብ አውሮፓን፣ ሰሜንና ምሥራቅ አፍሪቃን የሚያካልለው የሳተላይት ሥርጭቱ፥ ለተቀረው ዓለም ዝግጅቱን በኢንተርኔት በመጫን እንደሚያስተላልፍ ተጠቅሷል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር ሕንፃ በተሰጡት ስምንት ቢሮዎች ውስጥ ሥራውን በማከናወን ላይ የሚገኘው አገልግሎቱ፤ በቀጣይ፣ የአኹኑን የኦዲዮ ስቱዲዮ በዘመናዊ መልክ የማደራጀት ዕቅድም ይዟል፡፡

ዘጠኝ አባላት ያሉትና በስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ እና የምሥራቅ ጎጃም ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ የሚመራው ቦርዱ፤ ተጠሪነቱ ለሥራ አስኪያጁ የኾነ ኤዲቶሪያል ቦርድ እና ሰባት አባላት ያሉት የዝግጅት ኮሚቴ ሠይሟል፤ በቅርቡም፣ ከፍተኛ የሥርጭት ቴክኒክ ክህሎትና ልምድ ያለው የምክትል ዋና ዳይሬክተር እንዲኹም የ22 ሠራተኞች ቅጥር ለማካሔድ የሚያስችል መስፈርት አውጥቶ ማጠናቀቁም ተገልጧል፡፡

መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል

ዋና ዳይሬክተሩ መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል

በመጀመሪያው ዙር ከ10 ሰዎች በላይ ተወዳድረውበታል በተባለው የዋና ዳይሬክተሩ ቦታ፣ በቦርዱ መመዘኛ መሠረት ለመጨረሻው ዙር ካለፉት አምስት ሰዎች አንዱ የኾኑትና በመጨረሻው ፈተና ቅድሚያውን ይዘው የተመረጡት መ/ር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል፤ በመጀመሪያ ዲግሪ ከቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሥነ መለኰት፤ በኹለተኛ ዲግሪ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ምሩቅ ናቸው፡፡ ቀደም ሲል በመንበረ ፓትርያርክ ቤተ መጻሕፍት ወመዘክር እና ቅርስ መምሪያ እንዲኹም በውጭ ጉዳይ መምሪያ በሓላፊነት ሠርተዋል፡

በተያያዘ ዜና፣ ከሚያዝያ 26 ቀን ጀምሮ ላለፉት ኹለት ሳምንታት ኢየሩሳሌምን የጎበኙት ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለሱ ታውቋል፡፡ በጉብኝታቸው፤ የእስራኤል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ የመንግሥታቸውን የሃይማኖቶች ጉዳይ ክፍል እና የፖሊስ አካላትን ያነጋገሩ ሲኾን፤ በኢየሩሳሌም ይዞታ ካላቸው ጥንታውያን ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት አባቶች እንዲኹም ከገዳማቱ ማኅበረ መኮሳት ጋር መወያየታቸውም ተገልጧል፡፡

Presidentr Rivlin with the Ethiopian Orthodox Patriarch in Jerusalem

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ከእስራኤሉ ፕሬዝዳንት ሩቨን ሪቭሊን ጋር

pat jeru visit11

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ በኢየሩሳሌም ከግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክና የመንበረ ፓትርያኩ አባሎች ጋር ከተወያዩና የመታሰቢያ ስጦታ ልውውጥ ካደረጉ በኋላ

ከሊቃነ ጳጳሳቱ፤ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም፣ ብፁዕ አቡነ ኢሳይያስ እና ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ጋር በጉብኝቱ የሰነበቱት ፓትርያርኩ፤ ዛሬ ተሲዓት በኋላ አዲስ አበባ ሲደርሱ፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የመምሪያ እና የድርጅት እንዲኹም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሓላፊዎች፤ ከየክፍላተ ከተማው የተውጣጡ የአድባራት አለቆች በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አዳራሽ አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው ተመልክቷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

Advertisements

18 thoughts on “የቤተ ክርስቲያናችን የ24 ሰዓት የቴሌቪዥን አገልግሎት ከቀናት በኋላ የሙከራ ስርጭት ይጀምራል

 1. walelign May 17, 2016 at 12:50 pm Reply

  ELlllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllllll betam des yilan

 2. Anonymous May 17, 2016 at 2:30 pm Reply

  Betam Des Yilal

 3. Mulatu May 17, 2016 at 3:09 pm Reply

  መናፍቃኑ(ተሀደሶው) ጉድ ፈላበት፤ እንዳይጀመር የገቡት ፅዓትም አፈርበላ።

 4. Anonymous May 17, 2016 at 5:52 pm Reply

  Elllllllllllllllllllllllllllll

 5. Anonymous May 18, 2016 at 3:16 am Reply

  minm enquan bnzegeym mejemeru gin betam betam des ylal.!ayzon bertu.

 6. yene May 18, 2016 at 5:30 am Reply

  ayeeeeeeeeee! how can we be sure that the media will be free from tehadiso intervention or political intervention of the government. believe me that both will try their best to control the program, don’t be fool.

  • Anonymous May 19, 2016 at 6:07 am Reply

   really, I highly agree with your idea

 7. Anonymous May 18, 2016 at 5:40 am Reply

  betamm dess yelal

 8. Anonymous May 18, 2016 at 8:00 am Reply

  Bete krstianachn Kezh blay yemesrat akm alat…..mechereshwn E/R yasmrew

 9. Anonymous May 18, 2016 at 4:58 pm Reply

  እልልልልልልልልልልልልልልልልል ደስ ስል

 10. Anonymous May 18, 2016 at 6:20 pm Reply

  Glory to God. May God gives us the strength to accomplish it with Orthodoxy.

 11. Anonymous May 18, 2016 at 7:20 pm Reply

  ምን የሉት ነው መታከክ ከማይመስሉ ጋር በማይመች አካሔ አትጠመድ የተባለው መፅሐፍ ው ቃል ተዘነጋ ???

 12. solomon May 19, 2016 at 6:14 am Reply

  በጣም ደስ የሚል ዜና ገና ሌላም መጨመር አለበት

 13. fesha negash May 19, 2016 at 9:12 am Reply

  በመጀመሪያው ዙር ከ10 ሰዎች በላይ ተወዳድረውበታል በተባለው የዋና ዳይሬክተሩ ቦታ፣ ሲባል ከእነማን ጋር ተወዳደሩ ለማለት ነው?? የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከመ/ር ዳንኤል ይልቅ ለቦታው አይቅርብመ ነበር ? ማለት በተማረው ትምህርትና በፈጣንነቱ

 14. Anonymous May 20, 2016 at 6:16 am Reply

  REALLY VERY GOOD.THANKS GOD!!!!
  BUT I HAVEcommments on SOME BETEKIHINET REPORTERS .
  (BENAZIRET KETEMA KIDUS GEBREL BETE KIRSTIAN YEMINFkINA TIMHIRT SIYASTEMIRU YETEGEGNU MENAFIKAN YEADDIS ABEBAWU LIUKAN SIHEDU ENDE GUM BENEW ENDE TIS TENEW TEFU) yemiketeru sewch endhi enkef zena reportrs mehon yelebachwm.
  yet hedu? timhirtacw mindnew? keyt metu? wodet hedu?….gizew melis yifligal.
  yemanem wode dirjitu biro TPLF yigba, menesawina kihinet yalachwun bihon.

 15. Anonymous May 20, 2016 at 6:18 am Reply

  english version of sign ……whre is THEWAHDO….not only orthodox need tewahido

 16. amani fantasticboy May 21, 2016 at 4:55 pm Reply

  betme arif

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: