ሰበር ዜና – የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ: ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለፓትርያርኩ የጻፈውን ጽሑፍ በማተሙ በጠቅ/ቤተ ክህነቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ተከሠሠ

Daniel Kibret Views on Sendek

  • ከስም ማጥፋት ወንጀል በተጨማሪ የ100 ሺሕ ብር የፍትሐ ብሔር ክሥ አቤቱታም ቀርቧል
  • ግንቦት 17 እና 26 ቀን በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት ይቀርባል
  • የሕግ አገልግሎት መምሪያው የጉዳዩ አያያዝ እና የክሡ አቀራረብ ጥያቄ አሥነስቷል

*                *                *

ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች ለማረጋገጥ እንደተቻለው፤ የሰንደቅ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል፥ ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 ቀን 2008 ዓ.ም. በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዋና ሓላፊ አማካይነት የክሥ ጽሕፈቱ ደርሶታል፡፡

በክሥ ጽሕፈቱ እንደተገለጸው፥ ከሣሹ፣ የሕግ አገልግሎት መምሪያው ዋና ሓላፊ እና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ወኪል አፈ መምህር አባ ገብረ ሥላሴ ጌትነት ሲኾኑ፤ ተከሣሹ ደግሞ፤ የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ ናቸው፡፡

የክሡ ምክንያት፣ ጋዜጣው በ11ኛ ዓመት ቁጥር 551 ረቡዕ መጋቢት 21 ቀን 2008 ዓ.ም. እትሙ“ፓትርያርኩ፡- ለኢትዮጵያ የደኅንነት፣ ለምእመናን የድኅነት ሥጋት” በሚል ርእስ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የተጻፈውን ጽሑፍ እንዲታተም በመፍቀዱ እና በማተሙ እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡

በ2000 ዓ.ም. በወጣው የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት ዐዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀጽ 43(7) መሠረት የቀረበ መኾኑ በተገለጸው የወንጀል ክሥ፤ ጋዜጣው በተጠቀሰው እትም ገጽ 20፤ በ1996 ዓ.ም. በወጣው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 43(1)(ሀ) እና 613(3) ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ተቋማዊ አሠራር ጥላሸት የሚቀባ እና የቤተ ክርስቲያኒቱን ፓትርያርክ ስም የሚያጠፋ እንዲኹም በመልካም ስም እና ዝናቸው ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ሕዝበ ክርስቲያኑ የቤተ ክህነቱን ተቋማዊ አሠራር እንዳይቀበል ለማድረግ ኾን ተብሎ የተጻፈ እንደኾነ ተገልጧል፡፡

ጽሑፉን በስድስት ነጥቦች በመክፈል ተፈጽሟል ያለውን የስም ማጥፋት ወንጀል ዝርዝር ሲያስረዳም፡-

  1. “… ምእመናንን የሚያጸና ጉባኤ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ ሕዝቡ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየመጣ ነው ሲሏቸው፤ ወጣቱ ትውልድ ቤተ ክርስቲያኑን ለማገልገል እየተጋ ነው ሲሏቸው፤ ዲያስጶራው ሕዝብ በእናት ቤተ ክርስቲያን ሥር ሆነ ሲሏቸው፤ ቤተ ክርስቲያንን የሚገልጥ ዐውደ ርእይ ሊዘጋጅ ነው ሲሏቸው፤ መንፈሳዊ የቴሌቭዥን ፕሮግራም ሊቀርብ ነው ሲሏቸው ያን ጊዜ ብዕራቸውን ይዘው ለማገድና ለመክሠሥ ይነቃሉ፡፡ የፓትርያርኩ ብዕር ግን ምእመናንን የሚያጽናና ጦማር ለመጻፍ የሚጨበጥ አይደለም፡፡ እንደ ጠንቋይ ብዕር ለማፍዘዝና ለማደንገዝ እንጂ፡፡” በማለት በተቋሟ የሚጻፉ ደብዳቤዎች ተቀባይነት እንዳይኖራቸው በመቀስቀስ፤
  2. “የመንግሥት ባለሥልጣናት ሳይቀሩ የገዛ ልጆችዎን ያወያዩ ሲሏቸው በራቸውን ጠርቅመው የሚዘጉ ፓትርያርክ በታሪክ የሚጀመሪያው መኾን አለባቸው፡፡ በሱራፊ ነበልባል የተዘጋች ገነት ስትከፈት በፓትርያርክ የተዘጋች የቤተ ክህነት በር ልትከፈት አልቻለችም፡፡” በማለት የቤተ ክርስቲያኒቱ ተቋማዊ አስተዳደር እንደተዘጋና ህልውና እንደሌላት በማስቆጠር ሐሰተኛ ወሬ በመንዛት፤
  3. “ዐውደ ርእዩ የማይደረግበት በቂ ምክንያት ከነበረ ቢያንስ ከሳምንት በፊት መግለጥ ይቻል ነበር፡፡ ዓላማው ግን ማበሳጨት፣ ዐመፅ ማስነሣት፣ ተስፋ ማስቆረጥና ምእመናንን ወደማይፈልጉት መሥመር መውሰድ ነው፡፡” በማለት በመንግሥታዊ አሠራር የታገደን ዐውደ ርእይ በቤተ ክህነቱ የታገደ አስመስሎ በማቅረብ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለዐመፅ ለማነሣሣት ስውር ቅስቀሳ በማድረግ፤
  4. “የዚኽች ሀገር ሰላም አይፈለግም? ምእመናን ሀገር እንደሌላቸውና መብት እንደሌላቸው ራሳቸውን እንዲቆጥሩ ይፈለጋል? ‹ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል› እንዲል ሀገሪቱ ያለባት ችግር አይበቃትም? ተጨማሪ ችግር ማምረት ይፈለጋል?” በማለት ሀገሪቱን ሰላም አልባ አድርጎ ከመቁጠሩም በላይ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሀገር ደኅንነት ስጋት አድርጎ በመሣል፤
  5. “እውነት መንግሥት በስሙ የሚሠራውን ያውቀዋል፤ ካወቀውስ ዝም ይላል? ቤተ ክህነቱ በሚያመጣው ዳፋ መከራ ለመቀበልስ ዝግጁ ነው?” በማለት የቤተ ክህነቱን አጠቃላይ መልካም ስም እና ዝና ጥላሸት በመቀባት፤
  6. “የገዛ ፓትርያርካችን ለእኛ ለምእመናን ድኅነትን እንዳናገኝ ስጋት ኾነውብናል፡፡ የታገሡትን ኹሉ ለክፋት በማነሣሣት ደግሞ ለሀገሪቱ ደኅንነት ሥጋት እየኾኑ ነው፡፡” የሚል ይዘት ያለው ጽሑፍ እንዲታተም በመፍቀድ እንዲታተም ያደረገ በመኾኑ በፈጸመው የስም ማጥፋት ወንጀል መከሠሡን ያትታል፡፡
Ferew Abebe, Editor-in-chief

ሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ አቶ ፍሬው አበበ

የክሥ መጥሪያውም፤ ዋና አዘጋጁ ግንቦት 17 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ኹለተኛ ወንጀል ችሎት ጠዋት 3፡00 ላይ እንዲቀርብ ማዘዙ ታውቋል፡፡

የሕግ አገልግሎት መምሪያው፣ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ “የዳንኤል እይታዎች” በተሰኘው የጡመራ መድረኩ(ብሎጉ) ለመጀመሪያ ጊዜ ዓርብ፣ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የጦመረውን ጽሑፍ፣ ጋዜጣው በመጋቢት 21 ቀን እትሙ ቀድቶ በማውጣቱ ተፈጽሟል ባለው የስም ማጥፋት ወንጀል የብር 100‚000(አንድ መቶ ሺሕ ብር) የኅሊና ጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ይወሰንለት ዘንድ የፍትሐ ብሔር ክሥም አቅርቧል፡፡

“በጥንታዊ እና ታሪካዊ እንዲኹም የሀገር ውለታ በኾነው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ላይ ለተፈጸመብን የስም ማጥፋት እና ክብረ ነክ ስድብ፣ በዐዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀጽ 41(1) እና (2) መሠረት ክቡር ፍ/ቤቱ ተመጣጣኝ እና አግባብነት ያለው የኅሊና ጉዳት ካሳ ብር 100‚000 እንዲከፈለን እንዲወስንልን እንጠይቃለን፡፡” ይላል – በቁጥር ሕ/አ/47/08 በቀን 18/08/08 ዓ.ም. ለፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረበው የጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ የክሥ ማመልከቻ፡፡ ጋዜጣውንና ኹለት የጠቅላይ ጽ/ቤቱን ሠራተኞችም በሰነድ እና በሰው ማስረጃነት ጠቅሷል፡፡

የጋዜጣው ዋና አዘጋጅም፣ ክሡን ለመስማት ግንቦት 18 እና መልስ ለመስጠት ግንቦት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቂርቆስ ምድብ 2ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ረፋድ 4፡00 ላይ እንዲቀርብ መታዘዙ ታውቋል፡፡

 

25 thoughts on “ሰበር ዜና – የሰንደቅ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ: ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ስለፓትርያርኩ የጻፈውን ጽሑፍ በማተሙ በጠቅ/ቤተ ክህነቱ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ተከሠሠ

  1. Getaneh Kassie May 10, 2016 at 5:17 pm Reply

    ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም………………….

  2. Eyerusalem May 10, 2016 at 6:38 pm Reply

    እኔ የምለው ወንጌልን መስበክ ወይስ ማህበረ ቅዱሳንን ? ለማህበረ ቅዱሳን ጥያቄ በየ ዋትሳፕ ግሩፕ በስመአብ አትበሉ ብላችሁ የምትከለክሉት ቆይ እናንተ ማናችሁ ተሀድሶ ? የህማማት መፅሀፍ በስመአብ ብሎ እየጀመረ እናንተ ግን ለምን ሰውን ታደናግራላችሁ ይልቁኑ መልካሙን ስራችሁን የማያጠፋ የጥላቻ መንፈስ በህዝቡ ላይ አትዝሩ በስመ አብ ሳንል የሴጣን መጫወቻ ወይም ሙስሊም ልታደርጉን ያሰባችሁ ይመስለኛል።

  3. Anonymous May 11, 2016 at 1:49 am Reply

    አሁን በዛ “ስለ ፅዮን ዝም አልልም” ህዝቤ ሆይ አሁን ተነስ አውሬውን ትዋጋው ዘንድ ከወንድማችን ጎን እንቁም

  4. Anonymous May 11, 2016 at 6:02 am Reply

    sewuyew eko lemenfesawi timhrt sayhon birachew leks endeminesa eyaregagetu new. Minekachew? Beka min yale entin min sayaderg aylekim yemibalew besachew mefetsemu ygermal

  5. Anonymous May 11, 2016 at 6:49 am Reply

    sme teftual blo sewn mekses berasu chirstosawi aydelem!!!

  6. GODOLIYAS May 11, 2016 at 6:53 am Reply

    sme teftual blo sewn mekses berasu begle chirstosawi aydelem!!!melkam sm yemigegnew melkam bemesrat enji wede frd bet bemehed aydelem!!!

  7. hazen May 11, 2016 at 7:17 am Reply

    Zelabaj memar kemetemtem yikdem ehete

  8. hazen May 11, 2016 at 7:25 am Reply

    awekesh aweksh biluwat alu? betekristiyanin beagbabu biyagelegiluwat man tsihuf yiitsifbache neber?

  9. Gebrekidan May 11, 2016 at 7:44 am Reply

    genzeb genzeb genzeb Kassa 100,000 Birr weys Tarik serto Tarik Mekeyer? How we can learn to be a Christian with such Money Lovers the so called ……

    Ayeeee Esti ante Firedewa.

  10. Anonymous May 11, 2016 at 7:51 am Reply

    የአባቶቼን ርስት አልሰጠም

  11. Anonymous May 11, 2016 at 8:31 am Reply

    abatochachin bedem yatsenuatin bet zere ibakachihu lemafresna yegenzeb bank atadrgu Minm inkuan lemewkes yemgebagn balhonim Ibakachu yeabatochn feleg sanketel abatnetn yesmna bank Alyam yesiltan anadrgew

  12. Anonymous May 11, 2016 at 11:12 am Reply

    ለክስ ከምተሮጡ መልካም ነገር ለመስራት፣ ወንጌልን ለማስተማር፣ በቤተክርስቲያኒቱ ሃይ የሚለው ሰው ያጣውን የክህደት ትምህርት መልክ ለማስያዝ ብተሰሩ እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ እመቤታችን ስለሆነች ለስቅለት ይሰገዳል ወይስ አይሰገድም; በሚል ጥያቄ የዋሁን ምዕመን ግራ የሚያጋባ ጥያቄ በማስነሳት በባሌ ዞን እመቤታችን ስለሆነች እንዳትሰግዱ ብሎ ምዕመኑን በማደናገር የሚበልጠውን እንዳያከናውን ያየነው የሰማነው በዚህ ዘመን ነው፡፡ አንዱ አባት ይሰገዳል ይላል ሌላው ደግሞ እንዳትሰግዱ ብሎ ግራ ያጋባል፡፡ በአከባቢው ያሉ አባቶቻችን “በ70 እና 80 ዓመታችን እንዲህ አይነት ነገር አልሰማንም አሁን ምን መጣ;” ሲሉ ስንሰማ፣ ምን ደረጃ ላይ እንዳለን ለማወቅ ምንም አያዳግትም፡፡ ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያኗ የራሷ ልሳን አላት ወይ; ካላት ለምን ለምዕመኗ ማስተዋወቅ አቃታት; ሕዝበ ክርስቲያኑንስ በምን በኩል ነው ወቅታዊ መረጃ የምታደርሰው; ቤተ ክርስቲያናችን ዘመኑን የዋጀች አለመሆኗን አውቀን ለለውጥ ብንሰራ መልካም ይመስለኛል፡፡

  13. Anonymous May 11, 2016 at 11:13 am Reply

    ቤተክርስቲያን አንድ ናት እባካችሁ የስጋ ፍቃዳችሁን መፈፀሚያ አታድርጓት እልህ እና ፉክክር በእግዚአብሔር ዘንድ ቦታ የለውም፡፡ ለጠላቶቻችን በር አትክፈቱብን

  14. Anonymous May 11, 2016 at 12:09 pm Reply

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈውን ጽሁፍ የሚደግፍ ሲሆን ፓትርያርኩና መሰሎቻቸው ብቻ ሊቃወሙ ይችላሉ፡፡ ምዕመኑ ተስፋ በናንተ ከቆረጠ ቆየ፤ አታውቁትም አንልም ታውቁታላችሁ፡፡ ራሳችሁን ብታርሙ አይሻልም፡፡

    ስንት ሌብነት ነው ያለው፡፡ የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከስልጣን በማግስቱ መባረር እራሱ የዘገባው ውጤት ነው፡፡ ካስፈለገ የእያንዳንዳችሀሁ ይወጣላችሁዋል፡፡ ሌባ ሁሉ፡፡ እውነትን መሸሸግ አይቻልም፡፡ ራሳችሁን ባታስገመግሙ ጥሩ ነው፡፡ ፓትርያርኩ እኔ በሌለሁበት ነው ያደረጉት እንዳይሉ ነው ውጪ መሄዳቸው፡፡ የሚሰራው ስራ ሁሉ ትክክል የውንብድና ነው፡፡ የተነገረው ልክ ነው፡፡ ራሳችሁን አስተካክሉ፡፡

    ክርስቲያን መሰደብ አይደለም፤ መመታትም ምንም ማለት አይደለም ለሱ፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደ ንጉስነቱ ሲሰደብ ተውት እግዚአብሔር ይሆናል የተናገረኝ ነበር ያለው ፡፡ የናንተ አይምሮ ግን ስጋዊ ስለሆናችሁ ተሰደብን አላችሁ መንፈስ ቅዱስ የለማ በባዶ፡፡ በሳቸው መንፈስ ቢኖር እንዲህ የወረደ ቦታ ባልተገኙ ነበር፡፡ እየወረዱ ነው የሄዱት ገና ይነገራዋል፡፡

    ሰውን የባሰ ዝም ያለውን አትቆስቁሱት አርፋችሁ ዝም ሲላችሁ ዝም በሉ፡፡ የተዳፈነ ነገር አትቀስቅሱ፡፡ እንደውም የሳቸውን ስም ለማጉደፍ የተነሱ አሉ ቤተክህነት ውስጥ ምክንያቱም ነገር እያጋጩ መኖር የሚፈልጉ ስለሚኖሩ፡፡ ስንት ሚሊዮን የሚበዘብዙትን ለምን ክስ አትመሰርቱም፡፡ ምንፍቅና የሚዘሩትን ለምን አትከሱም፡፡ ስንት ባለጌ አስተዳዳሪ እንዳለ ለምን አትከሱም ከአንዱ ደብር ወደ ሌላ ከማዘዋወር ይልቅ፡፡

    በሀገራችን ትልቁ ወንጀል ሙስና ነው ግን ስንት ሙሰኞች እያሉ ለምን ክስ አይመሰረትም ስንት ፍትህ ያጣ እያለ ለተራ ነገር መሮጥ፡፡ ፓትርያርኩ ይበልጣሉ ቤተክርስቲያን ፡፡ ቤተክርስቲያ ታሪክዋ ሲዛባ በሚዲያ ሲነገር ስትሰደብ ማንም አፉን ሲከፍት ዝም እያላችሁ አንድ ፓትርያርክ ተናገሩ ብላችሁ ዘራፍ፡፡ እኛኮ ቤተክርስቲን ከተደፈረች ቆየች ይህ ደግሞ የሳቸው አስተዋጽኦ ነው፡፡ ለሰዳቢ የሰጡ እሳቸው መከሰሰስ ያለባቸው እሳቸው፡፡ ለሙሰኛ ለዘረኛ ለሌባ ለጉበኛ ለመናፍቅ አሳልፈው የሰጡ እሳቸው መከሰስ ያለባቸው እሳቸው፡፡ እንደውም ምዕመኑ እንዳይነሳባችሁ፡፡ ፊርማ አሰባስቦ ለፍርድ እንዳያቀርባችሁ፡፡ አይቀርም ጠብቁ፡፡

    • Anonymous May 12, 2016 at 6:57 am Reply

      “ቤተክርስቲያ ታሪክዋ ሲዛባ በሚዲያ ሲነገር ስትሰደብ ማንም አፉን ሲከፍት ዝም እያላችሁ አንድ ፓትርያርክ ተናገሩ ብላችሁ ዘራፍ፡፡” you wrote what in my heart.

  15. Anonymous May 11, 2016 at 12:23 pm Reply

    ሃጸይ ዮሃንስ IV (4) ስዩመ እግዚኣብሄር ፡ንጉስ ጽዮን ወ ንጉሰ ንገስት ዘኢትዮጵያ፡ ፡

  16. Zelalem Mengistu May 11, 2016 at 1:40 pm Reply

    ቤተ-ክርስትያን አይደለም ሰውን ልተከስ ! ይቅር ተባባሉ ፣ አትካሰሱ ስትል ነው እኛ የምናውቃት ፤ ከዚህ ቀደም በቀድሞ ፓትርያርክ ላይ ብዙ ጊዜ ተጽፏል ፤ የኛ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እየገደሉት ነው ያዳናቸው ፤ የእኛ ክርስትና ምንድን ነው? ክርስቶስ ያስተማረንስ ምንድን ነው? ወንጌልስ ምንድን ነው የሚለው ? ይቅር ይበላችሁ !

  17. Anonymous May 11, 2016 at 2:51 pm Reply

    ስለ ፅዮን ዝም አልልም

  18. Alebachew Teka May 11, 2016 at 2:59 pm Reply

    …..ብዙ ማለት ይቻል ነበር ግን ምን ዋጋ ከለው፡፡
    በእኔ በኩል ክሱ አግባብነት አለው ብየ አላስብም፡፡ለማንኛውም ዲ/ን ዳንኤል የክርስቶስን ፈለግ ተከትሎ አውነትን አወጣ እንጂ መስሎ አልተራመደም አሁንም በአቋምህ እንድትፀና እግዚአብሔር ይርዳህ
    ድንግል ትከተልህ ፡፡ለእነሱም ማስተዋልን ይስጣቸው ቢያስተውሉ ኖሮ የተፃፈው ግልፅና ግልፅ ነበር፡፡

  19. shimels debeb May 12, 2016 at 7:09 am Reply

    yh hulu fetena new tewataw gn lemesnakloch woyolachew

  20. Anonymous May 12, 2016 at 11:05 am Reply

    የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት የጻፈውን ጽሁፍ የሚደግፍ ሲሆን ፓትርያርኩና መሰሎቻቸው ብቻ ሊቃወሙ ይችላሉ፡፡ ምዕመኑ ተስፋ በናንተ ከቆረጠ ቆየ፤ አታውቁትም አንልም ታውቁታላችሁ፡፡ ራሳችሁን ብታርሙ አይሻልም፡፡

    ስንት ሌብነት ነው ያለው፡፡ የየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከስልጣን በማግስቱ መባረር እራሱ የዘገባው ውጤት ነው፡፡ ካስፈለገ የእያንዳንዳችሀሁ ይወጣላችሁዋል፡፡ ሌባ ሁሉ፡፡ እውነትን መሸሸግ አይቻልም፡፡ ራሳችሁን ባታስገመግሙ ጥሩ ነው፡፡ ፓትርያርኩ እኔ በሌለሁበት ነው ያደረጉት እንዳይሉ ነው ውጪ መሄዳቸው፡፡ የሚሰራው ስራ ሁሉ ትክክል የውንብድና ነው፡፡ የተነገረው ልክ ነው፡፡ ራሳችሁን አስተካክሉ፡፡

    ክርስቲያን መሰደብ አይደለም፤ መመታትም ምንም ማለት አይደለም ለሱ፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንደ ንጉስነቱ ሲሰደብ ተውት እግዚአብሔር ይሆናል የተናገረኝ ነበር ያለው ፡፡ የናንተ አይምሮ ግን ስጋዊ ስለሆናችሁ ተሰደብን አላችሁ መንፈስ ቅዱስ የለማ በባዶ፡፡ በሳቸው መንፈስ ቢኖር እንዲህ የወረደ ቦታ ባልተገኙ ነበር፡፡ እየወረዱ ነው የሄዱት ገና ይነገራዋል፡፡

    ሰውን የባሰ ዝም ያለውን አትቆስቁሱት አርፋችሁ ዝም ሲላችሁ ዝም በሉ፡፡ የተዳፈነ ነገር አትቀስቅሱ፡፡ እንደውም የሳቸውን ስም ለማጉደፍ የተነሱ አሉ ቤተክህነት ውስጥ ምክንያቱም ነገር እያጋጩ መኖር የሚፈልጉ ስለሚኖሩ፡፡ ስንት ሚሊዮን የሚበዘብዙትን ለምን ክስ አትመሰርቱም፡፡ ምንፍቅና የሚዘሩትን ለምን አትከሱም፡፡ ስንት ባለጌ አስተዳዳሪ እንዳለ ለምን አትከሱም ከአንዱ ደብር ወደ ሌላ ከማዘዋወር ይልቅ፡፡

    በሀገራችን ትልቁ ወንጀል ሙስና ነው ግን ስንት ሙሰኞች እያሉ ለምን ክስ አይመሰረትም ስንት ፍትህ ያጣ እያለ ለተራ ነገር መሮጥ፡፡ ፓትርያርኩ ይበልጣሉ ቤተክርስቲያን ፡፡ ቤተክርስቲያ ታሪክዋ ሲዛባ በሚዲያ ሲነገር ስትሰደብ ማንም አፉን ሲከፍት ዝም እያላችሁ አንድ ፓትርያርክ ተናገሩ ብላችሁ ዘራፍ፡፡ እኛኮ ቤተክርስቲን ከተደፈረች ቆየች ይህ ደግሞ የሳቸው አስተዋጽኦ ነው፡፡ ለሰዳቢ የሰጡ እሳቸው መከሰሰስ ያለባቸው እሳቸው፡፡ ለሙሰኛ ለዘረኛ ለሌባ ለጉበኛ ለመናፍቅ አሳልፈው የሰጡ እሳቸው መከሰስ ያለባቸው እሳቸው፡፡ እንደውም ምዕመኑ እንዳይነሳባችሁ፡፡ ፊርማ አሰባስቦ ለፍርድ እንዳያቀርባችሁ፡፡ አይቀርም ጠብቁ፡፡

  21. Anonymous May 12, 2016 at 1:04 pm Reply

    ሰም አልባ ፓትርያርኩ ናቸዉ

  22. Yenegeta Bayeh May 13, 2016 at 7:16 am Reply

    በእውነት ትክክለኛ አባት ቢሆኑማ ኑሮ ተሰደብሁ ብለው ክስ አይሄዱም ነበር እንኮን እሳቸው ክርስቶስም ሲሰደብ ዝም ብሎል አሁንም ቢሆን ዲ.ን ዳንኤል ክብረት እውነቱን ነው!!!!

  23. Anonymous May 13, 2016 at 9:01 am Reply

    ሌባን ሌባ ማለት እኛ ባንልም እድሜ ለቴክኖሎጂ ሥራችሁ ዐይኑን አፈጥጦ ደረቱን ገልብጦ ታይቷል ይልቁን ንስሃ ግቡበት ሰው ማለት የዛሬን ስህተት ለነገ ከፍተኛ ትምርት የሚያገኝበት ነው ፡፡ ክርስቶስም ዳግም አትበድል አለ እንጅ ስላጠፋህ በእኔ ፋንታ ተሰቀል ፤ተወገር አላለለም ይቀርታ ከምንም በላይ ነው በአደባባይ መካሰስ አይገባም ማንም ከማን የተሸለ ስላልሆነ ፡፡ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 8 ላይ ከእናንተ መካከል ኃጢአት የሌለበት የመጀመሪያውን ድነጋይ አንስቶ ይውገር ነው የተባለው፡፡ እገዚአብሔር ልቦና ይስጠን

Leave a reply to Anonymous Cancel reply