ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ነገ ምሽት ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ

 • ጉብኝቱ÷ በእግዳት ውስጥ ላለው የዴር ሡልጣን ገዳማችን ዓለም አቀፍ ትኩረት እና ድጋፍ ለማሰባሰብ፤ ጉዳዩንም ወደፊት ለመግፋት ያግዛል፤ ተብሏል
 • ይዞታ ካላቸው ጥንታውያን ኦርቶዶክሳውያን አብያተ ክርስቲያናት እና ሌሎች አብያተ እምነት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል
 • የቀድሞውን ፓትርያርክ ሲወቅሱ የቆዩት የሀገረ ስብከቱ – ሊቀ ጳጳስ – ነበር የአኹኑ ፓትርያርክ፣ በአሳዛኝ ኹናቴ ላይ ላለ ይዞታችን መጠበቅ የሚጠቀስ ርምጃ እንዳላሳዩ ይወቀሳሉ
 • የግብጽ እና የኢትዮጵያ አኃት አብያተ ክርስቲያናት ሲኖዶሳዊ ውይይት ችግሩን እንደሚፈታው የገለጹት ፓትርያርኩ፤ ጉዳዩ በእስራኤል መንግሥት ስለተያዘ ተስፋ አለኝ፤ ይላሉ

*          *          *

Abune Matthiasፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ከነገ ሚያዝያ 26 ቀን ጀምሮ በእስራኤል የአንድ ሳምንት ሐዋርያዊ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡

ጉብኝታቸው፣ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት የታሪክና የቅድስና መካናት ጉዳይና ከዚኹ በተገናኘ ይዞታ ካላቸው አኃት አብያተ ክርስቲያናትና ሌሎች አብያተ እምነቶች ጋር ባለው ግንኙነትና የይዞታ አጠቃቀም ችግሮች ላይ እንደሚያተኩር ተገልጧል፡፡

ከጥንታውያኑ የአርመን እና የሶርያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በተጨማሪ፤ የግሪክ እና የሩስያ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካቶሊክ እና ሩማንያ የመሳሰሉት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ይዞታዎች እንዳሏቸው ይታወቃል፡፡

የፓትርያርኩ የውጭ ሀገር ሐዋርያዊ ጉዞ፥ የቤተ ክርስቲያንን ዓለም ዓቀፋዊነት የሚያረጋግጥና በውጭ ያሉትን አህጉረ ስብከት እንደሚያጠናክር በጋራ መግለጫው ያስታወቀው 34ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤከኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጎለብት በተለይም ከግብጽ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር ለቆየው ግንኙነት ተገቢና ልዩ ትኩረት የሚሰጥ እንዲኾን በታላቅ አጽንዖት ጠይቋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስም በጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤው መግለጫውን በማጽደቅ በትጋት እንዲሠራበት መመሪያ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡

ሦስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም. በመጀመሪያ ከሾሟቸው 13 ኤጲስ ቆጶሳት አንዱ አቡነ ማትያስ በወቅቱ የተመደቡት በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ነበር፡፡ “ከሦስት ዓመት የኢየሩሳሌም ቆይታ በኋላ በነበረው ወቅታዊ ችግር ምክንያት በ1974 ዓ.ም. በስደት መልክ ወደ አሜሪካ ተሻግረዋል፤” ይላል ለፕትርክና በዓለ ሢመታቸው የወጣው አጭር የሕይወት ታሪካቸው፡፡

ለ10 ዓመታት በስደት፣ ከ1984 ዓ.ም. ጀምሮ ደግሞ ለ15 ዓመታት የሰሜን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ ኾነው ከቆዩ በኋላ ወደ መጀመሪያው መንበረ ጵጵስናቸው ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የተመለሱት በ1999 ዓ.ም. ነበር፡፡

በፓትርያርክነት ከተሾሙበት የካቲት 2005 ዓ.ም. ወዲኽ የመጀመሪያ በኾነው የነገው የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ጉብኝታቸው፤ የዳግም ትንሣኤን በዓል አብረዋቸው ከሚጓዙት ብፁዓን አባቶች ጋር ያከብራሉ፡፡ እስከ ግንቦት 3 ቀን በሚዘልቀው ቆይታቸውም፣ በተለይም በዴር ሡልጣን ገዳም ጉዳይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እንደሚነጋገሩ ተጠቁሟል፡፡ ውይይቶቹ÷ የውጭ ግንኙነታችንን ከማጠናከር ባሻገርበእግዳት ውስጥ ለቆየው የዴር ሡልጣን ገዳማችን ዓለም አቀፍ ትኩረት እና ድጋፍ ለማሰባሰብ፤ በተወሰነ መልኩም ጉዳዩን ወደፊት ለመግፋት ያግዛሉ፤ ተብሏል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፥ በኢየሩሳሌም ሊቀ ጳጳስነታቸው ወቅት፣ ለዴር ሡልጣን መደረግ ለሚገባው የተደራጀ ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ እና ግፊት፣ ከመንበረ ፕትርክናው በቂ ድጋፍ እንዳልተደረገላቸው በመጥቀስ የቀድሞውን ፓትርያርክ ጭምር በየጊዜው በመውቀስ ይታወቃሉ፡፡

ይኹንና ቅዱስነታቸው፣ በሊቀ ጵጵስናቸው ወቅት ያደረጓቸው ጥረቶች በፓትርያርክነታቸው ችግሩን ለመፍታት የበለጠ እንደሚያግዛቸው ተስፋ ቢጣልበትም፤ ሦስተኛ ዓመቱን ባስቆጠረው ዘመነ ፕትርክናቸው፣ ከዕድሳት ማጣት በአሳዛኝ ኹናቴ ላይ ለሚገኘው የታሪክ እና የቅድስና ይዞታችን መጠበቅ የሚጠቀስ ርምጃ አለማሳየታቸውን በማንሣት የሚወቅሷቸው ጥቂቶች አይደሉም፡፡

Amb. Belaynesh and Deputy Amb. Leo here with Abune Mathias

ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በላይነሽ እና ምክትላቸው አምባሳደር ሊዮ ጋር

መፍትሔው፥ በግብጽ እና በኢትዮጵያ አኃት አብያተ ክርስቲያናት መካከል የሚካሔድ ሲኖዶሳዊ ውይይት እንደኾነ የሚናገሩት ፓትርያርኩ በበኩላቸው፤ “ጉዳዩ በእስራኤል መንግሥት የተያዘ ስለኾነ በመጨረሻ ውጤታማ እንኾናለን የሚል ተስፋ አለኝ፤” ሲሉ በሢመተ ፕትርክናቸው ማግሥት ለታተመው ዜና ቤተ ክርስቲያን መጽሔት በሰጡት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል፡፡

በቃለ ምልልሱ፣ “እኔ ወደ ኢየሩሳሌም[በኤጲስ ቆጶስነት] በሔድኩበት ወቅት ገዳሞቻችን ምንም ነገር አልነበራቸውም፤” ያሉት ፓትርያርኩ፤ ነገሥታቱ፣ መኳንንቱ፣ ወይዛዝርቱና ባላባቶቹ ለገዳሞቻችን የሰጧቸው ሕንፃዎችና ቤቶች በሙሉ “በቁልፍ ተይዘው” ይዞታቸውን በማጣት አደጋ ላይ እንደነበሩ አውስተዋል፡፡ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረትን ጨምሮ የበጎ አድራጊ አካላትን ድጋፍ በመጠየቅ  በርካታ ሕንፃዎችንና ቤቶችን በብዙ ሺሕ ዶላር ከዐረቦችና ከአክራሪ አይሁዶች እጅ በግዥ እንዳስመለሱና ጉዳያቸው ዛሬም በፍርድ ቤት የተያዘ እንዳሉም አስረድተዋል፡፡

Der sultan
አኹን በእጃችን ያለውን ዴር ሡልጣን የተረከብነው የወቅቱ መጋቢ ገብረ ማርያም በኋላ ብፁዕ አቡነ አብሳዲ እ.አ.አ በ1976 ዓ.ም. ቁልፉን ሲረከቡ እንደነበር ፓትርያርኩ በቃለ ምልልሱ አስታውሰው፤ ከማርጀቱ የተነሣ በአደጋ ላይ እንደኾነና ለዕድሳቱ ፈቃድ ሲጠየቅም፣ እስራኤላውያኑ፥ ከግብጾች ጋር ካልተስማማችኹ አይኾንም፤ በማለታቸው እስከ አኹን ምንም ማድረግ እንዳልተቻለ ተናግረዋል፡፡

“አኹን ያለው አማራጭ መፍትሔ የእኛ ሲኖዶስ ከግብጽ ሲኖዶስ ጋር ተወያይቶ ችግሩን ለመፍታት መሞከር ነው፤” ያሉት ፓትርያርኩ፤ “ጉዳዩ በእስራኤል መንግሥት የተያዘ ስለኾነ በመጨረሻ ውጤታማ እንኾናለን፤” ሲሉም ተስፋቸውን ገልጸው ነበር፡፡   

ግብጻውያን ኮፕቶች በግፍ በነጠቁት የዴር ሡልጣን ገዳም ይዞታችን ላይ በየጊዜው የሚያካሒዱትን ትንኮሳ ያላቆሙ ሲኾን፤ በዘንድሮውም የስቅለት በዓል ሁከት ለማሥነሳት ሞክረው እንደነበር ጉዳያችን ጡመራ (www.gudayachn.com) ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ሰበር ዜናው ዘግቧል፡፡

እንደዘገባው፥ በስፍራው ለትንሣኤ በዓል የመጡና በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ መቃብራችን አባቶቻችን ባቆዩት ቅርስ ላይ ይኾናልብለው ትንኮሳውን ለመከላከልና የመጣውን ለመቀበል በዝግጅት ላይ እንዳሉ በመካከል የእስራኤል ፖሊስ ገብቶ ጉዳዩን ለማብረድ ችሏል።

ግብፆች የዚኽ መሰሉን ግርግር በዴር ሱልጣን የኢትዮጵያ ይዞታ ላይ ሲፈጽሙ ይህ የመጀመርያው አይደለም። የዴር ሡልጣን ጉዳይ በኹሉም ወገኖች ትኩረት የሚሻና በተለይ በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ኹሉም ምእመናን በተደራጀ መልክ ሊንቀሳቀሱበት የሚገባ ነው፡፡ 

ሀገራችንና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያናችን፣ ንግሥት ሳባ ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በ1013 ዓመት ገደማ ወደ ኢየሩሳሌም ስትሔድ ሠራዊቷንና ጓዟን ካሳረፈችበት (1ኛነገ.10፤ 2ዜና. 9÷1-9) የአርባዕቱ እንስሳ እና የቅዱስ ሚካኤል ዴር ሡልጣን ጋር ሌሎች ሰባት የታሪክ እና የቅድስና ይዞታዎችም አሏት፡፡

የሀገረ ስብከቱ መንበረ ጵጵስና እና የገዳማቱ ጽ/ቤት የሚገኝበትና ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ ባጠመቀው በቅዱስ ፊልጶስ ስም የተሠራው ቤተ ክርስቲያን፤ ቀድሞ የነቢያት ሰፈር አኹን የኢትዮጵያ ጎዳና የምትገኘው ደብረ ገነት ኪዳነ ምሕረትአልዓዛር የሚባለውና የኢትዮጵያውያን መካነ መቃብር የሚገኝበት ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት፤ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ የተተከለው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን፤ በኢያሪኮ ከተማ የተሠራው የቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፤ ጌታችን ከተወለደበት ቦታ አጠገብ ያለው ቤተ ልሔም ኢየሱስ ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

 

 

Advertisements

7 thoughts on “ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ነገ ምሽት ወደ ኢየሩሳሌም ይጓዛሉ

 1. Astu. May 3, 2016 at 4:28 pm Reply

  Abune Mathias is good for nothing. He does not have courage, strength and ability to solve this problem. During his visit here in America I was hoping as he will try to reach out for divided church to unite. not alone the two synods he couldn’t unit the churches under his jurisdiction.
  For that matter what he did significant during his 15 years stay in America? Nothing

  • Anonymous May 4, 2016 at 12:57 pm Reply

   Bemin quanka tenagrew new gibtsochin yemiyasamnut yilkunim yetemare yetemeramere awoko yemisera abat yimeret Tim kumneger Bihonma Yebiladin Aymrim Ende?

 2. Misgina May 4, 2016 at 2:49 pm Reply

  I do not expect anything good from Patriarch Abune Matias. He is working hand-in-hand with those trying to distroy the Ethiopian Orthodox Church. He is a dead figure in the heart of many Christians. He is just a rubbish…

  • Anonymous May 7, 2016 at 6:53 am Reply

   NOT SIPLLY RUBISH HI IS GURBAG ONE ABA MATIYAS HAS NOT ABILITY TO LEAD ETHIOPIAN CHURCH HE IS FOOLISH HE IS DOING WHAT SOME EVIL one SAYING NEVER THINK HIM SELF HE HAS THE DEASES ALIZIMER NEVER REMEMBER ANYTHING EVEN HIS BREAKFAST HI IS STRUCHER EMPTY MIND FREE FROM A KNOWLE NEVER FEET FO ABA POULOS SEAT DOWN DOWN DOUN YAGERE SEW (JIL SIGAGAL EKA YIFEGAL) SO BEFORE THE DESTRUCTION OF THE CHURCH SHOULD BE ABOLISHED HIMSELF

 3. Selamu May 7, 2016 at 12:09 am Reply

  የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የእሥራኤል ጉብኝት ከፍተኛ ፋይዳ የሚያስገኝ ውጤት ሊያስገኝ ይችላል። በልዩ ልዩ ምክንያቶች ቅሬታ ቢኖርም ለዚህ አጋጣሚ ተገቢ የሚሆነው ግን፤ ለሐገርና ለቤተ ክርስቲያን የሚበጅ ውጤት እንዲገኝ እንዲረዳን ወደ ቸሩ የኢትዮጵያ አምላክ መጸለዩ ነው። ይቅናቸው!
  ጉዞዋቸው ግን ለተራ ሽር ሽር ሳይሆን ሁለት ግልጽ ውጤቶች ይጠበቅባቸዋል። እነዚህም፤ 1ኛ/ ኢየሩሳሌም የሚገኘው ታሪካዊ ገዳማችን (ዴር ሡልጣን) ንብረትነቱ የኢትዮጵያ መሆኑ ተረጋግጦ ለዘመናት የሚያስፈልገው ጥገና እንዲከናወንና የግብጽ (ኮብት) ቤተ ክርስቲያን ተገቢ ያልሆነ ውዝግብ እንዲቋረጥ ማድረግ፤ እና 2ኛ/ ኢትዮጵያዊው ጃንደረባ በጊዜው የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር የነበረ፤ በ34 ዓ/ም፤ ከኢየሩሳሌም ሲመለስ፤ በጋዛ መንገድ ላይ የተጠመቀበት ታሪካዊ ስፍራ ገዳም እና/ወይም ደብር በማቋቋም ሊከበር ስለሚገባው ይህንኑ በእሥራኤል መንግሥት ማስፈቀድ።
  ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች አሳክተው ቢመለሱ፤ ቅዱስ ፓትሪያርኩ ታሪካዊ ግዴታቸውን ተወጡ ማለት ይቻላል። ባዶ እጃቸውን ተመልሰው ምክንያት ከደረደሩ ግን ሌላ አሳፋሪ ሁኔታ ተጨመረ ማለት ነው። ለቁም-ነገር ያብቃቸው!

  • kmch21 April 10, 2017 at 7:12 am Reply

   Egziabher ke Ethiopian gar new

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: