ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ

MK Exhibition Ginbot2008

የአ/አበባ ከተማ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅና

 • የአዲስ አበባ አስተዳደር የከንቲባ ጽ/ቤት፣የሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍል ዕውቅናውን የሰጠው፥ ዛሬ፣ ሚያዝያ 11 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ ከጠዋቱ 3፡00 ላይ እንደኾነ የማሳወቂያ ቅጹ ያመለክታል፡፡
 • “የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ ማሳወቅ” በሚል ዓላማ ባገኘው ዕውቅና ከግንቦት 17 – 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ምሸት 4፡00 ድረስ ለሚካሔደውና ከ100 ሺሕ በላይ ተመልካች እንደሚጎበኘው ለሚጠበቀው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መንግሥት የፖሊስ ጥበቃ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
 • የማኅበሩ አመራር እና የዝግጅቱ ዐቢይ ኮሚቴ፣ ቀደም ሲል ከመጋቢት 15 እስከ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በዚያው በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ታቅዶ የነበረው የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ መርሐ ግብር ባልተለመደ ሕግና አሠራር እክል ከገጠመው ደቂቃ ጀምሮ፥ የአዲስ አበባ አስተዳደርንና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን ጨምሮ ከፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር እና ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ ሓላፊዎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶችን በትዕግሥት ሲያካሒድ ሰንብቷል፡፡
 • ውይይቶቹ በተካሔዱባቸው አጋጣሚዎች ኹሉ፣ መርሐ ግብሩን ለማስተጓጎል በማሰብ የአዲስ አበባ አድባራት አማሳኞች ያወጡትንና በሌላቸው ሥልጣን ለክልል መንግሥታት ሳይቀር ያሰራጩትን መግለጫ መግፍኤ በሚገባ ለማጋለጥ ወዲያውም ደግሞ፤ ማኅበሩን ዓላማና የአገልግሎት ስልቶች በጥልቀት ለማስገንዘብ መልካም አጋጣሚ የተፈጠረ ሲኾን፤ የማኅበሩ አመራርም፤ በመጨረሻ፣ ለ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ የከተማው አስተዳደር ለሰጠው ዕውቅና ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

patriarchate MK Exb approval and Exb logo

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ቀደም ሲል የጻፈው የድጋፍ ደብዳቤ

 • ኦርቶዶክሳዊው ምእመን፥ ትምህርተ ሃይማኖቱን፣ ሥርዐተ እምነቱን፣ ክርስቲያናዊ ትውፊቱንና ታሪኩን ተረድቶ ከሐዋርያዊት፣ ኵላዊትና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር ያለውን መስተጋብር እንዲያጠናክር ብሎም ድርሻውን ተገንዝቦ የበኩሉን እንዲወጣ የማድረግ  ዓላማ ያለውና ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀው ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ፣ የማኅበሩ ስትራተጅያዊ ዕቅድ አካል ሲኾን፤ በመደበኛው አሠራር፣ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት በወቅቱ ተገቢውን ድጋፍና ዕውቅና አግኝቶ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ ለመታየት የሰዓታት ዕድሜ ሲቀረው መታገዱ ይታወሳል፡፡
Advertisements

34 thoughts on “ሰበር ዜና – የማኅበረ ቅዱሳን ዐውደ ርእይ ከግንቦት 17 – 22 ቀን በኤግዚቢሽን ማዕከል እንዲካሔድ ዕውቅና አገኘ

 1. Anonymous April 19, 2016 at 1:09 pm Reply

  ጠላት ይፈር እግዚአብሄር ይክበር ይመስገን የእግዚአብሄር ልጆች ነንና ጠላትነ ድል እናደርጋልን

 2. Merawi YE Aresema Leje April 19, 2016 at 1:42 pm Reply

  YES

 3. Anonymous April 19, 2016 at 2:53 pm Reply

  እውነትን የያዘ ሁልጊዜም አይሸነፍም። ሀሰተኛ የሆነው ሰይጣን ሲያፍር ይኖራል ።

 4. Anonymous April 19, 2016 at 2:57 pm Reply

  Talaku Amlak Fetari Egizihabiher yimesgen lezih mekam zena, amen (3)!!!

 5. Anonymous April 19, 2016 at 3:05 pm Reply

  ተመስገን

 6. Anonymous April 19, 2016 at 3:49 pm Reply

  benageroch hulu Egzabeiare yeatmesagena yewn.

 7. Anonymous April 19, 2016 at 3:50 pm Reply

  ግንቦት 20ን እንዲያካትት ነው እንዴ እስከ አሁን እንዲዘገይ የተደረገው

  • Anonymous April 19, 2016 at 5:51 pm Reply

   መሰሪው መንግስት እንደዛ ያሰበ ይመስላል ::

  • Anonymous April 22, 2016 at 9:48 am Reply

   ginbot 20n man liyakebrilet newu?hulum wede exibition maekel silemihed malete newu…

 8. Aster April 19, 2016 at 4:33 pm Reply

  Egzhabher yemesgen

 9. Ashenafi April 19, 2016 at 4:46 pm Reply

  ኢግዝአብሔር ይመስገን

 10. Anonymous April 19, 2016 at 5:09 pm Reply

  Temesgen ,Temesgen, Temesgen

 11. Anonymous April 19, 2016 at 5:11 pm Reply

  Temesegen! !!!!!!!!!

 12. Anonymous April 19, 2016 at 5:16 pm Reply

  thanks to almighty God, እግዚአብሔርንም የ ያዝ መቼም ቢሆን አይሸነፍም።

 13. senay April 19, 2016 at 5:21 pm Reply

  ለሰላም ና ለቤተ ክርስቲያን እድገትና ክብር ያርግልን።በቤተክርስቲያን እየተሰሙ ያሉዘረኝነት የብሄር ጥላቻ ጠፍቶ በህዝበ ክርስቲያንና በማህበረ ካህናት መከባበርናመፋቀርእንዲኖር መድኀኔዓለም ይርዳን

 14. senay April 19, 2016 at 5:28 pm Reply

  በህልክና በብሄር ጥላቻ የሊቃውንቱ ስም ማጥፋት ይቅር

 15. Anonymous April 19, 2016 at 5:32 pm Reply

  የማሕበረ ቅዱሳን አውደ ርዕይ ሳይሆን መባል ያለበት የቤተ ክርስቲያኗ አውደ ርዕይ ተብሎ መስተካከል አለበት።

 16. Destaw Fetene April 19, 2016 at 7:15 pm Reply

  Des yilal

  • Anonymous April 20, 2016 at 3:42 am Reply

   እግዚአብሄር የሚሳነው ነገር የለም

  • Anonymous April 20, 2016 at 5:51 am Reply

   Amasagnu Haile Abrhana Nuredin yemimerut Yetifa Bdun Minyiwatew Ato Goitom /Goitre Keftegna yebetsira SIRA yitbkachewal Egzibisionu Endaykahed masdereg kalhone Yejemerut gin Yalatatamut Weber melke kkkkk

 17. abe April 19, 2016 at 9:59 pm Reply

  I hope Dn. Daniel Kibret apologizes for his visious attack of his holiness Aba Matias.
  His accusation /premature as usual/ contradicts the fact on the support letter.

 18. Anonymous April 20, 2016 at 5:32 am Reply

  ይህን ያደረገ እግዚአብሔር ይመስገን

 19. yeneneh April 20, 2016 at 5:32 am Reply

  how on earth we believe it again? when one reason fails the other will emerge. i do not believe until the exhibition is open and the program is safely conducted. may be , again, at the 11th hour to start the program, the patriarch will be directly/officially involved to ban it. until that period, different strategies could be devised for the ban. mind you! they ( the betekhinet and some elements of the government (particularly whose religions are protestant) do not sleep. they do have another conspiracy. so, i advise mk, as dn. daniel said, be wise and prophet for the possible challenges.

 20. Anonymous April 20, 2016 at 6:24 am Reply

  leteseteguagolebet kasa yekefel!!!!!!!!!!!!!!!

  • Anonymous April 20, 2016 at 2:46 pm Reply

   Ende American Ambasi Yaleshofer Beyedebru Bemehed 20 ena 30 shih yekote Gibr Sebsabiw Nibure ied Zarem ende Tilantu Alekochin Azawralhu Ekeyralhu eyale Bpatryarku Biro kebir Eskedolar eyagbesebese new lezihm Yeredaw andu Guday Bemahberu Thifo yaserachew Debdabe Sihon Betechemarim Eneigelen negre Egzihibtionu Enenegn yazegahut Bilo patryarkun Bematalelu new Ahun min yiwatew Degmo Minblo Yatalilachew Yihon

 21. seifeselassie April 20, 2016 at 9:11 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን፡፡ ምንም እንኳን ለጊዜው ቢታገድም በወቅቱ እግዚአብሔር በፈቀደ ጊዜ እናሳየዋለን ብዬ አምን ነበር፡፡ አሁንም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እውቅናውን ከሰጡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ታክሎበት ዐውደ ርዕይው በታላቅ ድምቀት ለሕዝብ ይታያል፡፡ ወቅቱም እግዚአብሔር በ21ኛ ክፍለ ዘመን የደም ሰማዕታት ለቤተ ክርስቲያን የሰጠበት ጊዜ 1ኛ ዓመት የሊቢያ ሰማዕታት የምናዘክርበት ስለሆነ መታሰቢያነቱም ለእነርሱ ይሆናል፡፡ ወጣት ሰማእታት በላፈው ዓመት በሰማዕትነት አክሊላቸው ቤተ ክርስቲያንን እንዳስጌጧት እና ኦርቶዶክሳዊነትን በደማቸው በዓለም አደባባይ እንደሰበኩ በዚህ ዘምን ያለን ወጣቶች ለዐውደ ርዕያችን የደም ላባችን በመስጠት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ኩላዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ቅድስት እና አንዲት መሆኗን በአለም አደባባይ እንመሰክራለን፡፡ ዐውደ ርዕይው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ አውደ ርዕይ ነው፡፡ በአራቱም ትይንት የተያዙት ቁም ነገሮች ለኦርቶዶክሳዊያኑ ሁሉ ይተላለፋል፡፡ በዐውደ ርዕዩም ሕዝበ ክርስቲያኑ ትክክለኛ የድዕነት መሥመር በያዘችሁ በኦርቶዶክ ተዋህዶ ጥላ ሥር በመሆኑ ታላቅ ክብርና ኩራት ይሰማዋል፡፡
  በዚህ አጋጣሚ የአውደ ርዕዩ ዐብይ ኮሚቴ የዘገየበት ነገር ካለ አሊያም ሊያሻሽለው የፈለገው ነገር ካለ ከወዲሁ ልዩ ትኩረት በመስጠትና ተፈላጊውን ዝግጀት በዚህ በአንድ ወር ውስጥ በማጠናቀቅ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡ ለዚህም ታላቅ የመንፈስ መነቃቃት በመፍጠር ቀደም ሲል ዐውደ ርዕይውን ለማሳየት የነበረውን መነሳሳት እጥፍ አድርጎ በከፍተኛ መንፈሳዊ ቁጭት ከተነሳሳን እና በአገልግሎቱ እግዚአብሔር ይከብርበታል ቤተ ክርስቲያን ትታወቅበታለች ብለን ስለምናገለግል ስኬታማ አውደ ርዕይ እንደምናሳይ አልጠራጠርም፡፡ እንግዲ ሕዝበ ክርስቲያን ዐውደ ርዕዩ በመታገዱ ያሳያችሁትን ቁጭት ከግንቦት17-ግንቦት22/2008ዓ/ም በሚካሄደው ዐውደ ርዕይ ከማኀበሩ ጎን በመሆን የበኩላችሁን አስተዋጾ እንደምታደርጉ ተስፋ አደርጋለው፡፡
  ረድኤተ እግዚአብሔ አይለየን፡፡

 22. Wudnesh Dessalew April 20, 2016 at 11:13 am Reply

  ኢግዝአብሔር ይመስገን

 23. Anonymous April 20, 2016 at 3:20 pm Reply

  ወሬኛ ሁላ አሁን የበሰበሰና ያረጀ ኰተት አሳያችሁና ምን ለውጥ ልታመጡ ክርስቲያንን ሊያሳርፈው የሚችለው የናንተ አውደ ርዕይ ሳይሆን እውነተኛው የጌታ ቃል ነው

  • ዳሞት April 21, 2016 at 4:12 am Reply

   ለአንተ ለእውሩ የበሰበሰና የአረጀ ነው። ለእኛ ለቤተክርስቲያኗ ልጆችና ለእውነት የቆሙት ግን የማያረጅ፣ መንፈስን ገዝቶ ልብን ደስ የሚያሰኝ፣ የቤተክርስቲያንን እምነት ሥርዓቷን፤ የወንጌል አስተምሮዋን የሚያስረዳ ነው። እግዚአብሔርም ያለና የነበረ ዘላለማዊ ነውና ለአንተ ለጨለምተኛ፣ ለከሃዲው የበሰበሰ ያረጀ ነው ማለት ነው? አንተ ክፉ ከሳሽ እግዚአብሔር ይገስፅህ።

 24. Mulea April 20, 2016 at 4:04 pm Reply

  Thanks to God

 25. Anonymous April 21, 2016 at 8:00 am Reply

  ቦ ጊዜ ለኩሉ እንዳለ ጠቢቡ ሶሎሞን ምናልባትም

 26. Dejene Alemu April 24, 2016 at 8:14 pm Reply

  Zeru kelete !!!

 27. wuditu haile April 26, 2016 at 6:50 am Reply

  temesgen ewnet bitqeberim tibeqilalech
  zare yebete kirtian telatoch yebezu betselot tigu ahunim

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: