መናፍቁ ከፍ ያለው ቱፋ: በአሰበ ተፈሪ ያልተፈቀደ ኅቡእ ጉባኤ በማካሔድ በቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ወደ ኮሌጁ የመመለስ ጥያቄው በፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ ውድቅ ተደርጓል

Kefyalew Tufa's complete dismissal

 • ከፍ ያለው፥ ከ22 ኅቡእ ተሰብሳቢዎች ጋር በፖሊስ የተያዘው በመኖርያ ቤት ውስጥ ነው
 • 5ቱ ግለሰቦች በፖሊስ ጣቢያው ተይዘው ሲገኙ፤ 17ቱ ጉዳያቸውን በውጭ ይከታተላሉ
 • ከፍ ያለውን ጨምሮ በመኖርያ ቤቱ ባለቤትና በ5ቱ ግለሰቦች ላይ ምርመራው ቀጥሏል
 • ፕሮቴስታንቱ የተስፋ ክሊኒክ ባለቤት ለከፍ ያለው ቱፋ ጠበቃ ለማቆም ይሯሯጣል
 • የከፍ ያለው ቱፋን የሖቴል መስተንግዶ የሸፈነው ይኸው ፕሮቴስታንታዊ ግለሰብ ነው

*               *               *

 • ከጅምሩ ሲከታተለው የቆየው የምዕ/ሐረርጌ ሀ/ስብከት፣ ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እየሠራ ነው
 • የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ፣ በሀገረ ስብከቱ ጥያቄ አስፈላጊ ማስረጃዎችን ልኳል
 • በቤት ለቤት ጉባኤያት ኑፋቄን በኅቡእ መዝራት፤ ከኮሌጁ የተባረረበት አንዱ ምክንያት ነው
 • የኮሌጁን ውሳኔ ለማሳገድ ላቀረበው ክሥ፤ የኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ችሎት ነገ ውሳኔ ይሰጣል
 • እየተማረ ጉዳዩን ለመከታተል በቃል ያቀረበውን ጥያቄ ችሎቱ ለ2ኛ ጊዜ ውድቅ አድርጎታል

Kefyalew Tufa's verdict

የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ኮሌጅ፥ የከፍ ያለውን ቱፋን መናፍቅነት በሚያረጋግጡ ተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ ተመሥርቶ የበላይ ሓላፊውን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ጨምሮ የአስተዳደር ጉባኤ አባላቱ፣ መምህራኑና የተማሪዎች መማክርቱ በያዙት የጋራ አቋም እና ኹሉም ባሳፈሩት ፊርማ ከደቀ መዝሙርነት በሙሉ ድምፅ ያባረረበት የመጋቢት 16 ቀን ውሳኔው፤ መናፍቁ ስለ ኮሌጁ ማንነትና ስለ ውሳኔው መነሻ በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ሳቢያ በፌዴራሉ መጀመሪያ ደረጀ ፍ/ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፩ኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት መጋቢት 23 ቀን ታግዶ ነበር፡፡ ይኹንና ኮሌጁ በእግዱ ላይ ባቀረበው የጽሑፍ አቤቱታና በደቀ መዛሙርቱ አንድነት ችሎቱ እገዳውን መጋቢት 29 ቀን አንሥቷል፤ የኮሌጁም ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ ይገኛል፡፡ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኝ ብሎጎች የመጋቢት 23ቱን ውሳኔ ብቻ በመጥቀስ፣ የኮሌጁ ውሳኔ ታግዶ ከፍ ያለው ቱፋ ትምህርቱን ቀጥሎ እንደሚገኝ ማስተጋባታቸውም እንደተለመደው የሌባ ዐይነ ደረቅና የሐሰት ቋት መኾናቸውን በገሃድ ያረጋገጡበት ሌላ ምስክር ኾኖባቸዋል፡፡


 • ከፍ ያለው ቱፋ፣ ስለተባረረበት ጉዳይ ለችሎቱ ባቀረበው የተሳሳተ መረጃ ወደ ኮሌጁ ተመልሶ እየተማረ ጉዳዩን እንዲከታተል ፍ/ቤቱ መጋቢት 23 ቀን በኮሌጁ ውሳኔ ላይ ያሳለፈውን እገዳመጋቢት 29 ቀን ባዋለው ችሎት፣ ስለ ውሳኔው በቀረበለት ትክክለኛ መረጃና ማብራሪያ፤ ደቀ መዛሙርቱም፥ “ከመናፍቅ ጋር አንማርም” ብለው በአንድነት ባሳዩት የተባበረ ቆራጥ አቋም እገዳውን አንሥቷልኮሌጁም፥ መናፍቁን በማባረር ያሳለፈው ውሳኔ ተፈጻሚ ኾኖ ይገኛል
 • ከፍ ያለው ቱፋ፣ በአሰበ ተፈሪ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ቡድኖች ያሰባሰቡለትን 22 ግለሰቦች በኅቡእ ለማሠልጠን በተዘጋጀበትና የተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኙ ማኅበረ ናታኒ አባል በኾነች አንዲት ሴት መኖርያ ቤት ውስጥ እጅ ከፍንጅ በተያዘበት ወቅት“የተፈቀደለት ሰባኪ/አገልጋይ” መኾኑን ለማስረዳት ከሞከረባቸው መንገዶች አንዱ፣ ችሎቱ በመጋቢት 29 ውሳኔው የሻረውን የመጋቢት 23 ቀን እገዳ ግልባጭ በማሳየትና የሴትዮዋ “ቤተሰብ ነኝ”  በማለት ጭምር እንደኾነ ታውቋል፤

 • በምሥራቅ ኢትዮጵያ፣ ባለፉት ጥቂት ወራት ከድሬዳዋ ሀገረ ስብከት ተነሣስቶ በምሥራቅ ሐረርጌ፣ በጅግጅጋ፣ በአሰበ ተፈሪና አካባቢው በአዲስ መልኩ በተፋፋመው የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተጋድሎአህጉረ ስብከት፣ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት፣ የሰንበት ት/ቤቶች እና ማኅበረ ምእመናን በተጠናከረ የአገልግሎት ስልትና ቅንጅት በመናበብ ዐውደ ትምህርታዊ ጉባኤያትን፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎችንና ውይይቶችን በስፋት እያካሔዱ ይገኛሉ
 • በአሰበ ተፈሪ፣ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኝነቱ በሚታወቀው ማኅበረ ናታኒ የታቀደው የከፍ ያለው ቱፋ ኅቡእ ስምሪት፤ ይህንኑ የተጋድሎ ግለት ለማዳከም ከመወጠን ባሻገር፣ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጋር በመቀናጀት ለከተማው ምእመናን ያዘጋጀውን ዐውደ ትምህርታዊ ጉባኤ የማወክ ተልእኮም እንደነበረው ተጠቅሷል፡፡

ማስታወሻ፡- በቀደመው ዘገባ አንዳንድ ነጥቦች ላይ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

 

Advertisements

8 thoughts on “መናፍቁ ከፍ ያለው ቱፋ: በአሰበ ተፈሪ ያልተፈቀደ ኅቡእ ጉባኤ በማካሔድ በቁጥጥር ሥር ዋለ፤ ወደ ኮሌጁ የመመለስ ጥያቄው በፍ/ቤቱ ለ2ኛ ጊዜ ውድቅ ተደርጓል

 1. Anonymous April 18, 2016 at 6:39 pm Reply

  ፍካሬ ዘፃድቃ ወዘሀጣን…ብፁ ብእሲ ዘኢሆረ በምክረ ረሲአን… ።ነዉና ቅሉ።

 2. Anonymous April 18, 2016 at 7:14 pm Reply

  ከፍያለው ቱፋ…በከተማችን በድብቅ ከሚማርበት ኮሌጅ በሚያራምደው ድብቅ አጀንዳ ከተባረረ በኋላ…መጀመሪያም እንዴት እንደገባ ይገርማል…መስፈርቱ ችግር እንዳለበት ያሳያልና…ውስጣቸው ቢፈተሽ ማለትም ኮሌጅ ተብዬዎቹ ብዙ ጉድ ይወጣል..እርሱን ወደፊት እናያለን…ምንም ክፋ ቢሰራባት የማትደብቀው ደብረጽዮን መጥቶ በንጽህና ነው የተባረርኩት ምንም ጥፋት የለብኝም የሚለው ድብቅ አጀንዳው ተጋለጠ..ንጹህ ከሆነ ጓዳ ውስጥ ምን አስደበቀው..ከቤተክርስቲያኒቱ ታቦት አያስፈልግም..ማርያም ምን ታደርጋለች…የቤተክርስቲያን ስርአት የወንጌል እንቅፋት ነው…እና መሰል አቋማቸውን ቀይሩ ተብለው ሲመከሩ እንቢ ብለው ከቤተክርስያይኒቱ አገልግሎት ከታገዱ ወጣቶችና…ምንም የማያውቁ ህጻናትን ሰብስቦ ማስተማርን ምን አመጣው…ስለዚህ በግልም ይሁን በማህበር የፈለገውን እምነት መከተል ይችላል…ነገር ግን ቤተክርስቲያኒቱን ተገን አድርጎ መሆን የለበትም…በተጨማሪም እዝራ የሚባለው ዘማሪ ለጾም መግቢያ አሰበ ተፈሪ በመጣበት ሰአት አነዚህን ከቤተክርስቲያን የታገዱ ልጆች ሰብስቦ ለምን ወደውጭ ወጣችሁ የይቅርታ ደብዳቤ አስገብታችሁ ተመለሱና ስራችሁን እዛው በድብቅ ስሩ አብረን እንሰራለን የሚል ምክር ሲመክር በድምጽ በተቀረጸ መረጃ እንዳለ ከሀገረ ስብከቱ የተረጋገጠ መሆኑን በአካል ሰምተናል…በጋሻውም ከልጆቹ ጋር ተገናኝቶ መሰል መልእክት አስተላልፎአል በመባሉና በወቅቱ በአሰበ ተፈሪና በሂርና ባገለገለ ወቅት ያስተማረው ትምህርት በምእመኑ መካከል ውዝግብ በመፍጠሩ በዶባ ያለውን አገልግሎት እንዳያካሂድ በሀገረ ስብከቱ ማገጃ ተጥሎበታል….ስለዚህ ምእመናን ልባችሁ ወደቤተክርስቲያኒቱ ወደቆመችበት እውነት እንዲያዩ ብቻ ሆኖ…በአሁን ሰአት የተዋህዶ የእውነት ብርሀን እየገፋ ስለመጣ…ምንም አይነት ጨለማ..በቤተክርስቲያንም በሀገሪቱም መቀመጥ አይችልም…የእሳት እራት…ብርሀን ፍለጋ ወደብርሀን መጥታ እንደምትጠፋ….በውጭም በውስጥም የተደበቁ ክፋቶች…የዲያብሎስ ተንኮሎች ለፍርድ ወደብርሀን እየመጡ ነው….ዘመኑ የፍርድ ነው…ክርስቲያን መባል ሳይሆን..ክርስቲያን መሆን…የክርስቶስን ኑሮ መኖር ነው ድህነት የሚያሰጠው…እንግዲህ እንንቃ…ይህች ሀገር የማርያም አስራት ናት…ከጽዮን ጋር የምትጣሉ በተለይ የሀሰት ክርስትናን እያራመዳችሁ በቤተክርስቲያን የተደበቃችሁ…ወዮ…

 3. Anonymous April 20, 2016 at 12:50 pm Reply

  Egzeabher lebetu melkam agelgay yazegajilin Arerinisa ahuns angeshegeshen

 4. sol April 24, 2016 at 12:36 pm Reply

  በሚገርም ሁኔታ አዲስ አበባ ስመጣ ከማንም ቤተክርስትያን እነዚህ መናፍቃን አያጋጥሙኝም እነ አዝማሪ ትዝታው ዘርፌ ……እነ pastor በጋሻውም አላገኛቸውም
  አየ ባገኛቸው ዉሀ በጠማው ድጋይ ነበር የማቦገነው ከእርስቴ ላይ አረም ሲዘራ ዝም ብየ ላይ ሞት ይሻላል
  በነገራችን ላይ መገድ ላይም ይሁን ቤተክርስትያን የእነሡን ድምፅ ስስማ ሒጀ አዘጋላው ቤተክርስትያን ላይ በዙ አይከፈትም ደግሞም ማንም ሳይጨቃጨቀኝ ይዘጋል መገድ ላይ በሞባይል ከፍቶ ምንፍቅናቸውን ስስማ ለምን ማተብህን በጥሰህ አዳራሽ አትገባም ሒድና አብረህ ዝፈን ስለው ሁሉም ይዘጋል።

  • Ehte Maryam May 11, 2017 at 10:08 am Reply

   Ykrta yene eht egziabher fikr enji dula wynm tlacha alastemarenm betkrstyanm abatochachinm yheninu new yastemarun enas betechalen smetawi banhun melkam new man yawkal and ken beykrta limelshache ychilal yemisanew yelemna emebrhan hulachinm behaymanotachin xenten endnkoy mljawa ayleyn ketesasatkug ykrta

 5. Anonymous April 24, 2016 at 12:36 pm Reply

  በሚገርም ሁኔታ አዲስ አበባ ስመጣ ከማንም ቤተክርስትያን እነዚህ መናፍቃን አያጋጥሙኝም እነ አዝማሪ ትዝታው ዘርፌ ……እነ pastor በጋሻውም አላገኛቸውም
  አየ ባገኛቸው ዉሀ በጠማው ድጋይ ነበር የማቦገነው ከእርስቴ ላይ አረም ሲዘራ ዝም ብየ ላይ ሞት ይሻላል
  በነገራችን ላይ መገድ ላይም ይሁን ቤተክርስትያን የእነሡን ድምፅ ስስማ ሒጀ አዘጋላው ቤተክርስትያን ላይ በዙ አይከፈትም ደግሞም ማንም ሳይጨቃጨቀኝ ይዘጋል መገድ ላይ በሞባይል ከፍቶ ምንፍቅናቸውን ስስማ ለምን ማተብህን በጥሰህ አዳራሽ አትገባም ሒድና አብረህ ዝፈን ስለው ሁሉም ይዘጋል።

 6. Anonymous April 24, 2016 at 12:38 pm Reply

  woye menafke medere kehadiwoch.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: