በቦሌ መድኃኔዓለም: ምዝበራ እና ለአገልግሎቱ የተሰጠው ትኩረት ካህናትን እያማረረ ምእመናንን እያሸሸ ነው፤ ለሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተዋጣው 400ሺሕ ብር የገባበት አልታወቀም

በካቴድራሉ አስተዳደር፡-
 • ደመወዝ ጭማሪ ለማጸደቅ 104ሺሕ ብር ለየማነ ዘመንፈስ ቅዱስና ለኤልያስ ተጫነ ተሰጥቷል
 • ኹለት ሕንፃዎች÷ ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅናና ያለጨረታ ከአካባቢው ዋጋ በታች ተከራይተዋል
 • የስፍራው ዋጋ በካሬ ከ400 – 500 ብር ቢኾንም ሕንፃዎቹ ከ54 – 120 ብር ነው የተከራዩት
 • የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ሰነዶች መኖራቸው አጠራጥሯል፤ ባንክ ለመግባቱም ማረጋገጫ የለም
በካቴድራሉ አገልግሎት፡-
 • የቀድሞውን መጋዘን ማረፊያ አድርገው የሚኖሩት ካህናት ለተለያዩ የጤና እክሎች ተዳርገዋል
 • ለቅዳሴው፣ ለማሕሌቱና ለስብከተ ወንጌሉ ትኩረት በማነሱ አገልግሎት ለመፈጸም ተቸግረዋል
 • አካባቢውን ያገናዘበ ልማት ቢታቀድም፣ ካቴድራሉ ጥራቱን የጠበቀ መጸዳጃ ቤት እንኳ የለውም
 • የካቴድራሉን ደረጃ የጠበቀ፣ ሳቢና ማራኪ አገልግሎት ባለመኖሩ ምእመናን ከአጥቢያው ይሸሻሉ
ዐሥር ዓመት ያስቆጠረው የካቴድራሉ ሰበካ ጉባኤ፡-
 • ከፍተኛ ሞያ እና ልምድ ያላቸው ምእመናን ቢገኙበትም አስተዳደሩ ሊያሠራቸው አልቻለም
 • በዕቅዱና በበጀቱ ለመሥራት አለመቻሉን በመጥቀስ፣ ጽ/ቤቱን “አሰናብቱን” እስከማለት ደርሷል
 • በርካታ አቤቱታዎችንና ማስረጃዎችን ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ቢያቀርብም መፍትሔ አልተገኘም
 • ከካቴድራሉ አቅምና ጥያቄ ውጭ፥ የሀ/ስብከቱን የዘፈቀደ የሰው ኃይል ምደባ ለመቀበል ተገዷል 
የካቴድራሉ አስተዳዳሪ፡-
 • ካህናቱንና ምእመናኑን በዐደባባይ መዝለፍ ያዘወትራሉ፤ አባትነትና መንፈሳዊነት ይጎድላቸዋል
 • አገልጋይ ካህናቱን በተወላጅነት መከፋፈል እና በጥቅም ማባበል የችግር መፍቻ ስልታቸው ነው
 • ለኤጲስ ቆጶስነት ደጅ ይጠናሉ፤ “እኔ እሻላችኋለኹ” እያሉ ከካህናቱ የንስሐ ልጆችን ይነጥቃሉ
 • “ለስድስት ዓመት ተሸክሞኖታል!” ያሉ ካህናት ስማቸውን በጸሎተ ቅዳሴ መጥራት አቁመዋል
 • የቦንዱን ጉዳይ ጨምሮ ጥያቄ ያነሡባቸው ካህናት፥ እንዲዛወሩ ሀገረ ስብከቱን እየተማፀኑ ነው
የካቴድራሉ ጸሐፊ እና ሒሳብ ሹም፡-
 • ለካቴድራሉ ደረጃና አገልግሎት የሚመጥን የሥራ ልምድና ብቃት የላቸውም
 • የሚቃወሟቸውን ካህናት በማዘዋወር በቅርብ ዘመዶቻቸው እንዲተኩ ያደርጋሉ
 • ለየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ባለው ቅርበት ከብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ተዛውሮ የተመደበው ሒሳብ ሹሙ፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎች በመላላክ ይታወቃል
 • ካቴድራሉ ከአካባቢውና ከደረጃው አንጻር፥ መንፈሳዊነትንና ቅድስናን የተመላ አባት፤ ችሎታው፣ ልምዱና ቅንነቱ ባላቸው የአስተዳደር ሓላፊዎችና ሠራተኞች እንዲዋቀር እየተጠየቀ ነው፡፡

*               *               *

Bole Medhanialem church bld

ቦሌ መድኃኔዓለም እና አካባቢው ቀደም ሲል “የንግሥት ሰፈር” እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ የንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ምኒልክ ርስት የነበረ ሲኾን ከየረር ተራራ ወደ አዲስ ዓለም ማርያም የሚመላለሱ ባሕታውያን ያርፉበት እንደነበር ይነገራል፡፡ በአኹኑ ወቅት ደግሞ ከአዲስ አበባ “ምርጥ” አካባቢዎች ተጠቃሹ ነው፡፡

በ1970ዎቹ መጀመሪያ ላይ የከፍተኛ 17 ቀበሌ 17 ጥቂት ነዋሪዎች ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ለመንግሥትና ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ በወቅቱ የከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር የተፈቀደው 9990 ካሬ ሜትር ቦታ በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የተባረከው፣ መጋቢት 16 ቀን 1971 ዓ.ም. ነበር፡፡ በቀበሌው ክልል ከነበረው ጫካ በተቆረጡ ዛፎች መቃኞውና የዙሪያው አጥር ከተሠራ በኋላ የመድኃኔዓለምና የመጥምቀ መለኰት ቅዱስ ዮሐንስ ጽላት በፓትርያርኩ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ተባርከው ጳጉሜን 6 ቀን 1971 ዓ.ም. ገብተዋል፤ የጻድቁ አቡነ አረጋዊ ጽሌም ጥቅምት 14 ቀን 1973 ዓ.ም. በብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሚካኤል ተባርኮ ገብቷል፤ “ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለምና መጥምቁ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ” ተብሎም በፓትርያርኩ ተሠይሟል፡፡

ዛሬ፣ ከሀገረ ስብከቱ አብያተ ክርስቲያናት መካከል በተላበሰው ዘመናዊ ኪነ ሕንፃው የሚታወቀውንና በ50 ሺሕ 474 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈውን ካቴድራል ለማነፅ እንቅስቃሴው የተጀመረው በ1973 ዓ.ም. ነበር፡፡ መቃኞው ወደ ሕንፃ እንዳይሸጋገር በመንግሥት ተከልክሎ የነበረ ቢኾንም የአጥቢያው ምእመናን፣ በጎ አድራጊዎችና ዕድሮች ተስፋ ሳይቆርጡ ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ አቋቁመው፣ ፕላን አዘጋጅተው ገንዘብ ሲያሰባስቡና መቃኞውን እያደሱ ይዞታውን ሲያስከብሩ ቆይተዋል፡፡

Bole Debra Salem Medhanialem

እግዚአብሔር የፈቀደው ጊዜ ሲደርስም፥ በውስጥ 2ሺሕ በውጭ ዑደት 2ሺሕ ምእመናንን በመያዝ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል፤ ፎቅና ምድር ያለው ዘመናዊና እጅግ ግዙፍ ሕንፃ፣ በወቅቱ ተመን በ32 ሚሊዮን 677 ሺሕ 452 ብር ለማሠራት ተቻለ፡፡ በዐሥር ዓመታት(ከ1987 – 1997 ዓ.ም.) ጊዜ ውስጥ ለተጠናቀቀው ሕንፃ፥ ሰበካ ጉባኤው፣ ማኅበረ ካህናቱ፣ የሰንበት ት/ቤቱ ወጣቶችና የአካባቢው ምእመናን ሐሳባቸውንና አንድነታቸውን በማቀናጀት የድርሻቸውን ተወጥተዋል፡፡

ማኅበረ ካህናቱ፥ ሙሉ ደመወዛቸውን ለሕንፃ ግንባታው አበርክተዋል፤ የንስሐ ልጆቻቸውን በማስተባበር፣ በየሰንበቱና በየበዓላቱ ቅስቀሳዎችንና ትምህርቶችን እየሰጡ ከፍተኛ ድጋፍ አሰባስበዋል፡፡ ማኅበረ ምእመናንም፥ የካቴድራሉን መብራቶች፣ መንበሮች፣ ሥዕሎች፣ የድምፅ ማጉያዎች፣ የወንበሮቹን ቀጸላዎችና ምንጣፎች ጨምሮ በርካታ ማቴሪያሎችንና የሥራ መሣርያዎችን በከፍተኛ ግዥዎችና በዓይነት በማቅረብና በመለገስ፤ የቤተ ልሔሙን፣ የጠበል ቤቱን፣ የግቢውን አስፋልትና በባለሞያ ዲዛይን የተተከሉትን ዐጸዶች የመሳሰሉትን ሙሉ ወጪ ሸፍነው አሠርተዋል፡፡

በብዙ ሺሕ ምእመናንና ካህናት ከፍተኛ አስተዋፅኦና ድጋፍ አምሮና ደምቆ የታነፀው የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለምና መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ወአቡነ አረጋዊ ካቴድራል ሥነ ውበትና ምቾት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ባሻገር ለኢትዮጵያውያንና ለውጭ ጎብኚዎች መስሕብነት ያለው ቢኾንም ደረጃውን የሚመጥንና የሚገባውን አስተዳደር ለማግኘት ግን አልታደለም፤ በፈንታው፥ ለማኅበረ ካህናቱ ደኅንነትና ሞያዊነት ደንታ ቢስ በኾኑ፤ ጠንቃቃ አያያዝን ለሚሻው የአጥቢያው ምእመን መንፈሳዊነትና ሥነ ልቡና በማይጨነቁ፤ ይልቁንም ለውስጥ አገልግሎቱ ሥርዓትና የተሟላ አፈጻጸም እንዲኹም ለስብከተ ወንጌሉ መጠናከር ዕንቅፋት በኾኑ፤ ካህናቱን በተወላጅነት በሚለያዩና ምእመናኑን በዋልጌነት በሚዘልፉ፤ የካቴድራሉን መብቶችና ጥቅሞች በሕገ ወጥ አሠራር ለነጋዴዎች አሳልፈው እየሰጡ በሚያማስኑ የአስተዳደር ሓላፊዎች እየተበደለና እየተመዘበረ ይገኛል፡፡

የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴው አዲሱን ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን በ1997 ዓ.ም. ሲያስመርቅ አካባቢውን መሠረት ያደረገ የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ ዕቅዶችን ቢያዘጋጅም፤ በተለይም በአኹኑ ወቅት በሓላፊነት የሚገኙት አስተዳዳሪ ከመጡበት ካለፉት ስድስት ዓመታት ወዲኽ ልማቱ ተስተጓጎሎ እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡“ለካቴድራሉ የሚመጥን አባትነትና መንፈሳዊነት ይጎድላቸዋል፤” የሚባሉት አለቃው ቆሞስ መልአከ ሰላም አባ መንግሥተ ኣብ ገብረ እግዚአብሔር፣ ከሰበካ ጉባኤው ዕውቅና ውጭ ግልጽነት በጎደለው አሠራር ከግለሰቦች ጋር በሚፈጽሟቸው ውሎች ካቴድራሉ በገቢ ማስገኛ ምንጮቹ አማካይነት ላቀዳቸው የማኅበራዊ ልማት ሥራዎች አቅም እንዳይፈጥር አድርገውታል፡፡

WOW PRIME HOUSE

የአድባራት የገቢ ማስገኛ ተቋማት፥ ወጥነት ባለው የኪራይ ውል ለአንድ ዓመት ብቻ እንዲያገለግሉ ኾነው የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥቅም በሚያስከብር መልኩ እንዲዘጋጁ ባለፈው ዓመት በቋሚ ሲኖዶስ የተወሰነው ለሀገረ ስብከቱ ተላልፏል፡፡ ይኹንና አስተዳዳሪው ባለፈው ኅዳር በካቴድራሉ በስተምሥራቅ የሚገኘውን ሕንፃ ምድር ቤት ለዋው ፕራይም ሀውስ በወር 100ሺሕ ያኽል ብር በማከራየት የአምስት ዓመት ውል ፈጽመዋል፤ የአካባቢው የወቅቱ የገበያ ዋጋ በካሬ ከብር 400 – 500 ቢኾንም 1800 ካሬ ስፋት ያለውና በዚኹ ተመን ከ810ሺሕ በላይ ወርኃዊ ገቢ ሊያስገኝ የሚችለው ሕንፃ ግራውንድ ግን በካሬ 54 ብር ነው የተከራየው፡፡ ድርጅቱ ግራውንዱን በብላሽ ከተከራየ በኋላ ከዲዛይኑ ውጭ የሕንፃውን ፓርኪንግ ይዞ መውጫ መግቢያውን ለግሉ ተቆጣጥሮታል፤ አጥሩንና ግድግዳውን ለማስታወቂያነት ይጠቀምበታል፡፡

G+1 with 30,000 monthly rent

ቋሚ ሲኖዶሱ ስለሦስተኛ ወገን ተከራዮች ያሳለፈውን ውሳኔም አለቃው ተፈጻሚ አላደረጉም፡፡ ከቤተ ክርስቲያን በዝቅተኛ ዋጋ ተከራይተው ለሦስተኛ ወገን የሚያከራዩ ወገኖች የሚያገኙትን ያልተገባ ጥቅም በመገንዘብ የሦስተኛ ወገን ተከራዮች ለአከራዮቻቸው ይከፍሉት የነበረውን ከፍተኛ ክፍያ ለቤተ ክርስቲያን እንዲከፍሉ በማድረግ ውላቸውን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንዲያደርጉ ታዝዟል፡፡ ይኹንና አስተዳዳሪው፣ በካቴድራሉ ጠበል ቤት አጠገብ የሚገኘውንና በወር 30ሺሕ ብር ለአንዲት ምእመን ያከራዩት ባለአንድ ፎቅ ሕንፃ፣ ተከራዩዋ ለተለያዩ ግለሰቦች በማከራየት ከ100ሺሕ ብር በላይ ወርኃዊ ገቢ እያጋበሱበት ነው፡፡

ግንባታ ለማስጨረስ በሚል ሥራው ያላለቀውን የካቴድራሉን ሕንፃ ከተከራየው አዲስ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ አምስት ሚሊዮን ብር በቅድሚያ ቢቀበሉም ሥራው እንደተባለው ሳይፋጠን መጓተቱ ገንዘቡ በምዝበራና ብክነት ሳይጠፋ እንዳልቀረ አስግቷል፡፡ ካለፈው ኅዳር ወር ወዲኽ በሙዳየ ምጽዋት ቆጠራው በተደረገው ጥንቃቄ በኹለት ሳምንት ጊዜ ውስጥ ከ700ሺሕ ብር በላይ የገቢ ልዩነት ቢታይም፣ “ገንዘቡ ባንክ ለመግባቱ ማረጋገጫ የለም፤” ይላሉ ምንጮች፡፡ ለዚኽም ያለፉት አምስት ዓመታት የቆጠራ ቃለ ጉባኤ በአግባቡ ተይዞ አለመገኘቱና የነበረው የአሠራር ግልጽነት መጓደል በአስረጅነት ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል ምዝበራው፣ “ጉዳይ ለማስፈጸም” በሚል ለሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች በሚሰጥ ጉቦም ይፈጸማል፡፡ የካህናቱና የሠራተኛው ደመወዝ ጭማሪ ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ በሀገረ ስብከቱ እንደጸደቀ ቢነገርም፤ ክፍያው የተፈጸመው ግን ከየካቲት ጀምሮ ነበር፤ የጥር ወር ጭማሪው ለምን እንደቀረ ለቀረበው ጥያቄ በአለቃው፣ በጸሐፊውና በሒሳብ ሹሙ የተሰጠው ምላሽ፣ ጭማሪውን ለማጸደቅ ሲባል ለኹለት የሀገረ ስብከቱ ሓላፊዎች መሰጠቱን የሚገልጽ ነበር፡፡

ኹለቱ ሓላፊዎች፣ በዝውውር የተወገዱት ሥራ አስኪያጁ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ ሲኾኑ መጠኑም 104ሺሕ ብር እንደኾነ ተጠቅሷል፡፡ ይኸውም የየማነ ከሥልጣን መወገድ ይወራ በነበረበት ሰሞን፣ አለቃው ወደ ፓትርያርኩ ቀርበው፥ ቅዱስ አባታችን፣ የማነ በኹለት ዱርዮዎች አስግድዶ ዘረፈን” ሲሉ ጸሐፊውንና ሒሳብ ሹሙን አጋልጠው ራሳቸውን ለማዳን ባደረጉት ሙከራ ታውቋል፡፡

“ቆለኛ እና ደገኛ” የሚባል ነገር በካቴድራሉ እንዳልነበር የሚናገሩት ካህናቱና ሠራተኞቹ፤ አለቃው፣ ጸሐፊውና ሒሳብ ሹሙ ከመጡ ወዲኽ ማኅበረ ካህናቱን በተወላጅነት እየለያዩ አንዱን በማቅረብና ሌላውን በመጉዳት እንዲያም ሲል ዝውውር እየጠየቁባቸው በማራቅ ጥቅማቸውን በሚያስጠብቅ የከፋፋይነት ስልት መጠመዳቸውን ያስረዳሉ፡፡ በዚኽም በመማረራቸው፣ መጋቢት 29 ቀን በካቴድራሉ ባካሔዱት ስብሰባ፥ ለስድስት ዓመት ተሸክሞኖታል” ያሏቸውን አስተዳዳሪ በግልጽ አስጠንቅቀዋል፤ ምሬቱ የባሳቸው አንዳንድ ካህናትም ስማቸውን በጸሎተ ቅዳሴ ከመጥራት መቆጠባቸው ተነግሯል፡፡

አስተዳዳሪውም ይኹኑ ጸሐፊውና ሒሳብ ሹሙ ግን ስሕተታቸውን ከማረም ይልቅ እንደለመዱት፣ የተቃውሞ እንቅሰቃሴውን ያስተባብራሉ ያሏቸውን ከዘጠኝ ያላነሱ ካህናትንና ሠራተኞችን ከካቴድራሉ በዝውውርና በእገዳ ለማራቅ የሀገረ ስብከቱን ጽ/ቤት ደጅ እየጠኑ ይገኛሉ፡፡ በተለይም ለሕዳሴው ግድብ ቦንድ የተዋጣው ብር 400ሺሕ፥ በአንድ በኩል፣ ለሀገረ ስብከቱ ነው የተሰጠው፤ በሚሉና ወደ ባንክ ገቢ ተደርጓል በሚሉ የሚጣረሱ ምላሾች የደረሰበት ካለመታወቁ ጋር ተያይዞ ካለፈው ዓርብ ጀምሮ ሀገረ ስብከቱ በካህናቱና በሠራተኞች ላይ አንዳች ርምጃ እንዲወስድላቸው በእንባ ጭምር በመማፀን ላይ መኾናቸው ታውቋል፡፡


 • ለሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተዋጣው 400ሺሕ ብር የገባበት አልታወቀም
 • ቦንድ ሳይሆን ስጦታ ነው፤ ተብሏል

(አዲስ አድማስ፤ ማኅሌት ኪዳነ ወልድ፤ ሚያዝያ ፰ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)

የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስና አቡነ አረጋዊ ካቴድራል ማኅበረ ካህናትና ሠራተኞች፤ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ቦንድ ያዋጣነው ከ400ሺሕ ብር በላይ ገንዘብ የገባበትን አናውቅም፤ አሉ፡፡ ገንዘቡ ከአራት ዓመት በፊት ከ160 በላይ ሠራተኞች ደመወዝ የተሰበሰበ መኾኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡ 

እንደ ምንጮቹ ገለጻ፤ ካህናቱ በወቅቱ በተደጋጋሚ ለካቴድራሉ አስተዳደር የቦንድ ግዢ የተፈፀመበት ሰርተፍኬት እንዲሰጣቸው ጠይቀው የነበረ ቢሆንም አስተዳደሩ ግን፣ “ገና ከባንክ ቤት አልመጣም”፣ “ይደርሳል” እና መሰል ምክንያቶችን እየሰጠ ቆይቷል፡፡ ከአራት ዓመታት በኋላም ግን፣ ሰርተፊኬቱ ይኸው አልደረሰም፤” ይላሉ ምንጮቹ፡፡

በመጨረሻም ካህናቱ እና ሠራተኞቹ ወደ ንግድ ባንክ በማምራት ጉዳዩን ለማጣራት እንደሞከሩ የጠቆሙት የካቴድራሉ ምንጮች፤ ባንኩም ብሩ ከእነርሱ ስለመሰብሰቡ የሚያውቀው ነገር እንደሌለ እንደገለጸላቸው ተናግረዋል፡፡

Komos Melake Selam Aba MengisteAb Gebra Egzeabhare
ኹሉም የካቴድራሉ ካህናትና ሠራተኞች የዓመት ደመወዛቸውን በኹለት ዙር ማበርከታቸውን የሚናገሩት አስተዳዳሪው ቆሞስ መልአከ ሰላም አባ መንግሥተ ኣብ ገብረ እግዚአብሔር፤ ለኹለተኛው ዙር መዋጮ የቦንድ ሰርተፊኬት መስጠታቸውንና የመጀመሪያውን ዙር በተመለከተ ግን የወቅቱ ሒሳብ ሹም ተከታትለው እንዲያስጨርሱ መወከላቸውን ገልጸዋል፡፡ “እኔም በወቅቱ እንደሌላው ሠራተኛ የአንድ ወር ደመወዜን ለግድቡ ሰጥቻለኹ፤ የቦንድ ሰርተፊኬት እኔም ስጠይቅ ነበር፤ የደረሰኝ የቦንድ ሰርተፊኬት ግን የለም፤” ይላሉ አስተዳዳሪው፡፡

በመጀመሪያው ዙር የተሰበሰበው ገንዘብ÷ በአንድ በኩል በሒሳብ ሹሟ አማካይነት ለሀገረ ስብከቱ ተሰጥቶ ለባንክ መግባቱ ሲጠቀስ በሌላ በኩል ደግሞ በካቴድራሉ ስም በቀጥታ ለባንክ ገቢ መደረጉን የሚገልጹ የሚጣረሱ መረጃዎች ተሰጥተዋል፡፡ “ወዴት እንደደረሰ ሊጠየቁ የሚገቡት የካቴድራሉ ሒሳብ ሹምና ተቆጣጣሪ ናቸው፤” የሚሉት መልአከ ሰላም አባ መንግሥተ ኣብ፤ ማስረጃ አምጡ ሲባሉ ነገ ከነገ ወዲያ እያሉ በዝምታ መቆየታቸውንና በመሀከልም ሒሳብ ሹሟ ከስድስት ወራት በፊት ወደ ሌላ ደብር መዛወራቸውን ይናገራሉ፡፡

“በወቅቱ እርሷ ለሀገረ ስብከት ነው የሰጠችው፡፡ ኹለተኛ ዙር ሲሰብሰብ የቦንድ ሰርተፊኬት ለሠራተኛው መጣ፤ ሠራተኛውም የመጀመሪያ ዙር ሰርተፊኬት ለምን እንዳልመጣ መጠየቅ ጀመረ፤ በኋላም የሀገረ ስብከት ሠራተኞች ሳይቀሩ የመጀመሪያው ዙር ሰርተፊኬት እንደተሰጣቸው ሰማን፤ ሒሳብ ሹሟን ወደ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ላክናት፤ ኾኖም ሀገረ ስብከቱ፥ ጉዳዩ የሚመለከተው ባንኩን ነው፤ ባንኩ ይስጣችኹ፤ አለን፡፡ እኛም ሒሳብ ሹሟን ወክለን ባንኩን ደብዳቤ ጽፈን ጠይቀናል፡፡ ሒሳብ ሹሟ ባንኩን ስትጠይቅ ባንኩ የተባለው ገንዘብ መግባቱን እያጣራኹ ነው፤ አለ፡፡ በመሀከልም ሒሳብ ሹሟ ወደ ዐማኑኤል ደብር ተቀየረች፡፡”

በወቅቱ የካቴድራሉ ሒሳብ ሹም የነበሩትና ከወራት በፊት ወደ ደብረ ገሊላ ቅዱስ ዐማኑኤል ካቴድራል የተዛወሩት እማሆይ እኅተ ማርያም ገብረ ሥላሴ በበኩላቸው፣ ከካቴድራሉ ውክልና እንደተሰጣቸው በአስተዳዳሪው የተጠቀሰውን አስተባብለዋል፡፡

“ውክልና ብሎ ነገር የለም፤ ለሀገረ ስብከትም የሰጠሁት ገንዘብ የለም፤” የሚሉት ሒሳብ ሹሟ ጊዜው በመራቁ የገንዘቡን ትክክለኛ መጠን ባያስታውሱትም፤ የካህናቱንና የሠራተኞቹን አስተዋፅኦ እንዲሰበስቡ በታዘዙት መሠረት ከተሰበሰቡ በኋላ አራት ኪሎ በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሥላሴ ቅርንጫፍ በካቴድራሉ ስም ገቢ ማድረጋቸውንና የገባበትንም ኮፒ ለሀገረ ስብከቱ መስጠታቸውን፤ ኦሪጅናል ሰነዱም ዝውውራቸውን ተከትሎ በካቴድራሉ ጽ/ቤት ታሽጎበት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ስለ ቦንድ ሰርተፊኬቱ ከካቴድራሉ ተቆጣጣሪና ጠቅላላ አገልግሎት ሓላፊዎች ጋር በመኾን የባንኩን ቦሌ መድኃኔዓለም ቅርንጫፍ መጠየቃቸውን አያይዘው የጠቆሙት ሒሳብ ሹሟ፤ “በመጀመሪያው ዙር የተሰበሰበው መዋጮ እንደ ስጦታ የሚቆጠር ስለኾነ ቦንድ አይሰጥም፤ የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ጠቅሰዋል፡፡   

 

Advertisements

5 thoughts on “በቦሌ መድኃኔዓለም: ምዝበራ እና ለአገልግሎቱ የተሰጠው ትኩረት ካህናትን እያማረረ ምእመናንን እያሸሸ ነው፤ ለሕዳሴ ግድብ ቦንድ የተዋጣው 400ሺሕ ብር የገባበት አልታወቀም

 1. Anonymous April 18, 2016 at 7:01 am Reply

  HARAWOCH, KENDEGNAW LEBA SELOMON BEKELEN BEMETEW MENGSTESEMAYAT ABINGDON BICHA LEMIN BEWR BIR 5METO SHIH YIKOTER YENEBERE MUD AYE MUTSIWAT BEAMAKAGNI 1.4 MILYON INDIKOTER YADEREGUT YE AHUNU TSEHAFINA HISAB KIFLNACHEW KESHI YACH BIR 30 SHIH BEWR YIGEB YENEBERE ZARE BIR 7.METO SHIH DERSOGNAL BEMAN BEAHUNU TSEHAFINA HISABESHUM NEW YIHM YADEREGEW YEYEMANE ASTEDADARI NEW LEMANGNAWM GILTSI YEHONE ENDET LEMIN MECHE BEMIL HUNETA ENDITARA BIDEREG BITASASBU TIRU NEBER

  • Anonymous April 19, 2016 at 6:50 am Reply

   ጥሩ ዘገባ ነው። ከካቴድራሉ በላይ ለቤተ ክርስቲያናችን ክብር ወሳኝ ቦታ በመሆኑ ማለቴ ነው፣ ግን ስለዘረፋው ስታወሱ ምነው እንደ መሐል ሜዳ ኳስ አከፋፋይ /ሚድ ፊልደር/ ዋናውን አከፋፋይ ሌባ ገንዘብ ያዡን አባ ወልደዮሐንስን ዘነጋችሁት፣ ቀደም ሲል በሞዴል 30 ገንዘብ ተቀባይነት፣ አሁን ደግሞ በገንዘብ ያዥነት ለ23 አመታት እያከፋፈለ እና ድርሻውን እየመዘበረ በመቶ ሺህ ብሮች በገዛው ኮንዶሚኔም ቤት ሴቶችን እንደ ሸሚዝ እየቀያየረ በሚፈፅመው ዝሙት ቤተ ክርስቲያናችንን እና ምንኵስናን እያስነቀፈ የሚገኝ ባለው የሚሊየን ብር ካፒታል ልቡ የደነደነ መሆኑን እንድታወቁት ነው። በቀጣይ በመረጃ የተደገፈ ዝርዝር ነገር በዚህ ወይም በተመሳሳይ ብሎጎች ጠብቁ……!

   • Anonymous April 20, 2016 at 2:11 pm

    ትክክል! አሁን እንኳን ባለፈው የማነ ዘሙስና ከካቴድራሉ ፀሐፊ ጀምሮ ብዙዎችን ሲቀይር “አባ” ወ/ዮሐንስ የተባለውን ገንዘብ ያዥ ዋና ሌባ አልቀየረውም ለምን መሰላችሁ ከሚዘርፈው ብር ላይ በየወሩ ለየማነ እጅ መንሻ ይሰጥ ነበረ አሉ።

 2. ውድ የሀራ ተዋሕዶ አዘጋጆች ስለ ካቴድራሉ የዘገባችሁት በተወሰነ መልኩ እውነትነት ቢኖረውም አሁን ባለው አስተዳደር ላይ ግን የተጋነነ ሀሰት አቀረባችሁ፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: