ሰበር ዜና -አማሳኙ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ተወገደ! የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪው ጎይቶኦም ያዩኒ ተተካ፤ 3 ተጨማሪ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችም ተነሥተዋል

Goitom Yayuni

በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምትክ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ዛሬ ከቀትር በኋላ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተመደቡትና ለልዩ ጸሓፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን መ/ር ጎይቶኦም ያዩኒ

 • የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ፤ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት አለነ፤ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዝዘዋል፤
 • ዛሬ ከቀትር በኋላ ከፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት ወጪ ኾኖ ማምሻውን ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት የደረሰው የሹም ሽር ምደባና ዝውውር፣የሠራችኹት ተመርምሮና ተገምግሞ የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣችኹ ድረስ” የሚልና በጊዜያዊነት የተደረገ ስለመኾኑ ተጠቁሟል፤
 • የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሕገ ወጥ መልኩ ከሥራ አስኪያጅነቱ ጋር ደርቦ በያዘውና ቀድሞ ሲሠራበት በነበረው የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ደብር ዋና ጸሐፊነቱ ይቀጥላል፤ “የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጣችኹ” በሚል ከተነሡት ሓላፊዎች ኹለቱ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ ተመድበዋል፤
 • ሊቀ ጠበብት ኤልያስ፥ በጠቅላይ ጽ/ቤቱ የገዳማት መምሪያ ጸሐፊነት፤ ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት አለነ፥ በመንፈሳዊ ፍርድ ቤት ጸሐፊነት መመደባቸው ተገልጧል፤ በደቡብ አፍሪቃ በስብከተ ወንጌል ተልእኮ ላይ ያሉት የሊቀ ትጉሃን ታጋይ ጉዳይ በእንጥልጥል ላይ ነው፤
 • በሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ ምትክ የሀገረ ስብከቱ ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ምክትል ሓላፊ አቶ ገብረ ሕይወት አስገዶም፤ በሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት አለነ ምትክ በተለያዩ አህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ የነበሩት መጋቤ ጥበብ ናሁ ሠናይ በለጠ ተመድበዋል፤
 • በሀ/ስብከቱ የፐርሰንት ፈሰስ፤ በገዳማትና አድባራት የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጭማሪዎች ቀበኛነት ባለሀብት የኾነው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ ውሳኔውን ለማስቀልበስ በዘመድ አዝማድ ሽማግሌዎች በኩል እየተሯሯጠ ነው፤
 • ያለረዳት ሊቀ ጳጳሱ ምርጫ፣ በፓትርያርኩ ቀጥተኛ ውሳኔ፣ ባለፈው ዓመት መጋቢት 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ውጭ የተደረገው የአማሳኙ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምደባ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለከፍተኛ ጭቅጭቅና ውዝግብ የሚዳርግ፤ ውሎ አድሮም ተጠያቂነትን የሚያስከትል ብሎም የሀገረ ስብከቱን ሠራተኞችና ምእመናን አንድነትና መንፈሳዊ ሕይወት የሚያናጋ እንደኾነ በመጥቀስ የወቅቱ ረዳት ሊቀ ጳጳስ እና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ለፓትርያርኩ በተደጋጋሚ ሲያሳስቡ እንደነበር አይዘነጋም፡፡
Advertisements

28 thoughts on “ሰበር ዜና -አማሳኙ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ተወገደ! የተሐድሶ ኑፋቄ ተላላኪው ጎይቶኦም ያዩኒ ተተካ፤ 3 ተጨማሪ የሀ/ስብከቱ ሓላፊዎችም ተነሥተዋል

 1. Anonymous April 4, 2016 at 3:19 pm Reply

  Yehun

 2. Berhanu Y.berhan April 4, 2016 at 4:05 pm Reply

  እግዚኦ ፀወነ ኮንከነ Sent from Huawei Mobile

  “ሐራ ዘተዋሕዶ” wrote:

  > a:hover { color: red; } a { text-decoration: none; color: #0088cc; } a.primaryactionlink:link, a.primaryactionlink:visited { background-color: #2585B2; color: #fff; } a.primaryactionlink:hover, a.primaryactionlink:active { background-color: #11729E !important; color: #fff !important; } /* @media only screen and (max-device-width: 480px) { .post { min-width: 700px !important; } } */ WordPress.com haratewahido posted: ” የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ፤ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ሥዩማን ወልደ ሰንበት አለነ፤ የዕቅድና ልማት ዋና ክፍል ሓላፊው ሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ ለጠቅላይ ጽ/ቤቱ ሪፖርት እንዲያደርጉ ታዘዋል፤ “

 3. ትዕግስቱ መገራ April 5, 2016 at 2:49 am Reply

  የማነ የሚበቃውን ያህል ዘርፎ የድርሻዉን ና የፈለገዉን ያህል ወስዷል፤፤አሁን ደግሞ ጎይቶም የድርሻዉን እንድወስድ እኮ ነዉ ይህንን ተሃድሶ በጎጥ የሰበሰቡት ይህ ጎጠኛ ፓትርያርክ;;

  • BK April 5, 2016 at 7:04 am Reply

   Yeap! you are right.

 4. Anonymous April 5, 2016 at 6:02 am Reply

  የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ በጣም ያሳዝናል፣ ደግሞ ሁሉም ከአንድ ብሔር መሆኑ ለምንድንነው? /ን ከእነርሱ የበለጡ ለቦታው የሚመች ሰው አጥታ ነው? ይሄስ ዘረኝነት አይደለም? ቤተክርስታንቱን በቅኝ ግዛት መያዝ አይደለም? በጣም ያሳዝናል

 5. Anonymous April 5, 2016 at 6:14 am Reply

  ይህን ስናገር በጣም በመሳቀቅም ጭምር ነው፡፡ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ቤተሰቦቼም የተወለድኩትም ትግራይ ነው፡፡የቤተሰቦቼን ሀገርም እወዳለሁ ፤ ነገር ግን የበለጠ ተዋሕዶ ሃይማኖቴንና ሀገሬን ኢትዮጵ እወዳለሁ፡፡ሁልግዜ ቅር ከሚሉኝ ነገሮች አንዱ በአብዛኛው የአመራር ቦታዎች ለምን የትግራ ሰዎቸረ በቻ እንደሚቀመጡ ነው፡፡ይህ ነገር ልማድ ሆኖ ከቀጠለ ሌሎች ሰዎች የመገለል ስሜት ስለሚፈጥ አደገኛ አካሔድ ነው፡፡አሁንም የማነ በሚባል ሌባ የተተኩት ተመሳሳይ ብሐር ናቸው፡፡ለምን ? በአመራርነታቸው የሚያገለግሉት ቤ/ክ ከሆነ ሌሎች ብሔሮች የህን የመፈጸም ብቃት የላቸው ? ወይስ በቤተክህነት የሚሰሩት ሌላ ስራ አለ? በጣም ያሳዝናል፡፡ቤ/ክ የሁላችንም ናት፡፡

 6. davaviskey April 5, 2016 at 6:16 am Reply

  ይህን ስናገር በጣም በመሳቀቅም ጭምር ነው፡፡ እግዚአብሔር ምስክሬ ነው ቤተሰቦቼም የተወለድኩትም ትግራይ ነው፡፡የቤተሰቦቼን ሀገርም እወዳለሁ ፤ ነገር ግን የበለጠ ተዋሕዶ ሃይማኖቴንና ሀገሬን ኢትዮጵ እወዳለሁ፡፡ሁልግዜ ቅር ከሚሉኝ ነገሮች አንዱ በአብዛኛው የአመራር ቦታዎች ለምን የትግራ ሰዎቸ በቻ እንደሚቀመጡ ነው፡፡

  ይህ ነገር ልማድ ሆኖ ከቀጠለ ሌሎች ሰዎች የመገለል ስሜት ስለሚፈጥር አደገኛ አካሔድ ነው፡፡አሁንም የማነ በሚባል ሌባ የተተኩት ተመሳሳይ ብሐር ናቸው፡፡ ለምን ? በአመራርነታቸው የሚያገለግሉት ቤ/ክ ከሆነ ሌሎች ብሔሮች የህን የመፈጸም ብቃት የላቸው? ወይስ በቤተ ክህነት የሚሰሩት ሌላ ስራ አለ? በጣም ያሳዝናል፡፡ ቤ/ክ የሁላችንም ናት፡፡

 7. ፍቅርተ ማርያም April 5, 2016 at 6:58 am Reply

  በቤተክርስቲያናችን ምን እየተደረገ እንደሆነ ግራ እየገባኝ ነው:: በቤተ ክህነት ያሉ አባቶች ምን እየሰሩ ነው፡፡ ለቤተ ክርስቲያናችን የሚጠቅም ሰው፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ፤ ሰውን የሚያፍር ሰው ጠፋ ወይስ ሌላ አላማ አላቸው? ሙሰኛን አንስቶ የሃይማኖት እፀጽ ያለበትን መሾም የከፋ ነው:: እኛ ከተቀበልናት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ሌላ ቤተ ክርስቲያን አላቸው እንዴ? ለምን አባቶች ስለተጠሩበ፣ ስለ ተሾሙበት ስለ አንዱቷ ቤተ ክርስቲያን አይማልዱልንም፡፡ አባታችን እባክዎ መጋውን የሚበትን ሥራ አይሥሩ፤አልያ ለመንጋው ለሚጨነቅ እረኛ አስረክቡን! ጥቂት ከአቡነ ሽኖዳ ህይወት ተምረው ያስተምሩን ስለ ድንግል ማርያም፡፡

 8. Anonymous April 5, 2016 at 7:24 am Reply

  ይሄ በጣም አሳፋሪ አነጋገር ነው ዲ/ን ጎይቶኦም ያይኑ የተሃድሶ ኑፋቄ ተላላኪ ብሎ ለመግለፅ የተሞከረው ዲ/ን ጎይቶኦም ያይኑ ፈፅሞ ሊገልፀው የማይችል ይልቅ ተሃድሶን አጥብቆ የሚቃወም እንደሆነ ነው እኔ የማውቀው፡፡የሚያሳዝነው ግን በፖለቲካ ሳይሳካላቹህ ሲቀር በቤተክርስትያን መምጣታቹህ ነው፡፡ እስኪ መሳቂያ አትሁኑ ቢቀርባቹህስ ፡፡

  • Dejene Alemu April 5, 2016 at 10:39 am Reply

   eshi

 9. fesha negash April 5, 2016 at 10:32 am Reply

  በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምትክ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት ዛሬ ከቀትር በኋላ በፓትርያርኩ ደብዳቤ የተመደቡትና ለልዩ ጸሓፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን መ/ር ጎይቶኦም ያዩኒ

 10. Anonymous April 5, 2016 at 10:33 am Reply

  የሚሳዝነዉ እኮ የማነ ማለት ልማታዊ ሌባ ምንም ችግር የለዉም የሚል አቋምያለዉ ሙሰኛ ነዉ እንደድሮ አዚህ በልቶ እዚያ ሄዶ መኖር አክትሟል! አሁን ማስረጃ ያላችሁ ልክ እንደ ኪዳነምህረት ሂሳብ ሹም ያለ እዉነተኛ ፤ ሃይማኖተኛ ለፀረ ሙስና በመቅረብ የተደረገዉን ሪፖርት ማድረግ ያስፍልጋል፤፤ በተጨማሪም የሰበካ ጉባኤ ምክትሎች ሂሳብ የምትፈርዉ ይህንን አይነት ኢ-ሃይማኖታዊ ድርጊት ተከታትሎ የማስፈፀም ግዴታ አለባችሁ፤፤

  ለወደፊቱ ትልቅ ት/ት የተወሰደ መስለኛል ገና ዘመቻዉ ወደ ሙሰኛ የደብር አለቆች ይዞራል፤፤ ይህ ደሃ ህዝብ ከሌለዉ ላይ ለእግዚአበሄር ብሎ የሰጠዉን መስዋት ልግላቸዉ ሲሞዳሞዱ፤ በፆሙ በዝጉብኝ ቡና ቤት አሼሼ ገዳዮ ሲሉ የማያፍሩ መኪና በመለዋወጥ የሚፀድቁ የሚመስላቸዉ አማሳኞች እየበዙ ነዉ፡፡ ስለሆነም ሁሉም መዕመን ነቅቶ እየጠበቀ ማጋለጥ የስፈልጋል፡፡

 11. Dejene Alemu April 5, 2016 at 10:38 am Reply

  I’m sorry, u r absolutely right Te’egistu Megera(first comment above)

 12. Anonymous April 5, 2016 at 2:11 pm Reply

  አቤት የመከራ ዘመን! አቡነ ማትየስ በቤተ ክርስቲንን ገለዋት ሊሞቱ እንደሆነ እርግጠኛ ሆኜ ነው የመነገራችሁ::

 13. Anonymous April 5, 2016 at 2:34 pm Reply

  ያሳዝናል የማነ ያንን ሁሉ የአስተዳዳሪዎች ቦታ በጉቦ ሸጦ መንግስት ባለበት አገር ላይጠየቅ ነው?

 14. Anonymous April 5, 2016 at 2:37 pm Reply

  ይኸ ዘረኛ የፖለቲካ ቁማርተኛ መነኩሴ ዛሬስ ደግሞ በከረባት አንገቱን ያነቀ ሰው በቤተክርስቲያን ላይ መሾም ጀመረ ይገርማል !!!

  አስተያየት የሰጠኸው ወንድማችን እውነታውን ደብቀህ በፖለቲካ ስላልተሳካላችሁ ማለትህ እየተሳሳትክ እንደሆነ ብታውቀው ጥሩ ነው እውነት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታይ እንደሆንክ እየተሰራ ያለው ጉዳይ ከምንወዳቸው ከትግራይ ወገኖቻችን ለማጣላት በወታደሩ ሲታይ ሹማምንቱ ትግሬ መቁጠር ይቻላል፣ በሃይማኖት ተቋማት ሱማምንቱ ትግሬ በሚኒስተር ደረጃ ያለውን አብዛኛው ትግሬ ለዚች አገር እያደረሰ ያለው የአንድ ጎጥ በደል ምንአልባትም ወደፊት እንደሯንዳው ቱክሲና ሁቱ እንዳይሆን ስጋት አለኝ ፡፡ወያኔዎች/ህዋቶች/ ብታስተውሉ ጥሩ ነው፡፡ በኦሮሞዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍና ግድያ፣ በአማራ በወልቃይት እየደረሰ ያለው የዘር ማጥፋትና ግድያ፡፡ እረ ስንቱ ይወራ ፡፡ አላማችሁ አገሪቱን እንዳልነበረች መበታተንና ታሪኳን ማጥፋት በሃይማኖቱ ገባችሁ በቢሔሩ ገባችሁ ወደብ አልባ አደረጋችሁ፡፡

  ቢጨንቃችሁ ደግሞ ሰሞኑን የያዛችሁት ትሪናፈ /ፕሮፓጋንዳ/ ስለ አድዋ ጦርነትና ታሪክ ስት ዘምሩ ሰምቸ እጅግ ተገረምኩኝ ምን አልባት በመጽሃፍ ቅዱስ ሃዋሪያት ጌታን ዳግም የምትመጣበት ቀን መቸ ነው ንገረን ሲሉት አልነግራችሁም አላቸውና እሽ ምልክቱን ንገረን ሲሉት የዳግም መምጫየ ጊዜ ሲደርስ ያኔ ጠብ ክርክር፣ ለሃይማኖቱ የሚቆረቆርና የሚጨነቅ ይጠፋል፣ እውነት ትመነምናለች፣ ህዝብ በህዝብ ላይ ይነሳል፣ ልጆች በአባቶች ወንበር ላይ ተቀምጠው ይፈርዳሉ የመሳሰሉትን ምልክቶች ነገራቸው፡፡ ያ ድርጊት ወያኔ/ህዋት/ ከገባ ጀምሮ እየታየ ያለው የትንቢት ቃል እየተፈጸመ ይገኛል፡፡ አፄ ሚኒሊክ ከውጭ ወራሪ ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው አገር አስከብረው በማቆየታቸው ዘመናዊነትን ለአገሪቱ በማስተዋወቅ ደረጃ ከፍተኛ ሚና በመጫወታቸው በወያኔ የታሪክ ጉዞ ሲወገዙ ሲረገሙ እንዳልነበረ ለጥቅማችሁ ስትሉ አድዋ ላይ ዩኒቨርስቲያችሁን ለመክፈት ፈልጋችሁ ስለአድዋ ህዝቡን ለማሞኘት የለመዳችሁትን ውሽታችሁን ስትደሰኩሩ ስሰማ እጅግ ገረመኝ፡፡ በሰፈራችሁት ልክ ቁናችሁን መሰፈሩ አይቀርም ብትጸጸቱ ና ንስሃ ብትገቡ መልካም ነው፡፡ የዋሁን የትግራይ ህዝብ ከሌላው ወገኑ ጋር በእናንተ የተነሳ ባታጣሉት መልካም ነው፡፡ እኔ የፖለቲካ ሰው አይደለሁም ወንድሜ ለእናንተም ለውሸታም ፖለቲከኞቹ ታሳዝኑኛላችሁ፡፡ምክንያት ፖለቲካ ውሸት፣ ጭቅጭቅና ንትርክ፣ ክህደት /አገርህን፣ሃይማኖትክን፣ ወገንህን ና ማንነትህን/ እስኪ እነዚህን ያልካደ ፖለቲከኛ ማን አለ?

  ልቦና ይስጣችሁ !! እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም ዘወትር ልጃን እየለመነች አገራችንን ከመበታተን ትጠብቅልን! ታስጠብቅልን ! አሜን!!! በእግዚአብሔር ቸርነትና ጥበቃ እንጅ በፖለቲከኞች አገር ስለማትጠበቅ፡፡

 15. fesha negash April 6, 2016 at 6:14 am Reply

  በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ምትክ፥ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅነት የተመደቡትለልዩ ጸሓፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ዝምድና እንዳላቸው የሚነገርላቸው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን መ/ር ጎይቶኦም ያዩኒ!!

  እንኳን ስራ አስኪያጅ ይቅርና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ተቀባዮች ስለት ገንዘብ ቆጣሪዎች እነ አብረኸት ብቻ ሆነዋል፡፡ እነሱ እኮ ሌላው ካላጎነበሰላቸው በቀር እንኳን የሀላፊነት ወይንም የገንዘብ ቦታ ይቅርና ተራ ሥራም አይሰጡት፡፡ እኔ የማደንቀው ግን የእነ ያማነ ሌብነት አላምር ሲለው በጊዜ በራሱ ፈቃድ ም/ሥራ አስኪያጅነቱን የለቀቀውን መምህር አእመረን ነው፡፡ አሁን ዘረኝነት ባይኖር ኖሮ እሱ በሐቀኝነቱ የዋና ሥረ አስኪያጅነቱን ቦታ መያዝ ነበረበት ግን ሌላ (ጎዣሜ) ነዋ!!

  ሪዛቸውን ያረዘሙ እድሜን የጠገቡ በገጻቸው መንፈሳዊነት ያለባቸው የሚመስሉ ውስጣቸው በጎጠኝነት የተሞላ አባቶች ተብዬዎች እጃችሁን ለእግዚአብሔር ሳትሰጡ መንፈሳዊ ሥራ የሰራችሁበት ሳይሆን የሳታችሁበት እድሜአችሁ ወደ ፍርድ እየነዳችሁ ነው ነው፡፡ ተው!! በቀሪ ዘመናችሁ ለእውነት ሥሩ፡፡ አናንተ ዘረኞች፣ የደብሩ አስተዳዳሪ እና ቢሮ ሰራተኛው ሙዳየ ምጽዋት ቀማኛ፣ ወጣቱ ሱሰኛ፣ ባለሥልጣኑ ቀማኛ፣ባለትዳሩ ሴሰኛ፣የእኛ የምትሉት ሥነ ምግባር አልባ ሆነ፡፡ ሁሉ ተበላሽቶ አይከብዳችሁም ቀሚስ እየጎተታቸሁ አባቶች ነን ስትሉ ልጆቻችሁ እነማን ነን…. እስቲ በእናንተ ወንበር የነበሩትን ቀደምት አባቶች አንብቧቸው፡፡ ማን ከማን ተምሮ ጥሩ ምግባር ይኑረው፡፡ እበቶች ሆናችሁ እኮ!!! እበት በእርጥበቱም ሆነ ሲደርቅ ያው ነው! ክብር የለውም!! አፍንጫ ይሰረስራል፣ ጥሩ መኣዛ የለውም፡፡

  እና ወዳጃችን አቅም እና ሙሉ እውቀት ያለው ሰው በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት ሥልጣን ይይዛል ብለህ ባታልም ጥሩ ነው፡፡ የጎጠኝነቱ ደመና ሲገለጥ እግዚአብሔር ለቤተ ክርስቲያን የፍቅርና የሰላምን ሐር ግምጃ ያለብሳታል ፡፡ ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡

 16. Anonymous April 6, 2016 at 7:41 am Reply

  Goitom’s father name is ‘ Yaynu’ not ‘Yayuni’. Check www​.httc.edu.et/#!history/czmc

 17. beza April 6, 2016 at 1:47 pm Reply

  ዝም በል ባክህ!! ለአንድ ተራ ዕጩ ሌባ ከምትቆረቆር ምናለ በጭንቅ በውጥረት ላይ ላልች ቤተክርስቲያን ብታስበ. አንታም ያው ነህ ተሃድሶ መናፍቅ…

 18. Anonymous April 7, 2016 at 6:50 am Reply

  ይህቺ ቤተክርስቲያን የትግሬ ብቻ ናት እንዴ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትም ሆነ በጠቅላይ ቤተክህነት ያሉት የተቆጣጠሩት እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ በጣም ሼም ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በምንፍቅናና በምዝበራ ታጥቀው የሚሰሩ ናቸው፡፡

 19. Anonymous April 7, 2016 at 9:46 am Reply

  የአይጥ ምስክር ድንቢጥ
  ጉልበተኛው ፓትርያርክ አባ ማትያስ ከማን እየመከሩ እየሰሩ ናችው ከሊቃነጳጳሳት ወይስ ከሌቦች አባ ማትያስ በሙያቸውና አበርክቶአቸው ሳይሆን ለመልካቸውና ረዥም እድሜቸው ተብሎ በማይውቁት ሀገር ፓትርያርክ ሆነው ሲሾሙ ሌብነትን ለማጥፋት ያልተጠበቀና ወቅቱን ያልጠበቀ ሙስናን የመዋጋት አዋጅ ለዓለም ሁሉ አሰሙ እውነት የመሰላቸው የቤተክርስቲያን ሎጆችም እሳቸውን ለመደገፍ የገንዘብ የሙያ ድጋፍ አበርክቶ ለማድረግ ቆርጠው ተነሱ ግን ሳይውሉ ሳይድሩ የቅኖች ሳይሆን የሌቦች አባ ሆነው እርፍ ሙስና አጥፊ ሳይሆኑ ስራ ሳይሰሩ / ሙስና ይጥፋ በማለት የኬክ ቀን / ቢዘጉም / ባልሰሩበት በየወሩና በየቀኑ የወርቅ፤ የብር ፤ የከበሩ አልባሳት ተሸላሚ ሆነው እርፍ አማካሪዎቻቸውም አዲስ አበባ ከገቡ 20 ዐመት ያልሆናቸውና ሙዳየ ሙጽዋት በመገልበጥና የቤተክርስቲያን መሬት ለ10 እና 20 ዓመታት በብር 0.5 እና በ.02 በማከራየየት የብዙ መኪናዎች ባለንብረትና ከከተማ እስከገጠር ዘመናዊ ቤቶችን የገነቡ ሀይሌ እና ዘካርያስ ሆነው ቀሩ ልባ አማካሪ ሌብነት ከሚያስፋፋ እውነት ሀቅ ይመክራል ‹‹ ከማን ጋር እንደዋልክ ንገረኝና ማን እንደሆንክ ልንገርህ›› የሚባለው ተረት እናስታውሰዎት እነዚህ ሰዎች ከየት አመጡት ዘካርያስ ሃዲስ ባለፈው 2 ዓመት የሠራው ቤት ቢያስጠላው ዛሬ ለዓለም ጉድ የሚያስብል ዘመናዊ ቤት እየሰራ ያለው ደመወዙ ስንት ሆኖ ነው እሱም ሚስቱም ልጆቹም የቤተክርስቲያን /የሙድዬ ሙጽዋት/ ተቀጣረዎች ናቸው ከየት አምጥቶ ነው ታድያ ፓትርያርኩ ይህን ሰው በቀን 3 ጊዜ ስልክ ደውለው በማማከር ነው ከቤተክርስቲያ ሙስና የሚጠፋ ወይስ ጠቁሩ ሌባ ይጥፋ ቀዩ ሌባ ይኑር እያሉን ነው አሁን ዘካርያስ ሀዲስ አባማትያስን በስልክ አዝዤ ወንድሜን የአስተዳደር ሃላፌ አስደርጌአለሁ ከዚህ ቦሃላ ደጀጠኞች ወደኔ ኑ እያለ በማወጅ ላይ ነው ሀይሌ በበኩሉ ከዚህ ቦሀላ አሁን ያስቀመጥነው ሥራአስኪያ እነስን እያማከርክ ሥራ ተብለዋል ከዚ ቀን ጀምሮ መተኛት አያስፈልግም አለቆች ይቀየራሉ በዚህ የዐመቱ ድርግ በበልግ ይክሰናል እያሉ ለአባ ማትያስ እንደዳንኤል ክችረት ደረቅ የጥላቻ አባባል ሳሆን በጨዋ ደንብ ምን ትላላችሁ በዚህ ላይ እነወያይ ወንድሞቼ

 20. Anonymous April 9, 2016 at 7:32 am Reply

  እየሆነ ያለው ሁሉ ያሳዝናል ቤተክርስቲያኗ ባለቤት አልባ ሆናለች

 21. Anonymous April 11, 2016 at 2:35 am Reply

  Anonymous April 5, 2016 at 2:37 pm Reply ስለ ሃይማኖት የጻፍክ አስመስለህ ስለ ዘረጘንነት ስለ ፖለቲካ ትችት ስድብ ለዚህ መድረክ አላስፈላጊ ሐተታ የዘረዘርከው ሰው እንዲሁም ይህን መሰል ንግግር እየተናገራችሁ ራሳችሁ ከዘረኝነት ነጻ የሆናችሁ መስላችሁ ለመታየት የምትሞክሩና የቤተክርስትያን ጉዳዮች በሚነሱበት መድረክ እየገባችሁ የፖለቲካ አላማችሁን ለማሳካት ቅስቀሳ የምታደርጉ አንዳንዶቻችሁም ከተሐድሶዎች ያልተለያችሁ የቤተክርስትያናችን ፈተናዎች ናችሁ። ክርስትና ትግሬ የገባበትን ጓዳ ጎድጓዳውን ሁሉ እየተከታተሉ እዚ ጋር ይህን ያህል ትግሬ አለ አማራ ግን የለም እያሉ መከታተል አይደለም ይህን አማራ አለ ኦሮሞ ግን የለም ይህን ያህል …….ብሄር አለ ……ግን የለም እያሉ ጊዜ ማባከንም አይደለም። የቤተክርትያንን ችግሮች ለማቃለል እንዲህ ብንሰራ ይህን ብናደርግ በእንዲህ አይነት ህጋዊ አካሄድ ብንሄድ እንዲህ አይነት መረጃ ብናቀርብ በእንዲህ አይነት ጉዳይ የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ብንወያይ በቋንቋ ችግር የቤተክርትያን አስተምህሮ ያልተዳረሰባቸውን አካባቢዎች እንዲህ እንዲህ አድርገን ብናስተምር ቤተክርትያን ውስጥ የመሸጉ የቤተክርስትያን ተቃዋሚዎችን የኑፋቄ አራማጆችን በዚህ በዚህ መልኩ ወይ ለማሳመን መጣር የማይመኑትን ደግሞ የህግ ባለሞያዎችን ተጠቅሞ በህግ እርምጃ ማስወሰድ ወዘተ. ሀሳቦች መፍትሄዎች እርምጃዎች ላይ ማተኮር እንጂ የትግሬና የአማራ ቆጠራ መፍትሄ አደለም። ችግሩ ትግሬ ወይም አማራ መሆኑ አይደለም። ቸግሩ ያለው ልብ ላይ አመለካከት ላይ አስተሳሰብ ላይ እምነት ላይ ነው። ዘሩ ምንመ ይሁን ምን ፖለቲካ አመለካከቱ ምንም ይሁን ምን ልቡ አመለካከቱ አስተሳሰቡ እምነቱ ታማኝነቱ ከኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርትያን ጋር ነው ወይስ ከመናፍቃን ጋር ነው ከዘራፊዎች ጋር ነው ወዘተ ነው መታየት ያለበት። ሌሎች ሲሳደቡ ስላየን እኛም ዝም ብለን መሳደቡ መፍትሄ አይሆንም። በኔ እይታ ስለቤተክርስትያን በሚደረጉ ውይይቶች ውስጥ ጥልቅ እያሉ ከዚህ ዓለም ሕልፈት በሁዋላ ቦታ የሌለውን አላፊ ጠፊ የሆነውን ለስጋዊ ኑሮ ካልሆነ በስተቀር ለነፍስ አንዳች የማይጠቅመውን ፖለቲካ በደጋፊም ሆነ በተቃዋሚ ፖለቲከኞች መስበክና ማሰበክ ራሱ ሙስና ነው። እና እባካቹ ስድብ የምታበዙ ወንድሞች እህቶች ከትችትና ከሃፍረት ውጪ ምንም ጥቅም ለማይሰጡ ንግሮች ምላሳችንን አናሰለጥን። ይህን ስል ግን ኑፋቄን አትቃወሙ በቤተክርትያን ስም የሚነግዱ ሰዎችን አታጋልጡ እያልኩ አይደለሁም ስለኑፋቄ ልትናገሩ ጀምራቹ ስኢትዮጵያ መጥፎ ፖለቲከኞችና ጥሩ ፖለቲከኛች በተዘዋዋሪ መንገድ ስብከት ውስጥ አትግቡ። ለፖለቲካው ጆሮ የሚያጣብብ ከበቂ በላይ መድረክ ስላለ በዚያ ተጠቀሙ ማለቴ ነው። እግዚአብሔር ሁላችንንም ያሰተካክለን ቤተክርስትያን ላይ ችግር የሚፈጥሩትንም ከጥፋታቸው መልሶ ያጠፉትን በእጥፍ ክሰው ቤተክርስትያናችንን የሚያገለግሉ ለህጓ ለስርዓቷ ለትውፊቷ ጠበቆችና ታዛዦች ያድርግልን። ጥላቻን አስወግደን ፍቅርን ብንሰብክ ጠላት የነበረው ወዳጅ ይሆናል። ጥላቻን ብናስፋፋ ግን ውጤቱ መላያየትና ጸብ ነው የሚሆነው።

  • Anonymous April 12, 2016 at 7:22 am Reply

   ሰናይ ውእቱ

 22. Anonymous April 16, 2016 at 9:08 am Reply

  ሀሳቦች መፍትሄዎች እርምጃዎች ላይ ማተኮር እንጂ የትግሬና የአማራ ቆጠራ መፍትሄ አደለም። ችግሩ ትግሬ ወይም አማራ መሆኑ አይደለም። ቸግሩ ያለው ልብ ላይ አመለካከት ላይ አስተሳሰብ ላይ እምነት ላይ ነው። ዘሩ ምንመ ይሁን ምን ፖለቲካ አመለካከቱ ምንም ይሁን ምን ልቡ አመለካከቱ አስተሳሰቡ እምነቱ ታማኝነቱ ከኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርትያን ጋር ነው ወይስ ከመናፍቃን ጋር ነው ከዘራፊዎች ጋር ነው ወዘተ ነው መታየት ያለበት።

 23. senay April 24, 2016 at 2:22 am Reply

  እኔ የሚግርገመኝ መቼ ነው እውትኝኛ የክርስትና ህይወት የምንኖረው የፍቅር የሰላም እያችለ እናት ቤተ ክርስቲንያ ትብሰካለች ልጆችዋ ግን አይፋቀሩም ።ወይስ የግድ ግራኝ መሀመድ ይምጣ ለምንድነው ሰው ሁሉ ብሔርተኛ የሆነው በቤትክርስቲያን ያለው ሁሉ እኮ ክርስይንያ ስህሆነ ነው

 24. senay April 25, 2016 at 4:55 am Reply

  በትግራይ ህዝብ ላይ የስም ማጥፋት ወንጀል እየፈጸማችሁ ነው። ትግሬ ትግሬ እያላችሁ ከገጸ ምድር ለማጥፋት ዘመቻ ይዛችኌል። ግን የትግራይ ህዝብ ቤተክርስቲያንን ለኢትዮጵያ ያስረከበ የሃይማኖት ና የቅድስናችሁ መሰረት ነው ትግሪኛ ተናጋሪዎች በቤተ ክርስቲያን ብታዩም እነሱ ከርስቲያኖች ሰለሆኑ ነው ታድያ እነኚህ ክርስቲያኖች ወዴት ይሂዱ የክርስቲያኖች አምላክ እንዳይቆጣባችሁ አስቡበት

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: