ፓትርያርኩ: የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን “ቀንደኛ ሌባ” አሉት፤ አማሳኝ አጋሮቹ “አእምሯቸውን እናስተካክላለን” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል ደጅ እየጠኑለት ነው

 • በሕመምተኛ ልጁ ሕክምና ስም በርካታ አጥቢያዎች በ፻ሺሕዎች እያወጡ በሰጡበት ኹኔታ፥ እኔ ሳላውቅ ስሜን ለማስጠፋት የተሠራ ነው በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል እየጣረ ነው
 • ግማሽ ሚሊዮን ብር እንዲሰጠው የተወሰነበት የእንጦጦ ኪዳነ ምሕረት አስተዳደር ኮሚቴ ውሳኔ ቃለ ጉባኤ፣ በአስተዳደራዊ ውሳኔ ተሽሮ ውሳኔውን በሚያስተባብል ሌላ ቃለ ጉባኤው እንዲቀየር ሓላፊዎቹን አስገድዶ ነበር
 • ድጋፉን የሰጠነው ተዋቅሮ በተላከ ኮሚቴ በተጠየቅነው መሠረት ነው፤ ያሉት ዐሥር የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባላት ትእዛዙን ባለመቀበላቸው በየማነ ከሥራና ከደመወዝ ታግደው ነበር
 • የእገዳ ርምጃውንና አጠቃላይ ኹኔታውን ከገዳሙ ሓላፊዎች ያዳመጡት ፓትርያርኩ፥ እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችኹ ሲሉ ገሥጸው ጉዳዩ በአስቸኳይ እንዲጣራ አዘዋል
 • በሥራ አስኪያጅነት ሥልጣኑ አጥቢያዎችን በማስፈራራት ከብር 3 ሚሊዮን በላይ የሰበሰቡለት አማሳኝ አጋሮቹ፥ እርሱ አያውቅም፤ ከግል ገንዘባችን ነው የረዳነው” በሚል ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳንና ምዝበራውን ለማስተባበል ልዩ ጽ/ቤታቸውን ደጅ እየጠኑለት ነው
 • “እገሌንና የእገሌን ልጅ አሳክመናል፤ ከኪሳችን እንጂ ከሙዳየ ምጽዋት አልነካንም፤” የሚሉት አማሳኞቹ፥ “የቅዱስነታቸውን አእምሮ እንቀይራለን” በሚል ጉዳዩን ለማዳፈን ይንቀሳቀሳሉ

*               *               *

(አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፰፻፵፭፤ ቅዳሜ መጋቢት ፲፯ ቀን ፳፻፰ ዓ.ም.)(ቃለ ጉባኤውን ከዜናው በታች ይመልከቱ)

His Holiness warning the GM Yemane
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ለልጃቸው ሕክምና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑላቸውን የእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ዐሥር የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን ከሥራና ከደሞዝ ያገዱ ቢኾንም ፓትርያርኩ እግዱን ሽረውታል፡፡

ሥራ አስኪያጁ፣ “ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ” በሚል ገንዘብ በማሰባሰብ ላይ እንደነበሩ መዘገቡ የሚታወስ ሲኾን፤ ከእንጦጦ ሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ብቻ ግማሽ ሚሊዮን ብር በገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ እንዲሰጣቸው ቢወሰንም፤ የገዳሙ ሒሳብ ሹም ክፍያውን አልፈጽምም በማለታቸው ውዝግብ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በሥራ አስኪያጁ እግድ ተላልፎባቸው የነበሩት የአስተዳደር ኮሚቴ አባላት፣ ሥራ አስኪያጁ ከትላንት በስቲያ፣ መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም. በጽ/ቤታቸው ጠርተዋቸው፣ “ስሜን ለማስጠፋት እኔ ሳላዛችኹ ኾን ብላችሁ የሠራችኹት ነው፤” በሚል ግማሽ ሚሊዮን ብር ለመስጠት የወሰኑበትን ቃለ ጉባኤ ውሳኔውን በሚያስተባብል አስተዳደራዊ ውሳኔ ሽረው ቃለ ጉባኤን እንዲቀየሩ እንዳዘዟቸው ይናገራሉ፡፡

በሥራ አስኪያጁ ዕውቅና ተዋቅረው ከተላኩት የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴዎቹ ሦስቱ መጥተው በጠየቁት መሠረት መኾኑን በመጥቀስ በተለይ የገዳሙ አለቃ በስተርጅና እንደማይዋሹና ኹለት ቃል እንደማይናገሩ በማስረዳት፣ የሥራ አስኪያጁን፥ “ውሳኔያችኹን በውሳኔ አስተባብሉ’’ ትእዛዝ ባለመቀበላቸው፤ “በስሜ አጨብርብራችኋዋል፤ እኔ ይሰጠኝ ብዬ አላዘዝኩም፤ ሒሳብ ሹሟ ክፍያውን አልፈጽምም ማለታቸው ትክክል ናቸው፤ ልታግዷቸው አይገባም ነበር፤” በማለት ኹሉንንም ከሥራና ከደመወዝ ማገዳቸውን እንዳሳወቋቸው ገልጸዋል፡፡

“ሥራ አስኪያጁ እገዳውን ካስተላለፉብን በኋላ የታገድንበትን ደብዳቤና የገንዘብ ድጋፉን የወሰንበትን ቃለ ጉባኤ ይዘን ቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በመግባት አስረዳናቸው፤” ያሉት የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት፣ የገንዘብ ድጋፉን ስለሰጡበት ኹኔታና ስለ እግዱ የሚከተለውን ብለዋል፡-

“የሲ.ኤም.ሲ ቅዱስ ሚካኤል አለቃ፣ የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም እና የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ጸሐፊዎች መጥተው አዋጡ አሉን፤ ባናዋጣ እንደምንባረር ዛቱብን፤ ትባረራላችሁ፣ ርምጃ እንወስድባችኋለን ሲሉን እኛ ምን እናድርግ? ወደን አይደለም፤ ከሥራችን እንባረራለን፤ ከደረጃችን እንወርዳለን፤ ማን የሚሰማን አለ? ሰበብ ፈጥሮ ነው የሚያግደን፤ ፍትሕ የሚሰጠን አጥተን ነው ይህን ያደረግነው፤ ሒሳብ ሹሟን፥ እነርሱን አግጄ ወደ ሥራ እመልስሻለሁ ብሎ በማለሳሰለስ እኛን ኹላችንን አገደን፡፡”  

ፓትርያርኩ፣ “ገንዘቡ በትክክል ወጥቷል ወይ?” ብለው የጠየቋቸው ሲኾን እነርሱም፥ “አዎ፣ አሰባሳቢ ኮሚቴዎች መጡ፤ አግዙን ብለው ጠየቁን፤ እንዲሰጥ ተፈራርመን ወሰንን፤ እኛ ማወራረድ ስላለብን ቸግሮን በቃለ ጉባኤ ተፈራርመን ሰጠነው እንጂ ሌሎቹ አጥቢያዎች በእጁ አይደለም ወይ ያለሰነድ የሰጡት፤” በማለት ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል፡፡

አቤቱታውን ያዳመጡት ፓትርያርኩ፤ የሀገረ ስብከቱን ሥራ አስኪያጅና የገንዘብ ርዳታ የወሰኑትን አቤቱታ አቅራቢዎች፣ “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችሁ፤ እኔ ታምሜአለሁ ብላችሁ 500 ሺሕ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ነው ወይ? ገመናችሁ ባይወጣ ስትሞካከሹ ትኖሩ ነበር፤” በማለት መገሠጻቸው ተነግሯል፡፡

እገዳውን በተመለከተም፣ “ማን ላይ ነው ጨዋታ የሚጫወተው፤ እርሱ ንጹሕ መስሎ እናንተን ሕግ ተላላፊ ለማድረግ አይችልም፤” በማለት በአስቸኳይ እገዳው ተነሥቶላቸው ወደ ሥራቸው እንዲመለሱና ጉዳዩም እንዲጣራ በልዩ ጽ/ቤታቸው በኩል ለሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ ትእዛዝ መስጠታቸው ታውቋል፡፡

ጉዳዩ የብዙዎች መነጋገርያ ከመኾን አልፎ በፓትርያርኩ ተግሣጽና ውሳኔ ክፉኛ መረበሹ የተነገረለት የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ባለፈው ቅዳሜ ረፋድ አማሳኝ አጋሮቹን በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ በመጥራት፣ እርሱ ሳያውቅ ከየግላቸው እንደተሰበሰበና የአጥቢያዎቹ ገንዘብ እንዳልተነካ በማስመሰል የሚያስረዱ አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ ወደ ፓትርያርኩ መላኩ ተገልጿል፡፡

Yemane with parish heads
“እኛ የኃይሌን[ኃይሌ ኣብርሃ] ልጅ ሌላም አሳክመናል፤ ግን ከራሳችን ከግል ገንዘብ ነው፤ ለእርሱም ያደረግነው ይኼን ነው፤ እርሱ ግን አያውቅም፤”
በማለት፣ ሕጋዊነት ሳይኖራቸው ቁጥጥር የማይደረግበትን ገንዘብ በሕክምና ድጋፍ ስም በማሰባሰባቸው ከሚከተላቸው ተጠያቂነት ራሳቸውን ለማዳንና ሥራ አስኪያጁም በሚሊዮኖች የመዘበረበትን አካሔድ ለማስተባበል የፓትርያርኩን ልዩ ጽ/ቤት ደጅ በመጥናት ላይ መኾናቸው ተመልክቷል፡፡ “ከኪሳችን የመርዳት ልምድ ስላለን ቅዱስነታቸውን አግኝተን አእምሯቸውንና አመለካከታቸውን ማስተካከል አለብን፤” በሚል ተግሣጻቸውን ለመመለስና ለመቀየር ማቀዳቸው ታውቋል፡፡

ከአሰባሳቢ ኮሚቴው አባላት፡- የገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የሲ.ኤም.ሲ ቅዱስ ሚካኤል፣ የመካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል፣ የሳሪስ ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ የጀሞ ቅድስት ሥላሴ፣ የገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ የጻድቁ አቡነ አረጋዊና ገብረ ክርስቶስ፣ የደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ አለቆች፤ የሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም አለቃና ጸሐፊ፤ የብሔረ ጽጌ ቅድስት ማርያም አለቃና ሒሳብ ሹም፤ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ዑራኤል አለቃና ተቆጣጣሪ፤ የብሥራተ ገብርኤል ጸሐፊና ሒሳብ ሹም፤ የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም፣ የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሩፋኤልና የደብረ አሚን ጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ጸሐፊዎች ይገኙበታል፡፡

*               *               *

Entoto KidaneMihiret Admin
የሐመረ ኖኅ ኪዳነ ምሕረት ገዳም አስተዳደር ኮሚቴ የስብሰባ ቃለ ጉባኤ
የስብሰባ ቀን፡- 25/06/2008 ዓ.ም.
የስብሰባ ቦታ፡- በገዳሙ አስተዳደር ቢሮ
የስብሰባ ሰዓት፡- ከቀኑ 3፡00 ጀምሮ
ተሰብሳቢ አባላት
 1. ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል – የገዳሙ አስተዳዳሪና የጉባኤው ዋና ሰብሳቢ
 2. ክቡር በኵረ ትጉሃን ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር – የገዳሙ ምክትል አስተዳዳሪና የጉባኤው ምክትል ሰብሳቢ
 3. መልአከ ፀሐይ አባ ቀለመ ወርቅ አዳሙ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
 4. መ/ር አባ ማቴዎስ ከፍያለው – የገዳሙ አስተዳዳር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
 5. አባ ገብረ ትንሣኤ ብሬ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
 6. ሊቀ ጠበብት ተከሥተ ብርሃኑ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
 7. መሪጌታ ፍሬ ስብሐት አለነ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
 8. መሪጌታ አክሎግ ደሴ – የገዳሙ አስተዳደር ጉባኤ አባል – የጉባኤው አባል
 9. መዘምር አብርሃም አንዳርጌ – የገዳሙ አስተዳደር ኮሚቴ አባል – የጉባኤው አባል
 10. ቀሲስ ዘነበ ብርሃኑ – የገዳሙ ዋና ጸሐፊ – የገዳሙ ጸሐፊ ኾነው በተገኙበት ስብሰባ ተደርጓል፡፡

የዕለቱ ጉባኤ በጸሎት ተከፈተ፡፡ የዕለቱን ስብሰባ አጀንዳ ክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል የገዳሙ አስተዳዳሪና የጉባኤውም ሰብሳቢ ለጉባኤው አባላት ሲያስረዱ፤ ክቡር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ልጃቸውን ለማሳከም ይችሉ ዘንድ ቀደም ሲል ለዚኽ ዓላማ የተዋቀሩ ኮሚቴዎች መጥተው ድጋፍ እንድናደርግ ጠይቀውን ሳለ እስከ አኹን በኛ በኩል የአዎንታም ኾነ የአሉታ መልስ ያልሰጠን ሲኾን ሌሎች ገዳማትና አድባራት ግን ቀድመውን ለዚኽ ዓላማ የተቻላቸውን የሰጡ ስለኾነ እኛም ይህንኑ መሠረት አድርገን ከሌሎች ገዳማትና አድባራት መለየት የሌለብን በመኾኑ በዚኽ ዙሪያ በጋራ ተመካክረን የተቻለንን ድጋፍ ለክቡር ሥራ አስኪያጅ ለልጃቸው ማሳከሚያ የሚውል ድጋፍ ማድረግ በምንችልበት ዙሪያ በጋራ መክረን አንድ ውሳኔ ላይ መድረስ እንድንችል የተደረገ ስብሰባ ነው፤ ሲሉ ሰብሳቢው ለጉባኤው አባላት በማስረዳት ጉባኤያቸውን አጠቃለዋል፡፡

የጉባኤው አባላትም ከክቡር ሰብሳቢው የተሰጠውን አጀንዳ ገለጻ በጽሞና ከማድመጥ በመነሣት በመሠረተ ሐሳቡ ዙሪያ ጉባኤው ሲመክር፣ አኹን ላይ የቀረበው አጀንዳ ተገቢነት ያለው መኾኑ ቢታመንም ከተጠየቀበት ጊዜ አንሥቶ እስከ አኹን መዘግየቱ ተገቢ አለመኾኑን ጉባኤው የተቸ ሲኾን ያም ኾነ ይህ አነሰ በዛ የሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ በወቅቱ ይደረግ እንኳ ቢባል በሰዎች እጅ መላኩ ጥርጣሬ ውስጥ በመገባቱ የተነሣ ነገ ዛሬ ሲባል ሊዘገይ እንደቻለ የጋራ ግንዛቤ ተወስዶ ያም ኾነ ይህ አኹንም ቢኾን ድጋፍ ካደረጉ ከሌሎች ገዳማትና አድባራት እኛ መዘግየታችን ቢታመንም ድጋፍ ማድረጉ የረፈደ ስለማያሰኝ የገዳማችን ታላቅነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ ታይቶ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅ በጉባኤው አጠያያቂ ኾኖ አልተገኘም፡፡

ስለኾነም ለዚኽ ለተቀደሰ በጎ ዓላማ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ የተገባ መኾኑ ታምኖ ለክቡር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለታማሚ ልጃቸው ማሳከሚያ ይረዳቸው ዘንድ ዓላማውም የሰውን ፍጡር የማዳን በጎ ምግባር ስለኾነ ከገዳሙ ገቢ ላይ ብር 500‚000(አምስት መቶ ሺሕ) ወጪ እንዲመደብ ኾኖ ከዚኹ ውስጥ ብር 300‚000(ሦስት መቶ ሺሕ) በገዳሙ ስም፤ ቀሪው ብር 200‚000(ኹለት መቶ ሺሕ ብር) ደግሞ በገዳሙ ሠራተኞች ስም ተሰይሞ ለክቡር ሥራ አስኪያጅ በክቡር ሊቀ ሊቃውንት ቆሞስ አባ ገብረ ማርያም ገብረ መስቀል የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪና የጉባኤው ሰብሳቢ እጅ እንዲያደርሱ ሲል ጉባኤው ሙሉ ሓላፊነት በመስጠት ልዩነት በሌለው ድምፅ ወስኖ የዕለቱን ስብሰባ 4፡30 ሰዓት በጸሎት ዘግቶ ፈጽሞ ተነሣ፡፡

የዋና እና የምክትል ሰብሳቢውን ጨምሮ የዐሥር የአስተዳደር ኮሚቴው አባላት የማይነበብ ፊርማ አለው

Advertisements

30 thoughts on “ፓትርያርኩ: የማነ ዘመንፈስ ቅዱስን “ቀንደኛ ሌባ” አሉት፤ አማሳኝ አጋሮቹ “አእምሯቸውን እናስተካክላለን” በሚል ምዝበራውን ለማስተባበል ደጅ እየጠኑለት ነው

 1. Anonymous March 28, 2016 at 6:46 am Reply

  የማነ ዘመንፈስቅዱስ ቤተክርስቲያንን ሳይበትን እሱ ቤተክርስቲያንን የሚለቅ አይመስልም። እግዚአብሄር ይየው።
  ጸልዩ።

  • fekadu gebere March 28, 2016 at 11:57 am Reply

   በቤተ መቅደስ ቁጭ ብለው የሚነግዱትን ሙሰኞችን:
   ቤተክርስትያንን የሚጠቅሙ እየመሰሉ የሚያራቁቱትን.
   ይሁዳዊ አሰራር የሚሰሩትን አማሳኞች እግዚአብሔር ን
   ሳይፈሩ ; ጥሩ እየሰራን ነው የሚሉ በእውነት እግዚአብሔር ዝም የሚል ይመስላችኋል ቀን አለው ዝም
   አይልም ይፈርዳል ይመነጥራል ስንዴው ከገለባው እንደሚለይ ሁሉ።በግፍ የተኮነኑትም ነጻ ይወጣሉ። ግን
   በፍቅር ሆነን በመጸለይ ታሪክ መቀየር ይቻላል።
   እንጸልይ እንበርታ በፍቅር ለቤተክርስታንያችን.
   ሮሜ ፩፪÷፩ ወንድሞቻችን ሰውነታችሁን ለእግዛብሄር ሕያውና ቅዱስ ደስ የሚያሰኝም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኀራኄ እማልዳችኋለሁ ይህም በእውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።፪
   ይህን አለም አትምሰሉ ልባችሁንም አድሱ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን ፥ፍጹሙንም መርምሩ።
   ሰለዚህ መጻህፍት እንዱህ ካለን ልናስተውል ያስፈልጋል ማለት ነው እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!!!!@

  • Anonymous March 28, 2016 at 12:00 pm Reply

   በቤተ መቅደስ ቁጭ ብለው የሚነግዱትን ሙሰኞችን:
   ቤተክርስትያንን የሚጠቅሙ እየመሰሉ የሚያራቁቱትን.
   ይሁዳዊ አሰራር የሚሰሩትን አማሳኞች እግዚአብሔር ን
   ሳይፈሩ ; ጥሩ እየሰራን ነው የሚሉ በእውነት እግዚአብሔር ዝም የሚል ይመስላችኋል ቀን አለው ዝም
   አይልም ይፈርዳል ይመነጥራል ስንዴው ከገለባው እንደሚለይ ሁሉ።በግፍ የተኮነኑትም ነጻ ይወጣሉ። ግን
   በፍቅር ሆነን በመጸለይ ታሪክ መቀየር ይቻላል።
   እንጸልይ እንበርታ በፍቅር ለቤተክርስታንያችን.
   ሮሜ ፩፪÷፩ ወንድሞቻችን ሰውነታችሁን ለእግዛብሄር ሕያውና ቅዱስ ደስ የሚያሰኝም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኀራኄ እማልዳችኋለሁ ይህም በእውቀት የሚሆን አገልግሎታችሁ ነው።፪
   ይህን አለም አትምሰሉ ልባችሁንም አድሱ እግዚአብሔር የሚወደውን መልካሙንና እውነቱን ፥ፍጹሙንም መርምሩ።
   ሰለዚህ መጻህፍት እንዱህ ካለን ልናስተውል ያስፈልጋል ማለት ነው እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለን አሜን!!!!!@

 2. Anonymous March 28, 2016 at 8:03 am Reply

  Betam yemigremew ewnte leju tamobte kehone yemhrte gets Egziabhyre hono sale kebetu bgef gnzeb sebsebona zerfo dehnte Endyte yegegnal Almtadel endezi newe

 3. ገ/እግዚአብሔር March 28, 2016 at 8:24 am Reply

  እኔ የማይገባኝ ነገር ጋዜጠኛ ለቤ/ክ ሥራ አስኪያጅነት እንዴት ሊመረጥ ቻለ? ያውም ለአ/አ ሀገረ ስብከት የትግርኛ ጋዜጠኛ ተፈልጎ ተቀጠረለት፡፡ ይህ ቀልድ መፍትሄ እንደማያጣ አትጠራጠሩ፡፡ ………. መልሱም ሁሉን አቀፍ ይሆናል፡፡

 4. hagos March 28, 2016 at 9:56 am Reply

  You will see….. this is a drama since the issue comes into the public. At the end of the day, he will be rewarded by the patriarch himself.

 5. Mareta March 28, 2016 at 10:24 am Reply

  “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችሁ፤ እኔ ታምሜአለሁ ብላችሁ 500 ሺሕ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ነው ወይ? ገመናችሁ ባይወጣ ስትሞካከሹ ትኖሩ ነበር፡፡

 6. Mareta March 28, 2016 at 10:25 am Reply

  “እርሱ ቀንደኛ ሌባ ነው፤ እናንተም ሌቦች ናችሁ፤ እኔ ታምሜአለሁ ብላችሁ 500 ሺሕ አውጥታችሁ ልትሰጡኝ ነው ወይ? ገመናችሁ ባይወጣ ስትሞካከሹ ትኖሩ ነበር፤” በማለት መገሠጻቸው ተነግሯል፡፡

 7. Anonymous March 28, 2016 at 10:34 am Reply

  I feel very sorry for our church. abatoch yehin aynet asafari sira yemiseru kehone bewnet we don’t have religion malet nw. E/her mechereshawun yasamirilin.

 8. Tiruwork Abera March 28, 2016 at 10:36 am Reply

  አሁንም የድንግል ልጅ ያጋልጣቸው! የዚህ የድሃ ሕብረተሰብ የደም ገንዘብ እውነቱን አሁንም ያውጣ! በአጠቃላይ እሱ የሾማቸው የቤተክርስቲያን ጠላቶች፣ የአይሁድ ወገኖች ናቸው! እመብርሃን አሁንም ታጋልጣቸው ጉዳቸውን እንዲህ ታውጣው!!! ለሁሉም በትጋት እንፀልይ የቤተክርስቲያን ሰዎች መስለው ቤተክርስቲያንን የሚመዘብሩ! ምርጥ ምርጥ አማሳኞች!!! አቤቱ ጌታሆይ አንተ እውነተኛ ዳኛ ነህ አትዘግይ! ታምራትህን አሳይ!!!

 9. Anonymous March 28, 2016 at 10:39 am Reply

  Diros kemusegna ena kemusegna tebabari min yetebekal!

 10. Anonymous March 28, 2016 at 10:40 am Reply

  Yeweyanie Gazietegna Diros !!!

 11. dereje megerssa March 28, 2016 at 11:27 am Reply

  ፓትርያርኩ የማነን ገሰፁ ምናምን የሚባለው ጠብ የፉገራ ፌክ እንደሆነ ማንም ያውቀዋል፡፡ ዐሁን ይቺ ምስጢር ስለዎጣች በሰው ፊት ቅሌታቸውን የመሸፋፈን ስራ እየሰሩ ነው፡፡ ፓትርያርኩ ሙስና ለማጥፋት ተባበሩኝ ብለው የተጠናውን ዘመናዊ የአሰራር መመሪያ ገደል ከተው የሙስናውን ጌታ ሾሙት፡፡ ከዚያም ጥናት ይሰራ ተብሎ የሙስናዉን ግዝፈት የሚሳይ ዝርዝር ጥናት ሲቀርብላቸው ባስቸኩዋይ ይተግበር አሉ፡፡ ዐሁን ያንን ነገር እንዳይነሳ ተብሎ በጀርባ በኩል መመሪያ የተሰጠ በሚመስል ደረጃ ሆን ተብሎ እንዲረሳ እየተደረገ ነው፡፡ የውሾን ነገር ያነሳ ውሾ ነው ሆነ ነገሩ፡፡ ይሄም የአንድ ሰሞን ቅሌትን ከህዝብ ፊት ሸፋፍኖ የመውጫ መንገድ እንጂ በቁምነገር የሚወሰድ አይደለም፡፡ እኛም አውቀናል ጉድገዋድ ምሰናል እነዳለችው አይጥ…..በዚህ ማንንም ማታለል አይቻልም፡ መድሃኔዓለም ግን በቤቱ ላይ የሚቀልዱት ላይ ጅራፍ ማንሳቱ አይቀርምና ለዚያ ተዘጋጁ፡፡

  • ትዕግስቱ መገራ March 29, 2016 at 3:53 am Reply

   አባ ማቲያስ ይህችን ሙድ እዚያዉ ያድርጏት፤፤ወሬ ብቻ እንደሆኑ ድፍን ኢትዮጵያዊ ና እርስዎም ያዉቇታል፤፤እኔን አሁን የሰለቸኝ የእርስዎ ወሬ ነዉ፤፤ You are doing this to build your public image. You have lost it already

 12. Anonymous March 28, 2016 at 11:28 am Reply

  ወይ ጉድ በመጀመሪያ እነዚህ ሌቦች ብሩን ከራሳችን ኪስ ሲሉ አያፈሩም እነሱ በየትኛው ገቢያቸው ነው ወይ አለማፈር እንደው ስወ ይታዘበናል አይሉም እግዚአብሄርን ባይፈሩ ፍጥጥ ያለ ሌብነት እገዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ .አንተ ደግሞ የማነ የምትባል ስው ምን አይነት ሰይጣን የሰፈረብህ ስው ነሀ የህዝብ ገነዘበ እየበላህ ልጅህን እገዚአብሄር እንዳይነጠቅህ እንዳተ ስራ እማ ቢሆን ………..

 13. mekdes March 28, 2016 at 11:32 am Reply

  ወይ ጉድ በመጀመሪያ እነዚህ ሌቦች ብሩን ከራሳችን ኪስ ሲሉ አያፈሩም እነሱ በየትኛው ገቢያቸው ነው ወይ አለማፈር እንደው ስወ ይታዘበናል አይሉም እግዚአብሄርን ባይፈሩ ፍጥጥ ያለ ሌብነት እገዚአብሄር ይቅር ይበላችሁ .አንተ ደግሞ የማነ የምትባል ስው ምን አይነት ሰይጣን የሰፈረብህ ስው ነሀ የህዝብ ገነዘበ እየበላህ ልጅህን እገዚአብሄር እንዳይነጠቅህ እንዳተ ስራ እማ ቢሆን ………..

  • Anonymous March 28, 2016 at 1:46 pm Reply

   Abatachin abune Mathias , melkam mesrat gudatun yingerugn ? ? ?………lela malte silemalchil .

 14. Anonymous March 28, 2016 at 2:02 pm Reply

  ምንም አይመጣም ዝርፊያው ይቀጥላል፡፡ አባ ማትያስ ለሙድ ነው ቀንደኛ ሌባ ብለው የተናገሩት፡፡ ቤተክርስቲያኗ ዘራፊና አዘራፊ እረኛ እንጅ መቸ ጠባቂ አባት አላትና! የማነን ማን ነክቶት፤ በጌታዋ የምትተማመን በግ ላቷን ዘብ ታሳድራለች ይባላል እኮ፡፡

 15. anonymous March 28, 2016 at 3:29 pm Reply

  He knows the collection of money in his name. I know he is money lover. He is here to collect money. He is permitted to do it.

 16. Anonymous March 28, 2016 at 4:13 pm Reply

  NIGIST ADES EBALHU seshom yalibela seshar ykochewal y balal adel hulum silitann meketa bemadireg new ymesraw gin egzeabher libona sitachew l ijun egzeabher ymarew.

 17. ትዕግስቱ መገራ March 29, 2016 at 4:00 am Reply

  አባ ማቲያስ ይህችን ሙድ እዚያዉ ያድርጏት፤፤ወሬ ብቻ እንደሆኑ ድፍን ኢትዮጵያዊ ና እርስዎም ያዉቇታል፤፤እኔን አሁን የሰለቸኝ የእርስዎ ወሬ ነዉ፤፤ የአቡነ ቀለምንጦስን ስልጣን ሸረዉ ይህንን ሙሰኛ የሾመዉ ማን ነዉ፤፤ በዘር ነው ይህንን ሙሰኛ ፖለትከኛ አምጥተዉ የሾሙት

 18. Rosa Gadme March 29, 2016 at 5:22 am Reply

  O Yemane,,,,Bergit Ewente new? Sorry Pls neseha geba

 19. ፋንታሁን ሲራታ March 29, 2016 at 9:10 am Reply

  እኔ የሚገርመኝ አባ ማቲያስ ና የማኔ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ዘርፈዋል ብሎ ሌላውን አካል ስከሱ አልነበረም? ከኪሳቸው አዋጣንለት የሚሉት እነሱ ምልዬነር የንሆኑት ከዬት አምጥተው ነው ? ልታዩ ይገባል። የአባ ማቲያስ ግሣጸም አሉ እንዲባልላቸው ነው እንጂ ቁም ነገር የለውም ። ማን ማንን ይገሥጻል።

 20. emihertab March 29, 2016 at 7:08 pm Reply

  ምናልባት የማነ እርግጥ በልጁ መታመም ጨንቆት ሊሆን ይችላል፤ በዚህ ዓይነት የተበላሸ ህይወት የገባው፡፡ ምንም ቢሆን ግን ምህረትንና ጤንነትን ፈጣሪ እንደምሰጥ አውቆ በታማኝነት ቢያገለግል ለእርሱም ለቤተክርስትያንም መልካም ነበር፡፡ ግራ የሚገባኝ ግን በርካታ የቤተክርስትያን አስተዳዳሪዎች መነኮሳት ናቸው፡፡ መነኮሳት ሚስትና ለጅ የላቸውም፡፡ ለማን ነው ታዲያ ገንዘብ የሚያጠረቅሙት? ትተውት በባዶ ሜዳ የሚሄዱትን ገንዘብ ባይሰበስቡ መልካም ነበር፡፡ አባ ማትያስም ታሪካዊ ስህተት በቤተክርስትያን ላይ ባይሰሩ መልካም ነው፡፡ እኛ ምዕመናን የቤተክርስትያንን ሰላምና ዕልውና እንደመፈለጋችን መጠን ተግተን ልንጸልይ፣ የቤተክርስትያንን ትምህርትም ጠንቅቀን ለንማርና ልናስተምር ይገባል፡፡

 21. john March 30, 2016 at 8:20 am Reply

  እኔ የሚገርመኝ አባ ማቲያስ ና የማኔ የቤተ ክርስቲያንን ገንዘብ ዘርፈዋል ብሎ ሌላውን አካል ስከሱ አልነበረም? ወይ ጉድ በመጀመሪያ እነዚህ ሌቦች ብሩን ከራሳችን ኪስ ሲሉ አያፈሩም እነሱ ከኪሳቸው አዋጣንለት የሚሉት እነሱ ምልዬነር የንሆኑት ከዬት አምጥተው ነው ? ልታዩ ይገባል።

 22. Sara Sara March 31, 2016 at 8:16 am Reply

  በመጀመርያ እሱ ጋዜጠኝ ነው ማነው ይህንን ሥልጣን የሠጥው?በእግዚአብሔር ቤትመቅደስ ቁጭ ብለው የሠይጣንን ስራ የሚሠሩ የይሁዳ ዘሮች እግዚአብሔር የማይፈሩ ሰውን የማያፍሩ ልብ ይስጣቸው ።
  በጣም በጣም የሚገርመው በአለም ውስጥ እንደ ቤተክርስትያን ውስጥ ግፍ፡ሙስና ፡ዘረኝነት፡ሌብነት የለም በጣም የከበደው ቤተ/ክ ነው ።
  እግዚአብሔር ያዘገያል እንጂ የሚቀድመው የለም
  እውነት የአለም መድሀኔት መድሀኔ አለም ይፈርዳል ።

 23. Anonymous April 1, 2016 at 2:12 am Reply

  እባካችሁ አባቶች ማስተዋል እግዚአብሔር የሰጣችሁ ለጠፋን ለኛ ፀልዩልን አምላክ እንዲቀርበን አሜን.

 24. zeleke April 28, 2016 at 9:24 am Reply

  I Yemane genzeb mewudedih bemider lijihn na sigahen, besemay nefisihn Yakatilal. Tinant kibur abatacin tibal neber. zare degmo kendegna leba. Negese? E/r bete kirstiyanachinn begun sayhon debelowun kelbesut Yyadgilen.

 25. zeleke April 28, 2016 at 9:35 am Reply

  gin eko seytan Tibebegna new. sint kale E/R bemnmarbt werkama giza yenanten asafari tegibar asinebeben. ene Ymilewu Yemtasitemrut na Ymitsbkut wengel enanten aymelektime ende? >

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: