ሰበር ዜና – የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: በኑፋቄ ተግባር ያገኘውን ደቀ መዝሙር አባረረ፤ የሦስት ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ጉዳይ እየታየ ነው

 • ውሳኔውን፥ በሽምግልና፣ በዛቻና በማስፈራራት ለመቀልበስ እየተሯሯጠ ነው

PPPየሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፥ ከኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርት፣ ሥርዐትና ትውፊት ውጭ ኑፋቄን ሲያስፋፋና ሲተገብር በተጨባጭ አግኝቸዋለኹ፤ ያለውን አንድ ደቀ መዝሙር ከኮሌጁ ማሰናበቱ ተገለጸ፡፡

ከፍ ያለው ቱፋ የተባለው ግለሰብ፣ በቀን ተመላላሽ የሦስተኛ ዓመት ሰሚነሪ ደቀ መዝሙር ሲኾን፤ በኮሌጁ ውስጥ በኅቡእ ኑፋቄን ሲያስፋፋና በቅጥረኛነትም ከኮሌጁ ወደ መናፍቃን ጎራ አንዳንድ ደቀ መዛሙርትን እየመለመለ ሲቀሥጥና ሲያስኮበልል መቆየቱ ተጠቅሷል፡፡

በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የሚመራ፥ የአስተዳደር፣ የመምህራንና የደቀ መዛሙርት መማክርት ጉባኤ÷ መጋቢት 16 ቀን ባካሔደው ስብሰባ፣ የመናፍቃን ቅጥረኛ ኾኖ በሚንቀሳቀሰው ደቀ መዝሙር ላይ ሲሰበሰቡ የቆዩ የድምፅ እና የመተማመኛ ማስረጃዎችን ከመረመረና ደቀ መዝሙሩንም አቅርቦ ከጠየቀ በኋላ ከኮሌጁ ጨርሶ እንዲሰናበት ልዩነት በሌለው ድምፅ መወሰኑ ታውቋል- “ከመጋቢት 19 ቀን ጀምሮ በኮሌጁ እስከ መጨረሻው እንዳይማሩ ተሰናብተዋል” ይላል፤ ዛሬ ከቀትር በኋላ ከአስተዳደር ምክትል ዲኑ ቢሮ የወጣው ደብዳቤ፡፡

ተሰናባቹ ከፍ ያለው ቱፋ፣ የደቀ መዝሙርነት መታወቂያውን ለኮሌጁ ሬጅስትራር ክፍል በማስረከብ ኮሌጁን ለቆ እንዲወጣ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው ሲኾን፤ የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲንና የጥበቃ ክፍል ሓላፊ  ውሳኔውን እንዲያስፈጽሙ በደብዳቤው ግልባጭ ትእዛዝ ተላልፎላቸዋል፡፡

በተመሳሳይ አኳኋን፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት፣ የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ርምጃውን በደብዳቤው ግልባጭ እንዲያውቁት ተደርጓል፤ ከ150 በላይ መደበኛ የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜያት፤ የሴሚነሪ እና የቀን ተመላላሽ ደቀ መዛሙርት በተገኙበት፣ ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በኮሌጁ አዳራሽ በተካሔደ ውይይት፤ ደብዳቤው በንባብ ሲሰማ ደቀ መዛሙርቱ ለውሳኔው ያላቸውን ከፍተኛ ድጋፍ ገልጸዋል፡፡

ካለፈው ጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በብፁዕ ሊቀ ጳጳሱ ትእዛዝ በተቋቋመ ኮሚቴ ማስረጃዎቹ ሲሰበሰቡ እንደቆዩ በውይይቱ መግቢያ ተገልጧል፤ የአስተዳደሩ ሓላፊዎች በወቅቱ እንዳስታወቁት፣ “ኮሌጁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተቋም በመኾኑ ከሌሎች አዳራሽ ለመቀላወጥ በሚሔዱና ሲቀላውጡም በተገኙት ላይ ቤተ ክርስቲያን የማያዳግም ርምጃ ትወስዳለች፡፡”

በሌላ በኩል፣ ኮሌጁ የሃይማኖት ሕጸጽ የተገኘባቸውን ተጨማሪ ኹለት ደቀ መዛሙርትና ከፍተኛ የሥነ ምግባር ጉድለት የተገኘበትን አንድ ደቀ መዝሙር ጉዳይ እየመረመረ ሲኾን እገዳን ጨምሮ ቀኖናዊ ቅጣት ሊተላለፍባቸው እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ ከእኒኽም አንዳንዶቹ፣ በኮሌጁ በማታው ክፍለ ጊዜ የሚማሩትን እንደ ዘካርያስ ሐዲስ ያሉ የለየላቸውን አማሳኞች ባካተተ ሽምግልና እንዲኹም፤ በሓላፊዎቹ ላይ በመዛትና በማስፈራራት ውሳኔውን ለማስቀልበስ እየተሯሯጡ እንዳሉም ተሰምቷል፡፡

ለጥንታዊው የአብነት ትምህርት ትኩረት የሚሰጠው አንጋፋው ኮሌጅ፣ በቀንና በማታው ክፍለ ጊዜ ከ800 በላይ ደቀ መዛሙርትን ተቀብሎ በመጻሕፍት ትርጓሜያትና በሴሚነሪ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

*               *               *

ለኮሌጁ መደበኛ ደቀ መዛሙርት በንባብ በተሰማበት ወቅት በድምፅ ተቀርፆ ወደ ጽሑፍ የተገለበጠው የደብዳቤው ይዘት የሚከተለው ነው፤

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ

ቁጥር፡- 899/2/233/08
ቀን፡- 19/07/2008 ዓ.ም.

ለደቀ መዝሙር ከፍ ያለው ቱፋ
አዲስ አበባ፤

ጉዳዩ፡- ከሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተሰናበቱ መኾኑን ስለማሳወቅ

እርስዎ የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በቀን ተመላላሽ የ3ኛ ዓመት የሴሚነሪ ደቀ መዝሙር ሲኾኑ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውጪ የኾነ የኑፋቄ ትምህርት እያስተማሩና እየተገበሩ ያሉ መኾኑን ስለርስዎ የተሰበሰበው ማስረጃ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓ.ም. የኮሌጁ አስተዳደር፣ መምህራንና የተማሪዎች መማክርት ባሉበት የድምፅና የመተማመኛ ማስረጃዎችን ከመረመረ በኋላ እርስዎን አቅርቦ በመጠየቅ ከቤተ ክርስቲያኒቱ ዶግማና ቀኖና ውጪ የኾነ ትምህርት የሚያስተምሩና የሚተገብሩ መኾኑን በኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ የሚመራው ጉባኤ ልዩነት በሌለው ድምፅ አምኖና አረጋግጦ እስከ መጨረሻው እንዲሰናበቱ ወስኗል፡፡

ስለዚኽ በጉባኤው ውሳኔ መሠረት ከመጋቢት 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኮሌጁ እስከ መጨረሻው እንዳይማሩ የተሰናበቱ መኾኑን እየገለጽን ይጠቀሙበት የነበረውን የኮሌጁ የደቀ መዝሙርነት መታወቂያ በዚኹ ዕለት ለሬጅስትራር ክፍል በማስረከብ ኮሌጁን ለቀው እንዲወጡ በጥብቅ እያስጠነቀቅን ጉዳዩንም የኮሌጁ አካዳሚክ ምክትል ዲንና የጥበቃ ክፍል ሓላፊ እንዲያስፈጽሙ በዚኹ ግልባጭ የታዘዘ መኾኑን እናስታውቃለን፡፡

ከመንፈሳዊ ሰላምታ ጋር
ማሞ ከበደ
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ
አስተዳደር ምክትል ዲን

ግልባጭ

 • ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት
 • ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት
 • ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
 • ለመ/ፓ/ጠቅ/ጽ/ቤት የትምህርትና ማሠልጠኛ መምሪያ
 • ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት
 • ለኮሌጁ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ

አዲስ አበባ

Advertisements

18 thoughts on “ሰበር ዜና – የሰዋስወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ ኮሌጅ: በኑፋቄ ተግባር ያገኘውን ደቀ መዝሙር አባረረ፤ የሦስት ተጨማሪ ደቀ መዛሙርት ጉዳይ እየታየ ነው

 1. Anonymous March 28, 2016 at 3:28 pm Reply

  በጣም ወሳን መረጃ

 2. Anonymous March 29, 2016 at 2:29 am Reply

  የዘመኑ ኑፋቄ አራማጆቼ ተሀድሶ ያልገቡበት የለምና ሁላችንም ይህችን ቤተ ክርስቲያን ለመጠበቅ ሀላፊነት አለብን

 3. Anonymous March 29, 2016 at 3:41 am Reply

  ገና ይቀጥላል!

 4. እየሱስ ጌታ ነው March 29, 2016 at 4:51 am Reply

  ይኤኔ መዳን በክርስቶስ ነው ብሎ ነው። አድለኛ ነው ለዚህ ክብር ስለበቃ። ተሀድሶ ለቤተክርስቲያናችን።

  • ዳሞት March 30, 2016 at 4:55 pm Reply

   ለእየሱስ ጌታ ነው
   ጅብ የማያውቁት ሀገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ
   አቶ ወይም ወይዘሮ፦ ለመሆኑ “እየሱስ ጌታ ነው” ማለት መፈክር ነው ወይስ አዝማች ነው? ስሙን እንሿን አስተካክለህ መጻፍ ሳትችል መፈክር አዝማች ሆንክ። ኢየሱስ ነው ወይስ “እየሱስ” ነው ትክክል? መጽሐፍ ቅዱስ የአስቀመጠው “ኢየሱስ” በዚህ አይነት ነው። ታዲያ ያንተ “እየሱስ” ከየት መጣ? ከጥልቁ ነው? የአንተ ” እየሱስ” የሰማኸው ከአጋንት ድምፅ ነውን? ኢየሱስ ጌታ ነው ማለትስ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ ማለትስ ምን ማለት ነው? ጌታ ማለት ምን ማለት ነው? መቸም መጽሐፍ ቅዱስ በጩኸት ውከት ኢየሱስ ጌታ ነው በሉ አይልምና ምን ትለው ይሆን?
   አቶ ወይም ወይዘሮ በመፈክር በደረቅ ቃላት ህይወትም ሆነ መዳን የለም! ለመዳን ማመን፤ እምነትንም በሥራ መፈፀም ተገቢና ዋነኛ ነው። አምኖ ያልተጠመቀ አይድንም! ለሥጋ ተግባር ማደለቢያና ከእውነተኛው የመዳኛ መንገድ ማፈንገጫ፤ እንዲሁም ባዶነትን ማለባበሽ ቃላት እየመዘዙ እንደበሽተኛ መዋጋትም ሆነ መፈከር ህይወት አይሆንም፣ መዳን አይገኝበትም።
   አቶ ወይም ወይዘሮ፦ ” ይኼኔ መዳን በክርስቶስ ነው ብሎ ነው” ነው ያልከው። ለመሆኑ መዳን በክርስቶነስ ነው ማለት ምን ማለት ነው? ዝምብሎ መዳን በክስቶስ ነው፤ እንድንበት ዘንድ ከሰማይበታች የተሰጠን ስም ኢየሱስ ነው፤ ወዘተ እያሉ እንደገደል ማሚቶ ማንቧረቅ ነውን? አይምሰልህ! እግዚአብሔር ሰው አይደለምና አይታለልም። እንሿንስ ስሙን መጥራት ይቅርና በስሙ ተራራ ብታገለባብጥ ክርስቶስ እንደፍጡራን አይታለልምና ንቃ። በክርስቶስ መዳን ማለት ክርስቶስ ሰርቶና አድርጎ በማድረግ፣ በቃሉ ትምህርት የነገረንን በመፈፀም እንጂ በስሙ በመነገድ፣ በማጭበርበር፣ በማወናበድ፣ ኢየሱስ ኢየሱስ ወይም ክርስቶስ ክርስቶስ በማለት አይደለም። ሥም በመጥራት ቢሆንማ ኖሮ አባትህ ሰይጣንም በዳነ ነበር! ምክንያቱም እራሱ ሰይጣን ኢየሱስንም ጳውሎስንም አውቀዋለሁ እናንተ ግን ማን ናችሁ በማለት የኢየሱስን ስም ጠርቶታልና ነበር። ክርስቶስን የካዳችሁ ብትሆኑም ቅሉ፤ ታምናላችሁ ቢባል እንሿን መዳን በማመን ብቻ አይቻልም። ምክንያቱም አሰማሪህ ሰይጣንም በማርቆስ 5፥7-8 ባለው ኢየሱስ የልዑል እግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ስሙን በመጥራትና ማዳንም ማጥፋትም የሚችል መሆኑን በመንቀጥቀጥ ያምናል። ግን አይድንም!
   አቶ ወይም ወይዘሮ፦ ከላይ እንድ ርዕስ የተጠቀምኩበት ” ጅብ በማያውቁት አገር ሔዶ ቁርበት አንጥፉልኝ” የሚለው አባባል በትክክል ይገልጥህ ይመሥለኛል። ጅብ አያውቁኝም ብሎ ጠቅልሎ የሚውጠውን ቁርበት አንጥፉልኝ አለ እንደ ተባለው ምሳሌ ሁሉ ፤ አንተ(ች) የማታውቁትን ወንጌል፣ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ በማለት ስም በመጥራት የማያውቁትን ለመንከሥ እንጂ አንዳች እውነተኛ ፍሬ የላችሁምና ነው። በተጨማሪም የሌላ ቤት ሆነህ(ሽ) ቤተኛ መምሰልህ(ሽ) ነው አባባሉን የምትጋሩት።

  • Anonymous April 2, 2016 at 10:50 am Reply

   kale hiwet yasemah

  • Anonymous April 11, 2016 at 9:05 am Reply

   Egzihaber abzeto yebarkhe. yemisema lib lalew tinish neger bekiw new

 5. Anonymous March 29, 2016 at 5:54 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን አባታችን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ረጅም ዕድሜ ይስጥልን፤፤
  የከፍተኛ ትምህርት ተቅዋሙ አመራር አባላት አምላከ ቅዱሳን ሃይልና ጸጋውን ያብዛላችሁ
  በበረከቱ ይጎብኛችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁ የሰመረ ይሁን ፡፡ ጥቃቅን ቀበሮዎችን ማጥመዱ ይቀጥልልን…..
  ይህን የመሰለ ዜና ከቅድሰት ሥላሴ ከፍተኛ ትምህርት ተቅዋም መቼ እንሰማ ይሆን ? ? ? ? ? ? ?

 6. Anonymous March 29, 2016 at 5:56 am Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን አባታችን ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ረጅም ዕድሜ ይስጥልን፤፤
  የከፍተኛ ትምህርት ተቅዋሙ አመራር አባላት አምላከ ቅዱሳን ሃይልና ጸጋውን ያብዛላችሁ
  በበረከቱ ይጎብኛችሁ የአገልግሎት ዘመናችሁ የሰመረ ይሁን ፡፡ ጥቃቅን ቀበሮዎችን ማጥመዱ ይቀጥልልን….
  ይህን የመሰለ ዜና ከቅድሰት ሥላሴ ከፍተኛ ትምህርት ተቅዋም መቼ እንሰማ ይሆን ? ? ? ? ? ? ?

 7. Anonymous March 29, 2016 at 7:01 am Reply

  kesu tadiya lemen asfelege baqi kezehe belaye yet ale ena

 8. Anonymous March 29, 2016 at 7:02 am Reply

  ye MK siraw ewunet slehone gena yiketilal.

 9. Anonymous March 29, 2016 at 9:37 am Reply

  ጅምሩ ጥሩ ነው ገና ብዙ ይቀረዋልና በርቱ

 10. Anonymous March 29, 2016 at 10:00 am Reply

  nice

 11. Anonymous March 29, 2016 at 2:42 pm Reply

  እግዚአብሔር ስራ የሚሰራበት ጊዜ አለው

 12. Anonymous March 30, 2016 at 9:50 am Reply

  እግዚአብሔር ስራ
  ውን የሚሰራበት ጊዜ ነው

 13. Anonymous April 1, 2016 at 9:03 am Reply

  Endeminachihu? kolfe Debre Mitmak K. Philipos yalewun zebut lehulum bete kirstian timihrt yihonlal

 14. zeorthodox April 4, 2016 at 5:33 am Reply

  great!

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: