የማኅበረ ቅዱሳን ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ ቅድመ ዝግጅት ሒደት እውነታዎችና ቀጣይ ወቅታዊ ጥረቶች

 • በታቀደው መርሐ ግብር የማካሔድ ጥረቱ ዛሬም ተጠናክሮ ይውላል
 • ዛሬ ከቀኑ 10፡00 በዋናው ማእከል ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል
 • የዝግጅቱ ቀጣይነት፣ ጊዜና ቦታ የሚታወቀው በሚሰጠው መግለጫ ነው

patriarchate MK Exb approval and Exb logo
ጳጉሜን 5 ቀን 2007 ዓ.ም.
– የማኅበሩ የሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት፣ ማኅበሩ በአራት ዓመት ስትራተጅያዊ ዕቅዱ ያካተተውን የዐውደ ርእይ ልዩ ዝግጅት ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማሳሰቡን በመጥቀስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ እንዲጻፍለት ጠየቀ፤

ጳጉሜ 5 ቀን 2007 ዓ.ም. – የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የዝግጅቱን መካሔድ ፈቅዶ፥ ከዚኽ በፊት እንደተለመደው ኹሉ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም በመጠየቅ ለኤግዚቢሽን ማዕከል እና የገበያ ልማት ድርጅት የድጋፍ ደብዳቤ ጻፈ፤

መስከረም 03 ቀን 2008 ዓ.ም. – የማኅበሩ ጽ/ቤት በዋና ጸሐፊው፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ ደግሞ በዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት በስድስት አንቀጾች የተዘረዘረ የአገልግሎት ውል በመፈራረም የጠቅላላ ዋጋውን 35 በመቶ ብር 200 ሺሕ ቅድመ ክፍያ ፈጸመ፤

ጥቅምት ወር 2008 ዓ.ም.፡- የ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ ዝግጅት ዐቢይ ኮሚቴ፣ በማኅበሩ የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ ተቋቋመ፤

 • ከአንድ ሺሕ በላይ የሰው ኃይል በማቀፍ በአምስት ዋና ዋና ክፍሎች (የትዕይንት ዝግጅት፤ የማስታወቂያና ቅስቀሳ፤ የሥነ ሥርዓት፣ የአዳራሽ እና የቴክኒክ አካላት) የተዋቀረው ዐቢይ ኮሚቴ፣ ጊዜያዊ ጽ/ቤቱን በዋናው ማእከል አንደኛ ፎቅ ከፍቶ የድርጊት መርሐ ግብሩን በማጸደቅ ሥራውን ጀመረ፤

ታኅሣሥ ወር 2008 ዓ.ም.፡- ዐቢይ ኮሚቴው የልዩ ዐውደ ርእዩን ዝግጅት ለብዙኃን መገናኛዎች እና እንደ ሐዊረ ሕይወት ባሉ የብዙኃን መድረኮች በሰፊው በማስተዋወቅ የመግቢያ ትኬት ሽያጭ ማካሔድ ጀመረ፤

ጥር 17 ቀን 2008 ዓ.ም.፡- ዐቢይ ኮሚቴው፥ “ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን: አስተምህሮዋን እንጠንቅቅ፤ ድርሻችንን እንወቅ!!” የሚለውን የዐውደ ርእዩን መሪ ቃል እና መለዮ(ሎጎ) በዋናው ማእከል ጽ/ቤት አዳራሽ ከ300 በላይ እንግዶችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ይፋ አደረገ፤

01awde r 02

ጥር እና የካቲት፤ 2008 ዓ.ም.፡- ዐቢይ ኮሚቴው፥ የማኅበሩን የሥራ አመራር እና የሥራ አስፈጻሚ ጉባኤ እንዲኹም የዝግጅት ኮሚቴውን አባላት ጨምሮ ፍላጎቱ ያላቸው ተሳታፊዎች ኹሉ በተገኙበት፣ በየሳምንቱ ረቡዕ ባዘጋጀው የግምገማ መድረክ፣ የአራት ትዕይንቶችንና የልዩ ክውን ጥበባት መሰናዶውን ጠቅላላ ይዘትና አቀራረብ በተደጋጋሚ በማስተቸት ዝግጅቱን አጠናቀቀ፤

መጋቢት ወር መባቻ ሳምንታት፡- ዐቢይ ኮሚቴው በአገልግሎት ውሉ መሠረት የአዳራሾች ዝግጅት እና የትዕይንት ክፍሎች ዐቅዱን (floor plan and partition design) ለኤግዚቢሽን ማዕከሉ አስተዳደር በማቅረብ የቴክኒክ ክንውኑን በጋራ ቀጠለ፤ የትዕይንቱን ቁሳቁሶችም ማጓጓዝ ተጀመረ፤

መጋቢት 12 ቀን 2008 ዓ.ም.፡- በተፈጸመው የአገልግሎት ውል የክፍያ ኹኔታ አንቀጽ 4 መሠረት ማኅበሩ ቀሪውን ብር 400 ሺሕ ያኽል የመጨረሻ ክፍያ ለኤግዚቢሽን ማዕከሉ አስተዳደር ፈጸመ፤

መጋቢት 14 ቀን 2008 ዓ.ም.፡- በአገልግሎት ውሉ መሠረት፣ ዐውደ ርእዩ ከመጋቢት 15 – 21 ቀን 2008 ዓ.ም. ክፍት ኾኖ በሚቆይባቸው ሰባት ቀናት ለሥራ የሚያገለግለውን ጊዜያዊ ቢሮ ቁልፍ ዐቢይ ኮሚቴው ከማዕከሉ አስተዳደር ተረከበ፤

መጋቢት 14 ቀን ረፋድ 3፡50፡- የተረከቡትን ቢሮ ለሥራ ዝግጁ በማድረግ ላይ የነበሩ የዐቢይ ኮሚቴው የአዳራሽ እንዲኹም የቅስቀሳና ማስታወቂያ ክፍሎች ሓላፊዎች ወደ ማዕከሉ የዋና ሥራ አስኪያጅ ቢሮ በጸሐፊዋ አማካይነት በድንገት ተጠሩ፤

 • ሓላፊዎቹን ከኹለት ባልደረቦቻቸው ጋር የተቀበሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ፥ በአካሔድ ላይ ክፍተቶች ስላሉ በአስቸኳይ ተሰብስበን መነጋገር ስላለብን ነው ያስጠራናችኹ፤ በማለት ዐውደ ርእዩን ለማካሔድ ፈቃድ ስለመኖሩ ጠየቁ፤
 • ማኅበሩ ዕውቅና ከሰጠውና ተጠሪ ከኾነለት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የፈቃድ ደብዳቤ ማጻፉንና ከማዕከሉ ጋር ከሰባት ወራት በፊት ውል ተፈራርሞ አስፈላጊውን ክፍያ መፈጸሙን የጠቀሱት የዐቢይ ኮሚቴው ሓላፊዎች፣ ቀደም ሲል በማዕከሉ የተስተናገዱት ሦስት ዐውደ ርእዮችም በዚኹ አሠራር መሠረት መካሔዳቸውን በማስታወስ በማኅበሩ በኩል የሰነድ ይኹን የአካሔድ ክፍተት እንደሌለ አስረዱ፤

መጋቢት 14 ቀን ረፋድ 4፡40 – 6፡00፡– የማዕከሉ ዋና ሥራ አስኪያጅ ተጨማሪ የአስተዳደር ኮሚቴ አባላትን በመያዝ ከማኅበሩ አመራሮች እና አስፈጻሚዎች እንዲኹም ከዐቢይ ኮሚቴው አባላት ጋራ ባካሔዱት አስቸኳይ ስብሰባ፥ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ዐውደ ርእዩን ለማካሔድ የምትችሉበት የፈቃድ ደብዳቤ አምጡ፤በሚል “የአካሔድ ክፍተት” ያሉትን አስታወቁ፤

 • ማኅበሩ ዐውደ ርእዩን ለማካሔድ ፈቃድ ማቅረብ ያለበት ዕውቅና ከሰጠውና ተጠሪ ከኾነለት አካል መኾኑን ጠቅሰው ማኅበሩም ይህንኑ የድጋፍ ደብዳቤ በወቅቱ ከጠቅላይ ጽ/ቤቱ አግኝቶ ያቀረበ በመኾኑ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ማጻፍ አለበት የተባለው ፈቃድ፥ በማዕከሉ አሠራር ያልተለመደ፣ በወቅቱ ያልቀረበ እና ጨርሶም ሕጋዊ አግባብነት እንደሌለው ተወካዮቹ አስረዱ፤
 • የሚመለከታቸውን የከተማውን አስተዳደር ሓላፊዎች ለማነጋገር ከቀትር በኋላ በተደረገው ጥረትም፣ ለዐውደ ርእዩ ከአስተዳደሩ እንዲጻፍ ስለተጠየቀው የፈቃድ ደብዳቤ የሚያውቀው ነገር እንደሌለና አሠራሩም በአስተዳደሩ የሕግ ማህቀፍ እንደሌለው ለማረጋገጥ ተቻለ፤
 • ለሰላማዊ ሰልፍ እና ለስብሰባ ፈቃድ በመስጠት ከሚታወቀው የከተማው አስተዳደር አጽፉ፤ በሚል የተጠየቀው የፈቃድ ደብዳቤ አሠራር፣ አራት ዐውደ ርእዮችን በጠቅላይ ቤተ ክህነት ዕውቅና እና ፈቃድ ሲያካሒድ ለቆየው የቤተ ክርስቲያኒቱ ሕጋዊ አካል ማኅበረ ቅዱሳን፥ ሊቀርብ የማይችል፤ በኤግዚቢሽን ማዕከሉ አሠራር ያልተለመደ መኾኑንና በማኅበሩ በኩልም አንዳችም የአካሔድ ክፍተት እንደሌለ ከማዕከሉ አስተዳደር ጋር መተማመንና መግባባት ላይ ተደረሰ

A.A exhibition Center 2008

 • ይኹንና ተሲዓት በኋላ 9፡30 ገደማ፣ የኤግዚቢሽን ማዕከሉ አስተዳደር፣ በቁጥር ኤማ/1085-520-21/08 በዋና ሥራ አስኪያጅ ታምራት አድማሱ “አስቸኳይ” በሚል ለማኅበሩ በጻፈው ደብዳቤ፣ ዛሬ ሊካሔድ የነበረው ዐውደ ርእይ “ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ያልተሟላ በመኾኑ” በሚል ዝግጅቱን ለማካሔድ አስቸጋሪ በመኾኑ መሰረዙን አስታወቀ፤
 • በልምድ ያልነበረንና በሕግም የማይታወቅን አሠራር ከጊዜው ውጭ በመጨረሻው ሰዓት የጠየቀውን ትክክለኛ አካል ማንነት በማወቅ፣ የመክፈቻ ጊዜው እክል የገጠመውን ዐውደ ርእይ በመርሐ ግብሩ መሠረት ለማስቀጠል በየፊናው ጥረት ሲያደርግ ያመሸው የማኅበሩ የሥራ አመራርና የሥራ አስፈጻሚ እንዲኹም የዝግጅት ዐቢይ ኮሚቴው ለጋራ ምክክር አስቸኳይ ስብሰባ በመቀመጥ ሌሊቱን አጋምሷል፡፡

መጋቢት 15 ቀን 2008 ዓ.ም.፡- ወራትን ባስቆጠረው መርሐ ድርጊት መሠረት ከብር 2 ሚሊዮን በላይ የቅድመ ዝግጅት ወጪ የተደረገበት ልዩ ዐውደ ርእዩ፥ ዛሬ፣ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በሚከናወነው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ለሕዝብ እይታ ክፍት የሚኾንበት ዕለት ነበር፤

 • የማኅበሩ አመራርና ዐቢይ ኮሚቴው ይህንኑ መርሐ ግብር አስቀድሞ በታቀደው መሠረት ለማስቀጠል የሚያደርገውን ጥረት ዛሬም ቀጥሎ የሚውል ሲኾን፤ ውሎውንና የደረሰበትን ውጤት ከቀትር 6፡00 ጀምሮ በማጠቃለልና በመገምገም አንድ ውሳኔ አድርጎ ከቀኑ 10፡00 ላይ በዋናው ማእከል ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡
 • ማኅበሩ፣ የልዩ ዐውደ ርእዩን እውንነት፣ ትክክለኛ ጊዜና ቦታም፤ በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫው ለምእመኑ በይፋ እንደሚያሳውቅ ይጠበቃል፡፡

ለቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተህምሮ፣ ለኦርቶዶክሳዊነት ዓለም አቀፋዊነትና ሐዋርያዊ ተልእኮ እንዲኹም ከቤተ ክርስቲያን ነባራዊና ወቅታዊ ተግዳሮቶች አንጻር ከምእመኑ ለሚጠበቀው ድርሻ ልዩ ትኩረት የሰጠው ልዩ ዐውደ ርእዩ፣ ከመቶ ሺሕ በላይ ተመልካቾች እንደሚጎበኙት ግብ የተያዘበት ነው፤ ከ40‚000 በላይ የመግቢያ ትኬቶችን አስቀድመው የገዙ ምእመናንም የመጀመሪያዎቹ ጎብኚዎች ለመኾን በከፍተኛ ጉጉት ይጠባበቁታል፡፡

Advertisements

14 thoughts on “የማኅበረ ቅዱሳን ፭ኛው ዙር ልዩ ዐውደ ርእይ ቅድመ ዝግጅት ሒደት እውነታዎችና ቀጣይ ወቅታዊ ጥረቶች

 1. TIRSIT WUBIE March 24, 2016 at 10:35 am Reply

  አባቶቼ እና ወንድሞቼ ትዕግስት የበዛላችሁ ናችሁና አሁንም ጨምሮ ጨማምሮ ይስጣችሁ የቤተክርስትያንን ጥፋት እና ውርደት
  ለሚፈልጉት ደግሞ ልብ ይስጣቸው ከጸሎት ውጪ ሀይል የለኝም አይዟችሁ

  2016-03-24 1:55 GMT-07:00 “ሐራ ዘተዋሕዶ” :

  > haratewahido posted: ” በታቀደው መርሐ ግብር የማካሔድ ጥረቱ ዛሬም ተጠናክሮ ይውላል ዛሬ ከቀኑ 10፡00
  > በዋናው ማእከል ጽ/ቤት ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል የዝግጅቱ ቀጣይነት፣ ጊዜና ቦታ የሚታወቀው በሚሰጠው መግለጫ ነው ጳጉሜን
  > 5 ቀን 2007 ዓ.ም. – የማኅበሩ ሥራ አመራር ጉባኤ ጽ/ቤት በአራት ዓመት ስትራተጅያዊ ዕቅዱ ያካተተውን የዐውደ
  > ርእይ ልዩ ዝግጅት ለሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማሳሰቡን በመ”
  >

  • Anonymous March 24, 2016 at 11:31 am Reply

   አቤቱ ደግ ነገር አሰማን፤

 2. Anonymous March 24, 2016 at 1:34 pm Reply

  በርቱ አይዟችሁ የተዋሕዶ ልጆች ኹላችንም በጸሎትም በሃሳብም አብረናችሁ ነን።

  ፈርኦን “ወንድ ወንዱን ግደሉልኝ” ያለው፣ እንደእናንተ አይነቱን ለቤተክርስቲያኑ ወንድ የሆነላትን አካል በምሳሌ ሳይሆን አይቀርምና፣ ጠንክሩ በርቱ።

  “ እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር!”

  • Anonymous March 24, 2016 at 5:10 pm Reply

   እግዚአብሔር እቅፍፍፍፍ ድግፍፍፍፍፍ ድርጋችሁ እሱ ቢዘገይም ሚቀድመው ማንም የለም ክርስትና ብዙ ችግር አለው ለታገሰ እንደ አባቶቻችን ድል አለው እመብረሃን በፀሎቶ ታስባችሁ እኔ አጥያተኛዋ ሳ ይገባኝ ተማፀኩኝ እንደቸርነቱ ይስማኝ እንደኔ ሐጥያት ሳይሆን በርቱ

 3. Anonymous March 24, 2016 at 5:44 pm Reply

  ፈጣሪ ከእናንተጋር ይሁን ፈጣሪ ሃይማኖታችንን ይጠብቅልን

 4. Anonymous March 25, 2016 at 4:47 am Reply

  Ay Melkam Astedadre!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! Kibur Teklay Minister semtew yihon? Hizeb menakun, Ye 7 wre zegejet bemechereshaw 1 ken mena mehonu. Merhagibru baymeleketachewem hezeb mebedelu gin ….

 5. Anonymous March 25, 2016 at 4:47 am Reply

  በርቱ አይዟችሁ የተዋሕዶ ልጆች ኹላችንም በጸሎትም በሃሳብም አብረናችሁ ነን።

  ፈርኦን “ወንድ ወንዱን ግደሉልኝ” ያለው፣ እንደእናንተ አይነቱን ለቤተክርስቲያኑ ወንድ የሆነላትን አካል በምሳሌ ሳይሆን አይቀርምና፣ ጠንክሩ በርቱ።

  “ እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር!”

 6. fesha negash March 25, 2016 at 7:52 am Reply

  በቅድሚያ ማህበረ ቅዱሳን የቤተ ክርስቲያንን ልእልና ደፍቆ በላይዋ ላይ ሌላ መዋቅር የዘረጋ ሰይጣናዊ ማህበር መሆኑን ብዙ የቤተ ክርስቲያን ምእመናን ያልተረዱት ጉዳይ ነው፡፡ በመሆኑም ማህበሩ በቤተ ክርስተያን ውስጥ ሊይዝ የሚገባውን ህጋዊ እና መንፈሳዊ መሰረት ምን ምን ሊሆን እንደሚገባው ለተከታዮቿ ማስተማር ማሳወቅ የቤተ ክርስቲያኒቱ ግዴታ ነበር አልተደረገም፡፡ ይህም የማህበሩ ጥቅም እንዲጠበቅ በሚሰሩ የሲኖዶስ አባለት ትብብር የተደረገ ፤አነርሱም አብዝተው ለማህበሩ በሚሰጡት ድጋፍ የተነሳ ነው፡፡ በእውነቱ እነዚህ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን ያልገባቸው፣ በገቡት ቃል ኪዳን መሰረት ለቤተ ክርስቲያኒቱ እና መንጋው ጠበቃ መሆንና መሥራት ያልቻሉ በመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ሳይሆን በግብታዊነት የጵጵስና ሹመት የተቀበሉ ናቸው፡፡ ያሳዝናል!!!!
  የማህበሩ አመራሮች ዛሬም የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ነን እያሉ ከማዕከላዊ አሰራር ውጭ ተሀድሶ ወረረን ፣ ገዳማት ተቃጠሉ፣ መምህራን ተሰደዱ ወዘተ.. በሚል ማደናገሪያ የዋሑን ምእመን ይነዱታል፣ ገንዘቡን ይዘርፉታል፣ለአመጽም ያነሳሱታል፡፡ እነርሱ የሚነዱት ምእመን በቤተ ክርስቲያኒቱ አባቶች በእውነትና በፍቅር ተይዞ ቢሆን ቤተ ክርሲቲያን የት በደረሰች ነበር ፡፡
  አሁን ፓትርያርክ ማትያስ ማህበሩን ሕጋዊ እና መንፈሳዊ መሰረት ለማስያዝ እየወሰዱ ያሉት እርምጃ ትክክል ቢሆንም በሚመሯት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እየተፈጸመ ያለውን ሙስና እና ሰይጣናዊ አሰራር ሊነኩት ስላልፈለጉ ግን ዘረኝነታቸው ከፓትያርክ ጳውሎስ የከፋ ነው፡፡ እስቲበእውነት ለቤተ ክርስቲያን ከተቆረቆሩ የማህበሩን ኤግዚቪሽን እንዳሳገዱት በታማሚ ልጁ ስም ከየአድባራቱ በሚሊዮኖች ገንዘብ የሚዘርፈውን የአ/አ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅ ከያዘው ከሁለቱም ሥልጣኑ ያግዱት፡፡
  እስቲ በዘረፋና በዝሙት ሥራ ተጠምደው ካሉት በመቶዎች ከሚቆጠሩ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ጸሐፊዎች…… ቢያንስ በተጨባጭ ማስረጃ የርኩሰት ሥቸውን ከሚያውቁት መካከል ሁለት ሶሰቱ ላይ እርምጃ ይውሰዱ እና ምእመኑን ያስደስቱ፡፡ አያደርጉትም እንጂ!! ኔትወርኩ አይነኬ ነውና፡፡
  በአንድ ወቅት የደርግ ባለሥልጣን የነበሩ ኮሎኔል ኢሀዲግ አ/አ ሳይገባ ከድተው ከውጭ ጋዤጠኛ ሲጠይቃቸው የመለሱት መልስ ለዚህ አስተያየቴ መደምደሚያ ይሁን ፡፡ የተጠየቁት ስለ ደርግም ስለ ኢሀዴግም የተሸለው ነገር እንዲናገሩ ነበር ፡- እሳቸው ሲናገሩ ግን ‹ሁለቱንም በሁለት እጆቼ እዋጋቸዋለሁ› ነበር ያሉት ፡፡ አሁንም ማህበር ቅዱሳንም ሆነ የፓትርያርኩ አመራር ከበደል ርቀው እና ሁሉም ከጥፋቱ ተመልሶ ለእውነተኛ መንፈሳዊ አገልግሎት ለመሥራት ካልተስማሙ ለቤተ ክርስቲያን አይጠቅሙም ሁለቱም በርኩሰት ሥራ የተጠምዱ የቤተ ክርስቲያን ጠላቶች ናቸው፡፡ ለእኛ ለምእመናን የሚያዋጣን ግን የእነርሱን በደል እለት እለት መስማት ሳይሆን የእግዚአብሔርን ፍርድ በጸሎት መጠባበቅ ብቻ ነው፡፡

  • Anonymous March 25, 2016 at 10:39 am Reply

   የተሃዲሶ/ፐሮቴስታንን አካል በመሆንህ ብዙም አልገረመኝም አንተ ማን ሆነህ ነው ማህበሩን የምትተች ምንስ እውቀት ኑሮህ እንደልብ በቤተክርስቲያን ላይ መፈንጨታችሁን በመታገሉ ለማህበሩ የማይገባ ስም ሰጠኸው ጠላት በበዛ ቁጥር ግን ማህበሩ እየጠነከረ እንደሚሄድ ማወቅ አለብህ እግዚያብሄር ልቦናህን ከፍቶ የማህበሩን ማንነት ያሳይህ አስተያየት ስሰጥም ጎራህን ለይተህ ስጥ

 7. tadi wolde March 29, 2016 at 8:24 am Reply

  አማሳኙ አይዞህ! መጥፊያህ ደርሷል እና አትቸኩል፤፤

  በርቱ አይዟችሁ የተዋሕዶ ልጆች ኹላችንም በጸሎትም በሃሳብም አብረናችሁ ነን።

  ፈርኦን “ወንድ ወንዱን ግደሉልኝ” ያለው፣ እንደእናንተ አይነቱን ለቤተክርስቲያኑ ወንድ የሆነላትን አካል በምሳሌ ሳይሆን አይቀርምና፣ ጠንክሩ በርቱ።

  “ እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር!”

 8. tadi wolde March 29, 2016 at 8:29 am Reply

  አማሳኙ ተሃድሶ/ፕሮቴስታንት አይዞህ! መጥፊያህ ደርሷል እና አትቸኩል።
  በርቱ አይዟችሁ የተዋሕዶ ልጆች ኹላችንም በጸሎትም በሃሳብም አብረናችሁ ነን።

  ፈርኦን “ወንድ ወንዱን ግደሉልኝ” ያለው፣ እንደእናንተ አይነቱን ለቤተክርስቲያኑ ወንድ የሆነላትን አካል በምሳሌ ሳይሆን አይቀርምና፣ ጠንክሩ በርቱ።

  “ እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር!”

 9. tadi wolde March 29, 2016 at 8:33 am Reply

  አማሳኙ ተሃድሶ/ፕሮቴስታንት አይዞህ! መጥፊያህ ደርሷል እና አትቸኩል።

  በርቱ አይዟችሁ የተዋሕዶ ልጆች ኹላችንም በጸሎትም በሃሳብም አብረናችሁ ነን።

  ፈርኦን “ወንድ ወንዱን ግደሉልኝ” ያለው፣ እንደእናንተ አይነቱን ለቤተክርስቲያኑ ወንድ የሆነላትን አካል በምሳሌ ሳይሆን አይቀርምና፣ ጠንክሩ በርቱ።

  “ እንበለ መከራ ኢይትረከብ ጸጋ እግዚአብሔር!”

 10. Anonymous April 20, 2016 at 10:05 am Reply

  የተሃዲሶ/ፐሮቴስታንን አካል በመሆንህ ብዙም አልገረመኝም አንተ ማን ሆነህ ነው ማህበሩን የምትተች ምንስ እውቀት ኑሮህ እንደልብ በቤተክርስቲያን ላይ መፈንጨታችሁን በመታገሉ ለማህበሩ የማይገባ ስም ሰጠኸው ጠላት በበዛ ቁጥር ግን ማህበሩ እየጠነከረ እንደሚሄድ ማወቅ አለብህ እግዚያብሄር ልቦናህን ከፍቶ የማህበሩን ማንነት ያሳይህ አስተያየት ስሰጥም ጎራህን ለይተህ ስጥ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: