የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሤራና አቀንቃኞቹ የተጋለጡበት የድል ጉባኤ ‐ በዲላ

photo4
በዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና ዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስ አድባራት ሰበካ ጉባኤና በማኅበረ ቅዱሳን የዲላ ወረዳ ማዕከል በመተባበር የተዘጋጀው መንፈሳዊ ጉባኤ ከመጋቢት 2 እስከ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. ለአራት ተከታታይ ቀናት ተካሒዷል፡፡ ጉባኤው የተደረገው፥ የሲዳማ፣ ጌዴኦ፣ አማሮና ቡርጂ ዞኖች ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሰበካ ጉባኤውና በወረዳ ማዕከሉ በጋራ ለቀረበለት ጥያቄ፣ የካቲት 25 ቀን 2008 ዓ.ም. በቁጥር 9130/6/1/2008 በተጻፈ ደብዳቤ ፈቃድ በመስጠቱ ነው፡፡

የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በማጋለጥ ሤራው በቂ ግንዛቤ ተይዞበት፤ ምእመኑና አገልጋዩ ከኑፋቄው ተጽዕኖዎች ተጠብቆ ሥርዐተ አምልኮውንና አገልግሎቱን በቀናች እምነትና ሥርዓት እንዲፈጽም ማብቃት፤ ከጉባኤው ዐበይት ዓላማዎች አንዱ ነበር፡፡ በአራቱ ቀናት በጉባኤው ያገለገሉት ሰባክያነ ወንጌል፣ መምህራኑ፥ ዲ/ን ኢንጅነር ስንታየሁ ጅሶ፣ ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ እና ዲ/ን ታደሰ ወርቁ ሲኾኑ ዘማርያኑም፥ በኵረ ዘማርያን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ፣ ዘማሪት መሠረት ማሞ እና ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ ናቸው፡፡ በጉባኤው ከዲላና አካባቢው የመጡ ከዐሥራ አምስት ሺሕ በላይ ምእመናን የተገኙ ሲኾን፥ ከወትሮ በተለየ ማኅበረ ካህናቱ ማስታዎሻ ደብተር እየያዙ መርሐ ግብሩን ሲከታተሉ መታየታቸው የጉባኤው አስደሳች ገጽታ ነበር፡፡

photo9
በፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ የሰባክያንና የዘማርያን ጥምረት፣
የኑፋቄውን ሤራ በሚያጋልጡ ትንታኔዎቹ የሚታወቀው ዲ/ን ታደሰ ወርቁ፣ ጉባኤው በተጀመረበት ቅዳሜ፣ መጋቢት 3 ቀን፥ “የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ዋነኛ አራማጆችና አቀንቃኞች የወቅቱ ቁመና” በሚል ርእስ በፓወር ፖይንት የተደገፈ ሰፊ ገለጻ አቅርቧል፡፡

photo3
ጉባኤተኛው ገለጻውን በጥሞና በመከታተል ላይ ሳለ ግን፣ “የትውልድ ቦታችን ነው፤ ማን ይነካናል!” ያሉ የኑፋቄው ጋሻ ጃግሬዎች ሁከትና ግርግር በመፍጠር ጉባኤውን ለማሰናከልና ጉዳቸውን ለመሸፈን ሙከራ ማድረጋቸው አልቀረም። ሦስት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አቀንቃኞች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፣ ‹‹ኢየሱስ ጌታ ነው! መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው! ኢየሱስ ያድናል! ወንጌል ብቻ ስበከን! ስለ ተሐድሶ ለምን ታወራላችሁ?…›› እያሉ በመጮኸ ሰላማዊውን ጉባኤና ጉባኤተኛ ማወክ ጀመሩ፡፡ ሥርዐት አድርጉ ቢባሉም የሚሰሙ ኾነው አልተገኙም፡፡ እንዲያውም ቦታውን ሲያተራምስ ከኖረው የስድብ መምህራቸው በጋሻው ደሳለኝ የቀጸሉትን ዘለፋ በደብሩ አለቃ ላይ ያወርዱባቸው ጀመር፡፡

በስድባቸውና በዘለፋቸው ጉባኤው ባለመፈታቱ ተስፋ ቆርጠው ምእመኑን በአይሬቤነት መሳደባቸውን ተያያዙት፤ ከዘላፊዎቹም አንዱ፣ ‹‹ኧረ በኢየሱስ ተነሡ! የማይታመን ሕዝብ!›› ሲል ተደምጧል፡፡ ከዚኽም አልፈው ለደብድብ ተጋብዘዋል፡፡ በዐመፁ አብሮን ይሰለፋል ያሉት ጉባኤተኛ ለቤተ ክርስቲያኑ ወግኖ ቆመ፤ በብዙ ታግሦአቸው ሲያበቃም፣ ‹‹ውጡልን፤ የተጀመረው ገለጻም ይቀጥል፤ እውነቱን ማወቅ እንፈልጋልን፤›› እያለ በአንድ ድምፅ አደብ እንዲገዙ አደረጋቸው፤ ገለጻውም እንዲቀጥል በጭብጨባና እልልታ አቋሙንና ፍላጎቱን አረጋገጠ፡፡

በሕዝቡ ምርጫና ይኹንታ ከተቋረጠበት በቀጠለው ትምህርታዊ ገለጻ፣ የአሠማሪዎቻቸው ድብቅ ሤራ ሲጋለጥ ተመለከቱ፤ ከእነርሱ ውስጥም አንዳንዶቹ ለወረዳው ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅና ለስድብ አለቃቸው በጋሻው በሞባይል ለማስተላለፍ ሲጥሩ ታይተዋል፡፡ ድርጊታቸውን የታዘቡ አንድ አረጋዊም፣ ‹‹የምትልኩለት እንዲማርበት ከኾነ አንድ ነፍስ እያዳናችሁ ነውና ያስመሰግናችኋል፤ እንዲህ ተባልክ ለማለት ከኾነ ግን ግፊቱን አትጨምሩበት፤ እግረ መንገዳችሁን ግን ‹ተሐድሶነት እከክ አይደለም፤ አይጋባም፤ ተሐድሶ የለም› ያልከው የኑፋቄው አቀንቃኝ ስለኾንክ እንደኾነ ከገለጻው ተረድቻለው በሉልኝ፤›› ብለዋቸዋል፤ የዕለቱ ጉባኤ በታቀደው መሠረትና በተያዘለት ሰዓት ግቡን አሳክቶ በዚኽ መልኩ በሰላም ተጠናቀቀ፡፡

እኒኽ አካላት፣ ቀድሞም ጉባኤውን ለማስተዋወቅ የተለጠፉ ፖስተሮችን በመቅደድ የዲላ እና የአካባቢው ምእመናን መረጃው እንዳይደርሳቸው ለማድረግና ዝግጅቱን ለማስተጓጎል ሲንቀሳቀሱ ሰንብተዋል፡፡ በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ምንነት፣ ዓላማ፣ የማደናገርያ ስልቶች፣ መዋቅራዊ ሤራና አደጋ፣ የፋይናንስና የፕሮፖጋንዳ ምንጮቻቸው እንዲኹም የምእመናን ድርሻን በምስል ወድምፅ አስረጅዎች በማስደገፍ የቀረበው ገለጻ፣ በሕዝቡ ውስጥ ቁጭት መፍጠሩን ሲመለከቱም፤ ከመርሐ ግብሩ ፍጻሜ በኋላ በሦስት መልኩ ሊገለጹ የሚችሉ የማሰናከያ ርምጃዎችን መውሰድን መረጡ፡፡

የመጀመሪያው ማሰናከያቸው፡– የደብሩን አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ ወርቁን ክብረ ነክ በኾኑ ቃላት በመሳደብና በማስፈራራት ለመማታት መጋበዝ ነበር፡፡ አባ ታዬም÷ ‹‹ለአፍ ዳገት የለውምና መሳደቡን ተሳደቡ፤ የምመራትን ቤተ ክርስቲያን ማወክ ግን አትችሉም፤ ቤተ ክርስቲያንን የማስከበር ሕጋዊ ርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ትመከሩ እንደኾነ ተመከሩ፤ ይህን ማድረግ የሚተናነቃችሁ ከኾነ ቅጽረ ቤተ ክርስቲያኑን ለቃችሁ ውጡ፤›› ሲሉ አስጠንቅቀዋቸዋል፤ በዘላፊዎቹ ስድብና ዛቻ ሳይንበረከኩ በአባታዊ ቆራጥነት ገሥጸዋቸዋል፡፡

photo2
አስተዳዳሪው መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ አለመንበርከካቸውን ሲረዱም ኹለተኛው ማሰናከያቸው የነበረው በሐሰት መክሠሥ ነበር፡፡ ወደ ዞኑ ፖሊስ መምሪያ በመሔድ፣ ‹‹አባ ታዬ አስደበደቡን›› ብለው የፈጠራ ክሥ አቀረቡ፤
ድርጊታቸውን ሲቪል በለበሱ ፖሊሶች ክትትል ሥር ስለነበር በፖሊሶቹ እማኝነት ክሡ የተገላቢጦሽ ኾነ፡፡ ተጠያቂነቱ ወደ እነርሱ እየመጣ መኾኑን ሲያውቁም ክሣቸውን ትተው እብስ አሉ፡፡

እብስ ባሉበት፣ ወደ ጉባኤ ያልመጣውን ምእመን ለማደናገር በከተማው የፈጠራ ወሬ በማውራት ወደ ሦስተኛው ርምጃቸው ተሸጋገሩ፡፡ ‹‹ብጥብጥ ተነሥቶ ጉባኤው ተቋረጠ፤ በብጥብጡ ሰው ተጎድቷል፤ ነገም ብጥብጥ ሊነሣ ስለሚችል ለቅዳሴም ኾነ ለጉባኤ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳትሔዱ፤›› ብለው የሐሰት ወሬአቸውን ነዙ፡፡

አኹንም የኾነው ግን በተቃራኒው ነበር፡፡ ቤቱ የቀረ ሰው የለም በሚያሰኝና ከወትሮው በተለየ ኹኔታ ምእመኑ በነቂስ በመውጣት ቅዳሴ አስቀደሰ፤ የዕለቱን መዝሙር፣ ምስባክና ወንጌል በማመስጠር በጉባኤው መምህራን የተሰጠውን ትምህርተ ወንጌልም በአትኩሮት አዳምጦና ለቀትር በኋላው ጉባኤ ቀጠሮ ይዞ በሰላም ወደየቤቱ ተመለሰ፤ ለሐሰተኛ ወሬአቸውም ሕዝቡ ቦታ አለመስጠቱም በዚኹ ተረጋገጠ፡፡

ምእመኑ በተለይም ደግሞ ይተባበረናል ብለው የጠበቁት ወጣት እንደተቃወማቸውና ጀርባውን እንደሰጣቸው የተገነዘቡት የጥፋት መልእክተኞቹ፥ የወረዳውን ሊቀ ካህናትና የስብከተ ወንጌል ሓላፊ በበጋሻው ደሳለኝ አማካይነት በማግባባት የቀትር በኋላውን ጉባኤ ለማሳገድ ጥረት አድርገው ነበር፡፡ ይኹንና ጉባኤው በደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጠያቂነት፣ በወረዳ ቤተ ክህነቱ አሳሳቢነትና በሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ሰጪነት የተፈቀደ በመኾኑ የሚታገድበት አግባብ አልነበረም፤ እንዲያውም ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ገብርኤል ዳግመኛ ጥብቅ መመሪያ በማስተላለፋቸው በተጀመረበት እንዲቀጥል ተደርጓል፡፡

የእሑድ ከቀትር በኋላው ጉባኤ በታቀደለት መርሐ ግብር መሠረት እንደሚካሔድ ርግጥ ኾነ፡፡ በጋሻው ደሳለኝና ጉዳይ አስፈጻሚዎቹም ይህንኑ ሲያረጋግጡ በወረዳው ቤተ ክህነት ሊቀ ካህንና በአንድ የፖሊስ አባል ተባባሪነት፣ ‹‹ተሐድሶ አትበሉ፤ ተሐድሶ ሳትሉ ጉባኤውን አካሒዱ›› የምትል ግብ አሳች ምክር አመጡ፡፡ ግብ አሳችነቷን የተረዱት የደብሩ አስተዳዳሪና ሰበካ ጉባኤውም ምክሪቱን ስላልተቀበሏት ትምህርተ ወንጌሉ ለጉባኤው ከአዲስ አበባ በተጋበዙት መምህራን እንዲቀጥል ተደረገ፡፡

የዕለተ እሑዱ የትምህርት ክፍለ ጊዜም በሦስት የተከፈለ ነበር፡፡ የመጀመሪያው÷ ምእመናን፣ በስምና ዝና እንዲኹም በአገር ልጅነት ሽፋን ከሚሰጡ የኑፋቄ ትምህርቶች ዐይነ ልቡናቸውንም ኾነ እዝነ ልቡናቸው እንዲጠብቁ፤ ምንጊዜም ቢኾን የቤተ ክርስቲያን ራስ ክርስቶስን እንዲመለከቱ፤ ክርስቶስ አስቀድሞ የመረጣቸውንና ያከበራቸውን፥ በኋላም በስሙ ሰለ ስሙ ተጋድለው የድል አክሊል የተቀዳጁትን ቅዱሳንን አሠረ ፍኖት እንዲከተሉ የሚያሳስብ ትምህርተ ወንጌል በዲያቆን ኢንጅነር ስንታየሁ ጅሶ እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡

ኹለተኛው÷ ከክብረ ቤተ ክርስቲያንና ከክብረ ክህነት አንጻር የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄን በማጋለጥ የተሰጠው ትምህርታዊ ስብከት ነው፡፡ በዚኽ ትምህርት የቤተ ክርስቲያን ክብሯና የክብሯ መገለጫ የኾኑት መሠረታዊ ዕሴቶቿ ምን ምን እንደኾኑ፤ እኒኽ ዕሴቶቿ እንዴት ተጠብቀው ለዘመኑ እንደደረሱ፤ በዘመናችን የተነሡት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አራማጆችና አቀንቃኞች በምን ስልት እንደሚበርዟቸውና እንደሚቀስጧቸው፤ ምእመናን እነዚኽን ዕሴቶቻቸውን አምነው በማወቅ፤ ዐውቀውም በመጋደል ከፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን ብቻ ሳይኾን ከአድራሽ ፈረሶቻቸውም መጠበቅ እንዳለባቸው፤ ትርጓሜን ከምስጢርና ከዘይቤ ጋር የጠነቀቀ ትምህርት በዲያቆን ታደሰ ወርቁ ተሰጥቷል፡፡

????????

ሦስተኛውና የጉባኤው ፍጻሜ ትምህርት፣ ቅዱሳንን መስበክና መዘከር ከወንጌል መሠረታዊ ሐሳቦችና ከወንጌላውያኑ አስተምህሮ ጋር ተሰናስሎ በንባብና በአመሥጥሮ የቀረበው ነበር፡፡ በዚኽ ትምህርት ቅዱሳንን በትምህርትና በመዝሙር መስበክ እግዚአብሔራዊ ትእዛዝ፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ብያኔና ቀኖናዊ ድንጋጌ እንዳለው፤ ቅዱሳንን መስበክ ክርስቶስን መስበክ እንደኾነ፤ ቅዱሳንን መስበክ ከወንጌልና ከወንጌላውያኑ መውጣት ሳይኾን እንደውም ክርስቶስ በወንጌል የተወልንን ተስፋ መንግሥተ ሰማያትንና የወንጌላውያንን በረከት እንደሚያሰጥ፤ መናፍቃኑም ይኼን ዋጋ ለማሳጣት እንዴት እንደሚሠሩና መከላከያ መንገዱን ያመላከተ ትምህርት በዲያቆን ኢንጅነር ዓባይነህ ካሤ በጥልቀት ተሰጥቷል፡፡

በጉባኤው ፍጻሜ፣ መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም.፣ በነበረው የጻድቁ የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክብረ በዓል ላይ፣ በሰንበት ት/ቤት የተሰገሰጉ ጥቂት የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አቀንቃኞች ከያሉበት በመሰባሰብ በመሰሎቻቸው መዝሙር ተብዬ ጩኸቶች ምእመናን ትምህርት እንዳይማሩ ለማወክ ሞክረዋል፤ በሰንበት ተማሪነት ሽፋን ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን እንዲሠሩ በበጋሻው ደሳለኝ የተመለመሉት እኒኽ የጥፋት ወኪሎች ካልዘመርን ብለው ነበረና እንዲዘምሩ ሲፈቀድላቸው፣ የተላለፉትን ትምህርቶች በመቃወም መልኩ ያሰሟቸው ‹መዝሙሮች› በመሉ ለመናፍቃኑ እንደሚሠሩ በሕዝብ ፊት የተጋለጡበት ኾኗል፤ እግዚአብሔር ተኣምሩን የሚገልጥበት መንገድ ብዙ ነውና፡፡

በመዝሙር ሰበብ መድረኩን ከያዙት በኋላ፣ ታይቶ በማይታወቅ ኹኔታ መመሪያን በመጣስ ያለመርሐ ግብሩ ጥቅስ እየደነጎሩ በኑፋቄው አቀንቃኞች ‹መዝሙር› ለመፈንጨት ሲውተረተሩ ታይተዋል፡፡ በዚኽም ሳያበቁ፣ የመርሐ ግብር መሪውን መልእክትና አባቶችን በመናቅና በመዝለፍ ዐውደ ምሕረቱንና የድምፅ ማጉያውን አንለቅም በማለት ጉባኤውን በጸሎት ለመዝጋት እንኳ ዕንቅፋት ኾነው አምሽተዋል፡፡

????????

በፀረ ኑፋቄው ገለጻ ማንነታቸው፣ ሤራቸውና ስልታቸው ገሃድ ወጥቶ ሲጋለጥ፣ ርኵስ መንፈስ እስኪያሰክራቸው ድረስ ያሉበትን በመሳት በጉባኤ መካከል እየተንፈራፈሩ ጮኸዋል፤ መርሐ ግብሩን የማስተጓጎል ውጥናቸው ግን ከቶም ባለማሳካቱ ክፉኛ ተደናግጠዋል፤ ምሽቱን በየቦታው ተሰብስበው ቀጣዩን መርሐ ግብር ለማወክ ከተቻለም ለማስቆም ቢሞክሩም የያዘላቸው ነገር አልነበረም፡፡ ሕዝቡም ቁጣውን በመግለጹ የጀመሩትን ‹መዝሙር› ሳይጨርሱ እንዲያቆሙ ተደርገዋል፡፡ ከኦርቶዶክሳውያኑ ዘማርያን በኵረ መዘምራን ኪነ ጥበብ ወልደ ቂርቆስ፣ ዘማሪት መሠረት ማሞና ዘማሪት ወርቅነሽ ተፈራ ዘለግ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ ጣዕመ መዝሙራቸውን አሰምተው በጉባኤተኛውም ‹‹ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን›› ተብለዋል፡፡

በታላቁ የቤተ ክርስቲያን አርበኛ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ ወርቁ፣ ትዕግሥትና አስተዋይነት የተመላበት አመራር፤ በሀገረ ስብከቱ ለቤተ ክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች በኾኑ አገልጋዮችና የወረዳ ማእከሉ አባላት ጠንካራ መተባበር፣ ታጋሽነትና ትሕትና የሐራ ጥቃዎችን እኩይነት ማሸነፍ በመቻሉ የሐራ ጥቃን ማንነት በአግባቡ ያጋለጠው ጉባኤ በታቀደው መሠረት በስኬት ለመጠናቀቅ በቅቷል፡፡

እሑድ ማታ፣ በመ/ር ዲ/ን ዓባይነህ ካሴ የነገረ ቅዱሳን ትምህርት ማጠቃለያ እየተሰጠ በነበረበት ሰዓት፣ በደብሩ ውስጥ የነበረው ታላቅ ዛፍ በነፋስ ምክንያት ከሥሩ ተገንድሶ ከፍተኛ ድምፅ በማሰማትና የኃይል መሥመር በመበጣጠስ ወድቋል፡፡ በጊዜው ስንት ምእመን ሞተ(ተጎዳ) ተብሎ ሲጠበቅ፣ እንኳን ሰው በዛፉ ሥር የነበረው ሞተር ሳይክል እንኳ ምንም ሳይነካ በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ድንቅ ተኣምር ያለምንም ጉዳት መሬት ላይ አርፏል፡፡

የሚገርመው ነገር፣ ዛፉ የወደቀበት ስፍራ የሐራ ጥቃ ተሐድሶ አቀንቃኞች በዕለተ ቅዳሜ ሁከት ያነሡበትና አዘውትረውም ክፋት ለመምከር የሚሰበሰቡበት ሲኾን፤ እግዚአብሔር አምላክ የማንቂያ ደወል ያሳየበት ምልክት ነበር፤ ምእመናንም ለተደረገው ድንቅ ተኣምር እግዚአብሔርን አመስግነዋል፤ በጉባኤው ያገለገሉ ሰባክያነ ወንጌል መምህራንና ዘማርያንም ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡

ጥፋታቸው በግልጽ የተረጋገጠባቸውና ታርመው አልመለስ ባሉት ጥቂት የሰንበት ት/ቤቱ የኑፋቄው አቀንቃኞች እና የጥፋት መልእክተኞች ላይ በጉባኤው ማጠቃለያ ከአባልነት የማገድ ርምጃ ተወስዷል፡፡ ይኹንና አኹንም በድብቅ የሚንቀሳቀሱ እንዳሉ የጠቀሱት የዲላ መካነ ቅድስት ሥላሴ ወአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ እና የዲላ ዳማ ቅዱስ ጊዮርጊስና ጌቴሴማኒ በዓታ ለማርያም ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ ወርቁ፥ ምእመናን ይህንኑ ተረድተው እናት ቤተ ክርስቲያናቸውን ዘወትር በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው በቃለ ምዕዳናቸው አሳስበዋል፡፡

በቀና አስተዳደራቸውና በራስ አገዝ የልማት እንቅስቃሴአቸው በምእመኑ ዘንድ ተወዳጅ የኾኑት መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ታዬ በወቅቱ እንደገለጹት፣ሰው ድንጋይም ለማምለክ ነፃነቱ አለው፤ ነገር ግን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተሐድሶ መናፍቃንን ዓላማ ማራመድ አይቻልም፤ እኛም ለሃይማኖታችንና በኖላዊነት ለምንመግባቸው ምእመናን እስከ ደም ጠብታ ድረስ መሥዋዕትነት እንከፍላለን፤ በማለት ለፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ተጋድሎው ቀጣይነት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

አምላከ ቅዱሳን እግዚአብሔር በቀናች ሃይማኖት ያሉ አባቶቻችንና መምህሮቻችንን፣ ዘማርያንን፣ ምእመናንንና አገልጋዮችን ይጠብቅልን፡፡ የቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ለሚመኙት ልቡናቸውን ይመልስልን፡፡ አሜን፡፡

25 thoughts on “የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ሤራና አቀንቃኞቹ የተጋለጡበት የድል ጉባኤ ‐ በዲላ

  1. Anonymous March 23, 2016 at 4:56 am Reply

    ye Nufake timhrt Astemari man new??? ye eyesusn getanet wode gon bemetew yetebelashe wongel yemisebk new!!!

    • Anonymous March 25, 2016 at 10:24 am Reply

      arbak atzebarek eysus kerstos yegetoch geta yengusoch negus fetsum amelak new helkunes kenufake temhert weta

  2. Anonymous March 23, 2016 at 5:54 am Reply

    ስብሐት ወክብር ወአኮቴት ይደሉ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ በምድር ወበሰማያት በባሕር ወበቀላያት ወበኲሉ ፍጥረት ለዓለመ ዓለም አሜን!!!

    • Anonymous March 25, 2016 at 5:42 am Reply

      Amen leyikun

  3. Fisseha Tesfaye March 23, 2016 at 6:29 am Reply

    Egziabher bereketun tsegawn yadlachihu. Enanten ena Mahbere Kidusanen Yitebkilin

  4. ሄኖክ March 23, 2016 at 7:23 am Reply

    እግዚአብሔር ይስጥል!!! በወቅቱ የተካሄዱትን ስብከቶች በvideo ወይም በድምጽ የተቀረጽ ካለ የምናገኝበት መንገድ ቢኖር

  5. የማርያም March 23, 2016 at 8:35 am Reply

    Thank God. Betam des bilognal.

  6. Anonymous March 23, 2016 at 8:38 am Reply

    ይትባረክ እግዚአብሄር አምላከ አበዊነ ቅዱሳን………

  7. Anonymous March 23, 2016 at 9:13 am Reply

    ወይ ጉድ እንዲህም ታደርጋለህ እንዴ እባክህ ያደረብህን መንፈሰ ተሃድሶ ሰይጣን ይዞህ ወደ ገሃነም ከመውረዱ በፊት ተመለስ ከነ ጭፍሮችህ ንስሓ ግባ

  8. Anonymous March 23, 2016 at 10:54 am Reply

    aba selama errrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrr

  9. Anonymous March 23, 2016 at 10:56 am Reply

    aba selama errrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrrr

  10. Alemayehu Geremew March 23, 2016 at 1:30 pm Reply

    Egziabher yimesgen.

  11. Anonymous March 23, 2016 at 2:21 pm Reply

    egzyabher seytanin yiyazilin

  12. mengistu argaw March 23, 2016 at 4:11 pm Reply

    sele dinq siraw Egziabher yimesgen .Mahiberacinin yasfalin. atsirare dingil Mariyam ena atsirare betkiristiyanin yastagsilin.bertu tegadelu enigadel
    !!!

  13. Anonymous March 23, 2016 at 4:20 pm Reply

    THANKS TO ” GOD ”

  14. Anonymous March 23, 2016 at 5:11 pm Reply

    Thanks GOD!! Betam des yelal..

  15. Anonymous March 23, 2016 at 8:02 pm Reply

    Lela botam bemenafkan yemiwozagebu sewoch aluna dresulachew .yeh betam des yyilal.

  16. Anonymous March 23, 2016 at 10:12 pm Reply

    thanks to god

  17. Anonymous March 24, 2016 at 3:24 am Reply

    አለመታደል፡ የቤተክርስቲያኒቱ ታላቅ ዘፍ ከሥሩ ተገንድሶ ወደቀ አላቸው፡፡ በሥሩ ደግሞ ተሐድሶአውያን ይመክሩበት ነበር አላችሁ፡፡ በዚህም ዲያቆኑ እያስተማረ እያለ ወደቀ፡፡ ስለዚህ ይተአምር ለእናንተ መልካም ሥራ ማሳያ አደረጋችሁት፡፡ በጣም ያሳዝናል የማታፍሩ ምነው ዝም እንኳን ብትሉ፡፡ አጼ ዘርዓ ያዕቆበ ንጹሐን መንኮሳትን ፍጹም ሰብአዊነት በጎደለው አርሜናዊ አገዳደል ከገደላቸው በኋላ ለክብረ ሰማእትነታቸው የተከሰተውን ብርሃን ለነፍሰ ገዳዩ የወረደ ብርን ነው፡ ብሎ አንደዘገበው፡፡ አሁንም ታላቅ የዐውደ ምህረት ዛፍ ሲወድቅ ያለ ትርጉሙ ትርጉምን በመስጠት ኃጢአታችሁን ወደሌሎች ማዞር ጀመራችሁ፡፡ የወደቀው ዛፍ ሰው አለመጉዳቱ እውነት ነው፡ ተአምርም ሊያሰኝ ይችላል፡፡ ግን ሰውን ያልጎደበት ምክንያት የተሰበሰበው ሕዝብ ተንኮላችሁን የማያውቅ አማኝና ቅዱስ ሕዝብ ስለሆነ እግዚአብሔር ከልሎታል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ ነበራና ታላቅ የዐውደ ምህረት ዛፍ መውደቅ ግን የሚያሳየው የእናንተ ጽድቅ ሳይሆን ኃጢአት ነው፡፡ ታስገርማላችሁ ቤተክርስቲያኑ በመብረቅ ወይም በመንቀጥቀጥ ቢወድቅም ለእናንተ ቅዱስ ታአምር ነው፡፡ ልንገርህ የእናንተ ተአምር የሚሆነው የወደቀው ዘፍ ከወደቀበት ቢቆም፤ ወይም እንደ ወንጌሉ ቃሉ ከቅጥረ ቤተክርስቲያን የቆሞው ዛፍ ተነቅሎ በግቢው ቢተከል፡፤ወዘተ. እውነተኛ ተአምር ማለት ይቻላል፡፡ በእናንተ ጉባኤ የተደረገው ተአምር ግን የቤተክርስቲያኒቱ ድኖች የሆኑ ቅዱሳንን ያለ አግባብና ያለእውነተኛ አስተምህሮ እያሳዘናችሁ ስለምትገኙ ታላቅኑ ዛፍ ወደቀ፤ ክብረ ኦርቶዶክስ የሆነ ወንጌል በሐሰት በመስበካችሁ ታአምሩ አያችሁ፡፡ አሁንም ንስሐ የሚያስፈልጋችሁ እናንተና እናንተን ገድል ያስገቡ ላሉት መሰል አስተዳዳሪዎችና ጳጳሳት ነው፡
    ንስሐ ግቡ

    • Anonymous March 25, 2016 at 10:20 am Reply

      tenkhleh seltawekeb bhewenet lay afhen kefetek tehadso lezelalem yewedem begashaw yaden hendew henayalen

  18. Anonymous March 24, 2016 at 10:35 am Reply

    NSHA MIN ENDHONE TAWUKALEH?

  19. Anonymous March 24, 2016 at 2:03 pm Reply

    እነ በጋሻው እንደ ጆፌ አሞራ ለሚያንዣብቡባት ለሆሳዕናም ይህ ዓይነት ጉባኤ ያስፈልጋታል

  20. Anonymous April 2, 2016 at 5:15 pm Reply

    እጎዚአብሔር ቦናቸውን ያብራልን

  21. Anonymous February 10, 2018 at 11:19 am Reply

    አሜን

Leave a reply to Anonymous Cancel reply