ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ

His Grace Abune Yared

ብፁዕ አቡነ ያሬድ፤ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊና የሶማሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ

ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ባለፈው ሳምንት ሰኞ በሞተ ዕረፍት በተለዩት የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ምትክ፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ደርበው እንዲሠሩ መደባቸው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ ብፁዕነታቸውን የመደባቸው፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ የጀመረውን ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በመፈራረምና በወቅታዊ ጉዳዮች መግለጫ በማውጣት ባጠቃለለበት ውሎው ነው፡፡

ብፁዕ አቡነ ያሬድ በአኹኑ ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊና የሶማል/ጅግጅጋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው በመሥራት ላይ ይገኛሉ፡፡

በሀገረ ስብከቱ በሰሞኑ ግጭት የቃጠሎ ጉዳት ስለደረሰባቸው አብያተ ክርስቲያናት ጉዳይ የተወያየው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ከጠቅላይ ቤተ ክህነቱና ከሀገረ ስብከቱ በተውጣጣ ልኡክ ተጨማሪ ማጣራት እንዲካሔድና አስፈላጊው የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንዲደረግ በመወሰን ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡

የብፁዕ አቡነ ናትናኤል ሥርዐተ ቀብር በአሰላ ደብር ቅዱስ ደብረ መዓዛ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ገዳም ባለፈው ኃሙስ በተከናወነበት ወቅት፤ የልዩ ልዩ እምነት ተከታዮች፤ የዞኑ የመንግሥት ባለሥልጣናትና የእምነት ልዩነት ሳያደርጉ በገዳሙ የሚያሳድጓቸው ወጣቶች፣ “የሀገርና የሕዝብ አባት” በማለት በብፁዕነታቸው መለየት መሪር ሐዘናቸውን ገልጸዋል፤ ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ ብፁዕነታቸው ያለ ደግ አባት እንዲመድብላቸውም ጠይቀዋል፡፡

ለብፁዕ አቡነ ያሬድ መልካም የአገልግሎት ዘመን እንመኝላቸዋለን፡፡

Advertisements

2 thoughts on “ብፁዕ አቡነ ያሬድ የአርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ኾነው ተመደቡ

  1. weyinshet fikre March 8, 2016 at 3:42 am Reply

    አሜን አምለከ ቅዱሳን በሁሉ እያደመ ሙሉ ጤና ከረጅም እድሜ ጋር ያድልልን የብፅዕ አቡነ ናትናኤል ደግና ትሁት ጠቢብ አገልጋይ በረከታቸው ይደርብን ለአባታችንም ለአቡነ ያሬድ የበረከትና የደስታ ዘመን ይሁንሎ ቤተክርስቲያናችንን ከጥፋት ህዛቧንም ከስደት ከክህደት ካለማመን ይጠብቅልን አሜን

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: