ቅዱስ ሲኖዶስ: ፓትርያርኩ ሕግ አክብረውና መዋቅር ጠብቀው እንዲሠሩ አስጠነቀቃቸው፤ በሰላም ጉዳዮች ዛሬ መግለጫ ያወጣል

 • በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው መመሪያዎችና የጠሯቸው ስብሰባዎች ሕገ ወጥ ተብለዋል
 • ቋሚ ሲኖዶስ፥ የስምዐ ጽድቅን የፀረ ተሐድሶ ጽሑፍ ጨምሮ የተደረጉ መጻጻፎችን ይመረምራል
 • የፓትርያርኩ ጉዞዎች፥ ስፖንሰር ተገኘ በሚል ሳይኾን በቋሚ ሲኖዶሱ ማስወሰን ይኖርባቸዋል

Holy Synod on the excution of Eth Ortho christians in Libya
ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ መዋቅር ጠብቀው በሕገ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ተግባራቸውን እንዲያከናውኑና ሓላፊነታቸውን እንዲወጡ በቅዱስ ሲኖዶስ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው፡፡

ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ ባለፈው ሳምንት ዓርብ ከቀትር በኋላ ባካሔደው ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ፣ በማኅበረ ቅዱሳን ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ጽሑፎች ላይ ቀርበዋል ለተባሉ አቤቱታዎች የነበራቸውን አያያዝ፣ የወሰዷቸውን አቋሞችና የሰጧቸውን ምላሾች ገምግሟል፡፡

ፓትርያርኩ አቤቱታዎቹን ለመመልከት በሚል በራሳቸው የጠሯቸው የኮሌጆችና የጠቅላይ ጽ/ቤቱ መምሪያዎች ሓላፊዎች ስብሰባዎች፤ ማእከላዊ አሠራርን ያልጠበቁና አድሏዊ እንደነበሩ ጉባኤው ተችቷል፡፡ ከዚኽም ጋር በተያያዘ ፓትርያርኩ፣ ከልዩ ጽ/ቤታቸው በተጻፉ ደብዳቤዎች በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያስተላለፏቸው የክሥና የቅስቀሳ መመሪያዎች የቅዱስ ሲኖዶስን የምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መንፈስ የሚፃረሩና ሕገ ወጥ መኾናቸውን ያረጋገጠ ሲኾን በስብሰባዎቹ ወጥተዋል የተባሉ የአቋም መግለጫዎችም ተቀባይነት እንደማይኖራቸው ተገልጧል፡፡

ፓትርያርኩ ዛሬ ለተጀመረው ዐቢይ ጾም ባለፈው ሳምንት ዓርብ መግለጫ በሰጡበት አጋጣሚ፣ ቋሚ ሲኖዶሱ በብፁዕ ዋና  ጸሐፊው አማካይነት በጠራው በዚኹ ድንገተኛ ልዩ ስብሰባ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን በኃይለ ቃል ለማሸማቀቅ ሞክረዋል፤ ማኅበሩንም በተመለሱ ጥያቄዎችና በአሉባልታዎች ወንጅለዋል፡፡ “የማኅበሩ አባላት ናችኹ፤ ሒዱ ስላላችኹ ነው የመጣችኹት” በማለት የተናገሩት ፓትርያርኩ፣ ማኅበሩንም “ሀብታሞች ኾነዋል፤ ከመንግሥትም ገንዘብ ይሰበስባሉ፤ መንግሥት ይረዳቸዋል፤” እስከ ማለት ደርሰዋል፡፡

ተንኮል የተሸረቡባቸውንና በክፋት የተሞሉ መረጃዎችን ሳያጣሩና ሳይመዝኑ እንደተነገራቸው የሚያስተጋቡት ፓትርያርኩ፣ እኒኽን ኃይለ ቃላት የተናገሩበት የረፋድ ወኔ ግን አብሯቸው አልዘለቀም፡፡ ስብሰባው ከቀትር በኋላ ሲጀመር አንሥቶ ከፍተኛ መደናገጥ ታይቶባቸዋል፡፡ ማእከላዊ አሠራርን ሳይጠብቁ የፈጸሟቸውን መተላለፎች፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ በዝርዝር ለጉባኤው ያሰሙ ሲኾን በማኅበሩ ላይ ለሰነዘሯቸው ክሦችም ማስረጃቸውን እንዲያቀርቡ ጠይቀዋቸዋል፤ የማኅበሩ ዋነኛ የድጋፍ ምንጭ የአባላቱ አስተዋፅኦ መኾኑን የጠቀሱት ብፁዕነታቸው፣ በሒሳብ አሠራሩም ጠቅላይ ጽ/ቤቱ ከማኅበሩ ብዙ የሚማረው እንዳለም አልሸሸጉም፡፡

ለመዋቅራዊ መተላለፋቸውም ኾነ ከማኅበሩ አንጻር ለቀረቡላቸው የተጨባጭነት ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ያልሰጡት ፓትርያርኩ፣ ማእከላዊ አሠራርን ባለመጠበቅ በፈጸሟቸው ተግባራት በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ “አዋረዱን፤ አፈርንብዎ” እስከመባል የደረሰ ቅሬታ ቀርቦባቸዋል፤ በከፍተኛ ደረጃም ተገሥጸዋል፡፡

ፓትርያርኩ ከመዓርገ ክብራቸው አኳያ ከመሰል የደብዳቤ መጻጻፎች እንዲታቀቡ ጉባኤው በጥብቅ አስጠንቅቋቸዋል፤ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አደጋ በኮሌጆች የሚገኝበትን አስከፊነት አስመልክቶ የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ በዳሰሳ ጥናት ላይ ተመሥርቶ ያወጣውን ጽሑፍ ተከትሎ ፓትርያርኩ የሰጧቸው መመሪያዎችና ከማኅበሩ ጋር የተመላለሷቸው ደብዳቤዎችም በቋሚ ሲኖዶሱ እንዲመረመሩ በጉባኤው ተወስኗል፡፡ በይቀጥላልም ጉባኤው፣ ፓትርያርኩ በመሰል ጉዳዮች አስፈጻሚ የአስተዳደር አካላትን በቀጥታ መሰብሰባቸው ስሕተት በመኾኑ፣ ከብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋር እየተነጋገሩና በቋሚ ሲኖዶስ እየመከሩ ሕጉን አክብረውና መዋቅሩን ጠብቀው ከአድልዎ የጸዳ አመራር መስጠት እንደሚኖርባቸውም በጥብቅ አሳስቧቸዋል፡፡

pat mathias and Nebured
ግለ ታሪካቸውን ከማበላሸት አልፎ በክፉ ምክሮችና በሕገ ወጥ ደብዳቤዎች ቤተ ክርስቲያንን እያሳጣና እያስነቀፈ የሚገኘው የልዩ ጽ/ቤታቸው አሠራር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን በእጅጉ አሳስቧል፤ የልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃና የክፋት ተባባሪዎቹ ጉዳይም አስቸኳይ እልባት እንደሚያስፈልገው ከድንገተኛ ልዩ ስብሰባው በተጓዳኝ በስፋት የተመከረበትና አቋም የተያዘበት ወቅታዊ ነጥብ ኾኗል፡፡

የፓትርያርኩ የሀገር ውስጥም ኾነ የውጭ ጉዞ፣ ቋሚ ሲኖዶስ አስቀድሞ እያወቀው በዕቅድ መከናወን ያለበት ቢኾንም “የራሳችንን ወጪ ሸፍነን ቅዱስነታቸውን እናጅባለን” በሚሉ አማሳኝ ግብረ በላዎች ጭምር የቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ያለዕቅድ እየወጣ የሚባክንበት፤ ፓትርያርኩ እንደ ርእሰ መንበር  ሐዋርያዊ ተልእኳቸውንና አባታዊ ሓላፊነታቸውን ቤተ ክርስቲያኒቱን ለመወከል በሚያበቃ መልኩ የሚወጡበት ከመኾን ይልቅ “ስፖንሰር ተገኘ” በሚል ብቻ ከፍተኛ ስሕተት(የፕሮቶኮልም) የሚፈጸምበትና ክፋት የሚመከርበት እየኾነ እንደመጣም በጉባኤው ታይቷል፡፡

በመኾኑም ማንኛውም የፓትርያርኩ ጉዞዎችና የሚመደቡ ልኡካን፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያኑ መሠረት ለቋሚ ሲኖዶስ ቀርቦ አስፈላጊነቱ ታምኖበት ሲወሰን የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንተ ክብርና ሉዓላዊነት እንዲኹም የመንበረ ፕትርክናውን ፕሮቶኮል በጠበቀ ደረጃ እንዲፈጸም ጉባኤው አሳስቧል፡፡

ስለ ተቃጠሉ አብያተ ክርስቲያናት ከጠቅላይ ቤተ ክህነትና ከሚመለከታቸው አህጉረ ስብከት በሚመደቡ ልኡካን ተጨማሪ ማጣራት እንዲካሔድና አስፈላጊው የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ እንዲደረግ የወሰነው ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ በአገራችን ወቅታዊ የሰላም ጉዳዮች ላይም የመከረ ሲኾን በዛሬው ዕለትም በድንገተኛ ልዩ ስብሰባው ቃለ ጉባኤዎች ላይ በመፈራረም መግለጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡

 

 

 

 

Advertisements

38 thoughts on “ቅዱስ ሲኖዶስ: ፓትርያርኩ ሕግ አክብረውና መዋቅር ጠብቀው እንዲሠሩ አስጠነቀቃቸው፤ በሰላም ጉዳዮች ዛሬ መግለጫ ያወጣል

 1. Haftom Gebrehoiiwot March 7, 2016 at 7:25 am Reply

  አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር!!!
  ኦ አምላከ አበዊነ ቅዱሳን ዕቀቦሙ ነዊሐ መዋዕለ ላአበዊነ ጳጳሳት ወዕቀባ ለቤተ ክርስቲያንነ እመናፍቃን ከሐድያን፡፡
  እግዚአብሔር ይባርክሙ ሐራ ተዋሕዶ!!!

 2. Anonymous March 7, 2016 at 7:57 am Reply

  በክፉ ምክሮችና በሕገ ወጥ ደብዳቤዎች ቤተ ክርስቲያንን እያሳጣና እያስነቀፈ የሚገኘው የልዩ ጽ/ቤታቸው አሠራር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን በእጅጉ አሳስቧል፤ የልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃና የክፋት ተባባሪዎቹ ጉዳይም አስቸኳይ እልባት እንደሚያስፈልገው ከድንገተኛ ልዩ ስብሰባው በተጓዳኝ በስፋት የተመከረበትና አቋም የተያዘበት ወቅታዊ ነጥብ ኾኗል

 3. Anonymous March 7, 2016 at 8:16 am Reply

  የሠላም ባለ ቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ሠላመ ቤተክርስቲያን ይጠብቅልን!

 4. Anonymous March 7, 2016 at 8:52 am Reply

  mech ysemaluna mesmiyachw nbure ed kaltefa bekere

 5. sileshi demelash March 7, 2016 at 9:39 am Reply

  Tebakiyachin ayankelafam

 6. Anonymous March 7, 2016 at 10:25 am Reply

  እግዚአብሔር በምህረቱ ቤተ ክርስትያናችንን ይጠብቅልን፡፡

 7. Mulatu March 7, 2016 at 10:26 am Reply

  አባቶቼን አምላክ ይጠብቅልን

 8. Anonymous March 7, 2016 at 10:30 am Reply

  Just Synod

 9. Anonymous March 7, 2016 at 12:58 pm Reply

  e/r eyale mene enhonale

 10. Nakachew Getnet March 7, 2016 at 1:16 pm Reply

  እግዚአብሔር በምህረቱ ቤተ ክርስትያናችንን ይጠብቅልን፡፡ አባቶቼን አምላክ ይጠብቅልን

 11. Anonymous March 7, 2016 at 1:27 pm Reply

  እነዚህ ዻዻት የቤተክርስቲያን ጠባቂዎች ወይስ የማቅ ጠባቂዎች ናቸው አከብራቸው ነበር የቤተክርስቲያን ጠባቂዎች መስለውኝ እንደ ቅዱስ መጽሐፉ ቃል”በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት” እንደሚል አሁን ግን ቤተክርስቲየን የሚለው ማቅ በሚል ለቀየሩት አዘንኩላቸው ይህ የምትለው ወይም የፃፍከው እውነት የነሱ ሃሳብ ከሆነ።

  • Anonymous March 7, 2016 at 3:21 pm Reply

   Leboo tehadiso err………dibinn….. bel

  • ኃይለ ስላሴ March 7, 2016 at 6:56 pm Reply

   ቱልቱላ መናፍቅ ዘረኛ አንተ ብሎ ጥቅስ ደርዳሪ፣ማፈሪያ እና ምን እንዲሆኑ ነው የፈለከው?አንተ የምትፈልገውን ዘረኛ?ተሃድሶ መናፍቅ?ፓስተር?

   • Anonymous March 9, 2016 at 1:20 pm

    እናንተ የእነዚህ ዻዻሳት ፍሬ መሆናቹ ያሳያል ም/ቱም ተሳዳቢ ናችሁና አቡነ ማትያስ ግን ንጹህና ነውር የሌላቸው አባት ናቸው ከማቅ ጋር መጣላታቸው በራስ መተማመን ያላችውና እንደነ አባ – – – አለመሆናቸው ነው የሚያሳየው እኔን በተመለከተ እኔና እናንተ በቤተክርስቲያን ትምህርት ፍርድ ብንቀመጥ እናንተ ሊቀ መናፍቃን ትሆኑ ነበር

  • Anonymous March 9, 2016 at 4:11 pm Reply

   really yes they are correct

 12. Anonymous March 7, 2016 at 1:30 pm Reply

  መልካም እረኛ ማለት እንዲህ ነው።

 13. Akele Getnet March 7, 2016 at 2:10 pm Reply

  እግዚአብሔር ይመስገን ሐሰት ቢገንም እውነትን አታሸንፍም፡፡

 14. […] ግለ ታሪካቸውን ከማበላሸት አልፎ በክፉ ምክሮችና በሕገ ወጥ ደብዳቤዎች ቤተ ክርስቲያንን እያሳጣና እያስነቀፈ የሚገኘው የልዩ ጽ/ቤታቸው አሠራር ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱን በእጅጉ አሳስቧል፤ የልዩ ጸሐፊው ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃና የክፋት ተባባሪዎቹ ጉዳይም አስቸኳይ እልባት እንደሚያስፈልገው ከድንገተኛ ልዩ ስብሰባው በተጓዳኝ በስፋት የተመከረበትና አቋም የተያዘበት ወቅታዊ ነጥብ ኾኗል፡፡ Continue reading→ […]

 15. Selamu March 7, 2016 at 3:19 pm Reply

  The EOTC Holy Synod deserves the highest compliments for demonstrating its courage at a time when its authority has been completely ignored. After all, according to EOTC regulations including the Fiteha Neguest, the Holy Synod is the church’s top authority under the directives of the Holy Spirit.

  The current and previous Patriarch (Abune Mathias and Abune Paulos) have repeatedly disrespected and ignored the Holy Synod. Examples of these unacceptable actions (or lack of actions) against the Holy Synod include the continuing presence of Abune Paulos’ statue although a clear decision had been made to remove it. Another example is the recent trip by Abune Mathias to Rome to meet with Pope Francis I without first obtaining the EOTC Holy Synod’s approval.

  The outcome of Abune Mathias’ meeting with Pope Francis I is yet to be declared. It would be a great shame if Abune Mathias failed to make a strong case with regard to the need for a Vatican apology to the Ethiopian people for its complicity with Fascist Italy.

  With regard to controversies concerning Mahbere Kidusan which is, in the most, a highly respected orgaznization, the normal process should be for a task force to be established by the Holy Synod to look into the issues in depth and arrive at an appropriate decision after a comprehensive and a fair consideration.

  May the Almighty God bless our beloved church and country and render the Patriarch and his supporters to exercise their authority in accordance with the church’s directives based on justice and the truth. May He also relieve us from the on-going shameful and dangerous level of corruption withing the church.

 16. Kassa belet March 7, 2016 at 4:29 pm Reply

  ውጭ ሀገር የሚገኙት ጻጻስ በዚህ በሲኖዳስ ስብስባ ላይ ለምን አይገኘም ወይስ ቩመታቸው ለዘላለም ነው ይታስበት ብዙ ጥፍቶች እየተጠረ ነውና

 17. ቹቹ ፀጋዬ March 8, 2016 at 6:18 am Reply

  አልቦ ነገር ዘይሰአኖ ለእግዚአብሔር !!!
  ኦ አምላክ አበዊነ ቅዱሳን ዕቀባ ለቤተክርስቲያንነ
  እመናፍቃን ከሐድያን።

 18. Anonymous March 8, 2016 at 6:34 am Reply

  ውጭ ሀገር የሚገኙት ጻጻስ በዚህ በሲኖዳስ ስብስባ ላይ ለምን አይገኘም ወይስ ቩመታቸው ለዘላለም ነው ይታስበት ብዙ ጥፍቶች እየተጠረ ነውና

 19. Anonymous March 8, 2016 at 6:38 am Reply

  Betam des yilal Egziabhair endemayitewen eregetgna neberku!

 20. Anonymous March 8, 2016 at 7:44 am Reply

  እናንተ የእነዚህ ዻዻሳት ፍሬ መሆናቹ ያሳያል ም/ቱም ተሳዳቢ ናችሁና አቡነ ማትያስ ግን ንጹህና ነውር የሌላቸው አባት ናቸው ከማቅ ጋር መጣላታቸው በራስ መተማመን ያላችውና እንደነ አባ – – – አለመሆናቸው ነው የሚያሳየው እኔን በተመለከተ እኔና እናንተ በቤተክርስቲያን ትምህርት ፍርድ ብንቀመጥ እናንተ ሊቀ መናፍቃን ትሆኑ ነበር

 21. Anonymous March 8, 2016 at 8:16 am Reply

  please Just once talk about Jesus Christ He is the truth, the way and the life! you always talk about you mahiberkidusan …. it can’t save people by itself and you always insult the fathers, you don’t have any respect for them because you sat on God’s chair , always you blame other, first be saved by believing Jesus! then you will see clearly what is Christianity
  mean

 22. bahran tariku March 8, 2016 at 9:38 am Reply

  እግዚአብሄር ቤተክርሰቲያናችንን ከተሀድሳ መነፍቃ ይታደጋት ዘንድ የተዋህዳ እንቁ ልጆች ተግታችሁ ፀልዩ

 23. DANI March 8, 2016 at 10:51 am Reply

  ፀልዩ በእንተ ሰላመ ቤተክርስቲያን!!!!!!!!!!!

 24. addisalem March 8, 2016 at 3:38 pm Reply

  Yechi tentawi ena kedamawi yehonche yenoh merkeb ersu yetebekat enji manem yelatem yehun enji sel ewenet yemiteguten yekerb sewoche ersu yerdachew!!!!!

 25. Anonymous March 8, 2016 at 6:55 pm Reply

  በውሸት ተጸንሶ በውሸት ተወልዶ በውሸት ያደገና በውሸት ወደ መቃብር አፋፍ የደረሰ የመናፍቃንና ጆቢራዎች ስብስብ ማኅበረ ሰይጣን አቡሃ ለሐሰት ተብሎ በተገሰጸው ዲያብሎስ መንፈስ በመነዳት አስቀድሞ ከቁጥጥሩ ሥር ባዋናቸው ግብረ በላ እና ምግበረ ብሉሾች አንዳንድ ጳጳሳትና እንዲሁም በሰው ታሪክና ጀግንነት ስም ዕድሜልክ ስያጭበሩብሩ የኖሩት የቅድመ አያቶቻቸውን ብልሹ ተራክ ለመድገም ደፋ ቀና በሚሉት ፖለቲከኞች መሰል ጳጳሳት በእውነተኛውና መናኝ ቅዱስ ፖትርያርክ ላይ የሞከሩት የማቅ ጠበቃነት በዜሮ ተባዝቷል፡፡ በሐራ እንደሰማነው ሳይሆን ቅዱስ ፓትርያሪኩ ከላይ ተደራጅቶ ለገቡት፡ የሰጣቸውን አምላካዊ መመሪያ ጥለው የማቅ ቅጠረኛ ጳጳሳት ከዛሬ ጀምረው ሚናቸውን እንዲለዩና ቅዱስነታቸውም ቤተክርስቲያኒቱን ከመጠበቅና ከማስጠበቅ ወደኋላ እንደሚያሉ አረጋግጧል፡፡ በመጨረሻም በአባ ሉቃስና በአባ ማቴዎስ ግፊት ተዘጋጅቶ በድብቅ ለፌርማ ቀርቦ የነበረውንም ቃለጉባኤና ምግለጫ ሙሉ በሙሉ ተቀይረዋል፡፡ ለዚህም የወጣውን መግለጫ ማንብብ በቂ ነው፡፡ማቅ በመንፈሳውያን ኮሌጆች የጻፈው ሕገ ወጥ ድርጊትም በሚገባ እንዲታይ እንዲመረመር መደረጉ ማቅ ለማዳን እንደተወሰነ በማስመሰል መቅረቡ እጅግ አስገራሚ ነው፡፡
  የዚህ እውነታ በሁለት ሦስት ቀን ውስጥ እናየዋለን፡፡

  Our beloved Patriarch Mattias, we are so proud of you, we the scholars, priests, preachers, true followers of our mother church; which is the Ethiopian Orthodox Tewahdo church, are with you, without us the some bishops who engaged with mk can not do anything without you and us, we can provide you all the necessaries documents, if they are not ready to repent from their mistake, they can get their wage of sin,
  once again we so proud of you

  Hara post it \
  if you do not post it I do not have any problem up to you

 26. Asfaw March 8, 2016 at 7:24 pm Reply

  ቅዱስ ሲኖዶስ ትንሽ ቢዘገይም አሁን ያስተላለፈው መልዕክት ግን በጣም አስደስቶኛል፡፡

 27. BFD March 9, 2016 at 11:15 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን እኮ የእግዚአብሄር ቅዱስ መንፈስ በበቁ አባቶች ላይ አድሮ ተኩላ ቀበሮ ውሻና አይጥ በቤተክርስትያን ቅጥር ግቢ እንዳይገባ አጥር አድርጎ የሠራው ነው፡፡ እግዚአብሄር የሠራውን ማንም ሊያፈርሠው አይችልም፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር የተጣሉ አማሳኞች ተሀድሶዎች እና ዘረኞች ግን ይጠሉታል፡፡

 28. […] on account of his pro-TPLF activities and dictatorial tendencies, according to report appearing on Hara ZeTewahdo. While requesting the patriarch to live by Church rules, the Synod’s statement has in […]

 29. Anonymous March 9, 2016 at 4:15 pm Reply

  really our fathers are made history

 30. Gosa Hailemeskel March 10, 2016 at 3:25 am Reply

  እግዚአብሄር ቤተክርሰቲያናችንን ከተሀድሳ መነፍቃ ይታደጋት ዘንድ የተዋህዳ እንቁ ልጆች ተግታችሁ ፀልዩ

 31. Anonymous March 10, 2016 at 8:57 am Reply

  AMLAKACHIN LEGNAM LE ABATOCHACHINM NISTUH LIB YIFTERLN!!!!!!!!

 32. Anonymous March 15, 2016 at 11:54 pm Reply

  Betekresetiyanene YalTbaki Yaletwat amelak Yekber Yemesgen!!!!!

 33. Anonymous March 22, 2016 at 9:11 am Reply

  derona Zendero;
  Dero haymanot Tqset;seerat teguadele sibale hulum Kefowe endetenekabete Neeb Ho belo bmnsate asefelagiwene eremete Yewesede nbre. ahene gene
  Museena
  Kehedete
  Nufakie
  Gotegnnete…. sefene Seerat Tetase, hulume nger xdega weste nwe xYtabale hulume zeem. Lmen Yehon????

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: