ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ መምሪያ ምላሽ ሰጠ፤ የስምዐ ጽድቅ ጽሑፍ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ግዴታችን አካል ነው፤ ደብዳቤውም መድረክ ስለተነፈገንና ፍትሕ ስለተጓደለብን ነው

 • ጋዜጣው ጽሑፎች፣ «መንፈሳዊ ኮሌጆቹ በአጠቃላይ የመናፍቃን መፈልፈያ ናቸው» አይሉም
 • በጋዜጣው አጻጻፍ አንዳንድ የቃላት አጠቃቀሞች ላይ ቅሬታ ካለ ለመወያየት ዝግጁዎች ነን
 • ጉዳዮቹን እንድናስረዳና የተፈጠረውንም ችግር ለመረዳት የውይይት መድረክ ይዘጋጅልን
 • በተለያየ መንገድ እንደጠየቅነው፣ በአካል የመወያያ ዕድል ማጣታችን በእጅጉ ያሳዝነናል 
 • ለሚታረም ነገር እርምት መውሰድና ስናጠፋም ይቅርታ መጠየቅ የአገልግሎታችን መርሕ ነው

*           *          *

 • ሰዎች እንደመኾናችንና ልንሳሳት ስለምንችል፣ በማንኛውም ደረጃ ተወያይተን የሚታረም ነገር ካለ አስፈላጊውን እርምት መውሰድ እና በትክክል ጥፋት እንዳጠፋንም ስንረዳ ይቅርታ መጠየቅ አንዱና ዋነኛው የአገልግሎታችን መርሕ ነው፡፡
 • በሀገራችን የተከሠቱትን ማኅበራዊ ችግሮች ለመፍታት ኹሉም አካል በየዘርፉ በሚረባረብበት በዚኽ ወቅት፣ ትልቅ ሓላፊነት ያለባት የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን አባትና ልጆች እንዲህ ዓይነት ደብዳቤዎችን በመጻጻፍ መጠመዳችን በእጅጉ አሳዝኖናል፡፡
 • ሕግ አውጥቶ፣ ሥርዓት ሠርቶ የሰጠን የቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻ ውሳኔ ሰጪ አካል የኾነው ቅዱስ ሲኖዶስ፣ በማኅበሩ አገልግሎቶች ላይ አኹንም እየተፈጠሩ ያሉት ዕንቅፋቶች እንዲታዩልንና አስፈላጊው እርምት እንዲደረግልን በታላቅ ትሕትናና አክብሮት እንጠይቃለን፡፡ (የደብዳቤውን ሙሉ ይዘት ከዚኽ በታች ይመልከቱ)007008009010

 

Advertisements

39 thoughts on “ሰበር ዜና – ማኅበረ ቅዱሳን ለፓትርያርኩ መምሪያ ምላሽ ሰጠ፤ የስምዐ ጽድቅ ጽሑፍ የቅ/ሲኖዶስን ውሳኔ የማሳወቅ ግዴታችን አካል ነው፤ ደብዳቤውም መድረክ ስለተነፈገንና ፍትሕ ስለተጓደለብን ነው

 1. Anonymous February 29, 2016 at 5:28 pm Reply

  ግሩም!

 2. Anonymous February 29, 2016 at 5:49 pm Reply

  ምድረ መናፍቅ ምን ይዋጥህ ?እርር ድብን በል::ማህበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያን ቀኝ እጅ ነው :: ከእግዚአብሔር የሆነ ሁልጊዜ አሸናፊ ነው ::

 3. Anonymous February 29, 2016 at 9:24 pm Reply

  Gud bel Gonder

 4. Anonymous February 29, 2016 at 9:38 pm Reply

  እግዚአብሔር ሁሌ ከኛ ጋር ነው ስራችሁን በትጋትና በጸሎት ቀጥሉ የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል አማላጅነት የቅዱሳኑ ጸሎት ሁሌ ይምራን አሜን፡፡

 5. Anonymous February 29, 2016 at 9:45 pm Reply

  መሐበረ ቅዱሳን የቤተክርስቲያናችን የጀርባ አጥንት የአገልግሎት ዘመናችሁ ይባረክ

 6. Anonymous February 29, 2016 at 10:30 pm Reply

  Egziabher hoy kegna gar hun amen amen amen amen

 7. Milkessaa Dawit March 1, 2016 at 1:39 am Reply

  “…መመሪያ ላለመቀበል …no no .ለመቀበል ተቸግሮ አያዉቅም

 8. Anonymous March 1, 2016 at 5:09 am Reply

  በጣም ጥሩ

  • Anonymous March 1, 2016 at 6:03 am Reply

   JIL SET WETWA YITMAYAL JILU MAHBERE KIDUSAN M YELELEWN MANINET ALEGN BIL MEJAJAJALU NEW ENJI MAHBER BETEKRSTIYANIN AYWEKLIM Kkkkkk Aretew Hara Hodsiyawk Doroma new

 9. Anonymous March 1, 2016 at 5:54 am Reply

  indinew metazez

 10. Anonymous March 1, 2016 at 6:08 am Reply

  አምላከ ቅዱሳን ከኛው ጋር ነውና አይዞአችሁ ፈተናው በድል ይጠናቀቃል፡፡

 11. Anonymous March 1, 2016 at 6:24 am Reply

  gurenoch

 12. Anonymous March 1, 2016 at 7:02 am Reply

  ቅዱስ ሲኖዶስ ፈርጁ የሚል ሥልጣን አልሰጣችሁም፡፡ተከታይ ለማስደሰት ሲባል ፣ እንዲህ ተናገሩ ለመባል፣ጎበዝና ከሁሉም የቤተክርስቲያኒቱ አካላት በላይ ለቤተክርስቲያን የሚቆረቆሩ ለመባል እየሄዳችሁበት ያለው እብሪት ከሞላ ጎደል ታውቋል፡፡ ቦርዱ ከተራ አባላት የተሻለ እና የሰከነ አመራር ማሳየት ሲገባው የአባላቱን የማኅበራዊ ሚዲያ መራሽ ስሜታዊነት ተከትሎ እያደረጋቸው ያሉ የተዛቡ ግንኙነቶች አሳሳቢ ናቸው፡፡ ዘላቂ ራዕይ ካላችሁ ግንኙነታችሁን አስተካክሉ፡፡ የግንኙነቱን መግዣ ያደረጋችሁት ፍቅርና መግባባትን ሳይሆን የተናገራችሁን ሁሉ ተደራጅቶ ስም በማጥፋት አንገት ለማስደፋት መሞከርን ነው፡፡

  ከላይ እስከ ታች ያሉ አባላት ለመናገር እንጂ ለማዳመጥ ዝግጁ አይደሉም፡፡ ሲበዛ እንከን ፈላጊነትና አማርኛ ፈላጭነት ይስተዋላል፡፡ ይህ የልጅ ተግባርን ያፋለሰ አካሄዳችሁ ወደ ሰ/ቤት እየተዛመተ ችግር እየፈጠረ ነው፡፡ ማኅበሩ ሁልጊዜ ከሁከት ጋር ስሙ መያያዙ በጊዜ ሂደት የሚፈጥረው አሉታዊ ጉዳት አለ፡፡ ሲበዛ የይስሙላ ታዛዥነት ታንጸባርቃላችሁ፡፡ብዙ ተቋማትና አህጉረ ስብከቶችን የምትመራ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ስማችሁ ከሚገባው በላይ ባለመግባባት የሚነሳ የእናንተ ብቻ ነው፡፡ በዚህ ላይ ትችትና ተግሳጽ ሲሰጥ ለመቀበል ያላችሁ ዝግጅት እጅግ በጣም አሳፋሪ ነው፡፡ ቤተ ክህነቱ የጻፋቸውን ደብዳቤዎች ተከታትሎ አያስፈጽምም የሚል ንቀት ስላለ እኩል መመላለስ ተለምዷል፡፡ ለተናገራችሁ ሰው ሁሉ ስም ማውጣት ከባድ የአፈና እና የድፍጠጣ ባሕሪ ነውና አስቡበት፡፡

  ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ማኅበረ ቅዱሳን እያሳየ ያለው ከመዋቅር ደጋፊነት ይልቅ የተገዳዳሪነት አዝማሚያ የተጠናወተው አካሄድ ጤነኛ አይደለም፡፡የማያቋርጥ አተካሮው በጣም አሰልቺ ሆኖብናል፡፡በተተኪው ትውልድ አእምሮ ላይም ጥሩ ያልሆነና አርአያነት የሌለው ተውፊት እያሰረጻችሁ ነው፡፡ይሄን ለማረጋገጥ ማኅበራዊ ሚዲያው ላይ በንቃት የሚሳተፉ አባላቶቻችሁን ጽሑፎች ይዘት በዳሰሳ መልኩ መፈተሽ ይቻላል፡፡በእነዚህ ማኅበራዊ መድረኮች ያሉ የማኅበሩ ሰዎች ማኅበሩ ላይ ምንም አይነት ትችት የሚሰነዝርን ሰው እንደ ክርስቲያን አያዩም፡፡ማኅበረ ቅዱሳን ላይ የተለየ አስተያየት መስጠት ሃይማኖትን እንደመካድ እየተቆጠረ ነው፡፡ይህም ማለት ማኅበሩ ሃይማኖቱን ተክቷል እንደማለት ሆኗል በአባላቱ አስተሳሰብ፡፡ማኅበሩ የአባላት ስነ ምገባር ላይ ብዙ መስራት ይጠበቅበታል፡፡

  አሁን ባለው ሁኔታ የማኅበሩ አባላት በማኅበራዊ ሚዲያው የሚንጸባረቅ አዝማሚያ ቤተክርስቲያንን ለነቀፋ የሚዳርግ ነው፡፡እየፈራችሁት ያለው ትውልድ እውቀትና ትሕትና መራሽ ስለመሆኑ በአደባባይ ቢናገርም በማኅበራዊ ሚዲያው የሚንጸባረቀው ባሕሪ ግን ሲበዛ ስሜታዊነትና ልክ የሌለው ራስን በመቆለል የተሞላ ጀብደኝነት የሚነበብበት ነው፡፡ማኅበሩ በሚዲያው ያለውን የበላይነት ሁለንተናዊ ቤተክርስቲያን ጥቅምና መዋቅራዊ አንድነት ለማስጠበቅ ሳይሆን ለጠባብ ማኅበር ተኮር ገጽታ ግንባታ እያዋለው ነው፡፡የሚያዳምጥ ጆሮና የሚያስተውል ልብ ሳይሆን ሁሉን ነገር አውቃለሁ ባይነትና የራስን አካዳሚክ ባክግራውንድ ተገን በማድረግ ተቋማትን የማቃለል ግልጽ አካሄድ አለ፡፡

  የምትጽፏቸው ደብዳቤዎች ከማንም በላይ ነን ለማለት ያለሙና ሲበዛ በፀጉር ስንጠቃና በለበጣ የተሞሉ ናቸው፡፡ይሄ ስሜታዊ አድርጋችሁ እየቀረጻችሁት ላለው ትውልድ ጊዜያዊ ሆታ ድጋፍ ያስገኛል፡፡ዘላቂ ለሆነ ለማኅበሩ ሕልውና እና አመኔታ ግን አይጠቅምም፡፡ እንደተማረ ሰው ሁኔታውን ብታጤኑት ጥሩ ነው፡፡

  • Anonymous March 1, 2016 at 7:54 am Reply

   Anonimous: አሁን የጻፍከው መልዕክት ትርጉሙ ለራስህ እንኳ ግልጽ አይመስለኝም፡፡ ሲበዛ በጥቅል ቃላት የተድበሰበሰ ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ በደብዳቤ ምላሽ መስጠት ተገቢነት ያለው ትክክለኛ አሠራር መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ከዚያ የተሸለ አሠራር ለመከተል ማኅበሩ ፈልጎ ዕድል ካላገኘ ያለው አማራጭ በዝምታ መጨፍለቅ ወይም አመጽ መስነሣት ሳይሆን ደረጃውን የጠበቀ ደብዳቤ መጻፍ ነው፡፡ የሆነውም ይኸው ነው፡፡ ቢያነስ የሥራ ደብዳቤ እንዴት ደረጃውን ጠብቆ እንደሚጻፍ ያስተምራል፡፡
   ሁለተኛም ለውይይት በር ይከፍታል፡፡ እኔ ያልኩት ካልሆነ ብሎ ድርቅ ማለትና ያም ሊባል የተፈለገው ነገር ሌላ ሳይሆን ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠፋ ሲሆን ከበሳል የቤተ ክርስቲያን ልጅ የሚጠበቀው እንዲህ ያለ የሰላም ዘንባባ የሚመስል መልዕት መላክ ነው፡፡ ሰላም ፈላጊ ዕድሉን ይጠቀማል፡፡ ሌላ ፍላጎት ያለው ደግሞ ሌላ የጥፋት እልህ ውስጥ በመግባት ራሱን ይበድላል፡፡
   የሆነው ሆኖ ግን ይህ መመላለስ ቤተ ክርስቲያንን በብዙ መንገዶች የሚጠቅማት እንደሚሆን አልጠራጠርም፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ሊያስተካክለው የሚገባውን ነገር ለማስተካከል ይገደዳል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የመሸጉ መናፍቃንም ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ይጋለጣሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተንሰራፋው ሙስናና ሥርዓት አልበኝነትም ቢያንስ ይቀንሳል፡፡ ይህ ሁሉ እንዲሆን ሰበብ የሆኑት ፓትርያርክም ሳያውቁት በለኮሱት እሳት ከማንም በላይ ይጎዱበታል፡፡ ለመልካም ባያስቡትም እግዚአብሔር ግን ሥራውን እየሠራባቸው ነው፡፡ ዮሴፍን የጎዱ መስሏቸው ለንግሥና እንዳበቁት እንዲሁ ማኅበሩን የጎዱ መስሏቸው የጥፋት ልጆች በገዛ ራሳቸው ጥፋት ቤተ ክርስቲያንን እየጠቀሟት በመሆኑ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ይክበር ይመስገን፡፡

  • Anonymous March 1, 2016 at 11:46 am Reply

   ante ye Tehadeso agelgay bareya neh.Orthodox Tewahedo lezelalem tenoralech!

  • Anonymous March 1, 2016 at 3:24 pm Reply

   ፍሬህን ቁጠር ማኅበረ ቅዱሳን፡፡እነዚህ ለማኅበራችን ያላጨበጨበ ሐራ ጥቃ ነው የሚሉ ሃይማኖትና ማኅበር በወጉ ለይተው ያላወቁ ተሳዳቢዎች ናቸው የማኅበሩ አሰዳቢዎች፡፡በጣም የሚገርመው አንድ ሰው ማኅበረ ቅዱሳንን እስከ ደገፈ ድረስ የፈለገውን ግለሰብና ጳጳስ ወይም ፓትርያርክ ቢሳደብ አባላቱ ተው፤ለማኅበራችን ያለንን ፍቅር እንደዚህ አይደለም መግለጽ ያለብን አይሉም፡፡እንዲያውም እንዲህ አይነት ስድብ አመንጭ ወጣቶች ስድባቸው እንደ ዝማሬ እና ቡራኬ ነው የሚታየው፡፡የሚሰደበው አካል ደግሞ ይሄን ሁሉ ተቆጪ የሌለው ተሳዳቢ ሲያይ የማኅበሩን አስተሳሰብ በበጎ ለማየት ይቸገራል፡፡ማኅበራችንን እንወዳለን ካላችሁ የሚበርዝና የሚከለስ አስተምህሮ ሲቀርብ ተቃወሙ፡፡በደፈናው ማንም ስለማኅበሩ አይናገር፤ከተናገረ ስም እናወጣለታለን ብሎ በአጓጉል ፈሪሳዊነት መዝመት ምንም አይፈይድም፡፡ምናልባት በገሀዳዊው እና በውስጣዊው አስተሳሰባችሁ መካከል ያለውን እውነተኛና የይስሙላ ባህሪ ለማየት መስታወት ይሆናል፡፡

   የማኅበሩ አባላት የሥነ ምግባር ደረጃ ክፉኛ እያሽቆለቆለና በቀደምቶቹ ምግባር ብቻ ማኅበሩ የዛሬዎቹን አባላቱን ነውር እየሸፈነ እንደሆነ ይሰማኛል፡፡እናንተ ከሁሉም ሰው የበለጠ የተማራችሁ ዶክተሮችና ኢንጅነሮች እንደሆናችሁ ይታወቃል፡፡እናንተ ላይ አስተያየት መስጠት ነውር እንደሆነ ዘወትር አስተያየት በሚሰጡዋችሁ ሰዎች ላይ ሁሉ በምትለጥፉት የመናፍቅነት ፍረጃ ተረድተናል፡፡ግን አንዳንድ ጊዜ የመሐይም ቃል ብተሰሙ አይጎዳችሁም፡፡ስለፈጠራችሁ በፌስቡክ እና በብሎግ ለማኅበሩ ያላችሁን ፍቅር ለመግለጽ ፓትርያርኩንም ሆነ ሌሎችን አካላት ከሰብእና ውጭ የሚያደርግ ቋንቋ አትጠቀሙ፡፡ማኅበሩ በዚህ ረገድ አባላቱን ግንዛቤ እንዲያስጨብጥ የሚል አስተያየት ቢቀርብ ማን ወንድ ነው ለማኅበሩ አስተያየት የሚሰጥ ስለምትሉ ምንም ማለት አይቻልም፡፡በተራ አባላትና ደጋፊነት ደረጃ ግን ለአንደበታችሁ ብትጠነቀቁ ጥሩ ነው፤ማኅበር ያባውን ፌስቡክና ብሎግ ያወጣዋል እየተባለ ነውና፡፡

  • ዳሞት March 1, 2016 at 5:38 pm Reply

   ለanonymous March 1, 2016 at 7:02am
   ከታዛቢነት ወደ አነኒሞስነት በማደግ መልካምና ተገቢ የሆኑትን መልክቶችና ተግባሮች በማጥቆርና በማጠልሸት አንተው ከሰህ አንተው በመፍረድ በምትነቅፈው የድረ ገጽ ሚዲያ ላይ ከእምነት የተነሳ ሳይሆን ከሥጋ ወገንተኝነት የተነሳ የሚመስለውን ተረትህን ጽፈህ ለማስቀመጥ ማንም አይቀድምህ። ገፁን ሞሉት እያልክ እንዳልከሰስህ አመለካከትህን የተቃወመውን ሁሉ ከማህበሩ ነው እያልክ የክስና የሥቀሉልን አይነት ጥሪህን ገፅ ሞልተህ አስቀመጥኸው።
   ትናንት ትሁት ካህን ነኝ ብለህ አንተው አንተነትህን እንዳላሞገስኸው ሌላውን “እኔ ብቻ” በምትል ሀረግ አሳሪነት ቃላት እየቀጠልህ ለማብጠልጠልና ለመንቀፍ ሥትጣጣር ትንሽ እንሿን እኔ እኔን ምን ነኝ ነበር ያልኩት ብለህ ለማሰብ አልሞከርህም።
   ማህበሩ እኔ ብቻ አላለምም አይልም። እንደ ማህበሩ ለእምነት ለቤተክርስቲያናቸው ዛቻና ሥም በማጥፋት ማሸማቀቂያ ሳይገታቸው የሚተጉ ብዙ አሉ። ማህበሩ ሥለሰራው ሥራ ባይናገር እንሿን ሥራ የሰራባቸው ቦታዎች ይመሰክራሉ።
   ለአንተ በተቀደሰው ሥፍራ እርኩሰት አለ መባል በተቀደሰው ቦታ ያለው ሁሉ እርኩስ ነው ተባለ ማለት ነው የሆነብህ። ከእናንተ አንዱ እኔን አሳልፎ ይሰጣል የሚለው የአምላክ ቃል ለአንተ ሁላችሁም አሳልፋችሁ ትሰጡኛላችሁ ማለት የሆነብህ። በሥንዴው መካከልና እክርዳድ መኖሩን መናገር ለአንተ ሥንዴው ሁሉ እንክርዳድ ነው ብሎ መፈረጅ ነው የሆነብህ። ስለ አንድ ነገር መኖር ጥቆማ ማድረግና በአጠቃላይ እንዲህ ናቸው ብሎ መፈረጅ እንደሚለያዩ የምታውቅም አይመስለኝ።
   ማህበሩ መልስ ባይሰጥ ኖሮ ደግሞ ሌላ ታወራ ነበር። ካሁን ቀደም ፓትራርኩን ለማነጋገር ጠይቀው የተከለከሉበትን ያሳዩንና እኔም ተጨምሬ ልጩህ ሥትል ነበር። መልስ ሲሰጡ ደግሞ ክፉና ጠማማ ሥለሆንህ ለምን መልስ ለሰጡ ” ቤተ ክህነቱ ተከታትሉ አያስፈፅም” ተብሎ ነው ሥትል ነገር ትሠራለህ። ለአንተ ቤተክህነት የምትለው ማንን ይሆን?
   በግድ እመን፤ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሁን ያለህ የለምና ለምን ወደ አመንህበት አትሔድምና ቤተክርስቲያንን ለአማኞቿ አትተዋትም። አንዴ ተሐድሶ ፕሮቴስታኒዝም የለም ሥትል፤ ሌላ ጊዜ እነሱን ማን ነው ፈራጅ ያደረጋቸው ስትል፤ ቆየት ብለህ ደግሞ ተሐድሶ የሆኑ አሉ ካሉ በመረጃ ያቅርቡ እያል የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደረቅ አይነት ሆነህ ሥትዘላብድ እንደነበረ አትዘንጋ! ይህ ደግሞ ያንተን ማንነት የሚያመላክት ነው።
   የሲኖዶሱ ልእልና ሲካድ፣ ውሳኔዎቹ ተፈፃሚ እንዳይሆኑ ሲታጎሉና ከፓትራርኩ ጋር ከተሰበሰቡት በአንዳን አለቆችና ሰራተኞች ቅዱሳን አባቶች ሲዘለፉ ምንም አልተሰማህም። ፓትራርኩን የተጠሩበትንና የያዙትን መንበር በማይመጥን ሁናቴ የማይገባ ቃላቶች ሲደመጡ ምንም አላሳሰበህም። ነገር ግን አባታችን ያነጋግሩን ጥፋታችንን ነግረውን ገስፀው መክረው ያርሙን ያሉትን እየገፉ፤ ግፈኞችን፣ ዘራፊዎችንና የእምነት ችግር ያለባቸውን አቅርበው በውሸት ተሸንግለው በተቀመጡበት መንበር ፊት አባቶችን ጀሮአቸው እየሰማ ማሰደብና ምን ሲኖዶስ አለ ማለትን ግን እምነትና የመልካም ሥነምግባር መገለጫ ማድረግህ ማን መሆንህን ያመላክታል።
   እግዚአብሔር ይንካህ!

 13. Anonymous March 1, 2016 at 7:31 am Reply

  ተግሳጽ ለኩሉ
  እኔ ያልገባኝ፡- ፓትርያርኩ የኮሌጁ የበላይ ጠባቂ ሆነው ኮሌጁ በስምዓ ጽድቅ ና በድረ ገጽ የተጻፈው ነገር አግባብ አይደለምና ጸሐፊዎቹ ይጠየቁልኝ ሲል ዝም ማለት ነበረባቸው?
  ሌላው ማኅበሩ ተቋሙን በጅምላ ከሚፈርጅ ግለሰቦችን በስም እየጠራ ቢጽፍ ጥሩ ይሆን ነበር፡፡መቼም ሰው መርካቶ ተሰርቄአለሁ ብሎ መርካቶ የሚኖርን ሁሉ ሌባ ማለት የለበትም፡፡በጥንት የአበው ት/ቤትም እነ አርዮስ እንደወጡ እነ ቅዱስ አትናቴዎስም ወጥተዋል፡፡ተቋምን መስደብ ልክ ነው ታሪክ ይቅር አይለውም፡፡የእኛ ልጅ ልጆች ሁሉ ሲማሩ ያን ታሪክ ያስታውሳሉ ወይም ስለተነቀፈ ብቻ ስንት የቤተ ክርስቲያን የወደፊት ተስፋ የሆኑ ወጣቶች ወደ ዚህ ተቋም እንዳይገቡ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡
  አ.አ. ዩ የታወቀ ተቋም ነው ግን በዚህ ተቋም የተማሩ በጎም መጥፎም የሥሩ ይኖራሉ ግን ግለሰቦች እንጂ ተቋሙ አይወቀስም፡፡
  ሌላው ማኅበሩ ከኮሌጆች የወጡ ምሩቃን ይህን ያህሉ እያለ በ ፐርሰንት ና ለ 25 የፕሮቴስታንት ማኅበራት መሪ እያለ ሲያስቀምጥ በጥናትና በመረጃ ማስቀመጥ ነበረበት፡፡ያም ቢሆን ግን እንደዚህ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? ለቤተ ክርስቲያን ጥቅሙ ይጎላል ወይስ ጉዳቱ? ለእኔ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ለምን? ፕሮቴስታንቶች ምእመኑን እናንተኮ ዝም ብላችሁ ነው መሪዎቻችሁ መ/ሪን ፕሮቴስታንት ናቸው እያሉ በሐሰት ምእመኑ ተስፋ እንዲቆርጥ የሚያደርጉትን ማኅበረ ቅዱሳን እውነት ናቸው ሁሉም ፕሮቴስታንት ናቸው እንንተ ብቻ ናችሁ የቀራችሁ እያለ የማስበርገግ ሥራ እየሠራ ይመስለኛል፡፡
  ለዚህም ስለ መናፍቃን በጻፈው መጽሐፉ አንድ ቀሚስ ለባሽ ወደ ፕሮቴስታንት መቀላቀሉን ፊት ለፊት ገጽ ላይ በማውጣት ነው፡፡
  ሌላ ለማኅበሩ የምጠይቀው ከማኅበሩ አባላት ስንት ፐርሰንቱ ፕሮቴስታንት መናፍቅ ሆኗል፡፡ነው የመላእክት ስብስብ ነው ብሎ ያስባል፡፡ሌላው ይቅር ከመደበኛ አገልጋዮቻችሁ እንኳን ስንቱን መናፍቅ ናቸው ብላችሁ እንዳባረራቹ ኅሊናችሁ ያውቀዋል፡፡ እናንተ ጋር በኃላፊነት የሠሩ አሁን የፕሮቴስታንት አቀንቃኝ የሆኑ የሉም ወይ?ታዲያ እግዚአብሔር ስንት ድብቅ ሰራዊት ማህበራት ሰ/ት/ቤት እ㝕ሉ ለምን እንደ ነቢዩ ኤልያስ እኔ ብቻ ለአምልኮትህ ቀንቼ አለሁ ሌላው ግን ክዲሃል የሚለውን የትዕቢት ቃል መረጣችሁ?
  ለመሄኑ ይህን ስልቱን እየቀያየረ የመጣውን ምንፍቅና መንፈሳዊ ኮሌጆች ከሌሉ በእናንተ ሥላሴ አንድም ሦስትም ናቸው በሚለው ኮርስ መግታት ይቻል ይመስላችኋል?
  ኮሌጁ በአንድ ጳጳስ የበላይ ኃላፊነት በሌሎች ጳጳሳት የቦርድ አባላትና በቅዱስ ፓትርያርኩ የበላይ ጠባቂነት እየተመራ ሳለ ለምን አጥር ዘላችሁ ተግሳጽ አማራችሁ፡፡አስፈላጊ ከሆነም አቡነ ጢሞቴዎስ እንኳን በመረጃ የተደገፈ ነገር አግኝተው ከአንድ ተማሪ ለመናፍቅነት የሚያስጠረጥር ነግር ካገኙበት ለማባረር ወደኋላ አይሉም፡፡እናንተ ሳትነግሯቸውም እምነተ ጠንካራ በሆኑ ደቀመዛሙርት ጠቋሚነት ከዚህ በፊት ብዙዎች በዚህ ምክንያት ከት/ት እንዳገዱ የታወቀ ነው፤፤
  ለመሆኑ እነዚህ ደቀመዛሙርት የተሳቡበት ምክንያት ምን እንደሆነ ና ይህለ ለመፍታት ያደረጋችሁት ምድን ነው፡፡እኔ አውቃለሁ የኔ ወንድም ከመንፈሳዊ ኮሌጅ ተመርቆ የእናንተ ሕንጻ ሥር ያለችውን ፈታሽ የማያህል ደመወዝ እየበላ ትዳር ሳይዝ በአንድ ጠረፋማ አካባቢ ለጉርሱ እንኳን እየቸገረው እንደሚያገለግል አውቃለሁ፡፡ታዲያ እንደዚያ እራሱን ለሃይማኖቱ ሰጥቶ የሚያገለግል ወንድሜ ይህን የናንተን ዜና በመጽሐየት ቢያነበው ምን እንደሚሰማው ታወሰኝ፡፡
  የሚገርመው ደግሞ በጽሑፋችሁ እኛ የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ ነው የጻፍነው ትላላችሁ፡፡ለመሆኑ በሲኖዶሱ ደቀመዛሙርቱ ጤነኛ ሆነው መጥተው መናፍቅ ሆነው ይሄዳሉ የሚለው የሲኖዶሱ ሐሳብ ነው ወይ እውነትስ ነው ወይ በጭራሽ በእናንተ የተነገረ ካልሆነ በስተቀር እውነትነት የለውም፡፡ሲመጡ መናፍቅ ሆነው ይምጡ ከተማሩ በኋላ የተጣራ መረጃ የላችሁም፡፡ለምሳሌ ፍቅሩ የሚባል የተባረረው (በማኅበረ ቅዱሳን ጠቋሚነት ሳይሆን በተማሪዎች )ገና ከጅምሩ በፍረሽነቱ የመናፍቃን በራሪ ወረቀት ይዞ ሲያሰራጭ ተይዞ ነው፡፡ዘውገ መላክ የሚባልም ወደ ኮሌጁ ከመግባቱ በፊት በሰ/ት/ቤትና በሰበካ ጉባኤ የምንፍቅና ችግር እንዳለበት ቀድሞ በሀገረ ስብከቱ ተገልጾ ነበር፡፡ዳንኤል የሚባል ከዝዋይ የመጣ የተባረረው ገባ ሴሚስተር እንኳን ሳይጨርስ በደቀመዛሙርቱ ቀድሞ በተገኘበት መረጃ አማካይነት ነው፡፡
  ታዲያ ጳጳሱም ደቀ መዛሙርቱም እየታገሉት ያለውን ምንፍቅና እኔ ካልነካሁት ማለት አግባብ አይደለም፤፡
  መናፍቃን ከየትም ሊኖሩ ይችላ ግን የተገኙበትን ቦታ ከመኮነን ግሰቦች ላይ ማድረግ ያሻል፡፡
  በዘጠናዎቹ በናዝሬት ቅድስት ማርያም ሰ/ትቤት አባላት በሙሉ በሚባልበት ሁኔታ በጅምላ ወደ መናፍቃን አዳራሽ ገብተዋል፡፡ሕዝቡ ግን አልተከተላቸውም በዘመናችንም የሆለታ ኪዳነ ምህረት ሰ/ቤት አባላት መናፍቃን ሆኑ ተብሉ ከ14 ዓመት በታች ካሉት እንዲመለመል ሆናል በማኅበራትም ደረጃ እንዲሁ አሉ፡፡ሕዝቡ እየለየ እየጠነከረ ይሄዳል፡፡
  በየጠረፉ የማጣጡት ለግቢ ጉባኤያትም ለመንፈሳዊ ኮሌጆችም ግብአት የሚሆኑ ጽኑዓን ክርስቱያኖችን የሚያፈራው ሰንበት ት/ቤት ሳይናገር ብዙ እንዳደረጋችሁና ብቸኛ የቁርጥ ቀን ልጅ ራሳችሁን ማድረጋችሁ ቅዱስ ስልዋኖስ ያለውን አባባል እንዳስታውስ ያደርገኛል”ዝናው ከሥራው የገነነበት ሰው ያልታደለ ነው”
  ቅርንጫፍ እንደ ቅርጫፍነቱ መሆን አለበት ከግንዱ ልብለጥ ካለ ግን ግንዱ ቅርንጫፉን መሸከም ስለሚያቅተው ተገንድሶ ይወድቃል፡፡
  በመንግሥት ብዙ የሲቪል ማኅበራት አሉ፡፡አጋዥ ድርጅቶች አሉ ነገር ግን ከላይኛው የመንግሥት ትእዛዝ የወጡ አይደሉም፡፡
  ይህን ስል ግን በቤተ ክህነቱ የበላይ አካላት ያለውን ዘርፈ ብዙ ችግር ሳልረሳ ነው፡፡ስለ ማኅበሩ ቤትርያርኩም ሆነ በአንዳንድ አለቆች የሚነገሩትን አግባብ ያልሆኑ ንግግሮቸ አግባብ እንዳልሆኑ እገነዘባለሁ፡፡
  ግን የእነሱ ስህነት በብዙሃኑ እየተነገረ ማኅበሩ ግን ፍጹም እንደሆነ ማሰብ አግባብ እንዳልሆነ ለመግለጽ ብቻ ነው፡፡ማኅበሩም ቢሆን መስተካከል ካበት መስተካከል አለበት፡፡ብዙሃን በሰሩት ሥራ መሃል አንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባል ካለ ማኅበረ ቅዱሳን ይህን አደረገ ተብሎ እንዲወራለት የሚፈልግ ነው፤፡
  የተሐድሶና የማኅበረ ቅዱሳን ሁለት ጽንፎች ያሰጉኛል፡፡

  • Dereje Megersa March 1, 2016 at 9:53 am Reply

   ወዳጀ ሆይ! ሥላነሳሃቸው ነጥቦች ያለኝን ምልከታ ላስቀምጥልህ፤
   የበላይ ጠባቂ እንደመሆናቸው አዎ ዝም ማለት የለባቸውም፡፡ ማለት ያለባቸው ግን እዚህ ላይ የፃፋችሁት ማስረጃ አላችሆይ? እስቲ አቅርቡት እና እንየው ነው፡፡ ሃላፊዎቹ ተቃውመዋልና ዉሸት ነው የፃፍነው ብላችሁ አስተባብሉ ግን አያስኬድም፡፡
   በስም ለመጠቀስ ሌላ ሂደት ስፈልጋል፡፡ አጠቃላይ ያለውን ሁኔታ አቅርቦ ዝርዝሩን ግን ለሚመለከተው አካል ነው ማቅረብ ያለበት፡፡

   ማህበሩ የመላዕክት ስብስብ ነኝ አልሳሳትም ለበት ጊዜ ያለ አይመስለኝ ያደረገው የራሱን ድርሻ መዎጣት ነው፡፡ ተማዎቹም ሆነ ሊቀ ጳጳሱ የሚያደርጉትን የሚተካ ዐይደለም፡፡
   አኁን ማህበረ ቅዱሳን ላይ ከመዝመት ስንት የሚሳስብ ቅድሚያ የሚሰጠው አስቸኩዋይ ስራ የለባቸውም ትላለህ? ያለንበት ሁኔታ ተግባብቶ በውይይት እና በመነጋገር መፍታት ሲገባ ከጥቅመኞች እና ሃራጥቃውያን ጋር በመተባበር የቤተክርስቲያንን ስም ማዋረድ ነበረባቸው ትላለህ?

  • Anonymous March 1, 2016 at 4:00 pm Reply

   እግዚአብሔር ይስጥህ Anonymous March 1, 2016 at 7:31 am ግን ለምን እናለባብሳለን?ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ኮሌጁ በማኅበረ ቅዱሳን ላይ ያለውን ቅሬታ ለቅዱስ ፓትርያርኩ ከማቅረቡ በፊት ለማኅበረ ቅዱሳን በአድራሻ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡ማኅበሩ ለዚህ የቅሬታ ደብዳቤ ምላሽ አልሰጠም፡፡ምላሽ ስጠን ተብሎ በኮሌጁ ሲለመን የነበረን አካል እድል አልተሰጠውም ማለት አስቸጋሪ ነው፡፡የጉዳዩ መነሻ የኮሌጆቹ አቤቱታ ሆኖ እያለ አቤቱታው ወቅታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የመጣውን የፓትርያርኩ መመሪያ ብቻ ማጮህ ፍትሐዊ አይደለም፡፡ማኅበሩ ጉዳዩን ከኮሌጆቹ ጋር በቅንነት ተነጋግሮና አለኝ የሚለውን ማስረጃ አቅርቦ ቢጨርስ እዚህ ደረጃ አይደረስም፡፡ይሄን መሠረታዊ ጭብጥ ለምን ማለባበስ እንደተፈለገ ግልጽ አይደለም፡፡

   ራሳችሁን በንጹሕ የኮሌጅ ደቀመዛሙርት ቦታ አስቀምጣችሁ ጉዳዩን እዩት፡፡ዘገባው ገና በርእሱ፡- ኮሌጁና ‹‹ደቀመዛሙርቱ›› ምን እና ምን ናቸው ብሎ ነው የሚጀምረው፡፡ደቀመዛሙርቱ የምትለዋን ቃል ለይቶ በትእምርተ ጥቅስ ውስጥ አስገብቶ ዘገባን መጀመር የተወሰኑ ተጠርጣሪ ደቀመዛሙርትን ለማግኘት ሲባል ሁሉንም ደቀመዛሙርት የጥርጣሬ ከበባ ውስጥ አስገብቶ መጀመር ነው የዘገባው አካሄድ፡፡በፍሬምናጦስ ኮሌጅ ኦርቶዶክሳውያን አንገት ደፍተው ተሐድሶዎች ግቢውን ተቆጣጥረውታል የሚል ዘገባ ለአንድ የፍሬምናጦስ ደቀመዝሙር የሚሰጠው ገጽታ ምን ያህል ጽልመት የተሞላበት ሊሆን እንደሚችል ግልጽ ነው፡፡መጀመሪያ ነገር ከሆነ ተቋም የሆነ ጊዜ ተሐድሶዎች ወጡ ማለት ተቋሙ የተሐድሶ መፈልፈያ ሆኗል አያሰኝም፡፡እንደ እሱ ከተባለ እኮ በ1993 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ የተወገዙት አምስቱ ተሐድሶ መነኮሳት መሪ የነበረው ‹‹አባ›› ዮናስ የአባታችን የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ምስጉን ተማሪ ነበር፡፡ዛሬ በዱባይ ያለውን የተሐድሶ ክንፍ እየመራ ያለ ‹‹ቄስ›› ተብዬ አንድ ወቅት የማኅበረ ቅዱሳን ንቁ አባል የነበረ ሰው ነው፡፡

   ተሐድሶን ስንዋጋ የተቋሙን ገጽታ በማጥቆር እንዳይሆን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡የተናበበ ሥራም ይጠይቃል፡፡ምንም ጥርጥር የለውም ማኅበሩ ባወጣው ዘገባ ኮሌጁና ደቀመዛሙርቱ ደስተኛ አይደሉም፡፡ከእነዚህ ኮሌጆች በሺ የሚቆጠሩ ምሩቃን ውስጥ ብዙዎቹ በገጠሪቱ ቤተክርስቲያን በትጋት በማገልገል ላይ መሆናቸው እየታወቀ በጥቂት እንክርዳዶች የተነሣ ሞራላቸውን የመንካት አካሄድ አሁን የተጀመረ አይደለም፡፡ተምረው በድካቸው የተጎናጸፉትን ቀሚስ ሳይቀር የማጣጣል ዘመቻ ይካሄድባቸዋል፡፡በዚህ ላይ የቤተክህነቱ አስተዳደርም ቢሆን የኮሌጅ ምሩቃንን ለአመራር በማብቃት ረገድ ያለው ሪከርድ አሳዛኝ ነው፤ተገቢ ቦታ አልተሰጣቸውም፡፡

   በ25 ዓመታት ውስጥ በንጉሡ ዘመን ከተከፈቱት ኮሌጆች ውጭ አንድ ኮሌጅ እንኳ አለመጨመሩና ካሉትም ውስጥ ወደ ሙሉ ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ያደገ ኮሌጅ አለመኖሩ ከላይ እስከ ታች ያለው ማኅበረ ምዕመንና ካሕን ለኮሌጆች መስፋፋት የሚሰጠውን ቦታ አነስተኛነት የሚያሳይ ነው፡፡ይህ ሳያንስ እንዲህ አይነት እሰጥ አገባ ውስጥ የሚከቱ ዘገባዎችን ያለ በቂ ጥንቃቄ እያወጡ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠን መመሪያ መሰረት ያደረግነው ነው ማለት ያስተዛዝባል፡፡ቅዱስ ሲኖዶስ ማኅበረ ቅዱሳን ከቅድስት ሥላሴ ኮሌጅ ለሚቀርብለት ቅሬታ ምላሽ አይስጥ ብሏል ሲባል አልሰማንም፡፡ማኅበሩ ለኮሌጁ በጊዜውና በወቅቱ መልስ ቢሰጥ ምንም ጉዳት አልነበረው፡፡ሀቁን ልባችን እያወቀው አንድ ጊዜ ከአፋችን ወጥቷል ብሎ ግትርነት ጥቅም የለውም፡፡

   • Ulata Yesus March 14, 2016 at 2:01 pm

    Mameri kidusanin bicha new yemekotatirot malet new bizo gidamat wusti eyegibo boles nin bimalet melekosen bimasekayet inemanachew inesunis manew yemekotatirachew megist new ways yehamanot abatochi ahunim bihon bizo abatochi alo yemenafik timert yemezero hulum esbe kirsetan sayawek kirto adelem wanaw jigir yalehu kirasachew P 1 mihunon gin egizabher eskimeferd lehulachinim tinatun yestin digag abatochim ayezowachihu egizabher melis alew

 14. Tiruwork Abera March 1, 2016 at 7:43 am Reply

  እግዚአብሔር ይባርካችሁ! እናንተ በአለት ላይ የተመሠረታችሁ ናችሁ፤ አሁንም በርቱ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ስለሆነ ሁሌም አሸናፊዎች ናችሁ ! ዳቢሎስ ይፈር እግዚአብሔር ይክበር ለዘለዓለሙ አሜን!!!

 15. Anonymous March 1, 2016 at 8:07 am Reply

  Yebete kiristiYanachinini fetena yasetagisilin!

 16. Anonymous March 1, 2016 at 8:56 am Reply

  የሰይጣን ዋና ስራው ድሮም መቃወም ነው፡፡ መልካም ስራ አይመቼውም፡፡
  ማህበሩ በፈጣሪ ፈቃድ የተመሰረተ በመሆኑ ወደፊት ይቀጥላል
  ጠላት በቤተ ክርስቲያን ላይ እንዳይፈነጭ ማድረግ በመቻሉ፣ህዝቡን ማስተማር በመቻሉ
  ህግና ስርዓት እንዲከበር በመስራቱ ብዙዎች አልተመቻቸውም፡፡ መናፍቃን፣ተሀድሶዎች
  ሌሎችም ማህበሩን የማይወዱት አላማቸውን ማሳካት ስላልቻሉ፣ማህበሩ እየተከታተለ ሴራቸውን
  ስለሚያጋልጠው ነው፡፡ ስለዚህ ስራችሁን በጽናት ወደፊት ቀጥሉ፣ፈጣሪ ከናተ ጋር ይሁን፡፡

 17. nigus March 1, 2016 at 9:18 am Reply

  ውድ ምሃበር ክዱሳን አናንተ ለሁላቺንም አርአያ፣ፍክር፣ ናቺሁ ፣ ከናንተ
  ውስጥ የተሳሳተ ካለ በማረም ,ትክክሎቺን ማበረታት ብቻና ብቻነው የናንተ ስራ ሌላውን አግዚአብሔር አለ ,ሁሌምምመኑ ከናንተ ጋር ነው ፣ አሁንማ ሁሉም በበአንክሮ ነው ሜደግፋቺሁ አግዚአብሔር ኢትዮጵያውያን ይባርክ

 18. Anonymous March 1, 2016 at 9:47 am Reply

  Waw, wedet eyamera new?

 19. santa March 1, 2016 at 11:22 am Reply

  egziabher kega gar yehun engi betekristiyanachinn lileyay yemeta neger new hulachinm wede fetari new abate malet yalebin …….emebrihan fergawan testbate kefetari tastarken…hulachinm yetewahdo legoch nen …………

 20. Serawit March 1, 2016 at 12:25 pm Reply

  wey gud ena ezih eyetebalegn geta lemeta new!

 21. Anonymous March 1, 2016 at 2:13 pm Reply

  እግዚአብሔር ያከበረዉን ማን ያዋርደዋል እርሱ ቢዘገይም የሚቀድመዉ የለም። የቤተክርስቲያናችን እራስ ጌታችን እና መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከ ፓትሪያሪኩም ሆነ ከ ጸሃፊዉ ንቡረዕድ “ ኤልያስ” በላይ ነዉ። ሚገርምኝ ግን ሃራጥቃወቹ ጤነኛ አስተያየት ሰጭ አካል መስለዉ ለመትፋት የሚሞክሩት መርዝ ነዉ። ሄሄሄሄይ…….. “እኛም ነቅተናል ጉድጏድ ቆፍረናል” አለች አይጥ::
  እድሜና ጤና ለማህበሩ አባላት:: እግዚአብሔር ይባርካቹ፤ በርቱ ገና ከዚ በላይ ትበዛላችሁ፤ በዚህ ሰአት ለቤተክርስቲያናችን ዋልታ እና መከታ ሆኖ ያገኘዉት ይህ ቅዱስ ማህበር ብቻ ስለሆነ እኔም ልቀላቀላችሁ ዝግጅቴን ጨርሻለሁ።

 22. Anonymous March 1, 2016 at 3:38 pm Reply

  እዉነተኛዋን መንገድ ፈልጉ በሱም ላይ ተመላለሱ፡፡ ማህበረ ቅዱሳን ምእመናን እንዳይናወጽ ቅዱስ ሲኖደስ የወሰናቸዉን ዉሳኔዎች ሁሉም አካል እንዲያዉቀዉ እና በጥንቃቄ እንዲያስተዉለዉ መጻፍቸዉ ስህተት አይደለም ፡፡ ማገናዘብ የተቸገሩትን እግዚአብሔር እንዲያስተዉሉ ይገስጻቸዉ፡፡

 23. Anonymous March 1, 2016 at 3:41 pm Reply

  በሻሻመኔ ቤተክርስቲያናት ተቃጥለው ካህናትና ምዕመናን መግቢያ አጥተዋል። እሳቸው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ከማኅበሩ ጛር ፊጥጫ ውስጥ ገብተው ይዳክራሉ። ምን ይባላል። አምላክ ልቦና ይስጣቸው ከማለት ውጪ።

 24. Anonymous March 1, 2016 at 3:44 pm Reply

  በሻሻመኔ ቤተክርስቲያናት እየተቃጠሉ ካህናትና ምዕመናን መግቢያ አጥተዋል። እሳቸው ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው ከማኅበሩ ጋር ፍጥጫ ውስጥ ገብተው ይገኛሉ። ምን ይባላል። አምላክ ልቦና ይስጥ ከማለት ውጪ።

 25. Abate Aynachew March 2, 2016 at 4:19 am Reply

  “ካልደፈረሰ አይጠራም “እንደተባለው ለማሕበሩ ዓላማ ስኬት እግዚአብሔር የራሱ መንገድ አለውና ሁላችንም በፀሎት እንበርታ፡፡

 26. Anonymous March 4, 2016 at 7:33 am Reply

  long live le mahibere kidusan………..museghoch anilakekim ……….. ahun hulum sile betchirstiyan maseb jemirwal

 27. የማርያም March 4, 2016 at 7:49 am Reply

  በርቱ ሀራጥቃ ሀራጥቃ ነው፡፡ ቢታጠብ አይጠራም እናንተ ግን ከንግግር በላይ ስራችሁ የታየ የታወቀ ነውና፡ አእላፍ እንከተላችኋለን፡፡ አምላከ ቅዱሳን በቤተክርስቲያናችን ላይ የተነሱትን ሁሉ ያስታግንስልን፡፡

 28. Anonymous March 4, 2016 at 10:35 am Reply

  ውድ የማህበረ ቅዱስን አባላት መቼም በሆን ውስጣችሁ አይጨነቅ፣ሁሌም ወደ ፈጣሪ ፀልዩ ፡፡ምክንያቱም ይህን እንዲሉ ያነሳሳቸው እግዚአብሔር በዚህ ምክንያት እውነቱ ሊገልፅ ይሆናል፡፡
  እኔ በጣም የሚገርመኝ ነገር ቢኖር ምንም የማያውቅና ያልተማረ ሰው የሚያስበው ሃሳብ ይሻላል ፡፡በጣም ይቅርታ ድፍረት እንዳይሆንብኝ በጣም ስለተሰማኝ ነው ምን እንስራ ፣የተዘጉ ቤተክርስቲያኖች ይከፈቱ፣የአብነት ተማሪዎች ድገፋ ይደረግላቸው እና የመሳሰሉትን በርካታ ነገሮች ከእያጥቢያ ቤተክረስቲያን ውስጥ ሆኖ የሚሰራ ማህበር ክስ መመስረት ምን ማለት ነው?አሁን በዚህ ሰዓት ይህ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆችን የሚያነጋግር ነገር ነው? ኸረ ስንት መናፍቃን የሚያደርጉትን ድርጊት እየተቆጣጠሩ ቤተክርስቲየንን መጠበቅ ይሻል ነበር፡፡ለማንኛውም ሌባ ሌባ ከአልተባለ አይደንግጥምና እግዚአብሔር እውነቱን ገልፆት እስከምናይ ድረስ ብታስቡበት ጥሩ ነው፡፡
  ለእኔ ማኅበረ ቅዱሳንን ማንም አልሰጠኝም፡፡ ማንም አይወስድብኝም፡፡ አባል የሆንኩት ለዓላማው እና ለመሠረተ ሃሳቦቹ እንጂ ለቢሮው እና ለግቢው አይደለም፡፡ እኔን ከማኅበሩ ቢሮ እንጂ ማኅበሩን ከእኔ ልብ የሚያወጣው ማንም አይኖርም፡፡

  አሁንም ቢሆን እየጸለይን ብንወያይ ችግሮች ይፈታሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ግን ጠንቋይ ይመስል የተጻፈን ነገር መፍራት የለብንም፡፡ ለእኔ ጽሑፍ አንዱ መነጋገርያ ነው፡፡ መተራረሚያ ነው፡፡ መማማርያ ነው፡፡

 29. Anonymous March 8, 2016 at 6:34 am Reply

  GOD I don’t want to judge , give us your mercy amen amen ame

 30. Hadas Temesgen March 30, 2016 at 7:19 am Reply

  Yekidusan Amilak bemihiretuna bechernetu Kidist Bete -Kiristian Yitebkatal ,yedingil mariam milja yekidusan bereket kenga ga newna eihitoch wendmoch ayizachu tegadilachu endekidusanu fire yaferal

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: