በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየተደረገ ያለው ድራማዊ መሸላለም፥ “ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው” ዓይነት ነገር ነው/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

Teshelalemu

 • የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና መሰሎቹ በወርቅ ሐብላት እና ብራስሌት ‘ሽልማቶች’ም ይበዘብዛሉ
 • ፐርሰንት አስከፍያለሁ ብሎ በ5 ወራት ብቻ የእጅ ሰዓት፣ የወርቅ ሐብላትና ብራስሌት ሰብስቧል
 • ከየአጥቢያው በኃይልና በግድ ፻ሺሕዎች ለሽልማት እየተሰበሰበ እርስበርሳቸው ይሞጋገሱበታል
 • ከንፋስ ስልክ ላፍቶ አጥቢያዎች ብቻ ከብር 300ሺሕ በላይ ተሰብስቦ ወርቃወርቅ ተሸላልመዋል
 • ራስን ለማጋነኛና ቦታ ለማግኛ የሚካሔዱ መደለያዎች ናቸው፤ ችግሩ በመሸላለም አይፈታም

/ታዛቢ የክፍላተ ከተማ ሓላፊዎችና ሠራተኞች/

*           *          *

 • ከምስክር ወረቀት ባለፈ ወርቃወርቅ እና ቁሳቁስ መሸላለሙ ወደ ሙስና ሊመራ ይችላል
 • በድርቅ ለተጐዱት ርዳታ በማሰባሰብ ላይ እያለን በየምክንያቱ መሸላለም ከትዝብት ይጥላል
 • ገባእተ ነግሁ ብዙ ሠርተው ቤተ ክርስቲያንን ለገባኡተ ሠርኩ ያስረከቧት ያለመሸላለም ነው
 • የሚገባችኹን ሠርታችኹ የሚገባንን እንጂ ከሚገባን በላይ አልሠራንም በሉ ተብለን ታዘናል

/ዜና ቤተ ክርስቲያንጥር እና የካቲት ፳፻፰ ዓ.ም./

*           *          *

Zena BeteK on A.A Dio
ዜና ቤተ ክርስቲያን ለሀገረ ስብከቱ የሚያሳስበው ዐቢይ ጉዳይ ቢኖር፣ ሀገረ ስብከቱ መኪናዎችን ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት የድካማቸውን ዋጋ በማሰብ በጉዳይ አስፈጻሚነት የመደባቸውን የራሱን ሠራተኞች እንደ ውጭ ሠራተኞች እንደ ውጭ ስፖንሰሮች ሊቆጥራቸውና ሊያጋንናቸው አይገባም፡፡ እንዲኹም በሥራ ብልጫ ላሳዩ አካላት የማበረታቻ ሽልማትና የምስክር ወረቀት መስጠት ሌላውን ለሥራ የሚያነሣሣ ቢኾንም ለተሸላሚውም ኾነ ለሸላሚው አካል ከምስክር ወረቀት ባለፈ ወርቃወርቅና ሌላም የቁሳቁስ ሽልማት መሸለሙ ወደ ሙስና ሊመራ ይችላል፡፡ መንግሥት የሚሸልመው አምራችና አትራፊ አካላትን እንጂ አክሳሪ አካላትን አይደለም፡፡

በተለይ በክፍላተ ከተሞች የተደረገውን መሸላለም በተመለከተ መጽሐፍ÷“ይወድስከ አፈ ነኪር” ማለትም የሌላው አፍ ያመስግንኽ፤ ይላል፡፡ አመስጋኞችም እነርሱ፣ ተመስጋኞችም እነርሱ፤ ሽልማቱ የተዘጋጀው በእነርሱ፣ ተሸላሚዎችም እነርሱ፣ “ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው” ዓይነት ነገር ነው፡፡ ወይም ማታ ማታ በቴሌቭዥን ከምናያቸው ድራማዎች ሌላው አዲስ ድራማ ነው፡፡ “ሙስና እየተዳከመ ሔዷል” ተብሎ በሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ የተነገረውንም ዐረፍተ ነገር ፈጽሞ ይሽረዋልና በዚኽ ጉዳይ ላይ ወደፊት ሀገረ ስብከቱ አጥብቆ ሊያስብበትና ለሽልማቱ ገደብ ሊያበጅለት ይገባዋል፡፡

በአኹኑ ጊዜ በሀገራችን በተከሠተው የድርቅ አደጋ ምክንያት፣ በአንድ በኩል በድርቅ ለተጐዱ ወገኖቻችን ርዳታ በማሰባሰብ ላይ እያለን በሌላ በኩል በየምክንያቱ ስንሸላለም መታየቱ ቤተ ክርስቲያንን ከትዝብት ላይ የሚጥል እንዳይኾን ማሰብ ያስፈልጋል፡፡ ገባእተ ነግሁ ብዙ ሥራ ሠርተው ያለፉትና ቤተ ክርስቲያንን ለገባኡተ ሠርኩ ያስረከቧት ያለአንዳች መሸላለም ነውና፡፡ ጌታችንም “የሚገባችኹን ሠርታችኹ የሚገባንን እንጂ ከሚገባን በላይ አልሠራንም በሉ፤” በማለት በቅዱስ ወንጌል አዞናልና፡፡

(ዜና ቤተ ክርስቲያን፤ ርእሰ አንቀጽ፤ ጥር እና የካቲት ፳፻፰ ዓ.ም./

Advertisements

13 thoughts on “በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እየተደረገ ያለው ድራማዊ መሸላለም፥ “ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው” ዓይነት ነገር ነው/ዜና ቤተ ክርስቲያን/

 1. TIRSIT WUBIE February 27, 2016 at 12:30 pm Reply

  የማነ ግን እንደ ድሮው ዜና ማንበብ ነበር የሚያምርበት

  2016-02-27 3:35 GMT-08:00 “ሐራ ዘተዋሕዶ” :

  > haratewahido posted: ” የማነ ዘመንፈስ ቅዱስና መሰሎቹ በወርቅ ሐብላትና በወርቅ ብራስሌት ‘ሽልማቶች’ም
  > ይበዘብዛሉ ፐርሰንት አስከፍያለሁ ብሎ በ5 ወራት ብቻ የእጅ ሰዓት፣ የወርቅ ሐብላትና ብራስሌት ሰብስቧል ከየአጥቢያው
  > በኃይልና በግድ ፻ሺሕዎች ለ‘ሽልማት’ እየተሰበሰበ እርስበርሳቸው ይሞጋገሱበታል ከንፋስ ስልክ ላፍቶ አጥቢያዎች ብቻ
  > ከብር 300ሺሕ በላይ ተሰብስቦ ወርቃወርቅ ተሸላልመዋል “ራስን ለማጋ”
  >

 2. Anonymous February 27, 2016 at 2:38 pm Reply

  ይገርማል አቡነ ማትያስ እና ሌቦቹ ለካ ማኅበረ ቅዱሳንን እንዲህ የጠሉት ይህን ጉድ፣ ምዝበራ እንዳናውቅባቸው ነው፡፡ የቤተክርስቲያን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ከፉዎችን ልቦና ይስጥልን፡፡

 3. Anonymous February 27, 2016 at 3:08 pm Reply

  Ene betam yegeremegnal yemane leje tamual belo kyeadebru kmudayemetsewat bemselochu amkagnenet k1million belaye yezerefena yazeref ahun esuna Elias sishelemu ayegeremem betekerstyanua tasazenalech ahun degemo bdmoz chemare sebebe eyezrefu new.

 4. Anonymous February 28, 2016 at 11:19 am Reply

  ምን ሰሩና ነው ሽልማቱ! ዐመፅ ስለቀሰቀሱ ይሆናል እንጂ፡፡ የሚያሳፍረው ፓትርያሪኩ መፍቀዳቸው፡፡

 5. Anonymous February 28, 2016 at 11:20 am Reply

  የገጠር አብያተ ክርስቲያናት እርዳታ በሚያስፈልጋቸው ወቅት ስንቱ ተርቦ ባለበት ሁኔታ እንደዚህ አይነት ነገር ማድረግ ተገቢ አይደለም፡፡ ማህበሩን ስለከሰሱላቸው የተደረገ ነው፡፡

 6. Anonymous February 28, 2016 at 11:21 am Reply

  ዜና ቤተክርስቲያንን እናመሰግናለን በዚሁ ቀጥሉ፡፡

 7. Anonymous February 28, 2016 at 11:23 am Reply

  ቤተ ክርስቲያንን ለበዘበዘ ሽልማት! ኑፋቄን ለማስፋፋት ለተነሳ ሽልማት!

  እማማ ኦርቶዶክስ ሞኝ ነሽ ተላላ፤
  የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

  • Anonymous February 28, 2016 at 12:20 pm Reply

   MAN BISHELEM NEW DES YEMILACHU MINEW YETADEWOSNA YEMAMYE SHILMAT ALAMESEGENACHIHUM ZEREGNINETACHU BEALEM TAWKEWAL ( WEYENO ARESEW WEYENO AFESW ) PERSENT LEMAYKEFLEW LEMAHBEREKIDUSAN NEW METEKES YALEBET DAWIT YARED SISHELEM FOTO ATITACHIHU NEW? TERA ZEREGNINET YET LIYADERSACHIHUNEW HAILESILASIE ZEMARYAMIN BAMBULANA BEBINO EYATALELACHU LE.EKUY ALAMACHIHU MELALAK YALCHALUTIN SEWOCH LAY YEMITASAYUT TILACHA MAHBERE KIDUSAN RASU ENDEAQAQWME RASU MEFRESU AYKERM

 8. Anonymous February 29, 2016 at 8:02 am Reply

  ቤተ ክርስቲያንን ለበዘበዘ ሽልማት! ኑፋቄን ለማስፋፋት ለተነሳ ሽልማት!

  እማማ ኦርቶዶክስ ሞኝ ነሽ ተላላ፤
  የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ!

 9. Tiruwork Abera February 29, 2016 at 8:37 am Reply

  አቤቱ የሚሰሩት አያውቁምና ይቅር በላቸው! ማስተዋልን ይስጣቸው! ይሄ በጣም ጸሎት ያስፈልገዋል ወገኖቼ! እጅግ አብዝተን ልንጸልይ ይገባናል! እግዚአብሔር ይህችን ቅድስት ወርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለማጥፋት በዋናዎቹ ላይ አድሮ የሚጥረው ሰይጣንነን እርሱ ያጥፋልን! ልቦናና ማስተዋልን፣ ይስጣቸው፣ አይነ ልቦናቸውን ያብራላቸው!!!

 10. Anonymous February 29, 2016 at 8:37 am Reply

  thanks to zena betekirstina.

 11. CHU February 29, 2016 at 8:52 am Reply

  HMMMMMMMMMM

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s

%d bloggers like this: