ፓትርያርኩ:ደንባዊ ህልውናውን የካዱት ማኅበረ ቅዱሳን፣ በስምዐ ጽድቅ ላወጣው የፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ ጽሑፍና በደብዳቤ ለሰጣቸው ምላሽ በአምስት ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ መመሪያ ሰጡ

PAT MK00PAT MKb

 • ማኅበሩ መመሪያውን በግልጽ ተቀብሎ በደብዳቤ ይቅርታ ካልጠየቀና ይህንኑም በኹሉም ሚዲያዎቹ ካልገለጸ “የማስተካከያ ሥራ ለመሥራት የምንገደድ መኾኑን በጥብቅ እናስታውቃለን፤” ብለዋል
 • “የማስተካከያ ሥራ” ያሉት፥ የማኅበሩን የኅትመት ሚዲያዎች ማገድ፤ በኮሌጆቹ የስም ማጥፋት ወንጀል ክሥ እንዲመሠረትበት ማድረግና ሌሎችንም አስተዳደራዊ ጫናዎችንና ማነቆዎችን እንደሚጨምር ተጠቁሟል
 • በመመሪያዎቻቸው፣ “ማኅበረ ቅዱሳን የተባለ ማኅበር” እያሉ በመጥራት፤ የመተዳደርያ ደንብ እንዳይኖረው አድርገው በአየር ላይ እንዳስቀሩት በመግለጽ ደንባዊ ህልውናውን ክደዋል፤ በቅዱስ ሲኖዶስ በሙሉ ድምፅ በጸደቀው መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ክፍሎችን አዋቅሮ የሚፈጽመው አገልግሎት፣ የብዝበዛና ቤተ ክርስቲያን የማታውቀው እንደኾነ ገልጸዋል

*                *               *

 • መመሪያው፥ ፓትርያርኩ፣ በቅዱስ ሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ እና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ እንዲኹም በቋሚ ሲኖዶሱ፣ ማዕርገ ክብራቸውንና ደረጃቸውን ጠብቀው እንዲሠሩ የተሰጣቸውን ምክር እና አስተያየት ባለመቀበል ያለመዋቅር በተጽዕኖ በጠሩት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር ጉባኤ አባላት ስብሰባ ተጠቅመው ያስተላለፉት ነው፡፡
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያንና በቃለ ዐዋዲው ድንጋጌዎች፣ ፓትርያርኩ የሚሰበስቧቸውና በርእሰ መንበርነት የሚመሯቸው ስብሰባዎች፥ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ፣ ቋሚ ሲኖዶስና የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ እንደኾኑ ሰፍሯል፤ ፓትርያርኩ፣ በመጀመሪያ ደረጃም ኾነ በይግባኝ የሚቀርቡ ጉዳዮች ታይተው ውሳኔ እንዲያገኙ ማድረግ ያለባቸው፣ ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ወይም ምክትላቸው በሚመሩት ጠቅላይ ቤተ ክህነት አልያም በቋሚ ሲኖዶስ ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መኾን ይገባዋል፡፡
 • ፓትርያርኩ የመምሪያና የድርጅት ሓላፊዎችን በሰበሰቡበት ወቅት፥ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢው፣ እኛን የሚሰበስቡን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ወይም ምክትሉ ናቸው፤ ከባድ ችግርም ሲፈጠር ቅዱስ ሲኖዶስ ተጠርቶ የሚመለከታቸው ኹሉ ባሉበት መወያየት እንጂ ጉዳዩ ብቻዎትን የሚያዩት አልነበረም ሲሉ የአካሔዳቸውን አድሏዊነትና መዋቅራዊ ስሕተት ጠቁመዋቸው ነበር፤ ፓትርያርኩ ግን ከስብሰባው ቀደም ብሎ አካሔዳቸውን እንዲያስተካክሉ የመከሯቸውን ብፁዓን አባቶች፣ “ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ፤ ውኃ ቢያንቅ በምን ይውጡ፤ ኹሉም አልታዘዝ አሉኝ፤ ሊቃነ ጳጳሳቱን አብረውኝ እንዲኾኑ ጠይቄአቸው ነበር፤ ነገር ግን ሊመጡልኝ አልቻሉም፤” በማለት ነበር ሊያሳጧቸው የሞከሩት፡፡ ማኅበሩም እንዲያወያዩት በተደጋጋሚ ጠይቆ ምላሽ በማጣቱ ለመጻፍ የተገደደውን ደብዳቤ፣ “ሕገ ወጥና ሥርዓት አልባ ደብዳቤዎችን አሻቅቦ ወደላይ በመጻፍ መሪዎችን መቃወም እያስፋፋና እያስለመደ መጥቷል” ሲሉ ነው በመመሪያቸው ያጣጣሉት፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን የሚፈጽመው፣ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሥር እንደመኾኑ፣ ጉዳዩ ከኹሉም በፊት በመምሪያው ሊቀ ጳጳስ እና በጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል እንዲታይ መደረግ ነበረበት፤ ፓትርያርኩ ግን፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁም ኾኑ ምክትላቸው ባልተገኙበት፣ የአስተዳደር ጉባኤ አባላትን በተጽዕኖ ሰብስበው ያስተላለፉትን መመሪያ ጠቅላይ ጽ/ቤቱም ኾነ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት እንዲያውቁት ያደረጉት በደብዳቤው ግልባጭ ነው፡፡
pat mathias and Nebured

መሳሳትን ልማዳቸው ያደረጉት ፓትርያርኩ፥ ሳያነቡ ይተቻሉ፤ ሳይመዝኑ ይወስናሉ፤ ሳያረጋግጡ ይመሰክራሉ!! በመዝባሪዎች አለቃ፣ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ የክፋትና የተንኰል ምክር !!

 • በስብሰባው ላይ ፓትርያርኩ፥ ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ከመጣኹ በኋላ ምንም ዓይነት መጽሐፍ አንብቤ አላውቅም፤ ሰዎች ከሚሉኝ ነው የምሰማው፤ ይኼ የሚባለውንም ሰምቼ ነው፤ ስለተነገረኝ የሰማኹት ነው፤ አላነበብኩትም፤ እንዲኽ እንዲኽ ብለው በነገሩኝ ነው፤ ሲሉ የክሥ እና የቅስቀሳ መመሪያ ያስተላለፉበትን የስምዐ ጽድቅ ጋዜጣን ጽሑፍ እንዳላነበቡት ተናግረዋል፤ ይህም በአንድ በኩል የበርካታ ስሕተቶቻቸውን ምንጭና መንሥኤ በሌላ በኩል ምን ያኽል በአማካሪዎቻቸው ተጽዕኖ ውስጥ እንደወደቁና የተንኰላቸውንም ክፋት በግልጥ አሳይቷል!! የሊቃውንት ጉባኤው ሰብሳቢበወቅቱ፣ “ከብፁዓን አባቶች ጋር በአንድነት እየሠሩ አይደለም፤ አማካሪዎች ቤተ ክርስቲያንን የሚያጠፉ ሌቦች የደብር አለቆች ናቸው፡፡ እርስዎንና አስተዳደርዎን ተቆጣጥረዋል፤ይህን ያስተካክሉ፤ ውጭ ያለውን ቅር ያሰኛል፤ ለሥራም የሚያበረታታ አይደለም፤” ሲሉ ነበር ኹኔታውን በከፍተኛ ቅሬታ የገለጹት፡፡
 • ማኅበረ ቅዱሳን፥ የቀድሞ የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕን፣ በቅድስና ደረጃ ሠይሞ ታቦት እንደቀረጸላቸውና ቤተ ክርስቲያንም በስማቸው እንዳነጻላቸው ተደርጎ በአማካሪዎቻቸው የተነገራቸውን አምነው በስብሰባው ወቅት፣ ለአቡነ ጎርጎርዮስ ሲኖዶስ ቅድስና ሳይሰጣቸው ቅድስና ሰጥተዋቸዋል፤ ታቦት አስቀርጸው ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸዋል፤ በቅድስና ደረጃ ብፁዕ ወቅዱስ ተብለው ቅድስና ተሰጥቷቸው እየተገለገለ ነው፤ ሲሉ መጥቀሳቸው፣ ፓትርያርኩ ይኹነኝ ተብሎ ስለ ማኅበሩ የሚደርሷቸውን መረጃዎች ሳያጣሩና ሳይመዝኑ አቋም እንደሚይዙና ውሳኔ እንደሚሰጡ በማያወላዳ መልኩ አረጋግጧል፡፡
 • በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሢመተ ፕትርክና በኋላ የተቀበሉትን ሓላፊነት በመዘንጋት ሊሳሳቱ እንደሚችሉ (fallible) ተመልክቷል፡፡ ከዚኽም በላይ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መጣሳቸው፤ በተሾሙበት ቀን የፈጸሙትን ቃል አለመጠበቃቸው፤ በአጠቃላይ ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር መፈጸማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ በተጨባጭ ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ሊወሰንም ይችላል፡፡
Advertisements

47 thoughts on “ፓትርያርኩ:ደንባዊ ህልውናውን የካዱት ማኅበረ ቅዱሳን፣ በስምዐ ጽድቅ ላወጣው የፀረ ተሐድሶ ኑፋቄ ጽሑፍና በደብዳቤ ለሰጣቸው ምላሽ በአምስት ቀናት ውስጥ ይቅርታ እንዲጠይቅ መመሪያ ሰጡ

 1. Zegiorgis February 25, 2016 at 6:10 am Reply

  “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፣ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” /ዮሐ 7፡51/
  ዛሬስ የገጠመን ይህን ዓይነት የአይሁድ ፍርድ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ የጠላቷ ጠባቂ ሲሆን ያየንበት ዘመን! ቅዱስነታቸው ለሞት አሳልፈው የሰጧቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች እግዚአብሔር ይጠብቃቸው።
  “አቤቱ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት፡ ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። ደሀ አደሆችና አባት የሌለን ሆነናል።” /ሰቆ ኤር 5፡1፟-2/

 2. samuel February 25, 2016 at 6:47 am Reply

  ኣባታችን ከእግዝኣብሄር ናቸውና እናክብራቸው
  “ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ”
  ከሁሉ በእግዝኣብሄር ተመርጠዋልና

 3. Anonymous February 25, 2016 at 7:16 am Reply

  ወንድሞቼ፡ እድሜዬ ከ ሀምሳ በላይ ወደ ስልሳውም ተጠግቷ።ብዙ የሃይማኖቱ እውቀቱም የለኝም።
  ያልገባኝ ነገር ግን፡…
  1) ብዙውን እነደታዘብኩት፤ ለምን ከወደ ቤት-ክህነት እንደዚህ እይነት መልእክት በወጣ ቁጥር በጣም ጥቂት አገልጋዮች/ባለሁበት በእሜሪካ/ ፈገግ ይላሉ? ይህ የጎጥ በሽታ?? እወይ ያለመታደል

  2)የደብዳቤውን ይዘት ልተውና፤ ግላባጭ የተደረገላቸው በተለይም ደህንነቱም፤ ፖሊሱም፤ ጠቅላይ ሚ/ር ቢሮም፤ (ክልሉን እንኳ እንጃ).. ወዘተ. እንደው ያገባናል እየተባለ ፋይል ይሰበስባሉ እንዴ?
  ነው እጥቢያ ቤተ ክርስቲያንም ሲጽፍ ግልባጭ ለቀበሌና ለወረዳ/ ለእድር የተለመደ ነው?
  ….ነው?
  3) በጽሁፍም በማማከርም ከሲኖዶሱ እባላት ይልቅ ከእነዚሁ የመንግስት እካላት ጋር ይተባበራሉን? ጠረጠርኩ!…

  ጭው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ እለ! “መንግስት እሁን(not tomorrow) ለራስህ ጣፍጥ”!

  ሁሉም ለበጎ ነው!

  ሳሙኤል/ ኦክላሆማ

 4. Anonymous February 25, 2016 at 7:53 am Reply

  ደብዳቤው ኮሌጆች ላይ ስለደረሰው ስም ማጥፋትና ቅሬታ ማኅበሩ ተገቢ ምላሽ ባለመስጠቱ የተነሳ የተጻፈ ነው፡፡ለእሱ ጥያቄ ማኅበሩ መልስ ሰጥቷል ወይስ አልሰጠም ነው ጥያቄው፡፡ከደብዳቤው መንፈስ ውጭ ሰው እንዲገነዘብላችሁ የምትፈልጉትን ብቻ ሐሳብ ለማስጨበጥ ስለምትፈልጉ የማይገናኘውን ታገናኛላችሁ፡፡ዋናው ደብዳቤውን ማያያዛችሁ ነው፡፡አረዳዱን እንደየኅሊናችን እንረዳዋለን፡፡

  ብሎጉ በማኅበረ ቅዱሳን እና በፓትርያርኩ ግንኙነት እየተጫወተ ያለው ሚና ከገንቢነቱ ይልቅ አሉታዊነቱ እንደሚበልጥ ግልጽ ነው፡፡ ማኅበሩ ከዚህ ብሎግ እና ከፌስቡክ ስሜታዊ አስተያየቶች በመነሳት ለራሱ የተሳሳተ ግምት እየሰጠ ወዳልሆነና አላስፈላጊ ፍጥጫ ውስጥ ራሱን እየጨመረ ነው፡፡ ነገሮችን ከስሜት እና ከእኔ ብቻ አውቃለሁ ስሜት ርቆ በማስተዋልና በምክንያታዊነት ቢያይ ለራሱም ለቤተ ክርስቲያን ዘላቂ ጥቅም መልካም ውጤት ይገኛል፡፡

  አማርኛ እና ዐረፍተ ነገር መሰንጠቅ፣ ራስን ብቸኛ አኦርቶዶክሳዊ አድርጎ ሌላውን ማራከስ፣ ፓትርያርኩ የራስን ድክመት ማለባበስ ትልቁ የማኅበሩ ድክመት ነው፡፡ ድክመቱን እንዳያይ ደግሞ ሚዲያውና ስሜታዊነት የሚጫናቸው አባላቱ አውረውታል፡፡ በእድሜ ታላላቅ የሚባሉት ቦርዱና የ6ኪሎ ዩኒቨርሲቲ አማካሪዎቹም ትኩረታቸው ራሳቸውን በጋዜጣና በማኅበራዊ ሚዲያ ማሻሻጭ እንጂ አለመግባባትን በውስጣዊ ንግግር የመፍታት ተሞክሮ አልፈጠረባቸውም፡፡ በዚህ ላይ የፓትርያርኩ ካሉት ፍንክች የማይሉ መሆን ሲጨመርበት ችግሩ ይንቀለቀላል፡፡ ይሄን ችግር እያሟሟቁ ስሜት ማናር የእናንተ ደስታ ነው፡፡

  • Dereje Megersa February 25, 2016 at 12:51 pm Reply

   ወዳጄ ሆይ! አንድ ሰው የተናገረውን የሚያስተባብለው መቼ ነው? ሌላው ውሸት ሲናገር፡ የተናገረከው ትክክል ዐይደለም ይሄ ይሄ ማስረጃ አለኝ ብሎ ማስረጃውን ሲያቀርብ የማስረጃውን ትክክለኛነት ከመመርመር ይልቅ የበላይ ስለሆነ ብቻ ውሸቴን እውነት ነው ብለህ ካላወጅህ አጠፋሃለሁ ማለት ትርጉም ይኖረዋል? ስለ ኮሌጆቹ የተፃፈው ተመርምሮ ሃሰት ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ተግሳጽም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ያ ባልሆነበትና ችግር አለባችሁ የተባሉት ስለወሰኑ ብቻ አስተባብል ማለት ትርጉም አልባ ዝባዝነኬ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ይሄንን ፊደል የቆጠረ ቀርቶ ያገሬ ባላገር እንኩዋን አይስተውም፡፡

   ዕንደእርሳቸው ዓይነት ትልቅ ሃላፊነት ላይ ያለ አባት በፆም በፀሎት ተወስኖ ልጆቹን ሲያጠፉ እመከረ የሚመልስ ፡ የሁሉንም ወገን ሰምቶ ፍትህ የሚጠነቅቅ እንጂ እንደዚህ አይነት አታካራ ውስጥ መግባት ፈፅሞ የማይጠበቅ ነው፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሃላፊነት እና ስራ ባለባቸው ሁኔታ ዐሁን ለቤተክርስቲንም ሆነ ለራሳቸው ምን ሊያተርፉበት ነው በእልህ እና በአውዳሚ ስራ የተጠመዱት? ችግሩ ዙሪያቸውን ጥቀመኞች እና የራሳቸው ዓላማ ያላቸው ግለሰቦች ናቸው የሚመራቸው፡፡ የሚሳዝነው እነዚያ ሰዎች የሚናገሩት ሁሉ እውነት ይመስላቸዋል ከዚ ውጭ ስላለው ነገር ፈፅሞ የሚያውቁት የለም፡፡

   ዕንደዚህ አይነት በአሉባልታ የተሞላ እና ትርጉም አልባ ደብዳቤ እንዲፅፉ እና ትዝብት ውስጥ እንዲወድቁ የሚያደርጉ አሳሳች የዲያብሎስ መልክተኞች መቸ ይሆን የሚላቀቁትና ነፃ የሚዎጡት? አሁን እርሳቸውን ለመውቀስ አልፈልግም ለእርሳቸውም ለቤተክርስቲንም ስል ብቻ ከነዚህ መሳቲወች ነፃ አውጣቸው ብየ ግን ሁል ጊዜ እፀልያለሁ፡፡

   አሁን እውነት ስንት የሚሰራ ስራ ሞልቶ የተሰራውን ለማፍረስ መታተር ምን ኣይነት አላማ ይኖረዋል? ሌላ የሰራውን ማፍረስ ቀላል ሊሆን ይችላል ለመስራት ግን ያለው አቀበት ብዙ ነው፡፡ እስቲ ከተሾሙ ጀምሮ ለቤተክርስቲን ምን አይነት ለውጥ አመጡ? ዐባቴ ሆይ እባከዎን ዙሪያዎን ከከበበዎ አረም ራስዎን ያላቅቁ እና ያባቶችዎን ፈለግ ይከተሉ፡፡

   • Anonymous February 26, 2016 at 6:54 am

    ትገርማላችሁ፡፡በፌስቡክ እና በብሎግ የማኅበሩ አፍቃሪዎች እያሽመኖነሞኑ ከሚያቀርቡላችሁ መረጃ ውጭ ምንም ለመስማትና ለማጣራት ዝግጁዎች አይደላችሁም፡፡ለተሐድሶ ሚዲያዎች መፈልፈል ትልቅ ፍግ የፈጠረ ከባድ ቡድንተኛ የሚዲያ ኔትወርክ አለ፡፡ኮሌጆቹ ቀጥታ ለማኅበሩ በአድራሻ የቅሬታ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡ነገር ግን ይሕ ቅሬታ በማኅበሩ አፍቃሪ ብሎጎች የሚዲያ ሽፋን እንዳያገኝ ተደረገ፡፡ በዚህ የማኅበሩ ቅንነት የጎደለው ዝምታ ቅሬታ የተሰማቸው ኮሌጆቹ ቅሬታውን ወደ ፓትርያርኩ ወሰዱት፡፡ በዚህ ጊዜ ፓትርያርኩ ማኅበሩ ማብራሪያ እንዲሰጥ አለማድረጋቸው ክፍተት ነው፡፡ ሆኖም የእሳቸው የአካሄድ ክፍተት ማኅበሩ ኮሌጆቹ ጥያቄ ላይ ያሳየውን ከቅንነት ውጭ የሆነ ምናልባትም ንቀት የተሞላበት ዝምታ ይቅር አያሰኝም፡፡

    ለራሳችሁ የምትሰጡት ግምት በጣም አስገራሚ ነው፡፡ሲጀመር በማኅበረቅዱሳን ቡራኬ አይደለም ቤተክርስቲያን እየኖረች ያለችው፡፡ሁሉንም ትሩፋታችሁን በሚዲያ ስለምታወጡት እኛ ብቻ ነን ቤተክርስቲያኗን ቀጥ አድርገን የያዝን ብላችሁ የምታስቡ ትመስላላችሁ፡፡ሲቀጥል በምትሰሩት ሥራ ሁሉ ከወረዳ እስከ ቤተክሕነት ያሉ የቤተክርስቲያኒቱ መዋቅሮች ያላቸውን ቀና ትብብር እና ተሳትፎ እንደ ቤተክህነት ተሳትፎ ያያችሁት አትመስሉም፡፡ከሁሉም በላይ አገልግሎታችሁ የቤተክርስቲያኗ የሕልውና ጉዳይ ለመሰኘት በጣም ረጅም ርቀት እንደሚቀረው አልተገለጸላችሁም፡፡የማኅበሩ አስተዋጽኦ በፐርሰንት ይቀመጥ ቢባል የአንድ ወረዳ ቤተክህነት በጀትም አይሸፍንም እኮ፡፡ሰው ክፉ አታናግሩ፡፡

    በማኅበሩ ከላይ እስከ ታች የተንሰራፋው የቤተክርሰቲያኒቷን መዋቅር የማስተሀቀር እና ከቅንነት የራቀ አንጓጣጭነት በታሪክ ታይቶ አያውቅም፡፡እጅግ አሳዛኝ አዝማሚያ ነው ያለው፡፡የአቡነ ሺኖዳንና አቡነ ጎርጎርዮስን ስም እየጠሩ በመንበሩ የሚሰየሙ አባቶችን ለክቶ መቁረጥ እንደ አዋቂነት ሆኗል የሚታው፡፡መዋቅሩ ከባድ የሚባል የሚዲያ ክፍተት አለበት፡፡ይሄን ሁላችንም እናውቃለን፡፡ሆኖም ማወቃችንን ክፍተቱን ለመሸፈን ሳይሆን ይብሱን አባቶችን ከምዕመናን የማቆራረጫ መልካም እድል አድረግን ወስደነዋል፡፡ክፍተቱን ማኅበሩን ብቻ ነጥሎ ለማጉላት በአንጻሩ ቤተክህነቱ የሚያከናውናቸውን የልማት እና የስብከተ ወንጌል ሁለንተናዊ እንቅስቃሴዎች አስተዳደራዊ እንከኑን ብቻ በማጉላት ለመሸፈን ሩጫ ነው፡፡

    ማኅበረ ቅዱሳን ውስጥ በእርግጠኝነት የትውልድ ክፍተት ተፈጥሯል፡፡በእነ ቀሲስ ደጀኔ እና ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ደረጃ ጥልቅ አንባቢ፣ሰባኪና ተንታኝ ትውልድ እየተፈጠረ አይደለም፡፡ከሞላ ጎደል ራሱን በሀገራዊ ትውፊትና ንባብ አበልጽጎ ብሔራዊ ማንነቱን አክብሮ የሚያስከብር ሳይሆን በአቡነ ሺኖዳ እየማለ ኢትዮጵያውያን አባቶችን ማነወር ትልቅነትና አዋቂነት የመሰለው ደካማ የሳይበር ትውልድ እየተፈጠረ ነው፡፡ዛሬ ከሞላ ጎደል ማኅበራዊ ሚዲያውን የአሉባልታ መድረክ የተቆጣጠረው ይሄ ትውልድ ነው፡፡

    ትውልዱ ተቆርቋሪነቱና እምነቱ ሳያንሰው እጅግ ስሜታዊ፣ራሱን ብቻ የሚያዳምጥ፣ለከንቱ ውዳሴ የተጋለጠ፣በቀላሉ በፍረጃና በሐሜት የሚነዳ፣የንባብ ሳይሆን የአሉባልታ ተገዥ፣በስክነት ከታላላቆች መመካከር እርሙ የሆነ፣ዘወትር ስለራሱ መብታ እና ስለሌላው ግዴታ ብቻ የሚሰብክ፣የተጋነነ እልህ እና ጀብድ የተሞላ፣ሁልጊዜ ራሱን ትክክል ለማድረግ የሚፈጥን፣ክፍተትን ለመድፈን ሳይሆን ለማላከክና ለማጮህ ብቻ የሚፋጠን፣ብዙ ሆኖ ስለተናገረ ትክክል የሆነ የሚመስለው፣ሁሉም የአካሄድ ልዩነቶች የጽድቅና የኵነኔ የሚመስሉት፣የሃይማኖት ቀናኢነት የሁሉም ኃጢአት መሸፈኛ የሚመስለው፣ሙሉ ሐሳብንና ጽንሰ ሐሳብን ለመረዳት ከመሞከር ይልቅ የተወሰኑ ቃላትን ቆንጽሎ በራሱ ትርጓሜ ለሚፈልገው ዐላማ አጀንዳ ፈጥሮ የሚጩዋጩዋህ፣በአጠቃላይ ልጅነቱ የሚያሳሳ ሆኖ ሳለ ለማቀፍ ደግሞ እሳትነቱ የሚፋጅ ትውልድ ተፈጥሮ ግራ አጋባን፤አምላክ ያብጀው፡፡

    የብሎጉ አዘጋጆች ደግሞ ስንትና ስንት ስድብ እንዳማታወጡት ሁሉ የሰው ሐሳብ መቆራረጣችሁ ያሳዝናል፤ ስለፈጠራችሁ እኛ ከማኅበሩ የተወሰኑ የአካሄድ ልዩነቶች ያለን ኦርቶዶክሳውያንን ደምጽም ለማክበር ሞክሩ፡፡

 5. TG Ka Harare February 25, 2016 at 8:02 am Reply

  ቅዱስ ፓትርያርኩ ማኅበረ ቅዱሳን በ5 ቀን ውስጥ ይቅርታ ይጠይቅ ያሉት እስካሁን በጻፏቸው ደብዳቤዎችም ሆነ በጠሯቸው ስብሰባዎች ላይ ማኅበሩ ዕውቅና የሌለው መተዳደሪያ ደንብ የሌለው በራሱ የተደራጀ መሆኑን ሲገለጹ ቆይተዋል፡፡
  ታዲያ ዛሬ መመሪያ ከሌለው ዕውቅና እና ተጠሪነት ከሌለው በምን አግባብ ይሆን ይቅርታ ይጠይቅ የተባለው፡፡ ይቅርታ የሚያስጠይቅ ምን ጥፋት ወይም ምን በደል ሰርቶ ይሆን? እባክዎትን ተሐድሶ መናፍቃን እኮ በግልጽ እቤትዎት ገብተው እርሶ የተቀመጡበት ወንበር ላይ ተቀምጠው እናስተምር ሊሉዎት ተዘጋጅተዋል፡፡ ስለዚህ ይህንን እየሰሙ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የማያስፈልግ ወይም ፍሬ የሌለው ነገር ከምታጽፉ ከሚያስፈርሙዎት ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅምና ነገ እርስዎን የሚያስመሰግን ታሪክ ሰርተው ቢያልፉ ታሪክ አይረሳዎትም በዚህ መልኩ ከሆነ ግን የታሪክ ተወቃሽና አሳዛኝ ታሪክ ትተው እንደሚያልፉ አይዘንጉት፡፡ ለእርስዎም ሆነ ለሚያሳስትዎት እግዚአብሔር አምላክ ማስተዋልን ያድላችሁ፡፡

  • Ameha February 25, 2016 at 8:06 pm Reply

   ይኼ የሚባለውንም ሰምቼ ነው፤ ስለተነገረኝ የሰማኹት ነው፤ አላነበብኩትም፤ እንዲኽ እንዲኽ ብለው በነገሩኝ ነው፤”

 6. TG Ka Harare February 25, 2016 at 8:35 am Reply

  ወይ ቤተ ክርስቲያን ስንት ሕይወታቸውን የሰዉልሽ አባቶች እንዳላሳለፍሽ ዛሬ እንዲህ አይነት አባት የኑርሽ? እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጣቸው ሌላ ምንም ማለት አይቻልም በዙሪያቸው ተሰብስበው ያሉትን የሚያሳስቱዋቸውንም ልብ ይስጣቸው፡፡ ማስተዋሉን ያድላቸው እላለሁ፡፡

 7. Abiy February 25, 2016 at 9:24 am Reply

  ሕገ ቤተ ክርስቲያናችን፣ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከሢመተ ፕትርክና በኋላ የተቀበሉትን ሓላፊነት በመዘንጋት ሊሳሳቱ እንደሚችሉ (fallible) ተመልክቷል፡፡ ከዚኽም በላይ፣ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን መጣሳቸው፤ በተሾሙበት ቀን የፈጸሙትን ቃል አለመጠበቃቸው፤ በአጠቃላይ ታማኝነታቸውና መንፈሳዊ አባትነታቸው በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት አጥቶ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር መፈጸማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ በተጨባጭ ከተረጋገጠ ከሥልጣናቸው እንዲወርዱ ሊወሰንም ይችላል፡፡

 8. De Azemach February 25, 2016 at 9:26 am Reply

  Agetuni Kelebate……..Weshoch kebebugn endale ……..

 9. Dereje Megersa February 25, 2016 at 12:52 pm Reply

  ወዳጄ ሆይ! አንድ ሰው የተናገረውን የሚያስተባብለው መቼ ነው? ሌላው ውሸት ሲናገር፡ የተናገረከው ትክክል ዐይደለም ይሄ ይሄ ማስረጃ አለኝ ብሎ ማስረጃውን ሲያቀርብ የማስረጃውን ትክክለኛነት ከመመርመር ይልቅ የበላይ ስለሆነ ብቻ ውሸቴን እውነት ነው ብለህ ካላወጅህ አጠፋሃለሁ ማለት ትርጉም ይኖረዋል? ስለ ኮሌጆቹ የተፃፈው ተመርምሮ ሃሰት ከሆነ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ሳይሆን ተግሳጽም ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ያ ባልሆነበትና ችግር አለባችሁ የተባሉት ስለወሰኑ ብቻ አስተባብል ማለት ትርጉም አልባ ዝባዝነኬ እንጂ ሌላ ሊሆን አይችልም፡፡ ይሄንን ፊደል የቆጠረ ቀርቶ ያገሬ ባላገር እንኩዋን አይስተውም፡፡

  ዕንደእርሳቸው ዓይነት ትልቅ ሃላፊነት ላይ ያለ አባት በፆም በፀሎት ተወስኖ ልጆቹን ሲያጠፉ እመከረ የሚመልስ ፡ የሁሉንም ወገን ሰምቶ ፍትህ የሚጠነቅቅ እንጂ እንደዚህ አይነት አታካራ ውስጥ መግባት ፈፅሞ የማይጠበቅ ነው፡፡ ብዙ መንፈሳዊ ሃላፊነት እና ስራ ባለባቸው ሁኔታ ዐሁን ለቤተክርስቲንም ሆነ ለራሳቸው ምን ሊያተርፉበት ነው በእልህ እና በአውዳሚ ስራ የተጠመዱት? ችግሩ ዙሪያቸውን ጥቀመኞች እና የራሳቸው ዓላማ ያላቸው ግለሰቦች ናቸው የሚመራቸው፡፡ የሚሳዝነው እነዚያ ሰዎች የሚናገሩት ሁሉ እውነት ይመስላቸዋል ከዚ ውጭ ስላለው ነገር ፈፅሞ የሚያውቁት የለም፡፡

  ዕንደዚህ አይነት በአሉባልታ የተሞላ እና ትርጉም አልባ ደብዳቤ እንዲፅፉ እና ትዝብት ውስጥ እንዲወድቁ የሚያደርጉ አሳሳች የዲያብሎስ መልክተኞች መቸ ይሆን የሚላቀቁትና ነፃ የሚዎጡት? አሁን እርሳቸውን ለመውቀስ አልፈልግም ለእርሳቸውም ለቤተ ክርስቲንም ስል ብቻ ከነዚህ መሳቲወች ነፃ አውጣቸው ብየ ግን ሁል ጊዜ እፀልያለሁ፡፡
  አሁን እውነት ስንት የሚሰራ ስራ ሞልቶ የተሰራውን ለማፍረስ መታተር ምን ኣይነት አላማ ይኖረዋል? ሌላ የሰራውን ማፍረስ ቀላል ሊሆን ይችላል ለመስራት ግን ያለው አቀበት ብዙ ነው፡፡ እስቲ ከተሾሙ ጀምሮ ለቤተክርስቲን ምን አይነት ለውጥ አመጡ? ዐባቴ ሆይ እባከዎን ዙሪያዎን ከከበበዎ አረም ራስዎን ያላቅቁ እና ያባቶችዎን ፈለግ ይከተሉ፡፡

 10. Anonymous February 25, 2016 at 3:41 pm Reply

  ahunim esat lay benzin atarkefkifu tewu yenante yazugn liqequgn malet ene bich negn tikikil malet yetignaw abat endastemarachihu alawqim.
  Mahberu enken alba aydelem sihtet enkuwan bayfetsim yetesalewun seyif lemalef yiqrta biteyiq aygodam kezia yiliq megedader man alebigninet ayawatam.
  esti yetignaw kahin new ye facebook ye blog ateqaqem yemiyawiq yihe hulu betekirstiyanin sedbo lesedabi asalfo yemisetew enante guya yadege be gibi gubae yetemare aydelem ende mahberun kebetekirstiyan meleyet aqitot yekahinatin kibir eyawarede wudase mariyam sayizeliq ke 4 aynaw gar ekul ohoto edit eyetederege yebetekirsiyan tebaqi ene negn yemil? ere bemin mesfert new ke abatoch gar chama melekakat tikikil yemihonew
  ye tint qininetachin yewahinetachin hulun amen bilen yeteqebelnbet yebereket zemen nafeqegn.
  esti yemahberer kidusan kadre agelgayoch kahinat yetignaw new kidase erasun chilo kediso yemiweta? tselote haymanot astekakiklo sayzelq ahdu ab lemalet difret yagegnew keyet new? kidase operasion aderego weta eyetebale lelaw degmo wudse mariyam sitadel meqdes yemidebeq yedebir astedadari hizb yemayawq eyemeselew seatatun kererto yemiyadergew defar… bicha defar behulim neger defar agelgay betemeqdesunim abatochinim yemidefir man alebign yemender awdelday hulu atrnosun yizotal
  lemehonu beyetignaw mesfert new ye 3 wer yeziway kors baleqinewun balediguwan ye aquwaqam ye hadisatina yebiluyati memehrun lemnqef certeficate ayhonim
  yetignaw qolo timihrt bet gebto temiro new ere tewu yemitazeb ale
  esti zewer bilachihu eygelegle yalewun bemedrek litay litay yemilewun agelgay temelketu
  hulu neger be tifozo eyehone new rega enibel betekiristiyanin yet linadersat new yasebnew?
  sedo masaded yibqa lezihich betekerstiyan yemitaznulat kehone ye face book ye blog fitawrariwochin esti letewsen gize minim endaytsifu zim bilew egziabhern enditebqu nigewuwachew esti legizew efoy enibel egziabher ersu endisera edil enistew subae tselot mihila be abatoch endiyaz yidereg
  beyibelt be mahberu sim nigdachewun yemiyaderutin america yalutin adeb endigezu nigeruwachew esti yetsetita gize yinuren
  ene yemilew mahibere hawariyat minew zim alu weyis enesun mesmat tewachihu
  Mechem kidus patriariku hone Nibure Ed Eliyas be minfiqna aytamum silezih chigru ye astedader new be sekene menged yifeta
  Egziabher tewahido haymanotachinin ketegafetechiw fetena ashagroat hulu endeqdmow yefiqr yemetesaseb zemen yamitalin
  Firhaten sigaten endemitgarugn tesfa alegn
  kelay yezerezerkut endale hono neger gin gulbetachewun saysesitu geteritun netekirstiyan yemiyageleglu tihut agelgayoch atibiya betekerstiyanachew hiywetachew yehonech be kininet yemiseru be zemenawi ketemaru behuwal abinet timihrt bet gebtew yemimaru ke america dires metitew yemimaru wustachewum layachewum kirstiyan yehonu alu egzabher enesun yabzalin

 11. Anonymous February 25, 2016 at 5:41 pm Reply

  ቅዱስ አባታችን እንበል ሳይገባቸው እንበላቸው በማህበሩ ላይ ስለተነሱ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እየመሩ ስላልሆነ፡፡ ድሮ ግብጻውያን እንዲህ አደረጉን እንል ነበር አሁን የኛው ሰው እንዲህ አደረጉን ብለን ትውልድ ሁሉ ወደ ፊት የሚያወራላቸውን ጉድ አገኘን ያሳዝናል፡፡ ሲጀመር ስለ ዶግማና ቀኖና ማን ነው ቀናዊ ሆኖ እየታገለ ያለው ስንል በባለፈው ማህበሩን በከሰሱት ውስጥ ቢያዩት ለመናገር ሞራሉም ድፍረቱም የለዎትም ነበር፡፡

  ለመሆኑ የሐዋርያት ትውፊት የቤተክርስቲያናችን ጥንታዊነት እየጠፋ ያለበት ሁኔታን እያስገነዘበ ያለው ማን ነው እናተ ናችሁ እንዴ ፡፡ እስርዎት ሆነው ስለ ሌብነት እንጂ ስለ ቤተክርስቲያን የሚያስብ ጭንቅላት ያለው አለ እንዴ፡፡ ቤተክርስቲያን እየተበጠበጠች ያለችው እርሶ በሚመድቡዋቸው ሌቦች አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች አይደል እንዴ ከተወሰኑት በስተቀር፡፡ ዛሬ የዚህን ማህበር መፍረስ የሚፈልጉት እነዚህ አልጠግብ ባዮችን ሰብስበው በማወያየት አይደል እንዴ፡፡ ማህበሩ እንኩዋን በጎ ፈቃደኛን እያስተባበረ በቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው መመሪያና መተዳደሪያ ደንብ እየተመራ የሚታይ ስራ ሰርቶ ስራውን አስመስክሮዋል የሰራውንም ስራ ወጪ ገቢ በየአመቱ በውጪ ኦዲተር ሳይቀር እያስመረመረ ሪፖርት ይደርሶታል አምስት ሳንቲም የምትጎድል የለችም እንደውም ለአገልግሎት ከራሳቸው ኪስ ሲያወጡ ነው የምናውቃቸው፡፡ የእርሶ አጃቢና ተመዳቢዎች አሉ አይደል እንዴ ምዕመና የሰጡትን ከቤተክርስቲያን ዘርፈው ኪሳቸው የሚከቱ፡፡ መኪና የሌለው አለ እንዴ አሁንማ እከሌ የተባለው አስተዳዳሪ ምን አይነት መኪና ነው፤ ስንት መኪና ነው ፤ ስንት ቤት አለው ፤ ባለስንት ፎቅ እየተባለ የሚወራው፡፡

  ከምዕመና ጋር ግጭት ውስጥ የሚገቡ አስተዳዳሪዎችን አንዱጋ ሲነቃ ተቃውሞ ሲበዛበት ሌላጋ ይመደብ የሚባለው ያደራጁዋቸው ሌቦች ቢሆኑ አይደለም እንዴ፡፡ እነዚህን ሌቦች ለመንካከብ የግድ የሌባ ተቃዋሚና ሚስጥር አዋቂ መጥፋት እንዳለበት ስላመኑበት ሩጫዎትን አበዙ ግን ምንም አይሆንም፡፡ ቁዋሚ ሲኖዶስ ተሰብስቦ በመንፈሳዊ ኮሌጆች ላይ ምርመራ ይደረግ ባለበት በቅርብ ቀናት የእርስዎ ልክ አይደለም ማለት ውንብድናው እረሶምጋ እንዳለ ያሳያል፡፡

  ለመሆኑ ቅዱስ እስጢፋኖስ ለፍርድ ሲያቀርቡት በሃሰት መልስ መስጠት ችሎ ነበር እናንተ ከበላይ ላለ መልስ መስጠት አይገባም ትላላችሁ ጠርታችሁ አነጋግራችሁት ታውቃላችሁ፡፡ ለመሆኑ ማን ነው የሃሰት ነገር ሲናገሩበት ዝም የሚል እርስዎ ጠርቶ ለምን እንዲህ አላችሁ ማለት ሲገባ እውነቱን መቀበል ሲያንገሸግሻችሁ እያደባችሁ ይህንን በማለትህ ብላችሁ ሱሪ በአንገት ትላላችሁ፡፡ የምንልህን ተቀበል ሲባል ዶግማና ቀኖና ድሮም የነበረውን አሁንም ብትሉት እንቀበላለን፡፡

  ሌባውን ከስራችሁ አድርጋችሁ የማይሰርቀውን ሌባ ብንልህም ዝም ብለህ እመን አይሆንም ለምን ለነገ ሌላ ክስ ያመቻልና፡፡ አልሰረኩም ቢል ዳኝነት መቆም ግድ ነው ፍትህ ይገኛልና አሁንም ፓትርያሪክ ሆይ አቁዋምዎትን አስተካክሉ፡፡

 12. Anonymous February 25, 2016 at 6:40 pm Reply

  እኔ እንዳነበብኩት ከፓትርያሪክ ጽ/ቤት ወጣ የተባለው ደብዳቤ የመጀመሪያው ማለት ነው መናፍቃን በማህበሩ ላይ በየብሎጋቸው፤ በፌስቡክ፤ በየመጽሔቶቻቸው ላይ ሲያወጡት ሲያወሩት የነበረ ሰውንም ያሰለቸውን ነገር ነው፡፡ ካስፈለገ ከዚህ ቀደም ማን እንደተናገረው ማቅረብ ይቻላል፡፡ አጠገባቸው ያሰቀመጡዋቸው ሙሰኞች፤ አማሳኞች ሌቦች ሰብስበው ሰጡዋቸው አገኘሁህ ብለው ፈረሙበት፡፡ ከዛም ማህበሩ በተባለባቸው ጉዳዮች ቀርበህ መልስ ስጥ መባል ሲገባው ምንም ሃሳቡን የሚገልጥበት እውነታውን ምንም ይሁን ስሜቱን የሚገልጥበት ሁኔታ ማመቻቸት የግድ ይላል፡፡ ያለበለዚያ ግን ሊቀ ካህናት ሰብስቦ እራሱ ሊሰቀል ይገባዋል ብሎ ለህዝቡ ውሳኔ እንዳሳለፈው አይነት ሆነ፡፡ ጌታን ላይሰሙት ውሳኔያቸውን ላይለውጡ ተናገር ብለውት ነበር እርሶ ግን አላደረጉም፡፡ ውሳኔዎት ከአይሁድ ካህናት የከፋ ያደርገዋል የማይጠበቅ፡፡

  ቅዱሳን ሐዋርያት አባቶቻችን ችግር ሲኖር ይህንን እንዲህ አድርጉ ብለው መመሪያ በደብዳቤ ሲያስተላልፉ ከቀበሌ እስከ ጠቅላይ ሚንስትር ድረስ ግልባጭ እያደረጉ አልነበረም ለምን ቤተክርስቲያን የራስዋ መዋቅር አላትና፡፡ ለሮሜ ሰዎች መልእክት ፍርድ ሲያስተላልፍ ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ንጉስ ድረስ ግልባጭ አድርገው አይደለም ታዲያ ቀኖና በመጀመሪያ የጣሰ ማን ነው፡፡ እነሱ ቢያደርጉ ለተጻፈብን መልስ የሰጠነው ይህንን ነው ብለው ነው፡፡ በመጀመሪያ በውስጥ ጠርተው ቢያናግሩዋቸው በውስጥ ያልቅ ነበር፡፡ እርስዎ ባወጡት ነገር ለምን መልስ ሰጠህ አይባልም እድሉን ቢሰጡዋቸው የቤተክርስቲያንን ህግ በጠበቁና ባስጠበቁ ነበር፡፡ እርስዎን እራሱ ለማህበሩ የዛ አይነት ደብዳቤ እንዲጽፉ ማን ፈቀደሎት፡፡ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል መናገር ሲገባዎት ስርአትና ደንቡ በማይፈቅድ መልኩ ሄደው ማህበሩን ደንብ ጣሰ ማለት ይገባልን፡፡

  ቤተክርስቲያናችን ከካቶሊክ ወይም ከሌሎች እምነቶች ከምትለይበት አንዱ ሰው ይሳሳታል ብላ መቀበልዋ ነው ይህ ደግሞ ቅዱስ ይባሉ እንጂ እርሶንም ይመለከታል፡፡ ዶግማ ቀኖና ትውፊት እምነትን በማስተማር በማሳወቅ በመጠበቅ በኩል ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ የሚገኝ ቢኖር ማህበረ ቅዱሳን ነው ይህንን እርሶም ጠንቅቀው ያውቁታል ግን ስርዓት አልበኞች እንደዚህ አይነት ሰው እንዲኖር አይፈልጉም ለምን ይህ የአባቶቻችን ስርዓት እምነት ቀኖና አይደለም ብለው የሚጠይቅ ተውልድ እንዳይኖር ስለሚፈልጉ ለማጥፋት በመጀመሪያ ማህበሩ መጥፋት ስላለበት ማህበሩን ለማጥፋት በርስዎ በኩል ብቅ አሉ፡፡ ባይገርምዎት የቤተክርስቲያኒቱን ህልውና ያስደፈሩት እርስዎ ኖት፡፡ ግጭቶችን በቀላሉ መፍታት የምትችል ታላቅ በዓለምም ተመራጭ የምትሆነውን ቤተክርስቲያን ተራ ሰዎች አጠገብዎ አስቀምጠው አስደፈርዋት፡፡ በመዋቅርዋ ማንም ገብቶባት ድምጽዋም ተሰምቶ አይታወቅም ነበር አሁን ግን አዘንን አንገታችንን ዝቅ እንድናደርግ ሆነ እናዝናለን፡፡

  ከእርስዎ ምን እንማር ፡፡ ማህበሩን የሚያውቀው ብዙ ከብዙም ብዙ ነው፡፡ የሚታይ ነገር ነው የሚሰራው እርሶም ያውቁታል፡፡ የአንድ ሰው ነፍስ አስጨንቆት ጠረፋማ አካባቢ ሳይቀር መስዋእትነት ከፍሎ ከአህዛብነት ወደ ሐዋርያዊት ቤተክርስቲያን እንዲቀላቀሉ እያደረገ ያለን ማህበር ለመናገር መድፈርዎት ፍርደ ገምድልነት ነው፡፡ ይልቁንም አጠገብዎት ያሉትን ለአንድ አይደለም ኪሳቸው አይጉደል እንጂ ሰውን ወደ ምንፍቅና እየነዱት ያሉት ቤተክርስቲያኒቱን አለመረጋጋት ውስጥ እየከተቱዋት ያሉት እነሱ ናቸው ለምን አስተዳዳሪው እዘርፋለው ሲሉ አናዘርፍም ሲል ሰው በሚፈጠር አተካሮ ማለት ነው ይህ ደግሞ በብዛት እየተስተዋለ ነው፡፡ እስከምናውቀው ቅድስት ማርያም አጠገብዎ በርሰዎ የምትተዳደር ቤተክርስቲያን በብዙ ሚሊዩን የሚቆጠር ብር ነው የተዘረፈችው ይህንን አጣርተዋል ወይንስ ተጋርተዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ያባረራችሁዋቸው ሰዎች ሰበካ ጉባኤ አባላቱ ቤተክርስቲያኒቱን ለቀው መውጣታቸው በማን ሰበብ ይመስልዎታል፡፡ እንደዚህ አይነት ነገር ከተወሰኑት በስተቀር በብዛት እየተፈጸመ ነው፡፡ ታዲያ ማህበሩ ነው ምዕመናን ውስጥ አለመተማመን የሚፈጥረው የርስዎ ጋሻጃግሬዎች ናቸው፡፡

  በገንዘብ በኩል ማህበሩ የግሉን ሳሆን የቤተክርስቲያኒቱ አካል የሆኑትን ገዳማትን አድባራትን የአብነት ትምህርት ቤቶችን እየረዳ በሚያስፈልጋቸው እያሙዋላ ቢያንስም ምዕመናንን እያስተባበረ ይሰራል በተገቢውም ኦዲት አሰደርጎ ያሳውቃል ታዲያ ያን ጊዜ ለምን ይህንን የሰራችሁት ልክ አይደለም አይሉም ነበር ነው ጌታ እንደተከሰሰው የሀሰት ክስ ማግኘትዎት ነው፡፡ ይልቁንም ይህንን ያክል ሚሊዮን ብር ዘረፉ ተብሎ በየጋዜጣው ላይ ያለውን የአደባባይ ወሬ መፍትሄ ይስጡ፡፡ ህዝብ ተቃውሞ ያነሳባቸውን አይዞህ ማለት ትተው ህዝብ የደገፈውን አይኮርኩሙ፡፡

  ይቅርታ መጠየቅ ለማንም ያለ ነገር ነው፡፡ የተናገርኩት ልክ አይደለም ሳይሆን መረጃ ካለ ማህበሩ በጋዜጣው ላይ ያወጣቸው ነገሮች ላይ መረጃው እንዳለው አቅርብ ከተባለም እንደሚያቀርብ በመጠቆም ነገር ግን በጅምላ ሁሉንም የኮሌጆቹን አባላት የሚወክል አለመሆኑን እንደዛ የመሰላቸው ንጹሐን አባላት ካሉ ይቅርታ ማለት ምንም ማለት አይደለም ለምን ቢሉ ማህበሩ መልስ በሰጠባቸው ውስጥም ከተለያዩ የኮሌጁ አባላት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ እንደሰጠ ገልጾ ስለነበር አሁንም ማብራሪያ በመስጠት ቢገልጠው ችግር የለውም፡፡ ቅዱስ ፓትርያሪኩም ቢሆኑ ጠርተው በጻፉዋቸው ጉዳዮች ላይ መልስ መስጠት እንዲችሉ ባለመደረጋቸው በግልባጭ እንዲያውቁ የተደረጉት አካላትም ሆኑ ሌሎች ማህበሩን በተለየ አመለካከት እንዳያዩት የማህበሩን ምልከታ የተለየ እንዳያደርገው ማህበሩን ይከሱ የነበሩ የማህበሩ ባላንጣ የሆኑ ማህበሩን ሲከሱት የነበረበት መንገድ ስለነበር የማህበሩ ገጽታ በክሱ ላይ ምን እንደሆነ እንዲያውቁ እንዲሁም በማህበሩ ላይ በውስጥ ሆነው አሁንም ይህንን የሚያንጸባርቁ እንዳሉ ለመግለጥ እንጂ እርሳቸውን ለመንካትና ላለመታዘዝ እንዳልሆነ በመግለጥ ያጠፋን ከመሰሎትም ይቅርታ ማለት ምንም ማለት አይደለም፡፡

  ነገር ግን ይህ ይቅርታ ወደፊት አስገዳጅ ነገር ይዞ እንዳይመጣም መጠንቀቅ የግድ ይላል፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ሲኖዶስ በኮሌጁ ላይ ምርመራ ይደረግና ይቅረብ እያለ ባለበት ሁኔታ እሳቸው ከማይመለከተውጋ ተሰብስበው ለሚሉት ነገር እውቅና መስጠት ነገም ከማይመለከተውጋ ተሰብስበው ይፍረስ ወደማለት ለመሄድ መንገድ ይከፍታልና ነው፡፡ ይህንን ማለት አሁንም እሳቸውን መናቅ ሳይሆን ህገ ቤተክርስቲያንን ከማስጠበቅና ከመጠበቅ አንጻር ነው፡፡ እንደ ህገ ቤተክርስቲያን መወያየት ያለባቸው ከቁዋሚ ሲኖዶስጋ ነውና፡፡ ቁዋሚ ሲኖዶስ ስለኮሌጁ ማጣራት እያደረገ ይቅርታ ማለት እጅ መስጠት ነው፡፡ ለይቅርታ መገዛት ያለ ቢሆንም በህጉ ለመጣ ፍትሀዊ ሆኖ ለሚመጣ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ቤተክርስቲያን በገሃድ በሚዲያ ይቅርታ በሉ ብላም አታውቅም፡፡ ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳያችሁ እንዲገባ ጠይቁ ከዚህ በላይ የቤተክርስቲያን ትልቅ ጉዳይ የለምና፡፡

  ፓትርያሪኩን የምንለው ከመናፍቃን ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ያለውን ትጥቅህን ፍታ ከሚሉ ሌቦችን መናፍቆችን እረፉ ሊሉዋቸው ይገባል እንላለን፡፡

 13. Anonymous February 25, 2016 at 6:44 pm Reply

  ጾመ ነነዌን ጾሙዋት ነው ወይንስ ነገር ሲጎነጉኑባት አሳለፉዋት ነው የሚባለው፡፡

 14. Anonymous February 25, 2016 at 6:48 pm Reply

  ሐዋርያት ምንም ቢባሉ ከጌታችን ከመድሃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ነውና የተማሩት በደስታ አሳለፉ ያውም የማይገባቸውን እየተባሉ፡፡ እረስዎ ግን እውነቱ ሲነገርዎት ከማን የተማሩት ነው የተናገረውን ሰው ለምን አልከኝ ብለው አደባባይ የሚከሱት፡፡ ቅዱስ ዳዊት አንዱ ቢመታው ተውት እግዚአብሔር አዞት ይሆናል ነው እንጂ ያለው በቆንጨራ ምቱት ልኩን አሳዩት ደፈርከኝ አላለም፡፡ እረሶ እንደ ቅዱስ ዳዊት ንጉስ ቢሆኑ ምን ሊያደርጉ እንደሚችሉ መገመት አያስፈልግም፡፡

 15. Anonymous February 25, 2016 at 6:50 pm Reply

  ፓትርያሪክ ቅዱስ ጴጥሮስ በተሰበሰበበት መንፈስ ቅዱስ ይወርድ ነበር ጸጋ ይበዛላቸው ነበር፡፡ እርስዎ በተሰበሰቡበት ምን እንደሚወርድ ገምቱት እንደነ ቀያፋ አይነት ስብሰባ ነውና፡፡ የሚሰበስቡት እነ ይሁዳን ነውና ፡፡

 16. Anonymous February 25, 2016 at 6:56 pm Reply

  እርስዎ በፓላስ ተቀምጠው ምን የመሰለ ወንበር ላይ ተቀምጠው ምን የመሰለ መኝታ ላይ ተኝተው የላመ በልተው ጠጥተው ምን በመሰለ መኪና ተንቀሳቅሰው ከወሮ በሎችጋ ተሰብስበው ሲያደቡ የማህበሩ አባላት ግን እስከ ጠረፍ የእግር ጉዞ በማድረግ አስተዋጽኦ ለቤተክርስቲያናቸው ያደርጋሉ፡፡ ከቀደሙት አባት ከአቡነ ጎርጎርዮስ የተማርነውን ተምረናል ከእርስዎ ምን ተማርን ምን ጻፉልን፡፡

 17. Anonymous February 25, 2016 at 6:59 pm Reply

  ስለ ተሃድሶ ምንም ማለት የለበትም ሲሉ እርስዎ ምን መረጃ ኖረዎት ነው አሁን ያሉት፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ እርሶ መርተውት የወሰነውን እንኩዋን ምን ደረጃ ደረሰ ብለው አያውቁም፡፡ ለእምነትዎ ተጋደሉ፡፡ አይምሰልዎ አቡነ ጳውሎስም ስንት ሲታጀቡ ስንት ሲያደርጉ የነበሩት ሁሉን ጥለው ሄደዋል፡፡

 18. Anonymous February 25, 2016 at 7:02 pm Reply

  ምን አለበት እንደ አቡነ ሺኖዳ ቢሆኑ፡፡ ምነው እንደ በፊቱ ጳጳስ ሆነው በቀሩ እንደዚህ ይሆናሉ ብለን አስበን አልመን አናውቅም ፡፡ እስቲ ከተናገሩት ውስጥ ስንቱን ፈጸምኩ ብለው እራስዎትን ጠይቀዋል ፡፡ ይህንን ቢያደርጉ ከማን ጋር እንደሚሰሩ ያውቁት ነበር፡፡ አሁንም ቶሎ ወደ ህሊናዎ ተመለሱ፡፡

 19. Anonymous February 25, 2016 at 7:03 pm Reply

  ጨው ለራሰህ ብለህ ጣፍጥ ነው እራስዎትን በህዝቡ ዘንድ ያስከብሩ ያለበለዚያ አንቱ አይደለም አንተ እንዳይመጣ ፡፡

 20. Anonymous February 25, 2016 at 7:05 pm Reply

  እስቲ ብቻዎትን ለጥሞና ለተወሰነ ሳምንት ወደ አንዱ ገዳም እዚህ ያለዎትን አስተሳሰብ ትተው ተቀምጠው ከማንም ሳያወሩ የሚያስቡትን ነገር የሰሩትን ነገር ትክክለኛነት ለመረዳት ሞክሩ

 21. Anonymous February 25, 2016 at 7:06 pm Reply

  ከማን ጋር እየሰራሁ ነው ለመሆኑ አሁን ብሞት ፍርዴ ምን ይሆን ብለው አስበው ያውቃሉ

 22. Ameha February 25, 2016 at 8:05 pm Reply

  wawu……. ይኼ የሚባለውንም ሰምቼ ነው፤ ስለተነገረኝ የሰማኹት ነው፤ አላነበብኩትም፤ እንዲኽ እንዲኽ ብለው በነገሩኝ ነው፤”

 23. Anonymous February 25, 2016 at 8:10 pm Reply

  ይኼ የሚባለውንም ሰምቼ ነው፤ ስለተነገረኝ የሰማኹት ነው፤ አላነበብኩትም፤ እንዲኽ እንዲኽ ብለው በነገሩኝ ነው፤”

 24. Anonymous February 25, 2016 at 8:28 pm Reply

  ፓትርያሪኩና ግብረ አበሮቻቸው ጽጌ ስጦታው ቅዱስ ሲኖዶስና ስህተቱ ብሎ ባሳተመው መጽሐፍ ላይ ምነው እርምጃ እንዲወሰድ አለማድረጋቸው፡፡ ይህንንማ ለምን ይነግሩዋቸዋል አያስፈልጋቸውም ፡፡ ኢየሱስና ዲያብሎስ በራስ ቅል ኮረብታ ቁማር ተጫወቱ ያለውን መናፍቅ ምነው ዝም ማለታቸው ፡፡ እንዲህ ተባልኩ ከማለት ለምን እንዲህ አልክ ብሎ መናፍቃንን መጠየቅ፡፡

 25. Anonymous February 25, 2016 at 8:35 pm Reply

  ምን ነው የማቅ ድብቅ አመራሮች ለባችሁ እንደ ፈርዖን ደነደነ ፡፡ ምናልባት በዚህ ርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ይገኛል ብላችሁ ይሆን? የማኅበሩን አባላት ከተሳሳትና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ ከሆነ እንቅስቃሴ ለመጠበቅና ለማዳን ሲባል እኮ ነው ይህ ሁሉ ትእግስት የሚደረገው፡፡ እውነቱ ልንገራችሁ ሕዝበ ክርስቲያኑ ከካህናቱና ከታቦቱ ጋር ይሰለፋል እንጂ ከእናንተ ጋር እንደማይሰለፍ ማወቅ ይገባችኋል፡፡
  ሌላው ማቅ ለሃያ ሦስት ዓመታት በቤተክርስቲያኒቱ የፈጸመው ግፍና በድል እንዲሁም በቤተክርስቲያኒቱ ስም ያግበሰበሰው ሀብት በዚርዝር በማቅርብ ይቻላል፡፡ በዚህ በሃያ ሦስት ዓመታት በእርሱ ምክንያት ምን ያህል ወጣት፤ ሰባክያን እና ምእመናን ከቤተክርስቲያኒቱ እንደፈለሱ ይታወቃል፡፡ በርካታ ሊቃውትም የሚፈጽመውን የተሳሳት ተግባር በመቃወማቸው በሚፈጥርባቸው ተጽዕኖና ፤ በቅጥረኞችና ምግባረ ብልሹ የሆኑት አንዳንድ መሰል ጳጳሳት ምክንያት አንደበታቸውን ዘግተው ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ጊዜ ገቢር ለእግዚአብሔር ወይም ቦ ጊዜ ለኵሉ እንደተባለው ጊዜው ደርሶና ለዚህም ይኄይሰነ ናድሉ ለእግዚአብሔር እምነ አድልዎ ለሰብአ፤ ማለትም ለሰው ከምናዳላ ለእግዚአብሔር ማድላት ይገባናል በማለት፡ ዛቻውን፤ ስድቡን፤ ከምንም ሳይቆጥሩ ታሪኩንና ማንነቱን ፤ ፍንትው አድርገው ያሳዩን የሃይማኖት ጅግኖቻችንን እናመሰግናለን፡፡ ትናንትና ይህ ችግር የአንድ መነኩሴ የአባ ሠረቀብርሃንና የማህበሩ ችግር ነው፡፡ ሲሉ የነበሩት የማቅ የነፍስ አባት ጳጳስ ፤ ዛሬ የብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ፤የቅዱስ ፓትርያሪኩ ፤ የመላው ሊቃውንት፤ ካህናት ፤ሰባክያነ ወንጌል ወጣቶች ጥያቄ ሆኖ ቀረበ፡፡ አባ ሠረቀብርሃን ወ/ሳሙኤል ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያና የድርጅት ኃላፊዎች ስለማኅበሩ አወቃቀርና እያስከተለው ያለ ጥፋት ብሎም በጊዜው ካልተስተካከለ ለወደፊቱ ስሊሚያስከትለው አደጋ በተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ ባቀረቡ ጊዜ “ዛሬ እኔና የሥራ ባልደረቦቼ ብቻ እንጮሀለን፡፡ አንድ ቀን ግን እናንትም ትጮሃላችሁ ፤ ሚልዮናችም ይከተሉታልና” ብለው ነበር፤ እንደተባለው ዛሬ ሁሉም በአንድ ድምጽ ተነስቷል፡፡ ስለዚህ ማቅና የማቅ ስውሩ አመራር ንስሐ ግቡ፡ ቅዱስ ፓትርያሪኩ ይቅርና እናንት፤ ቀኖና ቤተክርስቲያን እየጣሱ የሚገኙና ተጨባጭ መሪጃ የተያዘባቸው መሰል ጳጳሳትም ካልተመለሱና ንስሐ ካልገቡ አቶ ብለው የማሰናበት ሥልጣን አላቸው፡፡ ደግሞ የመላው ሊቃውንት፤ ካህናትና ምእመናን ወክልና ያላቸው እንጂ በጓዳ ገብተው የተመረጡና የተቀመጡ አይደሉም፤፤
  MK PLEASE BE WISE ENOUGH AND DO NOT BE FOOLISH ; RETURN FROM YOUR WRONG WAY AND REPENT FROM YOUR SIN, YOU HAVE TO LITESN THE VOICE OF THE LEADERS OF THE CHURCH.

  • Kuba February 26, 2016 at 2:13 pm Reply

   እዉነቴን ነዉ አንተ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የመናገር ሞራሉም ችሎታዉም የለህም፡፡ እኛ ተመልከች አጥተን በመናፍቃን መንጋጋ ልንወሰድ በደረስን ግዜ ለዛሬ ለብዙ ማንነታችን፤ ቤተክርስቲያንን ያሳወቀን ማነዉ? በቋንቋችን የስተመራን ማነዉ? እናንተ ለሆዳችዉ እንጂ ለነፍስ መች ተጨነቃችዉ? ለሌብነትና ለምንፍቅና ስለማይመቻችዉ ማህበሩን ትነቅፋላችዉ. ሌቦች፡፡

 26. Anonymous February 26, 2016 at 2:19 am Reply

  that’s the way you want and we do know that is your dream. just wait you will see , you are going to receive your wage soon if you are not repent and return back to the church

 27. Tazabiw February 26, 2016 at 3:39 am Reply

  ቤተክርስቲያናችን ከካቶሊክ ወይም ከሌሎች እምነቶች ከምትለይበት አንዱ ሰው ይሳሳታል ብላ መቀበልዋ ነው ይህ ደግሞ ቅዱስ ይባሉ እንጂ እርሶንም ይመለከታል፡

  ለሮሜ ሰዎች መልእክት ፍርድ ሲያስተላልፍ ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ንጉስ ድረስ ግልባጭ አድርገው አይደለም ታዲያ ቀኖና በመጀመሪያ የጣሰ ማን ነው፡፡

 28. Tazabiw February 26, 2016 at 3:42 am Reply

  ፓርትያርኩ እራሳቸው ናቸው ወይስ? …..እኔ እንደሚመስለኝ የጵጵስና ልብስ ለብሶ የሆነ ሰው እየሸወደን ይመስለኛል!

 29. Tazabiw February 26, 2016 at 3:52 am Reply

  @ Samuel
  ኣባታችን ከእግዝኣብሄር ናቸውና እናክብራቸው:How do you know he is from God? I hate silly interpretations of this type. When do you say is something from God? Do not attribute every evil to God. I think that is heresy.

 30. Anonymous February 26, 2016 at 6:01 am Reply

  “ሕጋችን አስቀድሞ ከእርሱ ሳይሰማ፣ ምንስ እንዳደረገ ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” /ዮሐ 7፡51/
  ዛሬስ የገጠመን ይህን ዓይነት የአይሁድ ፍርድ ነው። የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ የጠላቷ ጠባቂ ሲሆን ያየንበት ዘመን! ቅዱስነታቸው ለሞት አሳልፈው የሰጧቸውን የቤተ ክርስቲያን ልጆች እግዚአብሔር ይጠብቃቸው።
  “አቤቱ የሆነብንን አስብ፤ ተመልከት፡ ስድባችንንም እይ። ርስታችን ለእንግዶች፣ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ። ደሀ አደሆችና አባት የሌለን ሆነናል።” /ሰቆ ኤር 5፡1፟-2/

 31. Anonymous February 26, 2016 at 9:30 am Reply

  minm yikirta yemiyasteyik guday yelem ……. mahibere kidusanin yaferisut yihonal hine wist yegenbahun asitesaseb gin liyafersut ayicilum hine ye mahibere kidusan tiwlid negh………..ye mahibere kidusan guday ye betechirstiyan guday new ye betechirstiyan guday yene guday new……………bene dem betekirstiyan tilemelimalech

 32. Anonymous February 26, 2016 at 11:38 am Reply

  ይድረስ ለማኅበረ ቅዱሳን ወንድሞቼና እህቶቼ!!!
  የሰውን ኃጢአት በመቁጠር የጸደቀ የለምና ንስሐ ግቡ
  በግሌ ስለ ብፁዕ ወቅዱስ አባታችንም ሆነ ስለማናችሁም መከራከር አልችልም፡፡ ታዲያ ለምን አርፈህ አትቀመጥም ብትሉኝ ግን ወንድምህ ሲሳሳት ብታገኘው ምከረው ስለሚል ቃሉ ስለዚህ ጆሮ /ልቦናው/ ለሚያስተውል የበኩሌን ምክር ብሰጥ ብዬ ነው፡፡ እግዚአብሔር በቀባው ላለ እጅህን አታንሳ ተብሏልና፡፡ እርሱ አምላካችን አይሳሳትም፡፡ ማን ያውቃል እግዚአብሔር የሾማቸው ወይ ለደግ ወይም ደግሞ ለቅጣት የሆናልና እናንተ ግን የቡድን ስሜት ይዟችሁ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ እንዳትገኙ ልመክራችሁ እወዳለሁ፡፡
  ከሁሉም በላይ በመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን አስተያየት ለመስጠት የሞራል ብቃት ያላችሁ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም በምድራዊ ጥብብና እውቀት የሚለካ አይደለምና፡፡
  የልዑል እግዚአብሔር ሰላም ለእናንተ ይሁን!!!

  • Anonymous February 26, 2016 at 7:13 pm Reply

   ሰው አስተያየት እየሰጠ ያለው እሳቸው ልክ አለመሆናቸውን እንዲረዱ ነው፡፡ አሰተያየት ሰጪው ሁሉ የማህበሩ አባል ነው ማለት አይቻልም ነገር ግን ማህበሩ የሚሰራውን መልካም ስራ የሚደግፍ ይሆንና ስሜት ፈንቅሎት ሃይለ ቃል ሊናገር ይችላል፡፡ አንተም ለማህበረ ቅዱሳን ወንድሞቼና እህቶቼ ማለትህ ትክክል አይደለም፡፡ አባላቱ ይሁኑ አይሁኑ ሳታውቅ አትናገር፡፡ ሰው የስሜቱን ነው የሚያደርገው ጌታ አይሁድ እንዲይዙት ሲያደርግ ቅዱስ ጴጥሮስ ያዥውን አንዱን ጆሮውን ቆረጠው ጌታ ግን አይሁን አለው ማንን ቅዱ ጴጥሮስን ብቻ እንጂ ደቀመዛሙርቱን ሁሉ አይደለም፡፡ አስተያየትህ ፍትሃዊ ይሁን፡፡

  • Anonymous February 27, 2016 at 7:41 am Reply

   “ከሁሉም በላይ በመንፈሳዊ ኮሌጆቻችን አስተያየት ለመስጠት የሞራል ብቃት ያላችሁ አይመስለኝም፡፡”
   … እውን ከልብ ነው? ወንድሜ እህቴ!
   ያውም ለአስተያየት? …. እኔንጃ፤ ከዚህ የወረደ ምን አለ’።

   ምናልባት የዕድሜህን ክልል ባላውቅም ከአስራ ሁለት እመት/12/ በታች እንደማትሆን ግን እምናለው።

 33. Anonymous February 26, 2016 at 1:48 pm Reply

  ይበቃል
  እናት ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ባስተማረችን መሠረት ወደላይ ላለመመልከት እንዲሁም የሚጠበቅብንን ድርሻ ብቻ መወጣት እንደሚኖርብን ታላላቆችን ይልቁኑ የሃይማኖት አባቶቻችንን እንድናከብር ባስተማረችን ጥልቅ ትምህርት እስከ አሁን ድረስ ታግሰን ቆይተናል፡፡
  በየመኻሉም በተለያዩ ወቅቶች ቅጥፈትን ብልግናን ሲያሳዩ ምናልባትም ተታለው (ዙሪያዎን በሙሰኞች እና ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፉ ሌት ተቀን ከሚባዝኑ ነብሰ በላዎች ጋር ስለሚገኙ) ሊሆን ይችላል በሚል እራስን ከምንም በላይ በሚፈታተን ክፉ ስሜት እንኳ ሲሰማን በታላቅ ትዕግስት አልፈንዎት ነበር፡፡
  ይህም አልበቃ ብሎ በላይ በላዩ አከታትለው የሚፈጽሙትን ሴራም ተመልክተን ወደ እግዚአብሐር ለመጮኽ ሞክረንም ነበር፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ትዕግስት ይበልጥ የልብ ልብ እንዲሰማዎ አደረገ መሰለኝ ጭራሽ ዓይን ያወጣ እንኳን ከፓትርያርክ ከአንድ ወያላ ያነሰ ቅጥፈትና ድፍረት ይዘው በማን አለብኝነት ዘልቀዋል፡፡
  ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚገባው መሆኑ ስለማይቀር እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን ከዚህ በላይ ሲያፈርሱ ማየት አግባብ ባለመሆኑ ለፈጸሙት በደል ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ ከፍ ያለ እርምጃ ለመውሰድ ወይም እራሳችችንን ሰማዕት አድርጎ ለማቅረብ ከዚህ ዉጭ ጊዜ ባለመኖሩ እነሆ ልንፋለምዎ ተዘጋጅተናል፡፡ የታጠቁት መሣሪያ ይበላን ይል ይሆናል ቢሆንም ምናልባት የሀገሪቱን ጦር እንደተለመደው ያዙ ከሆነም ያንን ለመጋፈጠ ዝግጁ ነን፡፡ ብንሞት ሰማዕት ለመሆን ብንኖር ድላችንን ለማክበር እነሆ ተነስተናል፡፡
  ስም አጠራሩ ሳይቀር የሚያስጸይፈው አርዮስ ጳጳስ ነበር ልክ እንደዚህ እንደርሶ ቅጥፈቱን የሆነ ጊዜ ላይ ጀምሮ ነበር ነገር ግን በምክርና ተግሳጽ ታለፈ፡፡ ተመከረ ተዘከረ ተገሰጸ ግን ሊመለስ ባለመቻሉ ቅጥፈቱን ሌሎች አሕዛቦች ሰምተው ከሚሳለቁብብ በማለት ታፍኖ ተያዘ ፡፡ እርሱ ግን በደነደነ ልቡ ቅጥፈቱን አባብሶ ቀጠለ፡፡ ከዚያስ…ከዚያማ እንኳን አሕዛብ ምድርና ሰማይ ይስሙ በሚል ተለየ፡ እርስዎም እነሆ ጉድዎትን አይደለም አሕዛብ ማንም ይስማው እንጂ ከዚህ በኋላ ለመታገስ እንጥፍጣፊ አቅምም ሆነ ሞራል የለንምና እነሆ ጉድዎን ይዘን ወደ አደባባይ ብቅ ለማለት ዝግጅተ ማድረግ ሳያስፈልግ አነሆ እየመጣን ነው…. እግዚአብሔር የተጣላው ቦዘኔ ከመሆን ሁላችንንም በጨርነቱ ይጠብቀን፡፡

 34. Kuba February 26, 2016 at 2:18 pm Reply

  እዉነቴን ነዉ አንተ ስለ ማህበረ ቅዱሳን የመናገር ሞራሉም ችሎታዉም የለህም፡፡ እኛ ተመልከች አጥተን በመናፍቃን መንጋጋ ልንወሰድ በደረስን ግዜ ለዛሬ ለብዙ ማንነታችን፤ ቤተክርስቲያንን ያሳወቀን ማነዉ? በቋንቋችን የስተመራን ማነዉ? እናንተ ለሆዳችዉ እንጂ ለነፍስ መች ተጨነቃችዉ? ለሌብነትና ለምንፍቅና ስለማይመቻችዉ ማህበሩን ትነቅፋላችዉ. ሌቦች፡፡

 35. Yewbdar February 26, 2016 at 2:42 pm Reply

  ይበቃል
  እናት ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ባስተማረችን መሠረት ወደላይ ላለመመልከት እንዲሁም የሚጠበቅብንን ድርሻ ብቻ መወጣት እንደሚኖርብን ታላላቆችን ይልቁኑ የሃይማኖት አባቶቻችንን እንድናከብር ባስተማረችን ጥልቅ ትምህርት እስከ አሁን ድረስ ታግሰን ቆይተናል፡፡
  በየመኻሉም በተለያዩ ወቅቶች ቅጥፈትን ብልግናን ሲያሳዩ ምናልባትም ተታለው (ዙሪያዎን በሙሰኞች እና ቤተ ክርስቲያንን ሊያጠፉ ሌት ተቀን ከሚባዝኑ ነብሰ በላዎች ጋር ስለሚገኙ) ሊሆን ይችላል በሚል እራስን ከምንም በላይ በሚፈታተን ክፉ ስሜት እንኳ ሲሰማን በታላቅ ትዕግስት አልፈንዎት ነበር፡፡
  ይህም አልበቃ ብሎ በላይ በላዩ አከታትለው የሚፈጽሙትን ሴራም ተመልክተን ወደ እግዚአብሐር ለመጮኽ ሞክረንም ነበር፡፡ እንግዲህ ይህ ሁሉ ትዕግስት ይበልጥ የልብ ልብ እንዲሰማዎ አደረገ መሰለኝ ጭራሽ ዓይን ያወጣ እንኳን ከፓትርያርክ ከአንድ ወያላ ያነሰ ቅጥፈትና ድፍረት ይዘው በማን አለብኝነት ዘልቀዋል፡፡
  ስለሆነም ከዚህ በኋላ ሊሆን የሚገባው መሆኑ ስለማይቀር እንዲሁም ቤተ ክርስቲያንን ከዚህ በላይ ሲያፈርሱ ማየት አግባብ ባለመሆኑ ለፈጸሙት በደል ተመጣጣኝ ወይም ከዚያ ከፍ ያለ እርምጃ ለመውሰድ ወይም እራሳችችንን ሰማዕት አድርጎ ለማቅረብ ከዚህ ዉጭ ጊዜ ባለመኖሩ እነሆ ልንፋለምዎ ተዘጋጅተናል፡፡ የታጠቁት መሣሪያ ይበላን ይል ይሆናል ቢሆንም ምናልባት የሀገሪቱን ጦር እንደተለመደው ያዙ ከሆነም ያንን ለመጋፈጠ ዝግጁ ነን፡፡ ብንሞት ሰማዕት ለመሆን ብንኖር ድላችንን ለማክበር እነሆ ተነስተናል፡፡
  ስም አጠራሩ ሳይቀር የሚያስጸይፈው አርዮስ ጳጳስ ነበር ልክ እንደዚህ እንደርሶ ቅጥፈቱን የሆነ ጊዜ ላይ ጀምሮ ነበር ነገር ግን በምክርና ተግሳጽ ታለፈ፡፡ ተመከረ ተዘከረ ተገሰጸ ግን ሊመለስ ባለመቻሉ ቅጥፈቱን ሌሎች አሕዛቦች ሰምተው ከሚሳለቁብብ በማለት ታፍኖ ተያዘ ፡፡ እርሱ ግን በደነደነ ልቡ ቅጥፈቱን አባብሶ ቀጠለ፡፡ ከዚያስ…ከዚያማ እንኳን አሕዛብ ምድርና ሰማይ ይስሙ በሚል ተለየ፡ እርስዎም እነሆ ጉድዎትን አይደለም አሕዛብ ማንም ይስማው እንጂ ከዚህ በኋላ ለመታገስ እንጥፍጣፊ አቅምም ሆነ ሞራል የለንምና እነሆ ጉድዎን ይዘን ወደ አደባባይ ብቅ ለማለት ዝግጅተ ማድረግ ሳያስፈልግ አነሆ እየመጣን ነው…. እግዚአብሔር የተጣላው ቦዘኔ ከመሆን ሁላችንንም በጨርነቱ ይጠብቀን፡፡

 36. Anonymous February 26, 2016 at 6:09 pm Reply

  Yewbdar ነኝ ባዩ ደፋርዋና ጉዲታዊቷ ሴት ከሆንሽ !!!! በወንድ ልጥራሽና ስሚ

  አየህ! ድብቅ ተልእኮህን ማውጣት ጀመርክ፡ ምን ያህል ደፋርና ሃይማኖተ ቢስ እንደንክ ግልጽ ሆንክ፡፡ እናያለና ራስህን ለመሥዋት ስታዘጋጅ፡፡ ጥሩ ፖለቲከኛ በሰው ደም የምትነግድ የሃይማኖት ካባ የተከናነብክ፡፡ የማቅ ድቃላ፡ ዘርዓ ክርዳድ ወልዱ ለይሁዳ ሰያጤ እግዚኡ፡፡ አትሰማም እንጂ ንስሐ ግባ፡፡ ከጥፋትህ ተመለስ፡፡ ማሠርያህን አታሳጥር፡፡ መጻሕፍተ ሕገጋት (ቀኖና) ዘኦርቶዶክስ ተመልከት፡፡ ኦርቶዶክሳዊ ነኝ አትበል፡፡ እንዳንተ የመሰለ የኦርቶዶክስ ክርስቲያን አባልና አካል የለምና፡፡ አንተ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፤ ከካህናትና ከዲያቆናት ብሎም በአጠቃላይ ከምእመናን በላይ ነኝ ማለት ጀመርክ፡፡ ኦርቶዶክሳዊ አመራር ምን እንደሚል ተረዳ፡ ፍርፋርያቸውን የምትመኝላቸው ግብጻውያን ኦርቶዶሶችን ጠይቃቸው፡፡ እንዳንተ የመሰለ አባል ምእመን የላቸውም ፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያን ናቸውና፡፡ እውነት በቤተክርስቲያናችን ያነጣጠሩትን አፀራረ ቤተክርስቲያን ለመመከት ከሆነ ዓለማህ ማድረግ ካለብህ ከመሪዎችህና ከአባቶችህ ጋር ሆነህ ነው፡፡ ድኅረ ዘበቈልኩ ቀርን አዐቢዮ ለአቡየ እዝን ማለትህን አቁም፡፡ ትርጉሙ እንዲገባህ፡ ኋላ የበቀልሁ ቀንድ አባቴ ጆሮን እበልጠዋለሁ ማለትህ አቁም፡፡

 37. Anonymous February 26, 2016 at 6:11 pm Reply

  EGZIO patriarik bozene weyala bilo yemisadeb tiwulid ga deresin yasazinal ayi anchi Ethiopia meche yihon Egziabher beqa yemilish? Ere tewu dem bedem ayteram ere gonbes belu ere tewu …

 38. Anonymous February 26, 2016 at 6:45 pm Reply

  Anonymous February 25, 2016 at 6:40 pm Reply
  መልሱ ላንተ ነው፡፡

  መናፍቃን ዘራፊዎች ወዘተ ትላለህ፡፡ ምንኛ የተጎዳህ ሰው ነህ፡ እነማንም ነው መናፍቃን የምትላቸው? አሁንም በወንጀ ላይ ወንጀልን ተጨምራለህ፡፡ ሊቃውንቱንና የየመምሪያ ኃላፊዎችን ነው ? ፓትርያሪኩ ከማይመለከታቸው ጋር ይሰበሰባሉ ትላለህ! ሞኝ ነህ፡፡ ሲኖዶስ የሚሰበሰበው በዓመት ሁለት ጊዜ ነው፡፡ ፓትርያርኩ ከላይ እስከ ታች ካሉት ጋር የመወያየትና መመሪያ የመስጠት፤ መብት እንዳላቸው አታውቅማ! መቸ ተማርክና ሥርዓተ ቀኖና ዘኦርቶዶስ ፡ በማታውቀው ገብተህ ትፈተፍታለህ፡፡
  አንተ ራስህን ሌላ ተመልካችና ተቆርቋሪ መስለህ የቀረብክ የማቅ ባለሥልጣን፡፡ ይቅርታ መጠየቅ ምንም አይደለም ወዘተ ወዘተ ትላለህ፡፡ አንተ ማድረግ ያለብህ፡ የምታውቀውና ያገኘኸው ተሀድሶ በለው መናፍቅ ካለ ስሙና ማንነቱን ገልጸህ እንደ ሕጉ ከነማስረጃውና ከነ መረጃው ማቅረብ ነው እንጂ ያስተላለፍከው ፍረጃ እጅግ የተሳሳተ ነው፡፡ ወይም ለያንዳንዱ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር በማቅርብ ጉዳዩ እንዲታይ ማድረግ ነበረብህ፡፡ አሁን መሽቶብሃል፡፡ ያለአንዳች ቅደመ ሁኔታ ጥፋትን አምነህ ሁለትኛ እንዲህ ዓይነት ጥፋት እንደማትፈጽም፡ የምሰጥህንም መመሪያ ለመቀብል መዘጋጀት አለብህ፡፡ እስከ አሁን የረዱኝ ይረዱኛል ብለህ አተሞኝ፡፡ ማንነትህን ታውቃለህና፡፡ ምን ያህል ወንጅል እንደምተሠራ፡ በቤተክርስቲያኒቱ ስምና በንዋያተ ቅዱሳት ሁሉ ያለ አግባብ በስመ እግዚቪሽን የፈጸምከው ታውቃለህ፡፡ የከፈትካቸው የንግድ ተቋማትህ ወደግል እንዳዞርካቸው ታውቃለህ፡፡ አሁን ያለህ ጫፍ ላይ ነው፡፡ አምነህ መቀበል ወይም አይደለሁም ብለህ ራስህን ማግለል፡፡ ግን የትም አታመልጥም የሰበሰብከውም የትም አያመልጥም ገና ስለ አንተ ከአዲስ አበባ ጀምሮ በየአኅጉረ ስብከቱ ወይይቱ ይቀጥላል፡፡ ገና ረዳኋቸው ያልካቸው ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች አፍ አውጥቶው ይመልስሉሃል፡፡

 39. Anonymous February 26, 2016 at 9:00 pm Reply

  አብይ ጾምን በነገር ሊቀበሉ ነው ምን አለበት ለሰው አርአያ ብትሆኑ በሰላም የመኖርን ነገር ብታስቡ አካባቢዎን ያጽዱ፡፡ አቡነ ጳውሎስን ገደል የከተተ ሰው በሎች ናቸው በዙሪያዎት ያሉት፡፡

 40. Anonymous February 26, 2016 at 9:47 pm Reply

  ማህበሩ እነ አባ ኦርጋንን ሲያወግዝ ምነው ዝም ማለታችሁ ወይንስ በማውገዙ ተናዳችሁ ነው ልትቃወሙት መነሳታችሁ፡፡ ስንት የሚወገዝ እያለ የማይመለከተውን፡፡

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: