የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከአማሳኙ አለቃ ተማክሮ ያሳሰራቸው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን በዋስ ተፈቱ፤ሌሎች ሰባት ምእመናንንም ለማሳሰር ዶልተው ነበር

EgzAb Church000ለኹለት ቀናት በጉለሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በእስር ቆይተው ዛሬ ከቀትር በኋላ በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት ቀርበው ማምሻውን በአራት ሺሕ እና በኹለት ሺሕ ብር ዋስትና የተፈቱት፥ በአማሳኙ አለቃ አላግባብ የታገደው የደብሩ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር፣ የክፍለ ከተማው የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትና የደብሩ ሰንበት ት/ቤት አመራሮችና አባላት በቀጥታ ወደ አጥቢያቸው በማምራት በጸሎትና በመዝሙር ምስጋና አቅርበዋል፤ አቀባበል ያደረጉላቸውም ምእመናን፥ “ጀግኖቻችን ናችሁ፤ አርኣያ ኹናችሁናል፤ ከምንጊዜውም በበለጠ ተባብረን ቤተ ክርስቲያናችንን ከሙሰኞች እናጸዳለን፤” ሲሉ አጋርነታቸውንና ለቀጣዩ ተጋድሎም ዝግጁነታቸውን አረጋግጠውላቸዋል፡፡


 • “ሕገ መንግሥቱን ተላልፈው ሕገ ወጥ ደብዳቤ አሠራጭተዋል” ያለው ፖሊስ “ሌሎች የምንይዛቸው አሉ” በሚል የ20 ቀናት ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው ነበር፤ “አያሰጥም”/ፍርድ ቤቱ/
 • በማስፈራሪያዎች ያልተበገሩ በርካታ ምእመናን፣ በክፍለ ከተማው እና በችሎት ተገኝተው ድጋፋቸውን አሳይተዋል፤ “አርኣያ ኾናችኁናል፤ ደብራችንን ከሙሰኞች እናጸዳለን!”
 • የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፥ የቀሩት አስተባባሪዎች ካልታሰሩ ወደ ደብሩ መመለስ አልችልም፤ ያሉት አለቃ የጠቆሟቸውን ሰባት የሰንበት ት/ቤቱን አመራሮችና አባላት ዛሬ ለማሳሰር ባለፈው እሑድ ቃል ገብቶላቸው ነበር፤ “ችግር የለም፤ ስማቸውን ይዘህ ና!”
 • ከ18 ዓመት በታች ካሉ አዳጊዎች እስከ 70 ዓመት አዛውንት ድረስ ለእስር የተዳረጉበት የዕቅበተ እምነትና የፀረ ሙስና ተጋድሎ በአጥቢያው ምእመናን ባለቤትነት የሚደረግ ቢኾንም የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ማኅበረ ቅዱሳንን በሁከት ፈጣሪነት ወንጅሎበታል፡፡
 • መሠረተ ቢስ ውንጀላው፥ ከአማሳኙ አለቃ ጋር ተመክሮበት በጽሑፍ ከተዘጋጀ በኋላ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ታይቶና ይኹንታ ተሰጥቶበት በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎግ የወጣ ሲኾን አስፈጻሚውም፣ በኑፋቄ አራማጅነቱ ሳቢያ ከየደብሩ እየተባረረ በአኹኑ ወቅት በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ቤተ ክርስቲያን ‘ሰባኬ ወንጌልነት’ የተመደበ ግለሰብ እንደኾነ በማያሻማ መልኩ ተረጋግጧል፡፡
 • ሕጋዊው ሰበካ ጉባኤና የአካባቢው ምእመናን በዋናነት ከደብሩ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ በየደረጃው ምላሽ የጠየቁባቸውን የአማሳኙን አለቃ በደሎች በግልጽና ሚዛናዊ ማጣራት ተመልክቶ ውሳኔ ከመስጠት ይልቅ በኑፋቄ ብሎጎች መወንጀል ከዚያም አልፎ የዘመድ ሓላፊዎችን ተጠቅሞ በኃይል ርምጃዎች ፍላጎትን ለመጫንና ለማሸማቀቅ መሞከር ከቶም መፍትሔ አይኾንም፡፡
 • የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሀገረ ስብከቱ እንዳሰፈነው የሚለፍፈው ‘መልካም አስተዳደር’፤ በሕገ ቤተ ክርስቲያናችን ከሰፈረውና የቤተ ክርስቲያናችን አስተዳደር ከሚመራባቸው የመልካም አስተዳደር ዋነኛ መርሖዎች፥ መንፈሳዊነት፣ ፍትሐዊነት፣ አሳታፊነት፣ ግልጸኛነት፣ ተጠያቂነት፣ ተደራሽነትና ታማኝነት አንጻር በጥብቅ ሊፈተሽና ሊመዘን ይገባል፡፡

 

 

Advertisements

3 thoughts on “የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከአማሳኙ አለቃ ተማክሮ ያሳሰራቸው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ ምእመናን በዋስ ተፈቱ፤ሌሎች ሰባት ምእመናንንም ለማሳሰር ዶልተው ነበር

 1. TIRSIT WUBIE February 26, 2016 at 2:40 pm Reply

  እሺ ይቅርታ ጠየቀ እንበል ከዛስ?

 2. Anonymous March 21, 2016 at 10:01 am Reply

  እሺ

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: