በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ:የደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበርን ጨምሮ ከ14 በላይ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናን ታሰሩ፤“ሀገረ ስብከቱና ፖሊስ ለአማሳኙ አለቃ በማድላት በደል እየፈጸሙብን ነው”/ምእመናኑ/

Lique Maemeran Yemane ZeMenfes Kidus

የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ: ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ በአወዛጋቢ ኹኔታ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ከተሾመ ከነገ በስቲያ አንድ ዓመት ይኾነዋል፡፡ አብሮት የተሾመው ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ “…ነገሮች ይስተካከላሉ ብዬ ብጠብቅም ምንም ዓይነት መሻሻል ስለማይታይ” በሚል ለፓትርያርኩ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል፤ ከመልካም አስተዳደር መርሖዎች ጋር በመሠረቱ ሳይታረቅና “ምንም ዓይነት መሻሻል ሳይታይበት” ዓመት ላስቆጠረው ባዶ የማጭበርበርያ ዲስኩሩና አሠራሩ የቅርብ ምስክር ነው፡፡

 • ጠያቂ የሌለው የአማሳኞች ከለላ በመኾን ምእመናንን እያሸማቀቀና እያስለቀሰ ይገኛል
 • በብልሹ አስተዳደርና ሙስና የተባረሩትን አለቃ ንጹሕ ናቸው ብሎ እንዲመለሱ ጽፏል
 • የደብሩ ሒሳብ እንዳይመረመር በመከልከል ለአለቃው ምዝበራና ሙስና ሽፋን ሰጥቷል
 • በምእመናኑ ከተባረሩም በኋላ በደብሩ ገንዘብ ለብቻቸው እያዘዙበትና እያባከኑት ነው

*                   *                   *

 • ግልጽነት በጎደለው ማጣራት ምእመናኑን ጥፋተኛ በማድረግ በሕግ እንዲጠየቁ ወስኗል
 • የክ/ከተማው ፖሊስ፥ የሕገ ወጥ ትእዛዝ አስፈጻሚ በመኾን ምእመናኑን እያስጨነቀ ይገኛል
 • ምእመናኑ፣ በሳምንት ለኹለተኛ ጊዜ በእስር ቢንገላቱም የደብራቸውን ጥበቃ አጠናክረዋል
 • ለሚፈጠረው የሰላም መደፍረስና ሰብአዊ ጉዳት ተጠያቂው አለቃውና ሀ/ስብከቱ ይኾናሉ

*                   *                   *

ማነ ዘመንፈስ ቅዱስ: ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተጥሶ በአወዛጋቢ ኹኔታ በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅነት ከተሾመ ከነገ በስቲያ አንድ ዓመት ይኾነዋል፡፡ በአንድ ላይ አብሮት የተሾመው ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ “…ነገሮች ይስተካከላሉ ብዬ ብጠብቅም ምንም ዓይነት መሻሻል ስለማይታይ” በሚል በታኅሣሥ ወር መጀመሪያ ላይ ለፓትርያርኩ የዝውውር ጥያቄ አቅርቧል፤ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስም በጣልቃ ገብ ለጻፈበት የንብረት አስረክብ ደብዳቤም በሰጠው አጸፋ፣ “ከአንተ ጋር ለመሥራት ፍላጎት የለኝም፤ ወደፊትም እንዲኖረኝ የሚያስችል ኹኔታ አይታየኝም፤” ሲል ሓላፊነቱን አላግባብ ከመጠቀም እንዲታቀብ አሳስቦታል፡፡

በርግጥ፣ ሕገ ወጥ ምደባቸው ሀገረ ስብከቱን ሰላም እንደሚነሳው አስቀድሞ ቢነገርም ዘግይቶም ቢኾን እንደታየው፣ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ፣ ከአማሳኝ የአድባራት ሓላፊዎች ጋር በዓላማና በጥቅም ተሳስሮ ጠንካራ ሰበካ ጉባኤያትን በእገዳ ማዳከም፣ ለአቤቱታቸውም ወቅታዊ ምላሽ በመንፈግ እንዲፈርሱና በእስር እንዲንገላቱ ማድረግ መለያው አድርጎታል፡፡ ወራትን ባስቆጠረው የደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ እና ሌሎችም በርካታ አጥቢያዎች ውዝግብ የያዘው አቋምም፣ “ለሌሎች አድባራት አርኣያ እንዳይኾን” በሚል የዕቅበተ እምነት የፀረ ሙስናና የመልካም አስተዳደር ንቅናቄውን በኃይል ርምጃዎች በማስጨፍለቅ ማሸማቀቅ ኾኗል፡፡

በደብረ ሲና እግዚአብሔር አብ፣ የሰንበት ት/ቤቱን አባላትና ምእመናኑን በሕገ ወጥነት ፈርጆ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለኹለተኛ ጊዜ በገፍ በእስር እንዲንገላቱ አድርጓል፤ ሙስናቸውና ብልሹ አስተዳደራቸው በማስረጃ የተጋለጠባቸውን አለቃ ግን፣ ንጹሕ ናቸው በሚል ወደተባረሩበት ደብር እንዲመለሱ ወስኗል፡፡ ይህ የማናለብኝነት መንገዱ፥ በሚሊዮኖች ላካበተበት የዓላማና የጥቅም ትስስሩ ግልጽ ማሳያ፤ ከመልካም አስተዳደር መርሖዎች ጋር በመሠረቱ ሳይታረቅና “ምንም ዓይነት መሻሻል ሳይታይበት” ዓመት ላስቆጠረው ባዶ የማጭበርበርያ ዲስኩሩና አሠራሩም ተጨማሪ ምስክር ነው፡፡

*                    *                   *

EgzeabhareAb parish head

 

 

መልአከ ሰላም አባ ገብረ ሚካኤል ወልደ ሳሙኤል: መፍትሔ ባጣው ሙስና እና ብልሹ አስተዳደራቸው ሳቢያ በምእመናን ከተባረሩ ከ6 ወራት በኋላ በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከለላ ሰጭነትና “ከበላይ አካል ታዘን ነው” በሚሉ የክፍለ ከተማውና የአካባቢው ፖሊስ አባላት ድጋፍ  ወደ ደብሩ ለመመለስ እያወኩ የሚገኙ፤

የደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ምእመናን፣ ላለፉት ስምንት ወራት ግልጽና ሚዛናዊ ማጣራት እንዲካሔድባቸው ለሀገረ ስብከቱ ሲያቀርቧቸው የቆዩትና ምላሽ የተነፈጋቸው የአማሳኙ አለቃ በደሎች፤
 • የደብሩ የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ በትክክል ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ብቻ ስለመዋሉ ምርመራ እንዲደረግ የሰበካ ጉባኤው የምእመናን ተወካዮች በቃል እና በጽሑፍ በተደጋጋሚ ያቀረቡትን ጥያቄ አልቀበልም ማለታቸው፤
 • ይኸው የሙዳየ ምጽዋት ገንዘብ ምርመራ ጥያቄ በሰበካ ጉባኤው አባላት በመቅረቡ በማኅበረ ካህናት እና በማኅበረ ምእመናን ምልአተ ጉባኤ የተመረጠውን ሰበካ ጉባኤ ማፍረሳቸው፤
 • የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑን የሥዕል ሥራ አስመልክቶ ለምእመናን በዐውደ ምሕረት ተነግሮ የጨረታ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ሠዓሊውን 200 ሺሕ ብር ጉቦ እንዲሰጣቸው ጠይቀውት እምቢ በማለቱ “የሥዕል ሥራው ሕገ ወጥ ነው፤ ሀገረ ስብከቱ አላወቀውም” በማለት የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥዕል እንዳይሣል ማድረጋቸው፤
 • ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ማስፈጸሚያ ብቻ እንዲውል በጎ አድራጊ ምእመናን ለደብሩ የመኖርያ ቤት በስጦታ ሲያበረክቱ ተገኝተውና በጸሎት ባርከው ቤቱ ከተሸጠ በኋላ የተለያዩ ምክንያቶችን በመጥቀስ በድምሩ 680 ሺሕ ያኽል ብር ለግላቸው ወስደው ሲያበቁ ወደ ሀገረ ስብከቱ ሔደው፥ “ቤቱ ሲሸጥ አላውቅም፤ የሸጠው የሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ ምክትል ሊቀ መንበሩ ነው፤” ብለው የሐሰት ወሬ በማስወራት የኮሚቴውንና የንጹሐን አገልጋዮችን ስም ማጥፋታቸው፤ 
 • የሰንበት ት/ቤቱን ጠንካራ አመራር በሕገ ወጥ መንገድ በማፍረስ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ አራማጆች እንዲሰገሰጉበት ለማድረግ ብዙ ሙከራዎችን ማድረጋቸውና አኹንም ለዚሁ አፍራሽ ተግባር አጋዥ የኾኗቸውን ጥቂት ግለሰቦች በመያዝ፣ የሀገረ ስብከቱን ሹማምንት ተገን በማድረግ ሰንበት ት/ቤቱን ለማፍረስ ጥረት እያደረጉ መኾናቸው፤
 • ከእኒኹ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፀር ከኾኑ የኑፋቄው አራማጆች ጋር ኅብረት በመፍጠር የንጹሐን አገልጋዮችንና ምእመናንን ስም የሚያጠፋ የስድብ ጽሑፍ እና ሐሰት በፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ብሎጎቻቸው እንዲጻፍና እንዲሠራጭ እያደረጉ መኾናቸው፤

 • የደብራችን የሰንበቴ እና የጽዋ ማኅበራት፣ ለትምህርት ቤት ልማት ሥራ የሚውል 11ሺሕ ብር በነፍስ ወከፍ፤ በጠቅላላው ከመቶ ሺሕ ብር በላይ እንዲከፍሉ ከተደረገ በኋላ ለልማቱ ሥራ ሳይውል ያለአግባብ ማባከናቸው፤
 • ት/ቤቱ ራሱን ችሎ የመማር ማስተማሩ ሒደት በላቀ ደረጃ እንዲከናወን፣ በሰበካ ጉባኤው ታምኖበት በጋዜጣ በይፋ በወጣ ጨረታ አማካይነት የተሻለ ተቋም ተከራይቶት እንዲቀጥል ከተደረገ በኋላ የተለያዩ ተንኮሎችን በማቀነባበር ት/ቤቱ እንዳያስተምርና እንዲዘጋ ማድረጋቸው፤
 • የት/ቤቱን የአንድ ዓመት የኪራይ ዋጋ ከብር 300 ሺሕ በላይ ተቀብለው በት/ቤቱ ሒሳብ እንዲቀመጥና ከዚያ እየወጣ ት/ቤቱን የማስፋፋት ሥራ ሊሠራበት ሲገባ፣ ገንዘቡ ከታሰበለት ዓላማ ውጭ ውሎ እንዲጠፋ በማድረጋቸው፤
 • ት/ቤቱን የተከራየው ተቋም የደብሩን ወቅታዊ ችግር በመረዳት ገንዘቡ ይመለስልኝ ሳይል ሌላ አማራጭ በማቅረብ በ2009 ዓ.ም. ት/ቤቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያቀረበውን መልካም አማራጭ ባለመቀበል ቤተ ክርስቲያናችን በኪራይ ዕዳ እንድትከሠሥ ማድረጋቸው፤
 • እኒኽ የሰንበቴ እና የጽዋ ማኅበራት፥ ለምን የመረጥነው ሰበካ ጉባኤ ፈረሰ? ለምን የሥዕል ሥራው ቆመ? ለምን የሰንበት ት/ቤቱ አመራር እንዲፈርስ ተፈለገ? ለት/ቤቱ ልማት የሰጠነው ገንዘብ የት ገባ?...ወዘተ ብለው ጥያቄ በማቅረባቸው፣ “የመቃብር ፉካ ቸርቻሪ ዕድሮች ናቸው” በማለት ከሀገረ ስብከቱ ጋር በማጋጨት ሰንበቴዎችን ለማዘጋት እያሤሩ መኾናቸው፤
 • ካህናት እና ምእመናን በግልጽ የመረጧቸውን የሰበካ ጉባኤ አባላት በማናለብኝነት ካፈረሱ በኋላ እርሳቸው እና ግብረ አበሮቻቸው ውስጥ ለውስጥ መርጠው ያዘጋጁአቸውን ግለሰቦች ለመመደብ እና ለማስመደብ እየተንቀሳቀሱ መኾናቸው፤ ለዚኽም ተፈጻሚነት ከበላይ አጋሮቻቸው መመሪያ በጽሑፍ የተቀበሉ መኾናቸው፤
 • የጽዋ ማኅበራቱ የደብሩን ችግር በሽምግልና ለማየት በሞከሩበት ወቅት፣ “ችግሮቹን አስተካክላለሁ፤ ከሰበካ ጉባኤው ጋር ተስማምቼ እሠራለኹ” ብለው በዐደባባይ ከተናገሩና ለምእመናኑም የምሥራች ካሉ በኋላ ቃላቸውን ክደው በሕዝበ ክርስቲያኑ ላይ የክሕደት ተግባር መፈጸማቸው፤ 
 • በስብከተ ወንጌል በጀት ስም በየወሩ የሚወጣውን ገንዘብ በአግባቡ እንዳይወራረድ በማድረግ ለብዙ ገንዘብ መባከን ምክንያት መኾናቸው፤
 • የካላንደር እና የመጽሔት ሽያጭ ገንዘብ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሳይውል የእርሳቸውና የጓደኞቻቸው መጠቀሚያ እንዲኾን ማድረጋቸው፤ 
 • ወ/ሮ እቴነሽ የተባሉ ምእመን ለሕንፃው የሰጡትን ከብር 300 ሺሕ በላይ ገንዘብ ከምእመኑ ፍላጎት ውጭ ማባከናቸው፤ ከሌላም አንዲት ምእመን ለት/ቤት ልማት ሥራ ብለው ብር 70 ሺሕ ተቀብለው ወስደው የት እንዳደረሱት አለመታወቁ፤
 • ካህናትንና አገልጋዮችን ያለአግባብና ያለሰበካ ጉባኤው ዕውቅና የሚያግዱና የሚያባርሩ መኾናቸው፤ እንዲኹም ያሻቸውን ሰው የሚቀጥሩና የሚያስመድቡ መኾናቸው፤
 • አኹንም በምእመናን ከተባረሩ በኋላ በውጭ ኾነው የደብሩን ገንዘብ ብቻቸውን እያዘዙና እያባከኑት መኾናቸው፤

ከአለቃው ጋር በጥቅም የተሳሰሩት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅና አንዳንድ ሓላፊዎች፤ ነውረኛውን ግለሰብ ንጹሕ አድርገው የአጥቢያውን ምእመናን በመኰነን ወደ ደብራችን እንዲመለሱ ሕገ ወጥ ደብዳቤ ጽፈዋል፡፡
ይህን ሕገ ወጥ የሀገረ ስብከቱን ውሳኔ በሰላማዊ መንገድ በመቃወም፤ አለቃውም ወደ ቤተ መቅደስ እንዳይገቡ በመከላከል ቤተ ክርስቲያናችንን በማስከበር ሙስናንና ብልሹ አስተዳደርን እንድንከላከል በቅዱስ እግዚአብሔር አብ ስም እናሳስባለን፡፡
ልዑል እግዚአብሔር ሀገራችንን ይባርክልን፤ ቤተ ክርስቲያናችንን ከሙሰኞች ነጻ ያውጣልን፤ አሜን፡፡

(በማኅበረ ምእመናኑ ከተሠራጨው ጽሑፍ የተወሰደ፤ ተጨማሪ ደብዳቤዎችን ከዚኽ በታች ይመልከቱ)

Debra Sina EgzeabhareAb Church Egzab church row1EgzAb church row2EgzAb church row2aEgzAb church row3

Advertisements

8 thoughts on “በየማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ:የደ/ሲና እግዚአብሔር አብ ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበርን ጨምሮ ከ14 በላይ የሰንበት ት/ቤቱ አባላትና ምእመናን ታሰሩ፤“ሀገረ ስብከቱና ፖሊስ ለአማሳኙ አለቃ በማድላት በደል እየፈጸሙብን ነው”/ምእመናኑ/

 1. Alemayehu February 21, 2016 at 5:20 am Reply

  minyadirig ketera zena anibabinet wede millionior balehabit tekeyere yebetekiristian gud mechem ayalikim. D/n daniel yethede lemina ayitsifilinim lezih zemenrkus

 2. Anonymous February 22, 2016 at 7:30 am Reply

  This is happening all over Addis Ababa church. People should know that all is covered and they are playing by the people money who donate 5 cents from what they have reducing from their mouth.

 3. Anonymous February 22, 2016 at 8:38 am Reply

  የእናንተ ነገር አስቸጋሪ ሆኖ ቀረ፡፡ የሆነውንና የተከሰተውን ሁሉ በገለልተኛ አእምሮ እንደማቅረብ አንድ ጽንፍ ይዛችሁ ትዘግባላችሁ፡፡ የተወሰነውን ክፍል የኛ አይደለም ብላችሁ በአሳዛኝ ሁኔታ በመግፋት ለማግለል ትሞክራላችሁና እባካችሁ ጎደሎ እውነት ብቻ ይዛችሁ ለቀሳጢ በር አትክፈቱ፤ በሚዛናዊነት ዘግቡ፡፡ ስለተጠቀሰው ደብር ሲሆን የነበረውና አሁንም እየሆነ ያለው ይሄው ነው፤ የእናንተ ኢሚዛናዊ አቀራረብ ሰው የተጣራ መረጃ እንዳያገኝ እንቅፋት ሆኗል፡፡ እንደ ባሕል መድኃኒት አዋቂ ሁሉን ደብቃችሁ እኛ ብቻ አዋቂ ነን ማለት በዚህ በፈጣን ዘመን ደግ አይደለም፡፡ሁሉ በጊዜው መገለጡ ላይቀር ተቧድኖ እውነትን መቅበር አያዋጣም፡፡ እውነት የምትገኘው ደግሞ በሚዛናዊ ኅሊና እንጂ ተደራጅቶ እየቾሁ በማስጮህ አይደለምና ለሚናዊ ዘገባ በጥቂቱም ቢሆን ቦታ ስጡ፡፡የአንድ ቡድን ታማኝ ወታደር መሆንና ስለጽድቅ ለቤትክርስቲያን ወታደር መሆን ይለያያል፡፡

  • ዳሞት February 23, 2016 at 7:11 pm Reply

   ለanonymous February 22,2016 at 8:38am
   ትሁቱና አለመኛው ካህን ታዛቢው፦ ገለልተኛ ገለልተኛ እንዳልክ እንዲሁ ካለ እምነት ቀረህ። አለም ፈጣን ናት አይል! ምንም እንሿን በአም ላይ ከተፈናጠጥህባት ብትቆይም አሁንም ፈጣን ናት ብለሀልና ክነፍባት። አንተን የሚያስደስትህ የቤተክርስቲያን መዘረፍ፤ የክህደት መስፋፋት፤ የአንድ አካል ፈላጭ ቆራጭነትን አሜን ብሎ መቀበል፤ የቤተክርስቲያኗ ህግጋትና ቀኖና መጣስ፤ ክርስቶስን አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ ያለውም አንተ ከነቢያት አንዱ ነህ ያለውም ትክክል ነው መባልና የመሳሰሉት ናቸው አይደል። እውነታንና ክርስትናን ሥትፃረር እንዲሁ አለህ።

 4. Ene Dej February 22, 2016 at 9:10 am Reply

  Abatu Kemagna Lejum Endezawe. Abatu Z menfes ye gola mikael astedadari neberu Esachew endezihu kahinatun Abarerew abarew mudaye mitsewatun arakutew senbet timehirt betun b 1997/98 Azegetew Betekirstianun astedaderun abelashetew, menem ayinet yebetekirstian eweket sayinorachew kidase enkuwan memerat ayichilum neber Be meemenanu chuhet wede lela betekristian letifate tekeyirewal selezi Lej ye abatun geber Besera menu yidenkal.

 5. ዳሞት February 23, 2016 at 6:53 pm Reply

  ሕገ እግዚአብሔርንም ሕገ መንግስትንም የማይፈራና የማያከብር መልካም ያደርጋል ብላችሁ አትጠብቁ። በዚህ ዘመን በቤተክርስቲያኗ ጥቂት በማይባሉ አማሳኝ ሹማምንት ምንፍቅና አራማጆች ሀይማኖት(ክርስትና) ተፌዘ ተቀለደበት፤ ተበላ ተጠጣበት፤ ተዘረፈ የተንጣለለ ቪላና ፎቅ ተሰራበት፤ ውስኪ ከቁርጥ እየተማረጠ ተመተረ ተንደቀደቀበት። እንደሚባለውና እንደሚሰማው ከሆነ ለመናገር የሚያሳፍር ድርጊትን በቤተክርስቲያኗ ሐብት በየመሻታ ቤቱም የሚሰሩ አሉም ይባላል።
  ሕገ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን፤ ሕገ መንግስት ደግሞ በአገሪቱ ያለ ቢሆንም የሚፈፅማቸውም የሚያስፈፅማቸውም የለም። የሚፈፅማቸውና የሚያስፈፅማቸው ቢኖር ኖሮ መጠየቅ የነበረባቸው ሌሎች ነበሩ። ዳሩ ግን ሕገ እግዚአብሔርን ከእግዚአብሔር ታጋሽነት የተነሳ እግዚአብሔር እንደማያይና እንደማይፈር አሥመስለው ተዘባበቱበት። ሕገ መንግስቱን አንድም በባለጊዜነት፤ ሁለትም የተሰጣቸውን ሕገ መንግስቱን አክብረው የማስከበርና ለእውነተኛ ፍትህ እንዲሰሩ ኀላፊት በመተውና በመናድ በተራ ጎጠኝነት መንፈስ የተተበተቡትን በመጠቀም ለኢ-ሕገ መንግስታዊ ተግዳሮታቸው እየተገቀሙበት ይገኛሉ። ዛሬ ለእንደነ የማነ ዘመንፈስ አይነቱ ሰው ማሳሰርም ሆነ ማስፈራራት ቀላል ነው። ሕገ መንግስቱ ፈቅዶላቸው ሳይሆን የሚሔዱበት መንገድ ሌላ ሥለሆነ ነው።
  በሕገ እግዚአብሔርም ሆነ በሕገ መንግስቱ ቢሆን ኖሮ ሌሎችን ትተን እራሱ አሳሳሪው ተጠያቂና ታሳሪ ነበር። ግን ደግሞ በምድር ላይ የክፉው የአመፃና በንፁሐኑ ላይ በትርን የማሳረፍ ተግባር የሚፈፀምበት ሆነና ይኸው እያየን ነው። ሥራ የሚሰሩትና የሚሻሻሙት ሕገ እግዚአብሔርንና የቤተክርስቲያኗን ቀኖና በጠበቀና በተከተለ አይደለም። ሰው የሚያሳስሩትና የሚያስፈራሩትም በሕገ መንግስቱ አሰራር አይደለምም፤ ሕገ መንግስቱም ፈቅዶላቸው አይደለም። ሕገ መንግስትም ሆነ ህገ እግዚአብሔር እንዲሁም ቤተክርስቲያኒቷ አንድና ጥቂት አካላት የሆኑበት ጊዜ ነው።
  ሥለ ክርስትና(ሀይማኖት) መከራ መቀበል የሚገባ፣ የተገባ ነውና የታሰሩት መታሰራቸው በሥጋዊ እይታ ቢያሳዝንም ሥለምነታቸው ሥለሆነ ግን ደስ ይበላቸው። አይደለም እናንተ በቀራንዮ ተሰቅሎ ሞቶ ያዳንን ክርስቶስም የዘመኑን ሰዎች በሚመስሉት እስራትንም ግፍንም ተቀብሏል። አይደለም እናንተ “እናንተ የአለም ብርሃን ናችሁ” የተባሉት አባቶቻችንም እስራትን ጨምሮ ምን ያልተቀበሉት መከራ አለ። ከእኔ በተሻለና በላቀ ቃሉን ታውቁታላችሁና ደስ ይበላችሁ። ሥለ እውነትና ሥለ ቤተክርስቲያን( እምነታችሁ) ነውና እሥራታችሁ ደስ እያላችሁ ተጽናኑ። መከራ ፈተናው፤ እስራት ግርፍቱ ፤ እንዲሁም ሌላው አሥጨናቂ የተጣለት ተግዳሮት ተጀመረ እንጅ አላለቀም። ቀላሉ እንጂ ከባዱ መቸ ታለፈና። አይዟችሁ! ከእናንተ ጋር ያለው አምን ያሸነፈው ነውና። አይዟችሁ! ከእነሱ ይልቅ በእናንተ ዙሪያ ያሉት ቅዱሳኑ ይልቃሉና።

 6. Anonymous February 24, 2016 at 2:40 pm Reply

  I see his face in the Ethiopian TV before the year when I was abroad. How can he came in the church? relay our church is under the control of our politics.

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: