ሰበር ዜና – ቋሚ ሲኖዶስ: የተሐድሶ ኑፋቄ በኮሌጆች የሚገኝበትን ኹኔታ የሚያጠና ኮሚቴ ሠየመ፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ የእምነት መግለጫ ምላሽ እንዲሰጥ አዘዘ

 • በመንበረ ፓትርያርኩ ይፋዊ መግለጫ ይሰጥበታል
 • አሳታሚው እና ማተሚያ ቤቱ በሕግ ይጠየቃሉ

head-of-eotc-patriarchate ቋሚ ሲኖዶስ፥ በዛሬ፣ የካቲት 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ሳምንታዊ መደበኛ ስብሰባው፣ ለቤተ ክርስቲያናችን የህልውና ስጋት የኾነውን የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ከመከላከልና ከማጋለጥ አኳያ  ወሳኝ የኾኑኹለት ዐበይት ውሳኔዎችን አሳልፏል፤ ትእዛዞችንም ሰጥቷል፡፡

የተሐድሶ መናፍቃን፣ መንፈሳውያን ኮሌጆችን የእንቅስቃሴአቸው ዕንብርትና ማእከል(ስትራተጅያዊ ቦታ) በማድረግ የቤተ ክርስቲያናችንን አስተምህሮ በአጭር ጊዜ ወደ ፕሮቴስታንታዊ አቅጣጫና መንገድ ለመለወጥ በኅቡእ ስለሚያካሒዱት ዘመቻ የተወያየው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ ኹኔታውን በጥልቀት አጥንተው ለመጪው ግንቦት የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሚያቀርቡ የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ሠይሟል፡፡

በጥቅምቱ ምልዓተ ጉባኤ የተቋቋመውን የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ቋሚ ኮሚቴ በሚመሩት በብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል ሰብሳቢነት በኮሌጆቹ ላይ ምርመራውንና ፍተሻውን የሚያካሒዱት የኮሚቴው አባላት ብዛት ስድስት ሲኾኑ እነርሱም፡-

1) መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ 2) ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አገዘ 3) መሪጌታ ሳሙኤል አየሁ 4) ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ 5) ዶክተር በለጠ ብርሃኑ 6) ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ ናቸው፡፡

በሌላ በኩል ቋሚ ሲኖዶሱ፣ “ተሐድሶ ዘኦርቶዶክስ የእምነት መግለጫ” በሚል ርእስ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ግንባር ቀደም አራማጆች በኅቡእ ላሰራጩት የኑፋቄ ዐዋጅ፣ በመንበረ ፓትርያርኩ ይፋዊ መግለጫ እና በሊቃውንት ጉባኤውም መጽሐፋዊ ምላሽ እንዲሰጥበት በመወሰን ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡ Tehadesso Confessio እናድሳለን ባዮቹ ግንባር ፈጥረው፣ በስድስት ዐበይት ክፍሎች በ44 ገጾች ያዘጋጁትንና በሠኔ ወር 2007 ዓ.ም. በመጽሐፍ መልክ አሳትመው ያወጡትን ይህንኑ መግለጫ፣ በዚኽ ዓመት ጥቅምት ወር በድብቅ አስመርቀው በማሠራጨት ላይ ይገኛሉ፡፡ አሳታሚዎቹ፣ በሽፋኑ የማተሚያ ቤቱን ስም ብቻ በማስፈር ስማቸውን ባይጠቅሱም፣ “የወንጌል አገልግሎት ማኅበራት ኅብረት” በሚል ስም በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ግንባር የፈጠሩ የኑፋቄው አራማጆች መኾናቸው ተጠቅሷል፡፡ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ የሕግ አገልግሎት፣ ጉዳዩን እንዲከታተል በቋሚ ሲኖዶሱ ውሳኔ ትእዛዝ የተሰጠ ሲኾን ማተሚያ ቤቱ እንዲኹም አሳታሚዎቹ በሕግ እንደሚጠየቁ ተገልጧል፡፡

ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ“በማንነት ቀውስ ውስጥ ይገኛል” ላሉት የተለያዩ ቡድኖች የተሐድሶ እንቅስቃሴየጋራ ራእይና አቅጣጫ ለመስጠት” ግንባር ፈጥረው ያዘጋጁት ይኸው መግለጫ፥ ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያናችንን፣ “እንደ ማንኛውም በምድር ላይ ያለች ቤተ ክርስቲያን” በማለት ነው በተርታነት የሚጠቅሳት፡፡

ነቢያት በትንቢት፣ ሐዋርያት በስብከት፣ ሊቃውንት በትምህርት የተባበሩበትን፤ ትላንትም፣ ዛሬም ነገም ያልተለወጠውንና የማይለወጠውን የቀና እና የጸና ትምህርተ ሃይማኖቷን ደግሞ፣“ከመጽሐፍ ቅዱስ የራቀና ቅይጥ ነው፤ የስሕተት ትምህርቶችና ልምምዶች ተቀላቅለውበታል” በሚል ነው፣ ኦርቶዶክሳዊ ማንነቷን በፕሮቴስታንታዊነት ለመለወጥ “ተሐድሶ ያስፈልጋታል” የሚለው፡፡

ቤተ ክርስቲያናችን ተቋሞቿንና አባላቷን ከኑፋቄው ሤራ ለመጠበቅ በየጊዜው የወሰደቻቸውን የመከላከል፣ የማጋለጥና አውግዞ የመለየት ሉዓላዊና ሕጋዊ ርምጃዎቿንም በመኰነን በአሳዳጅነት ይፈርጃታል፤ ይህም ለኪሳራ እንደሚዳርጋት በመግለጽ ሉተራዊ ዓላማውን ገሃድ አድርጓል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው በጥቅምት 2008 ዓ.ም. ስብሰባው፣ የኑፋቄውን አጠቃላይ ወቅታዊ እንቅስቃሴ በማስረጃ አስደግፎ ለውሳኔ እንዲያቀርብ ቀደም ሲል የሠየመውን ኮሚቴ አፈጻጸም ገምግሞ ተጨማሪ መመሪያ የሰጠ ሲኾን፤ ሰባክያንና መምህራን የሚፈልቁባቸው የኮሌጆቻችን የውስጥ ይዘትም(አስተዳደራዊ መዋቅር እና አሠራር) እንዲፈተሽና ደቀ መዛሙርቱን በጥራት ለመቅረፅ የሚያስችል ተቋማዊ ኹኔታ የሚፈጥር ጥናት እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ በርእሰ መንበሩ እንደተነገረው፣ ምንጩ ድፍርስ ከኾነ የተጠማው መንገደኛ ውኃ ለመጠጣት ይቸገራልና”፡፡

የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ፣ ቀኖናዊና ታሪካዊ ትውፊት እንዳይፋለስ የመጠበቅና የማስጠበቅ ዓላማዎች ላሉት ቅዱስ ሲኖዶስ ተጠሪ ኾኖ የውሳኔዎቹንና የመመሪያዎቹን ተግባራዊነት የሚከታተለው ቋሚ ሲኖዶሱ፣ በዛሬው ዐበይት ውሳኔዎች፣ ኮሌጆቹን ከኑፋቄው ተላላኪዎች ለማጥራት በመጋደላቸው ከሥራ እና ከትምህርት ገበታዎቻቸው ከማባረር ጀምሮ የተለያዩ አድልዎች ሲፈጸሙባቸው ለቆዩትና አኹንም በተመሳሳይ ኹኔታ ውስጥ ለሚገኙት ቀናዕያን መምህራን፣ ሠራተኞችና ደቀ መዛሙርት ታላቅ የምሥራች ነው፤ ከኮሌጆቹም ውጭ በተጠናከረ አኳኋን እየተካሔደ ለሚገኘው የፀረ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ አድማሳዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ የሞራል ብርታት የሚሰጥ በመኾኑ ለፍፃሜው ተገቢው የተቀናጀ ድጋፍ ሊደረግለት ይገባል፡፡

Advertisements

26 thoughts on “ሰበር ዜና – ቋሚ ሲኖዶስ: የተሐድሶ ኑፋቄ በኮሌጆች የሚገኝበትን ኹኔታ የሚያጠና ኮሚቴ ሠየመ፤ ለፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶአውያኑ የእምነት መግለጫ ምላሽ እንዲሰጥ አዘዘ

 1. Gebeyehu Abebe Eshetie February 12, 2016 at 4:13 pm Reply

  ይበል የሚያሰኝ ጅምር ሥራ ነውና ከፍጻሜ እስኪደርስ የውስጥ አርበኞቻቸው ጩኸትና ትርምስ ሳያዘናጋን ሁላችን የየበኩላችንን ልንወጣ ይገባናል !!!

 2. Anonymous February 12, 2016 at 4:26 pm Reply

  አሪፍ ጅማሮ ነው። ፍጻሜውን ያሳምርልን።

 3. Dawit February 12, 2016 at 4:33 pm Reply

  መልካም ነገር ነው። ጥርስ አልባው ቋሚ ሲኖዶስ ይህንንም ማድረጉም ይበል ያሰኛል። ዋናው ነገር ሁላችንም ባለንበት እነዚህን የሉተር ደቃላ ተሃድሶዎች መንጥረን እናባር። ከአባቶቻችን ጎን እንቁም።

 4. Anonymous February 12, 2016 at 5:28 pm Reply

  እግዚአብሔር የአገልግሎት ዘመናችሁን ያርዝምልን በርቱልን የዚህ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆናችሁ።

 5. Ruhi February 12, 2016 at 5:34 pm Reply

  እግዚአብሔር ያበርታቸው፣ የተመረጡትን ኮሚቴዎች በቅንነት ከቤተክርስቲያን ትከሻ ላይ ተሃድሶን ያራግፉላት እድለኝነት ነው ለዚህ አገልግሎት መመረጥ ቤተክርስቲያን ካለችበት ውጥረት ቢታደጓት።ለእውነት እንዲሰሩ አምላከ ቅዱሳን ይርዳቸው።

 6. ዳሞት February 12, 2016 at 5:53 pm Reply

  አባቶቻችን ሆይ!እባካቸሁ በርቱልን! ትግነስት መታሳችሁ ይገባናል። ግን ትግስታችሁ ወደ ንስሃ አላቀረባቸውም። እናን እያላችሁ እንድትጠብቋትና እረኛ ሆናችሁ እንድታሰማሯቸው የተሾማችሁባቸው ቤተክርስቲያን መሳለቂያና ባለቤት አልባ አስመሰሏት። ለእምነታቸው የቆሙት በተለያዮ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተብጠለጠሉ፣ ጣዖት አምላኪም እየተባሉ ተዘለፉ
  አባቶች ሆይ!የቤተክርስቲያን እምነት ሥርዓቷ፣ ገድል ቱፊቷ፣ ቅዱሳንን ማክበሯ ተረታ ተረት እያሉ መናፍቃኑ ዘልፈው አረከሷት። ልጆቿንም ሥነልቦናዊ ቀውስውስጥ ለመክተት የማጥላላትና የማራከስ ዘመቻን ተግተው እየረጩ ነው።
  መናፍቃን ተሐድሶ ባዮቹ በቤተክርስቲያን ስም እየተጠቀሙ እጅግ ፀያፍና ኢክርስቲያናዊ ተግዳሮትን እያከናወኑ ናቸውና ከላይ እንዳልኩት መታገሳችሁ በፀፀት ወደ ንስሐ አላመጣቸውምና ተገቢውን ቤተክርስቲያንና መንጋዎቿን የማስጠበቅ እርምጃን አድርጉ። የተጠራችሁበት አላማ ቤተክርስቲያንንና በጎችን የበግ ለምድ ከለበሱ ተኩላዎች የመጠበቅ አንዱና ዋናው ነውና።
  በዝምታችሁ ብዛት የጠራ የሾማችሁ ክርስቶስ እንዳያዝንባችሁ እባካችሁ ዝም አትበሉ።

  • Anonymous February 12, 2016 at 9:20 pm Reply

   Damot ende damotra tenadafi gint yagegnehewun atinadef bura kereyu malet ayawatam bezigita merejana masreja bematenaker yihun enji be 1 jenber hulu yidereg atibel
   bemoqebet yasmesilihal
   awqalew yalew huneta ende egir esat lilebelibih yichilal gin benzin markefkef wutet ayametam
   yeseded estaun aqtacha satay ….
   bezehalefe siryet webe zyimetsie eqibet

 7. Anonymous February 12, 2016 at 9:14 pm Reply

  1) መጋቤ ሐዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ
  2) ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አገዘ
  3) መሪጌታ ሳሙኤል አየሁ
  4) ሊቀ ጠበብት ኤልያስ ተጫነ
  5) ዶክተር በለጠ ብርሃኑ
  6) ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬ
  ke enezih mahbere kidusan abal yalhone man new?Ere tewu
  man yarda yeqebere man yinager yenebere newuna negeru ke mahberu
  yet alu metsahift yasmesekeru?
  ewnet new liqe tebebt haregeweyin milue bekulehe nachew gin
  leloch kemahberu degafi wuchi yalut altekatetem ye 1 wegen endayhon

  • Anonymous February 13, 2016 at 2:13 pm Reply

   ውሳኔው ከቅዱስ ሲኖዶስ መሆኑን መርሳት ያለብን አይመስለኝም፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ደሞ መሪው ከወዴት እንደሆነ የምናምን እናውቃለን፡፡

 8. Habesha February 12, 2016 at 10:33 pm Reply

  ከይቅርታ ጋር ወይዘሮ ሮማን ማን ናቸው?

 9. Abiy February 12, 2016 at 11:16 pm Reply

  bertu belnal

 10. anonymously February 13, 2016 at 11:52 am Reply

  Afetsatsem yele? Kommitte bicha? Be Abune Hikiel ye mimeraw reports yetale?

 11. Shitahun February 13, 2016 at 3:05 pm Reply

  ተሐድሶ ፍፁም የለም ሲሉ የነበሩት ጊዜው አብቅቶ ፍሬው ከእንክርዳዱ የሚለይበት ወቅት በመድረሳችን እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡ ኮሚቴው ማህበረ ቅዱሳን ነው የሚለውን እንተወውና ሰለ ቅድሰስተ ቤተክርስቲያናችን በአንድነት እንስራ፡፡

 12. Anonymous February 13, 2016 at 5:20 pm Reply

  Who is Roman Tesfaye, More peoples become confused, so it is better to brief who is she for followers.

 13. ዲ/ን አለማየሁ ኃይሉ February 13, 2016 at 6:17 pm Reply

  ለምን አንዱ ነፋቂ አነዱ ተናፋቂ ይሆናል፡፡ ክርስቶስ እኮ አንድ ነዉ፡፡ እሱን ማመን ግን መሠረት ነው፡፡ ለምሣሌ ዳዊት አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ሲል መቼ ሌሎችን ጠራ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን ማመንና ማምለክ እንጅ አማራጭ ለምን ታበዛላችሁ? ለምን በመጽሐፍ ቅዱስ አስተምሕሮ አትዎሰኑም፡፡

  • Yonas February 14, 2016 at 11:00 pm Reply

   Be 1896 akababi meseleg ye Egypt Orthodox church bemn aynet adega wst andeneberech t yemnawkew enawkewalen sle ezih egna Orthodox christian be tselot bcha new magez yalebn::Egzieabher nufakie tehadsowochn lbona ystachew

  • annony February 15, 2016 at 8:04 am Reply

   ዲ/ን አለማየሁ ኃይሉ anten bilo Dn negn bayi. Hihenen newu betekirstian yastemarchih? አማራጭ ለምን ታበዛላችሁ? egna yeAmilak amarach alabezanim, alamelekinim, kidusan gin bizu betam bizu nachiw yiredunal, yamalidunal, engidih bekinat timotalih neji min tihonaleh? kidusanin kesilitanachew atawordachew ant tiwaredaleh enji, bel ahun Dikuna ayigebagnim bileh melis lib kaleh ena wede erasih ketemelesih.

  • Anonymous February 15, 2016 at 10:00 am Reply

   አንተ የበግ ለምድ የለበስክ ተኩላ መናፍቅ አይንህን ገልጠህ ተመልከት ለመማር እንጂ ለኑፋቄ አትፍጠን

 14. Anonymous February 15, 2016 at 5:54 am Reply

  ዲ/ን ተብየዉ ለነገሩ ዲ/ን መሆንህን አንተም አታዉቀዉ ሰዉ የማያዉቀዉን ሲጽፍ ያሳፍራል ከክርስቶስ ዉጪ ይመለካል ለማለት እንደፈለክ አመለካከትህ ያሳብቅብሃል፡፡ መናፍቅ መሆን መብትህ ነዉ የማታዉቀዉን እና ያልሆነከዉ መጻፍ ግን ኢሞራላዊ ነዉ

 15. ካሳሁን February 15, 2016 at 8:41 am Reply

  በመለኮት፣ በአገዛዝ በስልጣን አለምን ፈጥሮ በመግዛት ከባህርይ አባቱ ከአብ፣ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አንድ ቢሆንም የራሱ ፍፁም ገፅ ያለው በግብር ተወላዲ የሆነ ጌታ ብቻ ያለሆነ ነገር ግን የጌቶች ጌታ የአማልዕክት አምላክ የነገስታት ንጉስ የሆነ ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ኢሳ 9፡6። የተባለለት ነው፡፡ ደግሞስ አምላኪየ አምላኪየ ነጽረኒ ሲል መቼ ሌሎችን ጠራ ነው ያልከው እነማነን ማለትህ ነው እኔና አብ አንድ ነን ያለውን እንዴት ዘነጋኸው፡ ሌላም ልጨምርልህ፡ ሒዱና አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃቺሁ አለ እንጂ በኢየሱስ ስም መቼ አለና ነው፡፡ ክርስቶስን ሶስት አደረከው አኮ፡ ደግሞኮ አንድ ነው ብልሃል፡፡ ከሚደበላለቅባቺሁ መጥታቺሁ ለምን ሊቃውንትን አትጠይቁም፡ ፡

 16. legese kassa February 15, 2016 at 2:05 pm Reply

  በመጀመሪያ ቅ.ሲኖዶስ ለዚህ ውሣኔ በመድረሱ በቅ/ቤተክርስቲያን ሥም ሊመሰገን ይገባል፡፡ ሆኖም ግን በነዚህ አጽራረ ቤተክርስቲያ ላይ የማያዳግም እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ትግስቱ ከልክ ባላይ ነው፡፡ ቤ/ክርስቲያን እስክትጠፋ መጠበቅ ያለብን አይመስለኝም፡፡
  እግዚአብሔር ሀሣባችሁን ያስፈጽማችሁ!!!

 17. fesha negash February 17, 2016 at 6:06 am Reply

  ማህበረ ቅዱሳን የገንዘብ ምንጫቸው የሆነው ፒኤልሲ እንዳይዘጋባቸው በውስጥም በውጭም ባሉት ሆዳም ቅጥረኞቻቸውና አባላቶቻቸው ተሐድሶ ተሐድሶ የሚለውን ነጠላ ዜማ ያቀነቅናሉ፡፡ አሁን እነ በጋሻው መጀመሪያ መቼ ተማሩና ነው መናፍቅ የሆኑት ማ/ቅ አባላት እውነት ለሓይማኖት ከቆማችሁ እና አነሱ ተሐድሶ ከሆኑ ለምን አስተምራችሁ አልመላሳችኋቸውም፡፡ ሌላው እምነት አዲስ አማንያንን እያስተማረ አባላ ያደርጋል ፡፡ እናንተ ያለውን ስም እያጠፋችሁ ታሳድዳላችሁ ፡፡ በእውነት በእናንተ ላይ እግዚአብሔር ፍርድ ይሰጣል፡፡ በአገር ቤት ግን በአክራሪ ኦሮሞዎች ቤተ ክርስቲያናት እየነደዱ ነው፡፡ ለግል ጥቅማችሁ ብላችሁ ምእመናንን ከምትከፋፍሉ ንስሐ ገብታችሁ ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን ሕልውና በጋራ ሥሩ፡፡ በማህብር ስም ያቆማችሁትንም ፎቅ ለቤተ ክርስቲያን በፍጥነት አስረክቡ፡፡

 18. Anonymous February 18, 2016 at 10:20 am Reply

  እኔኮ የሚገርመኝ እሰው ቤት ሄዶ ማዘዝ መሞከር በጣም ይገርማል አጥኚዎቹ ምን ሊሉ ነው ሄደው ይሄ የጎድላችኋል ይህን ጨምሩ ሊሉ ነው ለሰው ያልተሟገቱ ምነው ቤተክርሲቲኗን ቱሪስት የሚጎበኛት የትኛው ኦርቶዶክስ ነው ሌላው አማኝ አይደለም እንዴ የቤተክርሰቲያኗን መጠቀሚያ እየገዛ የሚሄደው ስራ ለማስፈታት ነው አባቶች ሌላ ስራ የላቸውም ልጅ ያቦካው እንዳሆን የበሰለ አስተሳሰብ አይደለም ለኛ የሚበልጠው ሰው እንዳሄድ ወንጌሉን በማስተማር ማትረፍ እንጂ ቁሳቁስ ነብስ የለው ሲኦል እንዳግባ ነው ያዘኑለት መናፍቅ ሆኖ ፣ጌታም እኮ እስራኤላዊ ነው ስለወደደን እንጂ ስራራልን ጌታ የሞተው ለቁሳቁስ አይደለም ለኔና ላንተ ነው እባካቸሁ ወንጌሉን አስተምሩን ‹‹ጌታሆይ ቤተክርስተያናችን ከክፉዎች ጠብቅልን!!!! ››

 19. Atnatiwos Gashaw Desalegn February 19, 2016 at 8:04 am Reply

  lbytkereseteyane ymiyasebe swe bezu endmhabrqedusan yalu mahiberat endmiyaseflegu yerdale!!!areqne enasebe bmrja enenure!!

 20. Anonymous February 19, 2016 at 3:33 pm Reply

  Amazing! the decision of the holy syndo was made on October 2008, but try to take an advantage or to mislead the followers of the church. and to caver up the decision of the meeting of the leaders of the church witch was held on Thursday. i myself strongly believe that our church is surrounded by many enemies and one of the me the movement of Tehadso., to me mk and tehadso are the same. both of them are working differently for the sake of themselves. is mk is really want to stand against them, he has to be united with the church leaders and obey the cannon law of the church.
  let me ask you this. do you think that those people can fund out the movement of tehadso and others. this is really. unfair and unacceptable. Any way let protect our mother church together and we have to be united enough

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s

%d bloggers like this: